ልብ ወለድ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


✅ህይወት ትቀጥላለች አንዱን ከሌላው ድርና ማግ እያደረገች።
✅ውድ የቻናሉ ቤተሰቦች ፍቅርን እንዝራ ፍቅርን እንስበክ ፍቅርን እናቀንቅን።
✅ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችንና ሌሎች መጻጽፎችን ያገኙበታል።
.
.
For paid & cross promotion @hhtub

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


┈┈◦◎●◉† 💠💠💠 †◉●◎◦┈┈

📯 🔰 ኦርቶዶክሳዊ መፅሐፍት ቻናል 🔰 📯

▫️➱ በዚህ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል ላይ
👉 መፅሀፍትን በpdf 📚
👉 ድርሳናትን 📖
👉 ገድላትን 📖
👉 መንፈሳዊ ፊልሞችን 🎦
👉 መንፈሳዊ መዝሙሮችን 🔔
👉 መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎችን ❔
👉 ኦርቶዶክሳዊ ቻናሎችን 🔗
👉 ምስለ ስዕላትን 💒
👉 ጥቅሶችን 🔖
👉 ትምህርታዊ ፅሁፎችን 📝
👉 ግጥሞችን 📜 ያገኛሉ!!▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳  █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬⚜ ORTH🅾DOX PROⓂOTION ⚜
𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲
▫️10k - 50k members▫️
‌‌‌‌‌‌
┈┈◦◎●◉† 💠💠💠 †◉●◎◦┈┈


ልብ የሚሰብር ዜና
ታላቁ ድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ አረፈ።
ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በዓለማየሁ እሸቴ ቤት ሆኖ አሁን ለዘ-ሐበሻ እንደገለጸው ዓለማየሁ ቀኑን ሙሉ ከጓደኞቹ ጋር ሥለሥራ ጉዳይ ሲያወራ የዋለ ሲሆን ቤቱ በሰላም ከገባ በኋላ ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ የህመም ስሜት ተሰማኝ በማለት ከቤት ራሱ እየተራመደ ወጥቶ በታክሲ ወደ አይሲ ኤምሲ (iCMC General Hospital) ሆስፒታል ሄደ። በዚያ በህክምና እየተረዳ እያለ ነው ሕይወቱ ያለፈው። ዓለማየሁ ለኢትዮጵያ ብዙ ያደረገ ባለሙያ ነው። ሃገር ወዳድም ነው። ይህ ታላቅ አርቲስት በክብር እንዲሸኝ እና እንዲቀበር ዘ-ሐበሻ ጥሪውን ያቀርባል። ዓለማየሁ ከዚህ ቀደም የልብ ህመም ህክምናውን በተለያዩ ሃገራትና በሃገር ውስጥ ሲከታተል እንደነበር ይታወቃል።
ማዲንጎ አፈወርቅ፣ ኃይልዬ ታደሰ፣ ግርማ ተፈራ፣ መሳፍንት አወቀ፣ መሐመድ ኮይስ እና ሌሎችም የሙያ ባልደረቦቹ የዓለማየሁ ሕልፈት እንደተሰማ በቤቱ በመገኘት ቤተሰብ እያጽናኑ ይገኛሉ።
ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን። ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመጣለን።


ለልባሞቹ❤️❤️
ሌሊት ነበር፤ አንድ ሰው በመንገድ ላይ እየነዳ መኪናው በገዳሙ አቅራቢያ ይበላሽታል። እናም ወደ ገዳም ሄዶ በሩን አንኳኳ። መነኩሴው ወደ ውጭ ወጥቶ በሩን ሲከፍት “መኪናዬ ተበላሸ። እዚህ ለአንድ ሌሊት መቆየት እችላለሁን?” አለ። መነኩሴውም ጥያቄውን ተቀበለ። መነኮሳቱንም ማቆየት ብቻ ሳይሆን መገቡት አልፎ ተርፎም መኪናውን አስተካከሉለት።

ሰውየው ለመተኛት ሲሞክር እንግዳ የሆነ ድምጽ ሰማ። በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ስለዚያ ድምጽ መነኩሴውን ጠየቀ ነገር ግን መነኩሴው “መነኩሴ ስላልሆንክ ልንነግርህ አንችልም” አለው። ሰውየው ቅር ቢሰኝም አመስግኖት መንገዱን ቀጠለ።

ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ፣ ያው መኪና በተመሳሳይ ገዳም ፊት ለፊት ይበላሻል። አሁንም እንደበፊቱ ሁሉ መነኮሳት ተቀብለው መግበውት መኪናውን አስተካከሉለት። እናም ለመተኛት ሲሄድ ያኛው ሰውዬ ከዚህ ቀደም የሰማውን ተመሳሳይ እንግዳ ድምጽ ይሰማል።

በማግስቱ ጠዋት ስለዚያ ጫጫታ መነኩሴን ይጠይቃል፤ ግን መነኩሴም ተመሳሳይ መልስ ሰጡት “መነኩሴ ስላልሆንክ ልንነግርህ አልችልም" ሰውዬውም "ስለዚያ ድምጽ ለማወቅ መነኩሴ መሆን ግድ ከሆነ፤ እንዴት መነኩሴ መሆን እችላለሁ?” መነኩሴም መለሰ ፣ “መነኩሴ ለመሆን ከፈለክ የምድርን አሸዋ መቁጠር እና ቁጥሩን ለኔ መንገር አለብህ ይህን ስታገኝ መነኩሴ ትሆናለህ ”አለው።

ሰውየው ለዚህ ተግባር ተነስቶ ከአርባ ዓመታት በኋላ ተመልሶ የገዳሙን በር አንኳኩቶ “መላውን ምድር ተዘዋውሬ 222,345,323,954,110,958,203 የአሸዋ ጠጠር በምድር ላይ እንዳለ አገኘሁ” አለ።

መነኩሴ ሰውየውን በማመስገን “አሁን ወደ ድምጹ የሚወስደውን መንገድ እናሳይሃለን” አለው። መነኩሴ ወደ አንድ የእንጨት በር እየመራው “ሰውየው የሚፈልገው ድምፅ ከዚያ በር በስተጀርባ ነው” ሲል ሰው ተደሰተ። በሩን ለመክፈት ሲሞክር ግን ያ በር እንደተዘጋ ተረዳ። ስለዚህ በሩን ለመክፈት ቁልፉን እንዲሰጠው መነኩሴውን ጠየቀ። መነኩሴ ቁልፉን ሰጠው። ሰው በሩን ከፍቶ ከዚያ በር ጀርባ ከድንጋይ የተሠራ ሌላ በር አየ። ዳግመኛ ሰው በሩ እንደተቆለፈ ስላየ የዚያ በር ቁልፍ ጠየቀ። ሰው የድንጋይ በር ሲከፍት ከወርቅ የተሠራ ሌላ በር አገኘ ግን ተቆልፏል።

መነኩሴ የዚያን በር ቁልፍም ሰጠው። እንደገና ከሩቢ የተሠራ ሌላ በር ነበር። በሌላ ተከታታይ በር እስኪያልፍ ድረስ ይህ ይቀጥላል። በመጨረሻ መነኩሴ “ይህ የመጨረሻው በር እና እዚህ የዚህ በር ቁልፍ ነው” አለ። ሰውየው በመጨረሻ እፎይታ አግኝቶ በሩን ከፍቶ ገባ እና ከዚያ በር በስተጀርባ የድምፅ ምንጭ በማግኘቱ ተገረመ ግን ምን እንደ ሆነ ልነግራችሁ አልችልም .. ምክንያቱም እናንተ መነኩሴዎች አይደላችሁም።
*

ኃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን። ሌሎች ታሪኮችን እና የመጻሕፍት ጥቆማዎች ለማግኘት ገጻችንን ላይክ፤ ለሌሎች እንዲደርስ ደግሞ ሼር ያድርጉ። እናመሰግናለን!
*

ሁሉንም ነገር ማወቅ አለብን ብላችሁ ታስባላችሁ?
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንበብ ለንባብ
***


ከ"ሙኒክ ባሻገር" መፅሐፍ የተቀነጨበ...

"...ሁለቱ ሰዎች ለዘመቻው የምሥጢር ስያሜም ሰጥተውታል፡፡ ኦፕሬሽኑ ‹‹ዘመቻ ኢቅሪት እና ቢሪም›› የሚል ስያሜ የነበረው ሲሆን ስሞቹ የእስራኤል ጦር በ1948 ዓ.ም. ‹‹የደኅንነት ስጋት አለ›› በሚል ሰበብ ያፈናቀላቸው የጥንታዊያኑ የዐረብ ክርስቲያኖች መኖሪያ መንደሮች መጠሪያ ስሞች ነበሩ፡፡

እነዚህ የዐረብ ቤተሰቦች ከትውልድ ትውልድ፣ አያት ቅድመ-አያቶቻቸው ከኖሩባቸው የመኖሪያ መንደሮች እንዲወጡ ሲገደዱ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ትመለሳላችሁ ተብለው ነበር፡፡ ይሁን እና ከዐሥርት ዓመታት በኋላም ፍልስጤማዊያኑ ወደ ቀዬያቸው መመለሳቸውን እየተጠባበቁ ነበር፡፡ ምንም እንኳ አብዛኞቹ እስራኤላዊያን ስለዚህ አሳዛኝ ሁኔታ እውቀቱ ባይኖራቸውም ሁኔታው ለዐረቦቹ የሚጠዘጥዝ ቁስል ነበር፡፡..."

ጥላሁን ግርማ የቁጥር ሰው ነው። ፈረንጅ አገር ሄዶ ተምሮ "እናት አገር ትኑር ለኛ" በማለት በአፍም በመጽሐፍን አገሩን ያገልግላታል። ከዚህ ቀደም የትሬቨር ኖሃን "Born a crime" የአመጻ ልጅ ብሎ በጥራት አቅርቦልን ነበር። አሁን በአዲስ መጽሐፍ በድጋሚ ተከስቷል " One day in September "ን ከሙኒክ ባሻገር ብሎ። ግዙ፣አንብቡ፣ ጋብዙ... መጽሐፉን በሁሉም መጻሕፍት ቤት ውስጥ ታገኙታላችሁ።
***
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ


መህምሩ ለተማሪዎች ወደፊት ማሳካት የምትፈልጉትን ነገር በሙሉ ጽፋችሁ በነገው ዕለት እንድትመጡ ብሎ አዘዘ..
“በዚያ ምሽት ተማሪው ሕልሙን እና ማሳካት የሚፈልገውን ሁሉ ጻፈ እናም እንዲህ ይል ነበር በመጪው 10 ዓመታት የፈረስ እርሻ ባለቤት እንደሚሆን፣ አራት ሕንጻዎች እንደሚኖሩት፣ 200 ሄክታር የእርሻ መሬት እና 4,000 ካሬ ቤት እንደሚኖረው ጻፈ ለዚህም ዝርዝር የወለል ፕላን አዘጋጀ። እና በሚቀጥለው ቀን ለአስተማሪው አስረከበው። ከሁለት ቀናት በኋላ ወረቀቱን መልሶ ተቀበለ።
አስተማሪው ወረቀቱ ላይ ጉልህ "ኤፍ"አድርጎበታል። ልጁም ተበሳጭና መምህሩን ሄዶ አናገረ።

አስተማሪውም ይህ እንደ አንተ ላለው ወጣት ልጅ ከእውነታው የራቀ ሕልም ነው። ገንዘብ የለህም፣ የድሃ ቤተሰብ ልጅ ነህ፣ ምንም ሀብት የለህም። የፈረስ እርሻ ባለቤት መሆን ብዙ ገንዘብ ይጠይቃል። 4ሺህ ካሬ እና ትልቅ እርሻ ላንተ "ላም አለኝ በሰማይ ነው" ብሎ ተዛባበተበት። እናም እንዲህ አለ "ማታ እንዳዲስ ሊሳካ የሚችል እቅድ ጻፍና ውጤትህን አስተካክልልሃለው"

"ልጁ ወደ ቤቱ ሄዶ ብዙ አሰበበት። አባቱንም ምን ማድረግ እንዳለበት ጠየቀ። አባቱም "ተመልከት ፣ ልጄ፤ እዚህ ጋር የራስህን ሐሳብ መወሰን አለብህ። እኔ ግን በጣም አምንብሃለውና ልብህን ስማ" አለው።
በነገታው እቅዱን ምንም ሳይቀይር መልሶ ለአስተማሪቅ ሰጠ አስተማሪውም በ"ኤፍ ግሬዱ" ጸና።

ከዓመታት በኋላ ያ መምህር አርጅቶም እያስተማረ ሳለ አንድ ቀን ማለዳ ላይ በቴሌቭዥን የአንድ ወጣት ቃለመጠይቅ ይቀርብ ነበር... ወጣቱ ልጅ እያለ አሳካዋለሄ ካለው አንድም ያልቀረው የናጠጠ ሀብታም ሆኖ ነበር። እንዲህ አለ "ሕልሜን አስተማሪዬ ሊሰርቀኝ ሲታገል እንደምንም ነበር የተረፍሁት... እኔም ህልሜን እሱም ኤፉን ወሰደ"

የዛኑ ቀን መምህሩ ለተማሪዎቹ ወደፊት ማሳካት የምትፈልጉትን ጻፉልኝ ብሎ አዘዘ በነገታው መለሱለት ለሁሉም የሰጠው ውጤት "ኤ"ነበር።
*
ሞራል፡ መምህራን የጠቀሙ መስሏቸው የስንቱን ሕልም ሰረቁ። በሕልማችሁ አትደራደሩ ለማሳካት የምታስቡት ሁሉ የሚደረስበት እና የተደረሰበት ነው።
*

ይህ ጽሑፍ ላይ ያላችሁን ሐሳብ በኮሜንት አጋሩን
ከተስማማችሁም ሼር አድርጉት
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ


😘ብቀላ😘

🔥ምእራፍ 10

✍ደራሲ ማሪኮሪሊ ቬንዳታ
.
.
.
ካርሜሎ ኔሪ ሲል ድንጋጤዬን መከላከል አልቻልኩም። ሀብቱን እባቶቼ መቃብር ቤት ደብቆ አሁን ደግሞ የርሱን ሲጃራ እያጨስኩ እንድጓዝ የሚያደርገኝን አጋጣሚ ተጠራጠርኩ። ካርሜሎ ኔሪን ያውቁታል?» አልኩት


😘ብቀላ😘

🔥ምእራፍ 9

✍ደራሲ ማሪኮሪሊ ቬንዳታ
.
.
.
በቀይ ጽጌረዳ ፋንታ ቀይ ደም በአናትዋ ማፍሰስ ይገባል:: ፊትዋ የሀዘን ምልክት ጨርሶ የለበትም ፍቅርን ብቻ ያመነጫል ያ ከገነት በራፍ እንደሚፈልቅ ምንጭ ይጣፍጠኝ ነበር ድምጽዋ በሰራ አካላቴ እንደመርዝ ተሰራጨ በሰፊው ስታነበንብ ሰማኋት ። የሚባባሉት አንድ በአንድ አንጐሌን እያነደደ አዳመጥኩ ።«አንተ ተላላ ጉዶ ለመሆኑ ፋቢዩ ባይሞት ምን ይውጥህ ነበር አንድቀን ነገሩ ቢታወቅስ?»
«በብልሐትሽ እንዳመሉ ትይዢዋለሽ እስከመቼም የሚታወቅ አይመስለኝም ።»
«ብቻ እንኳን ሞተ አረፍኩ ። ከእንግዲህ ግን እንደፈለግነው ልትጐበኘኝ አይገባም አሽከር ገረዱ ያወራል ። ቢያንስ ስድስት ወር አዝኜ መታየት አለብኝ ።» «ግን እንዳትዘነጊ ፋቢዩ መሞቱ ጉዳትም አለው "ለሁለታችንም የገንዘብ ምንጫችን ነበር “» እንደቆመች በኔው ፊት ከደርዘን ጊዜ በላይ ሳማት በቀጠሮ ደሙን ለማፍሰስ ወደ ኋላ እንደሚሄድ ነብር ድምጼን አጥፍቼ ማፈግፈግ ጀመርኩ የእግሬ ኮሽታ ይሁን ሌላ ኒናን ጥርጣሬ አሳደረባትና' «እሽሽ ዝም በል ። እርሱ የሞተው ገና ትናንት ነው
ጳረሞት የራሱን ግቢ ይጐበኛታል ይባላል እኮ።እንዲያውም በሕይወት ዘመኑ ይህን ቦታ ይወደው ነበር ። እዚህ በመምጣታችን አጥፍተናል » እንደመጸጸት እያለች
«ምንም ቢሆን የልጄ አባት እኮ ነው ።» «ባልሽ መሆኑን መቼ አጣሁት በሳመሽ ቁጥር ቅናት ያቃጥለኝ ነበር ።» ከእናት ልጅ የምቀርበው ጓደኛዬ መቃብሩን በገዛ እጁ ሲቆፍር ቆሜ አደመጥኩ ። ባል ሚሽቱን ሲስም ውሽማ የሚቀናበት ጊዜ መጣ? ትከሻው ላይ በተበተነው ፀጉርዋ እየተጫወተ «ለምንድነው ለመሆኑ ፋቢዩን ያገባሽው?»አላት ። «የገዳም ኑሮ አሰልችቶኝ ነው ። ከዚህም በላይ እርሱ ሀብታም ነበር። ደሀ መሆንን እንደሞት እጠላለሁ ። በዚህ ላይ ደግሞ አፈቀረኝ ።» በኩራት ወደሰማይ አንጋጣ «አዎን በፍቅሬ አብዶ ነበር ።» «አንቺስ አላፈቀርሽውም እንዴ?"
«ለአንድ ሁለት ሳምንት አፍቅሬው ነበር መሰለኝ ። ከዚያም ወዲያ ጋብቻ ሆነ ። ሀብትም ክብርም እድልም ሰጠኝ ።» «ጋብቻሽ ከኔ ጋር ቢሆን ኖሮ ግን ምንም የምታገኝው ነገር የለም ማለት ነው? «አንተን በፍቅረኝነት መያዙ በቂ ነው " ከዚህ በላይ ሌላውን እርግጠኛ አይደለሁም ። አሁን ግን ነጻ ነኝ ። ነጻነቴን ማስከበር አለብኝ ። የፈለግሁትን ማድረግ እችላለሁ ።»ንግግርዋን አላስጨረሳትም የንዴትም የፍላጐት ግፊት ይዞት ጎትቶ ደረቱ ስር ጨመቃት «ኒና ልታሞኝኝ አትሞክሪ " የሰርግሽ እለት በፍቅርሽ ተነደፍኩ ። መልአክ እንዳልሆንሽ ስለማውቅ ጊዜዬን ጠበቅሁ " ባገባሽ በሶስተኛ ወር የፍቅር ምኞቴ ነገርኩሽ " ከዚያ በኋላ በነገርም በምልክትም ፈቃድሽን ገለጽሽልኝ ። ፋቢዮ ባልሽ የሆነውን ያህል እኔም የባልሽ ያህል ነበርኩ ። በሀጥያቴ አልጸጸትም ። ፋቢዩ
አምኖኝ ከአንቺ ጋር ሊለቀኝ አይገባም ነበር ። በገዛ እጁ ለሀጥያት ዳረገኝ።
ስለዚህ በምንም ምክንያት ከእጀ ልትወጪ አትችይም » ኒና በአነጋገሩ ተቆጥታ ከእቅፉ ለመውጣት ታገለች ። «ልቀቀኝ! ትዳፈራለህ በጣም አሳመምከኝ» ለቋት
ለአፍታ ብቻዋን ፀጥ ብላ ቆም እንዳለች እንደገና ይዞ ጨመጨማት «ይቅርታ አድርጊልኝ ላስቆጣሽ አልነበረም ። ውበትሽ ነው እንዲህ የሚያደርገኝ ። ፈጣሪ ወይም ሰይጣን ውበትሽን እንዲህ አስተካክሎ የፈጠረው ተሳስቷል ። የልቤ
ልብ የነፍሴ ነፍስ ነሽ ።» ካለብዙ ትግል ተጠጋችው ። ከንፈር ለከንፈር ተጋ
ጠሙ፡ እነርሱ በተሳሳም ቁጥር እኔንም አዲስ ሾተል አእምሮዬን ወጋው ። ሀሳቤንም እነርሱንም ማዳመጡ ግራ አጋባኝና ፈዝዤ ሳለሁ «ስለዚህ ፍቅሬን አትጠራጠሪ ጊዜ እንዲህ በግላጭ አጋጥሞን የፍቅር በረከቴን ገሸሽ አታድርጊ የጀመርንበትን ጊዜ ታስታውሻለሽ?ፋቢዮ የፕሌቶ መጽሐፉ ላይ ተደፍቶ እኛ ዜማ እየተለዋወጥን ስንዘፍን «ከሁሉ ፍቅር በላይ ያንቺ ፍቅር ይበልጥብኛል ያልኩሽ ትዝ ይልሻል» አላት ተያይዘው መራመድ ሲጀምሩ ባካሄዳቸው ሕሊናቸው ንፁህ ይመስላል ። ከዐይኔ እስኪሰወሩ ተመለከትኳቸው
ጨረቃዋ የደም ብርሀንዋን አለበሰችኝ ። መሬቱን በረገጥኰት ቁጥር የከዳኝ ይመስለኛል ። ምድርም ሰማይም የሰይጣን ሥራና መጫወቻ ሆኖ ታየኝ። ዓለም ላይ የምወዳት ሕይወቴን የምሰጣት አንዲት ሴት ታማኝ ልትሆንልኝ የማትችልበት ምድር ምን ዓይነት የሰይጣን ሥራ ናት ይህች እንድሕይወቴ'የልጄ እናት' በክብር ፈንታ ውርደት የመረጠች ምን መደረግ አለባት? ይኸስ ምንም ነገር ያልነፈግ
ሁት የአንጀት ጓደኛዬ ምን ቅጣት ይገባዋል?.«ሂድና ግደላት» ያለኝ የሽማግሌው ድምጽ በጆሮዬ እስተጋባ ።«ሽማግሌው ወንድ ነው።ከመቅጽበት ተበቀለ ። ግን ስለታም በቀል ምንድነው አልኩ ። ረጅም ስቃይ የሚሰጥ በቀል መምረጥ አለብኝ ። በደም ፍላት ገድዩ ወንጀለኛ ተብዬ መጠቆም የለብኝም ።» ጊቢዬ ውስጥ አረፍ አልኩ ።አፌ ደም እንደጐረሰ ነው ። ከንፈሬ ከትኩሳቴ ብዛት ተስነጣጥቋል መመለስ የማይገባኝ ግቢዬ ተመልሻለሁ ጻረሞቴ ግን አይደለሁም ። ለበቀል የተላኩ መሆኔ ገባኝ ።የነበረኝ ሀብት አብሮኝ ባይኖርም በመቃብር ቤቴ ያለው
የሽፍታው ሀብት ከበርቴ ሊያደርገኝ ይችላል ገንዘብ ደግሞ ሊሰራ የማይችለው ስለሌለ የበቀል ዓላማዬን አሳካበታለሁ " ፍጹም ተወዳዳሪ የሌለው በቀል መጠንሰስ አለብኝ ክርስቶስ ጠላቶቻችሁን ውደዱ ያለው በሴት ፍቅር ባለመጠመዱ ነው እኔ ግን ሬትና ማር ቀምሻለሁ " በቀሌን ለኔ እንደሚጥመኝ እደግሳለሁ " በቃ ወሰንኩ ትንፋሼ ቀለል አለኝ " የሶስት ዓመት ተበዳይ ቂሜን የምወጣው ረዘም ብሎ በተሰካ ሳንጃ ነው መነኩሴው እሬሳዬ
ላይ ትተውልኝ ያገኘሁትን መስቀል አውጥቼ ስሜ ቃል ገባሁ የቂም በቀል እርምጃዬን እስክ ፈጽም ላልተኛ በአምላክ ስም ቃል ገባሁ በጨረቃና ከዋከብት ለቃል ኪዳኔ ምስክሬ ሆነው ከተቀመጥኩበት ተነስቼ በገባሁበት የጓር በር ወጣሁና ዋናውን መንገድ ተያያዝኩ ኔፕልስ ያደግሁበት ከተማ ገብቼ እንደባይተዋር በሆቴል የመኝታ ክፍል ይዤ አደርኩ::ሰማይና ምድር ወገግ ሲል ማልጄ ተነሳሁ። " ሌሊቱን ያውጠነጠንኩት የበቀል እቅዴ ተስተካክሎ በኣእምሮዬ
ቅርጽ አውጥቷል። አሁን የቀረኝ በሥራ መተርጎም ብቻ ስለሆነ ድብቅ ዓላማዬን አንድ ብዬ ለመጀመር ባትሪ ፣መዶሻ እና ሚስማር ይዤ ከተመልካች ሁሉ ተደብቄ ወደመቃብር ቤቴ ጉዞ ጀመርኩ ። እንደደረስኩ መቃብር ቤቱ አካባቢ
ብቻዬን መሆኔን እየተገላመጥኩ አረጋግጬ በዚያው የሚስጢር መግቢያ ገብቼ የሀብቱን ሳጥን ከፈትኩ። ሳላምታታ የወረቀቱን ገንዘብ በመልክ በመልኩ እየለያየሁ በኪሴ ከተትኩ። "ከብርቅ ሀብቱ በያዝኩት ከረጢት አጭቄ ባለ ብዙ ሺ ፍራንክ ሆኜ የሀብቱን ሳጥን በያዝኩት መሣሪያ ዘግቼ በገባሁበት ቀዳዳ ተመልሼ ወጣሁ።

ተቻኩዬ ስለነበር አንዲት ደቂቃም በዋዛ ሳላሳልፍ ከኔፕልስ የሚያወጣኝ ጀልባ ፍለጋ ያን ዕለቱን ወደብ ወረድኩ። ጥቂት ሰዎችን ስጠያይቅ አንዲት ወደ ፓሌርሞ የምታመራ ጀልባ መኖርዋን ሰምቼ የጀልባዋን ካፒቴን አስፈልጌ አናገርኩ። ከብዙ ማጠያየቅ በኋላ የፊቱ ቆዳ በፀሐይ ንዳድ የጠየመ ዐይኖቹ ለማሳሳቅ የሚንቀዠቀዡ ካፒቴን አገኘሁ። ካፒቴኑ የጠየቀኝን ዋጋ ከፍዬ በጀልባ ውስጥ ቦታዬን ያዝኩ። "ያስከፈለኝን ገንዘብ በኋላ ሳስላ ከመደበኛው ጋር


😘ብቀላ😘

🔥ምእራፍ 8

✍ደራሲ ማሪኮሪሊ ቬንዳታ
.
.
.
ሽበቴን በዓሣ አጥማጁ ቆብ ደብቄ ክፍሉን ከፍቼ ለሽማግሌው ታየሁት ። ከድንጋጤው ብዛት የያዘውን እቃ ጥሎ..... ፡ «እረ በእመቤቴ ማርያም! በወጣትነት ዘመንህ እንዴት ጐበዝ ናያማረብህ ሰው ነበርክ» ብሎ ፍጥጥ ብሎ አየኝ " «የለም አንተ ሰው ጠንካራ ነህ አሁንም ተፈለግህ ጠላትህን መግደል ትችላለህ» አለኝ ኪሴ የተረፉ ሶስት ፍራንኮች አውጥቼ እግር ሹራብ ይፈልጉልኝ ብዩ ያወለቅሁትን ልብስ በነጻ ወረወርኩለትና እየመረቀኝ እግር ሹራቡን አውጥቶ ሰጥቶኝ ተላበስኩ
ኔፕልስ ከተማ ያልታየ አዲስ አለባበስና አዲስ ሰው መስዬ ቆምኩ « ለመውጣት ከተዘጋጀሁ በኋላ አንድ ሀሳብ መጣብኝ " ሁኔታ እንዲህ ተለዋውጦ ድንገት ኒና ብታ
የኝ አይጠና ሆድዋ ስለሆነች በድንጋጤ ጉዳት ያገኛታል ብዬ መሽትሽት ሲል መሄድን መረጥኩ " ጊቢዬም ስደርስ በዋናው በር አልገባም ። በጀርባ ገብቼ
ከአሽከሮቼ ለአንዷ አስረድቼ ኒናን ቀስ ብለው ነግረው ስለ ሁኔታዬ አለማምደው ብንገናኝ ይሻላል በዬ ከራሴ ጋር ተወያየሁ ። ሰላምታ ሰጥቼ ልወጣ ስል ሽማግሌው መጥቶ ክንዴን ያዝ ሲያደርገኝ ሊናገር የፈለገው ነገር መኖሩ ገባኝ " ራቅ ያለ መንገድ ነው
የምትሄደው?» ብሉ ጠየቀኝ ።በአወንታ ራሴን አወዛወዝኩ "ለማንም አልነግር' ሚስጢሩ አብሮኝ ይሞታል ሴትጋ ነው በሞቴ የምቴደው ይህን ሲጠይቀኝ ጓጉንቸር የመሰለ ተንኮል ፈላጊ ዐይኑ መልሴን ለመረዳት ይቅበዘበዝ ጀመር ።"አወን ሴትጋ ነው የምሄደው »እንደገና ክንዴን ጨበጥ ጨበጥ አረገና ክንድህ ገና እንደብረት የጠነከረ ነው። ሂድና ግደላት፥ ታማኝነትን ከነፈገችህ ጎደላት» አለኝ። እየሸኘኝ በራፉ ላይ ቆሞ እንደሰይጣን ጥፍራም ጣቱን እየነቀነቀ «እንደ መከርኩህ አድርግ» አለኝ።
ቀኑ በጣም ረዘመብኝ ጊዜ ለመግደል በከተማው ስመጣና ስወርድ እምብዛም የማውቃቸውን አላየሁም በተለይ ከበርቴዎች ኮሌራውን ፈርተው ነው መሰል በመ
ንገድ ላይ አላየኋቸውም ። በየሄድኩበት መአዝን ጥቂት ሰዎች አስክሬን ይዘው
ቀብር ሲሄዱ ማየትን ተላመድኩ:: የሬሣ ሣጥንም ውድ ስለሆነ ትልቁን አስክሬን በትንሽ ሳጥን ለማብቃቃት ቀባሪዎች የሙታን አጥንት እየሰበሩ ጉልበት አጥፈው ሳጥን ሲከቱ ማየት ታከተኝ» በሽተኛው ገና ስልም ከማለቱ ለቀብር ሲያዘጋጁት
ደግሞ ይህ የኔ ጉድ እንዳይደርስ «መሞቱን አስቀድማችሁ አረጋግጡ። ብዬ
ስጮህ የሟቹን ጭንቅላት እንደተድበለበለ ድንጋይ ከግራ ወደቀኝ እያጋጩ «ይኸ ህይወት ካለው እኔ አንገቴን እሰጣለሁ»ብለው ከፋኞች ዐይናቸውን አፈጠጡብኝ ያን ቦታ ጥዬ ወረድ ስል አንዲት ወፍራም ሴት ሬሳ ከሚሰበስቡት ጋር ትጣላለች ። «አንዲት ደቂቃ ስጡንና መሞት መኖርዋን እንለይ» ትላቸዋለች ። በርዋ ጠጋ ብዬ ስመለከት አልጋ ላይ አንዲት እንቅልፍ ያሸለባት የምትመስል እንቡጥ ሴት ልጅ ፀጉርዋን በትና ተኝታለች ። የፊትዋ ወዝ ገና አልተከተተም ። ከጐንዋ አንድ ሰው ደረትዋን ጥርቅም አድርጉ ፀጉርዋን ተላብሶ ሙቀት የማይሰጠውን ገላዋን ሞጭጮ ተኝቷል ነፍስዋ ከወጣ ጀምሮ ሙሉ ሌሊት ቀኑን ጨምሮ ላይዋ ደርቆ መዋሉንም ሴትየዋ በሩን እየጠበቀች በጆሮዬ ነገረችኝ በሩን በርግጄ ራሴን ስቼ
ጠባብዋ ክፍል ስገባ እንባ አንቆኛል የሞት እልህ ተናንቆኛል ።እንደምንም አለስልሼ ሰውዬ በእውነተኛ ፍቅር እኮ ሞት የለም» አልኩት ። ከሙታን መሀል የማይሞት ፍቅር አይቼ እንባዬ ቦዩን ስቶ በአራት መአዘን ፈሰሰ ። «ፍቅርህ እውነተኛ ከሆነ
ዘለዓለማዊነትን ስጠው» ብዬ ስጮህ ምስኪኑ ፍቅረኛ እጁን ሰብስቦ በተስፋ
መቁረጥ እያለቀሰ ቀና ብሎ አየኝ የቀዘቀዘ እጁን ደግፌ ከአልጋ ላይ ወረደ።
ሴትዮዋን ጠርቼ እሬሳዋን መከፈን ጀመረች ። ከዚህ ቤት እንደወጣሁ ትዝ ያለኝ የራሴ ሬሳ የወጣበትን ሻይ ቤት እንደገና መጐብኘት ስለነበር በብዙ ችግር ፈልጌ አገኘሁት ። የሻይ ቤቱ ባለቤት ብርጭቆውን እንደወትሮው እየወለወለ ፡ «እህ አቶ አሣ አጥማጅ ሥራው የተቃና ነበር» ብሎ አናገረኝ ። ለአፍታ ተምታታብኝ ።ወዲያው ሁሉን ነገር አስታወስኩና በፈገግታ አወንታዬን ከገለጽኩለት በኋላ «እርስዎስ
እንደምን ነዎት ፡ ኮሌራውስ?» አልኩት ። «የኮሌራው ነገር አይነሣ» አለኝ። ራሱን እየነቀነቀ«ሕዝቡ እንደ ዝንብ እየረገፈ ነው ። የትናንትናውንማ ቅዱስ ዮሴፍ
አይመልሱት።» «ምነው ምን ተፈጠረ ትናንት እኔ እኮ ገና መግባቴ ስለሆነ የከተማውን ዜና አልሰማሁም» እየተጠራጠረና በሀሳቡ እየተጨነቀ «የትናንቱን ጉድ እንዴት አልሰማህም? የባለፀጋውን ጌታ ሮማኒን በኮሌራ አሟሟት አልሰማህም?» አለማወቄን ጭንቅላቴን አወዛውዤ ገለጽኩለት «ምን ያደርጋል ወንድሜ እንደ ንጉሥ ይከበር የነበረው ባለፀጋ ጌታ ሮማኒ ዛሬ የለም ። ትናንትና የአጥቢያችን ትልቁ መነኩሴ ጐትተው እዚሁ ቤት አምጥተው እግርህ አጠገብ ያለው ቦታ አስተኝተውት ነበር ። አንሱኝ
መልሱኝ ሳይል ፣ ሀጥያቱንም ሀብቱንም ሳይናዘዝ በአንድ ቀን ጀምበር በተስቦው ተለክፎ ሞተ ። ጥቂት ከተከዘ በኋላ «ምን ይኸ ብቻ መሰልዎት ጉዱ ። እኒያ ቅዱስ መነኩሴ እስከመጨረሻው ሳይለዩ አስከሬኑን ሲከፍኑ በሽታው ያዛቸውና ዛሬ ጠዋት እርሳቸውም እንደሱው አፈርቀምሱ» በሀዘንና በድንጋጤ የቀረበልኝን ቡና እየመረረኝ ቀመስኩ ። ሀዘኔ ግን እንዳይታወቅ ተረጋግቼ ማድመጥ ጀመርኩ ።
«መነኩሴው የራሳቸውን የደረት መስቀል ደረቱ ላይ አድርገውለት አባቶቹ መቃብር አስተኙት ሰዓቱንና የሲጃራ መያዣውን ለባለቤቱ ሰጥተው መርዶውንም እርድተው በበሽታው በስለው ተመለሱ ኒናዬ ትዝ አለችኝና ጥያቄዬ ከአፌ አምልጦ ወጣ።
«የሟቹ ባለቤት ሀዘንዋን እንዴት ቻለችው መቼም አብዳ ይሆናል" ሴቶች እንኳ በሁሉ ነገር ያብዳሉ እንኳን ለባል ሞት ለበግና ፍየል ሞት ያብዳሉ ብቻ ቄሱ ተይዘው ስለ ነበር ይኽን ሁሉ አልተናገሩም ። » ይህን ስንነጋገር በበሩ እንድ ሰው በዝግታ እርምጃ አለፈ ። ጓደኛዬን ጉዶፈራሪን መሰለኝ ። ዘልዬ ልጠመጠም
በት ከጀልኩ ። የሆነ ነገር መለሰኝና በዐይኔ ተከተልኩት ፒፓውን ያጨሳል ከፊቱ ፈገግታ ይታያል ። እኔው ቅጽር ግቢ የሚበቅል የጽጌረዳ አበባ ኮሌታው ላይ ሰክቷል ።
ስሜቴ ሁሉ በአንድ ጊዜ አመድ ትቢያ ነከሰ ። ያየሁትን ማመን አቃተኝ ። የመጨረሻው ውድ ጓደኛው ገና ትናንትና ሞቶ የእርሱ ገጽታ ግብዣ ቤት የሚሄድ ደስተኛ ይመስላል እንዴት ሊሆን ይችላል? ከንዴቴ ብዛት ሳቄ መጣ ።ሌላም ሀሳብ በተቃራኒው መጣብኝ ። እኔ ጓደኛው የሞትኩት ገና ትናንት ነው ። የሀዘን ሥርዓት የሚጠይቀውን ገና ሳያሰላስል ይችላል ። ጽጌረዳውም ቢሆን ልጄ ስቴላ አድርጋለት እርስዋን ለማስደሰት ኮሌታው ላይ ትቶት ይሆናል ። ብቻ ለሁሉም ማምሻዬን ቤቴ ስገባ እረዳለሁ ብዬ ልከተለው የነበርኩትን ትቼ ሂሣቤን ከፍዬ በሌላ
አቅጣጫ መንገዴን ቀጠልኩ ።ሞትን አሸንፎ ወደ ፍቅርና ደስታ የሚመለስ ድል አድ
ራጊየሚሄደውን እርምጃ እየተራመድኩ ምሽትን እጠባበቅ ጀመር ትእግስቴ ሲያልቅ ጀንበርዋ ጠለቀች በጣም የተጠበቀው ምሽት መጣ።ንፋሱ ቀዝቀዝ ብርሀኑም ደብዘዝ እለ።ወደ ቪላ ሮማኒ የሚወስደውን ዋና መንገድ ይዤ ሳዘግም ፀሐይዋ
ትታው ያለፈችውን አድማስ ጨረቃዋ ዝግ እያለች ተረከበች የልቤ ትርታ እየጨመረ ጉልበቴ በደስታ ብዛት መደነቃቀፍ ጀመረ መንገዱ ግን ያለወትሮው ረዘመብኝ ። መድረስ አይቀር በመጨረሻው ዋና በር ደረስኩ
የግብዬ በር ግጥም ብሉ ተቸንክሮአል ። የቤቱ ጠረኑ አወደኝ ፈገግታዬ ሁሉ ተመለሰ።የሁኔታዬ መለዋውጥ ዋናውን በር አስከፍቶ የሚያስገባ ስላልሆነ በብርቱካን አጸድ


ሌሊቱ ምን ያህል ቢረዝም መንጋቱ አይቀረም 👆
ሳለ እግዚአብሔር ሳለ ፈጣሪ #የኢትዮጲያ ንጋት ይመጣል ..... ሊነጋ ሲል ይጨልማል አይደል የሚባለው....... ትንሿ ጨረቃ ብርሀኗ ይዛ ስትሸሸግ ትልቋ ፀሀይ አዲስ ቀንን ይዛ ከነሙቀቷ ከነብርሀኗ በሰማያዊው ሰማይ ላይ ታበራለች 🙏

#እግዚአብሔር ይመስገን ያንን ቀን እንናፍቀዋለን አምነናልና እናየዋለን ??

#ኢትዮጲያዊነት ለዘላለም ይኑር 👆
💚💛❤️
በድሮ ጊዜ ንጉሡ ጠቢቡን ሰው ጠርተው ጥያቄ ይጠይቃሉ "የዚህ ዓለም ደስታ ምንድነው?"
ጠቢቡም ፦ "መብላት ፣መጠጣት መፍሳት" ብለው መለሱ ። በዚህ ንግግራቸው የተበሳጩት ንጉሥ ከቤተ መንግሥታቸው አስገፍትሩው እንዲያስወጡ አሸከሮቻቸውን አዘዙ በዚህ ጊዜ ጠቢቡ አንድ ነገር ብቻ እንዲናገሩ በመለመን ፍቃድ አገኙና ይህን አሉ "የተከበርከው ሱልጣን! የተናገርኩት እውነት መሆኑን ታውቅ ዘንድ ትበላለህ ፣ትጠጣለህ ግን አትፈሳም/አትፀዳዳም/" በማለት ረገሟቸው ።

አንድ ሳምንት አለፈ ። ንጉሡ ይበላሉ ይጠጣሉ የሚወጣ ነገር ግን የለም። ሆዳቸው ተነፋ ፣ ቁርጠት አላስተኛ ፣አላስቀምጥ አላቸውና ስቃያቸው ሲበረታ ሊቁን አስጠርተው" አጥፍቻለሁ ይቅርታ አድርጉልኝ "በማለት ሲጠየቁ "ይቅርታ የማደርግልህ መንግስትህን ስትሰጠኝ ብቻ ነው " አሉ ። ንጉሡም ከስቃያቸው አንፃር ምርጫ ስላጡ በቃላቸው አረጋገጡላቸው ። ጠቢቡም ሰው የንጉሡ ሆድ በእጃቸው ጠሰቁት ። ሡልጣኑም አንድ ጊዜ ፈስተው "እፎይ !"አሉ።
ያኔ " አላመንከኝም እንጂ አስቀድሜ ነግሬሃለው ። አሁን ግን መንግስትህን በፈስህ ለወጥክ" በማለት የመጀመሪያውን የጠቢብ ንግሥናን በዚያን ዕለት አገኙ ።
***
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንባብ ለህይወት


☞☞ ከደራሲያን አለም
የአለም እውነታዎች!!

❍✰✰✰✰✰◉⚇◉✰✰✰✰✰❍

✍ የያዝከው ነገር በቂ መስሎ ካልታየክ፤ድፍን አለምን ብትጨብጥ እንኳን፤ሀዘንተኛ እንጂ ደስተኛ መሆን አችልም፤እናም ባለህ ነገር ፈጣሪን አመስግነህ ኑር።
✍ የሰው ዋጋው እየቀነሰ የዶሮ እና የእህል ዋጋ እየጨመረ ሲመጣ በርትተህ ፀልይ ፡፡
✍ሰዎች ስለ አንተ መጥፎነት ቢያወሩ አይድነቅህ ምክንያቱም ውሾች በማያውቁት ሰው ላይ ነው የሚጮሁት::

┈┈┈┈◎◎❍❍┈┈┈┈

✎ ጨውን ሺ ጊዜ ስኳር ብትለው ስሙን እንጂ ጣአሙን መቀየር አችልም።
✎ ከክፋት ስትርቅ ሰላምህን ታበዛለህ፤ቅንና መልካም ስትሆን ደሞ ከጭንቀትና ከጸጸት ትድናለህ።
✎ በሕየውትህ ሰዎችን ለመረዳት እንጂ ለመጉዳት አታስብ።
✎ ፍቅርና መልካምነት ከቃል ይልቅ መተግበርን ይፈልጋል።
✎ የውሸት ጎደኛ እና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ ሁለቱም ፀሐይ እስካሉ ድረስ ነው።

┈┈┈┈◎◎❍❍┈┈┈┈

☛ የፈጣሪ ስዕል እያልክ ስትስም ራሱ ፈጣሪ አክብሮ የፈጠረውን ሰውን ግን ረግጠህ በማለፍህ የወጣልህ አስመሳይ መሆንህን እወቀው፡፡
☛ ውሾች እና ድመቶች አልጋህ ላይ እንዲዘሉ እየፈቀድክ ድሆች ግን የግቢህ ድንጋይ ላይ እንዲቀመጡ ባለመፍቀድህ የፈጣሪህን ምህረት ጠይቅ፡፡
☛ ከዚህ አፍ እና ልብ ከተለያዩበት ቲያትረኛ ማንነትህ ፈጥነህ ውጣ ፡፡
⚠️የሳቀልኝ ሁሉ ስው እየመሰለኝ ጠላቴን ስጠብቅ ወዳጄ ገደለኝ😭
⚠️ ሰዎች ሆይ የሚቀድመውን ብናስቀድም የማይተወን ፈጣሪ ይከተለን ነበር ፡፡
 
📝 ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!!
══════❁✿❁ ═════


ይህንን ልብ እንበል!

የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸዉን እንኳ ያልጨረሱ ባለሃብቶችን አይተናል። ቋንቋ የእዉቀት መለኪያ ባይሆንም በእንግሊዘኛ የመግባባት አቅማቸዉ ፍፁም ደካማ የሆኑ ነገር ግን በስነጥበባት አለም ከዋክብት የምንላቸዉን ተዋናዮች አይተናል። በመንደር መድረክ መሪነትና አጫዋችነት ጀምረዉ ትላልቅ ቦታዎች ላይ የደረሱ ጓደኞችን አይተናል። ት/ታቸዉን እያቋረጡ ወደአትሌቲክሱና የስፖርቱ አለም የዞሩ ብዙ ድንቅ ሰዎችንም እናዉቃለን።

የእነዚህ ሁሉ መነሻቸዉ አንድ ነዉ።

ህይወትህን እስከመጨረሻዉ መለወጥና ለአንተም ሆነ ገንዘብ ለሚያስፈልጋቸዉ ወገኖችህ ልትደርስላቸዉ የምትችለዉ ዝነኛ መሆን ስትችል ብቻ ነዉ። ዝነኛ የመሆኛ መንገዶቹ ብዙ ናቸዉ። ሁሉም ግን አንተን ከድህነት አለም የማዉጣት አቅም አላቸዉ። በመንደር እስከሃገር ያለዉን እዉነት ልብ ካልከዉ ዝነኝነት ምን ያህል ሃይል እንዳለዉ ይገባሃል። በአንድ በተለየ ነገር ዝነኛ መሆን ከቻልክ ለዚህ ሲባል ሰዎች የበለጠ ሊከፍሉህ፣ ሊሸልሙህ፣ ሊያከብሩህና ቦታ ሊሰጡህ ዝግጁ ናቸዉ። ለዚያ ነዉ ሶስት አመት ሙሉ ደክመዉ ከዩኒቨርሲቲ ሲባረሩ እያየህ ምንም አይነት የት/ት አለም ያልነካቸዉ ሰዎች የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሲቀበሉ የምታየዉ።

ዝነኛ የሚያደርግህን ነገር ፈልግ። ሰዎች የሚወዱልህና የሚያደንቁልህን ነገር ለይ። ወደኋላ የሚጎትቱህን፣ የሚያሾፉብህንና ሊንቁህ የሚሞክሩትን ሰዎች ቆርጠህ ጣል። ፈጣን፣ አቋራጭ፣ ዘላቂና አስተማማኝ የህይወትና የገንዘብ ነፃነት ያለዉ በዚህ ብቻ ነው

ሼር ለሚወዷቸው👇👇👇👇👇👇


ለመኖር


ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪውን በወዳጁ ሰርግ ላይ ያየዋል። ሮጦ ሄዶም በትህትናና በአድናቆት ሰላም ካለው በኃላ "አስታወስከኝ?" አለው። አስተማሪውም ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ "ይቅርታ አላስታውስኩህም እንዴት እንደተዋወቅን ልትነግረኝ ትችላለህ?" በማለት መለሰለት፡፡

ወጣቱም ልጅ እንዲህ እያለ ተረከለት "3ኛ ክፍል እያለን ያንተ ተማሪ ነበርኩ። ታዲያ አንድ ቀን የክፍል ጓደኛዬን ቆንጆና ልዩ የሆነውን የእጅ ሰዓቱን ሰርቄበት ነበር። እሱም እያለቀሰ ሄዶ የእጅ ሰዓቱ እንደተሰረቀበት ላንተ ይናገራል፤ አንተም መጥተህ ልትፈትሸን ሁላችንም ክፍል ውስጥ ያለን ልጆች ዐይናችንን ጨፍነን እጃችንን ከፍ አድርገን ፊታችንን ወደ ግድግዳ አዙረን እንድንቆም አዘዝከን።

በዛን ጊዜ እኔ የፍተሻውን ውጤት ፈራሁ፤ የምገባበትንም አጣሁ። አስበው ሰዓቱ በኔ ኪስ ውስጥ ተገኝቶ ሁሉም ተማሪ ሌባ እያለ ሲሰድበኝ፤ ግቢ ውስጥ መጠቋቆሚያ ስሆን፤ ከት/ቤት ተባርሬ ወላጅ አምጣ ስባልና ወላጆቼ ይሄን አሳፋሪ ድርጊቴን ሲሰሙ። በዚህ ጭንቅ ውስጥ እያለሁ የፍተሻው ተራ ደርሶ እጅህ ወደ ኪሴ ሲገባና ሰዓቱን ቀስ አድርገህ ከኪሴ ስታወጣ ተሰመኝ፤ በቃ መጥፎ ዜናውን ልነገር ነው አለቀልኝ ብዬ ስጠባበቅ አንተ ግን ምንም ሳትል የመጨረሻው ልጅ ጋር እስክትደርስ ፍተሻውን ቀጠልክ። ፍተሻውም ሲያልቅ ዐይናችሁን ግለጡና ወደየቦታችሁ ተመለሱ አልከን። እኔ ግን መልሰህ ታስቆመኛለህ ብዬ መቀመጡን ፈራሁ። በጣም የሚገርመው አንተ ሰዓቱን አውጥተህ ለባለቤቱ መለስክለት፤ ግን ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኘህና ማን እንደሰረቀበት ምንም አልተናገርክም ነበር።

በት/ቤት ቆይታዬም ምን እንደተፈጠረ ማንም አላወቀብኝም ነበር፤ አንተም ምንም ብለኸኝ አታውቅም። እኔ ግን ስሜንና ክብሬን እንዳደንክና ስብዕናዬን እንደጠበክልኝ ዛሬም ድረስ አስታውስሃለው። አንተም ይሄን ታሪክ ቶሎ ትረሳለህ ብዬ አልገምትም አሁንስ አስታወስከኝ?" አለው።
አስተማሪውም በመገረም ውስጥ ሆኖ "ትንሽ ትንሽ አስታውሳለው በማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛሁ ግን አላስታውስም፤ ምክንያቱም ማን እነደሰረቀ ማወቅ ስላለፍለኩኝ እኔም ስፈትሻችሁ የነበረው አይኔን ጨፍኜ ነበር!!" አለው።
***
ይቅር መባባል ከባድ ነው?


ከ18 ዓመት በታች ሊግ ውስጥ ለአንድ ቡድን አብረን ስንጫወት ሳለ አንድ መልማይ ሊጎበኘን መጣና፤ "በዛሬው ግጥሚያ ከእናንተ መሃከል ብዙ ግቦችን ያስቆጠረ አንድ ልጅ አካዳሚውን ይቀላቀላል" አለ። እናም የኛ ቡድን ይህንን ግጥሚያ 3 ለ 0 አሸንፈ። የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥሬ ነበር አልበርት ሁለተኛውን በአስደናቂ ቴስታ ከመረብ አሳረፋት። ሶስተኛው ጎል ግን ለሁላችንም አስፈላጊ ነበር። አልበርት ከበረኛው ጋር አንድ በአንድ ተገናኘ እና አታልሎት አለፈ፤ እኔ ከኋላው እየሮጥኩኝ ነው። ማድረግ የነበረበት ግብ ማስቆጠር ብቻ ነበር እሱ ግን ኳሷን ወደኔ አቀበላት፤ ያኔ እኔ ሶስተኛውን ግብ ከመረብ አገናኘሁ። ስለዚህ ወደ አካዳሚው የምሄድበት ሁኔታ ተመቻቸ። ከጨዋታው በኋላ እሱን ለማየት ሄጄ ለምን ስል ጠየቅሁት። አልበርት እንዲህ ሲል መለሰ "አንተ ከእኔ ትበልጣለህ"። ይህን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ነው...

ይህን የሰሙ ጋዜጠኞች ወደ አልበርት ቤት ሄደው ይህ ታሪክ እውነተኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ጠየቁ። እሱም አዎ አለ። በተጨማሪም ከዚህ ጨዋታ በኋላ የተጫዋችነት ህይወቱ እንዳበቃ እና አሁን ስራ አጥ እንደሆነ ነገራቸው። ግን እንዴት ይህን የመሰለ አስደናቂ ቤት ፣ መኪና አለህ? ሀብታም ሰው ትመስላለህ። እንዲሁም ቤተሰብህን መንከባከብ ችለሃል። ይህ ከየት ይመጣል?" ሲሉ ጋዜጠኞች ጠየቁ፤ አልበርት በኩራት “ከሮናልዶ ነው” ብሎ መለሰ! ”
***
ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ጓደኛ አላችሁ?
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንባብ ለህይወት


Forward from: ንባብ ለ ሕይወት
ፖርቹጋላዊው ደራሲ እና ቅዱስ ላሊበላ
ደራሲው ድንቅ ጉዳይ ጽፏል!
(ጥበቡ በለጠ)

በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማለትም በ1520 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ፣ ሐገራችንን ጎብኝቶ፣ ስድስት አመታት ቆይቶ ወደ ሐገሩ ከተመለሰ በኋላ ስለ ኢትዮጵያ የተመለከተውን ታሪክ በግዙፍ መጽሐፍ አድርጎ ያሳተመው ቄስ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ ይባላል። አልቫሬዝ የፖርቹጋል መንግስት መልዕክተኛ ነበር። ኢትዮጵያን ከተመለከቱ ታላላቅ መጻሕፍት ውስጥ ከግንባር ቀደሞቹ ነው። የታሪክ ሀብት አለው።

አልቫሬዝ ወደ ቅዱስ ላሊበላ አብያተ- ክርስቲያናት ዘንድ አመራ። አያቸው። ደነገጠ። እንዴት ሊሆን ቻለ? እንዴትስ ተሰሩ? ምን ጉድ ነው? ብሎ ተገረመ። ፈዞ ተገርሞ አያቸው። በ1520 ዓ.ም። በኋላም ስለ ላሊበላ አብያተክርስትያናት በመጽሐፉ ላይ የሚከተለውን ጻፈ።

" ስለ ላሊበላ አብያተ - ክርስትያናት ላላያቸው ሰው እንዲህ ናቸው ፣ ይህንን ይመስላሉ ብዬ ብጽፍ የሚያምነኝ የለም። ነገር ግን የምጽፈው ሁሉ ዕውነት መሆኑን በኃያሉ በእግዚአብሔር ስም እምላለሁ!"

በማለት በመሐላ አስደግፎ "ዘ ፖርቹጊስ ሚሽን ኢን አቢሲኒያ" በተሰኘው ታላቅ መጽሐፉ ውስጥ አስፍሯል።

ላሊበላ ትንግርት ነው። የጥበባት ሁሉ አውራ ነው። የኢትዮጵያ የዐይን ብሌን ነው። የአለም ቅርስ ነው። ሐይማኖት ነው። ከምንም በላይ ውድ ነው። መተኪያ የለውም። በዋጋ አይተመንም። ኢትዮጵያ መስዋዕትነት ልትከፍልለት የሚገባ መንፈስ እና ሰጋዋ ነው። ካለ ላሊበላ ኢትዮጵያን ማሰብ አይቻልምና!
ፈጣሪም ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ይጠብቅልን።


Forward from: ንባብ ለ ሕይወት
አንዲት አሮጊት እናት ዘወትር በረባው ባልረባው የሚጨቃጨቁ እና የሚጣሉ ሁለት ወንድ ልጆች ነበራት፡፡ አለመግባባቶቻቸውን በምክር እና በተግሳፅ ለመፍታት ብዙ ሞከረች ግን ቀላል አልሆነላትም። እናም ስለ መበደል እና መጥፎ ተግባር እንዲሁም በቅራኔ መለያየት ስለሚያመጣው ነገር በተግባራዊ ምሳሌ ልጆቿን ለማስተማር ወሰነች፡፡

አንድ ቀን ልጆቹን አንድ ጥቅል ጭራሮ እንዲያመጡላት ጠየቀቻቸው፡፡ ይህን ካደረጉ በኋላ ጥቀል ጭራሮውን እንደታሰረ በእያንዳንዳቸው እጅ ላይ በማስቀመጥ የታሰረውን ጥቅል ጭራሮ እንዲሰብሩት አዘዘች፡፡ እነሱ በሙሉ ኃይላቸው ሞከሩ ነገር ግን መስበር አልቻሉም ፡፡

በመቀጠልም ጥቅሉን ፈታችና፤ ጭራሮውን በተናጠል በተናጠል ወስዳ እንደገና በልጆቹ እጅ ላይ አደረገች፡፡ ልጆቹም በቀላሉ ይሰብሯቸዋል ጀመር፡፡ ከዚያም እንዲህ አለች

“ልጆቼ ፣ አንድ አስተሳሰብ ካላችሁ እና እርስ በእርስ ለመተባበር ከተስማማችሁ፤ ጠላቶቻችሁ በቀላሉ የማያሸንፋቹና የማትበገሩ ጠንካራ ትሆናላችሁ። ግን በመካከላችሁ መለያየትና መከፋፈል ካለ በቀላሉ ልትሰበሩ ትችላላችሁ፡፡ ስለዚህም ህብረታቹን አጠንክሩና ጠላትን አስደንግጡት"
ልጆቹ ግን የሰሙ አይመስልም።
***
የዚህች አሮጊት እናት ስም ማን ነው?
እናንብብ እንወያይ ነጻ እውንጣ
ንባብ ለህይወት

20 last posts shown.

11 009

subscribers
Channel statistics