ከ18 ዓመት በታች ሊግ ውስጥ ለአንድ ቡድን አብረን ስንጫወት ሳለ አንድ መልማይ ሊጎበኘን መጣና፤ "በዛሬው ግጥሚያ ከእናንተ መሃከል ብዙ ግቦችን ያስቆጠረ አንድ ልጅ አካዳሚውን ይቀላቀላል" አለ። እናም የኛ ቡድን ይህንን ግጥሚያ 3 ለ 0 አሸንፈ። የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥሬ ነበር አልበርት ሁለተኛውን በአስደናቂ ቴስታ ከመረብ አሳረፋት። ሶስተኛው ጎል ግን ለሁላችንም አስፈላጊ ነበር። አልበርት ከበረኛው ጋር አንድ በአንድ ተገናኘ እና አታልሎት አለፈ፤ እኔ ከኋላው እየሮጥኩኝ ነው። ማድረግ የነበረበት ግብ ማስቆጠር ብቻ ነበር እሱ ግን ኳሷን ወደኔ አቀበላት፤ ያኔ እኔ ሶስተኛውን ግብ ከመረብ አገናኘሁ። ስለዚህ ወደ አካዳሚው የምሄድበት ሁኔታ ተመቻቸ። ከጨዋታው በኋላ እሱን ለማየት ሄጄ ለምን ስል ጠየቅሁት። አልበርት እንዲህ ሲል መለሰ "አንተ ከእኔ ትበልጣለህ"። ይህን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ነው...
ይህን የሰሙ ጋዜጠኞች ወደ አልበርት ቤት ሄደው ይህ ታሪክ እውነተኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ጠየቁ። እሱም አዎ አለ። በተጨማሪም ከዚህ ጨዋታ በኋላ የተጫዋችነት ህይወቱ እንዳበቃ እና አሁን ስራ አጥ እንደሆነ ነገራቸው። ግን እንዴት ይህን የመሰለ አስደናቂ ቤት ፣ መኪና አለህ? ሀብታም ሰው ትመስላለህ። እንዲሁም ቤተሰብህን መንከባከብ ችለሃል። ይህ ከየት ይመጣል?" ሲሉ ጋዜጠኞች ጠየቁ፤ አልበርት በኩራት “ከሮናልዶ ነው” ብሎ መለሰ! ”
***
ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ጓደኛ አላችሁ?
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንባብ ለህይወት