😘ብቀላ😘
🔥ምእራፍ 8
✍ደራሲ ማሪኮሪሊ ቬንዳታ
.
.
.
ሽበቴን በዓሣ አጥማጁ ቆብ ደብቄ ክፍሉን ከፍቼ ለሽማግሌው ታየሁት ። ከድንጋጤው ብዛት የያዘውን እቃ ጥሎ..... ፡ «እረ በእመቤቴ ማርያም! በወጣትነት ዘመንህ እንዴት ጐበዝ ናያማረብህ ሰው ነበርክ» ብሎ ፍጥጥ ብሎ አየኝ " «የለም አንተ ሰው ጠንካራ ነህ አሁንም ተፈለግህ ጠላትህን መግደል ትችላለህ» አለኝ ኪሴ የተረፉ ሶስት ፍራንኮች አውጥቼ እግር ሹራብ ይፈልጉልኝ ብዩ ያወለቅሁትን ልብስ በነጻ ወረወርኩለትና እየመረቀኝ እግር ሹራቡን አውጥቶ ሰጥቶኝ ተላበስኩ
ኔፕልስ ከተማ ያልታየ አዲስ አለባበስና አዲስ ሰው መስዬ ቆምኩ « ለመውጣት ከተዘጋጀሁ በኋላ አንድ ሀሳብ መጣብኝ " ሁኔታ እንዲህ ተለዋውጦ ድንገት ኒና ብታ
የኝ አይጠና ሆድዋ ስለሆነች በድንጋጤ ጉዳት ያገኛታል ብዬ መሽትሽት ሲል መሄድን መረጥኩ " ጊቢዬም ስደርስ በዋናው በር አልገባም ። በጀርባ ገብቼ
ከአሽከሮቼ ለአንዷ አስረድቼ ኒናን ቀስ ብለው ነግረው ስለ ሁኔታዬ አለማምደው ብንገናኝ ይሻላል በዬ ከራሴ ጋር ተወያየሁ ። ሰላምታ ሰጥቼ ልወጣ ስል ሽማግሌው መጥቶ ክንዴን ያዝ ሲያደርገኝ ሊናገር የፈለገው ነገር መኖሩ ገባኝ " ራቅ ያለ መንገድ ነው
የምትሄደው?» ብሉ ጠየቀኝ ።በአወንታ ራሴን አወዛወዝኩ "ለማንም አልነግር' ሚስጢሩ አብሮኝ ይሞታል ሴትጋ ነው በሞቴ የምቴደው ይህን ሲጠይቀኝ ጓጉንቸር የመሰለ ተንኮል ፈላጊ ዐይኑ መልሴን ለመረዳት ይቅበዘበዝ ጀመር ።"አወን ሴትጋ ነው የምሄደው »እንደገና ክንዴን ጨበጥ ጨበጥ አረገና ክንድህ ገና እንደብረት የጠነከረ ነው። ሂድና ግደላት፥ ታማኝነትን ከነፈገችህ ጎደላት» አለኝ። እየሸኘኝ በራፉ ላይ ቆሞ እንደሰይጣን ጥፍራም ጣቱን እየነቀነቀ «እንደ መከርኩህ አድርግ» አለኝ።
ቀኑ በጣም ረዘመብኝ ጊዜ ለመግደል በከተማው ስመጣና ስወርድ እምብዛም የማውቃቸውን አላየሁም በተለይ ከበርቴዎች ኮሌራውን ፈርተው ነው መሰል በመ
ንገድ ላይ አላየኋቸውም ። በየሄድኩበት መአዝን ጥቂት ሰዎች አስክሬን ይዘው
ቀብር ሲሄዱ ማየትን ተላመድኩ:: የሬሣ ሣጥንም ውድ ስለሆነ ትልቁን አስክሬን በትንሽ ሳጥን ለማብቃቃት ቀባሪዎች የሙታን አጥንት እየሰበሩ ጉልበት አጥፈው ሳጥን ሲከቱ ማየት ታከተኝ» በሽተኛው ገና ስልም ከማለቱ ለቀብር ሲያዘጋጁት
ደግሞ ይህ የኔ ጉድ እንዳይደርስ «መሞቱን አስቀድማችሁ አረጋግጡ። ብዬ
ስጮህ የሟቹን ጭንቅላት እንደተድበለበለ ድንጋይ ከግራ ወደቀኝ እያጋጩ «ይኸ ህይወት ካለው እኔ አንገቴን እሰጣለሁ»ብለው ከፋኞች ዐይናቸውን አፈጠጡብኝ ያን ቦታ ጥዬ ወረድ ስል አንዲት ወፍራም ሴት ሬሳ ከሚሰበስቡት ጋር ትጣላለች ። «አንዲት ደቂቃ ስጡንና መሞት መኖርዋን እንለይ» ትላቸዋለች ። በርዋ ጠጋ ብዬ ስመለከት አልጋ ላይ አንዲት እንቅልፍ ያሸለባት የምትመስል እንቡጥ ሴት ልጅ ፀጉርዋን በትና ተኝታለች ። የፊትዋ ወዝ ገና አልተከተተም ። ከጐንዋ አንድ ሰው ደረትዋን ጥርቅም አድርጉ ፀጉርዋን ተላብሶ ሙቀት የማይሰጠውን ገላዋን ሞጭጮ ተኝቷል ነፍስዋ ከወጣ ጀምሮ ሙሉ ሌሊት ቀኑን ጨምሮ ላይዋ ደርቆ መዋሉንም ሴትየዋ በሩን እየጠበቀች በጆሮዬ ነገረችኝ በሩን በርግጄ ራሴን ስቼ
ጠባብዋ ክፍል ስገባ እንባ አንቆኛል የሞት እልህ ተናንቆኛል ።እንደምንም አለስልሼ ሰውዬ በእውነተኛ ፍቅር እኮ ሞት የለም» አልኩት ። ከሙታን መሀል የማይሞት ፍቅር አይቼ እንባዬ ቦዩን ስቶ በአራት መአዘን ፈሰሰ ። «ፍቅርህ እውነተኛ ከሆነ
ዘለዓለማዊነትን ስጠው» ብዬ ስጮህ ምስኪኑ ፍቅረኛ እጁን ሰብስቦ በተስፋ
መቁረጥ እያለቀሰ ቀና ብሎ አየኝ የቀዘቀዘ እጁን ደግፌ ከአልጋ ላይ ወረደ።
ሴትዮዋን ጠርቼ እሬሳዋን መከፈን ጀመረች ። ከዚህ ቤት እንደወጣሁ ትዝ ያለኝ የራሴ ሬሳ የወጣበትን ሻይ ቤት እንደገና መጐብኘት ስለነበር በብዙ ችግር ፈልጌ አገኘሁት ። የሻይ ቤቱ ባለቤት ብርጭቆውን እንደወትሮው እየወለወለ ፡ «እህ አቶ አሣ አጥማጅ ሥራው የተቃና ነበር» ብሎ አናገረኝ ። ለአፍታ ተምታታብኝ ።ወዲያው ሁሉን ነገር አስታወስኩና በፈገግታ አወንታዬን ከገለጽኩለት በኋላ «እርስዎስ
እንደምን ነዎት ፡ ኮሌራውስ?» አልኩት ። «የኮሌራው ነገር አይነሣ» አለኝ። ራሱን እየነቀነቀ«ሕዝቡ እንደ ዝንብ እየረገፈ ነው ። የትናንትናውንማ ቅዱስ ዮሴፍ
አይመልሱት።» «ምነው ምን ተፈጠረ ትናንት እኔ እኮ ገና መግባቴ ስለሆነ የከተማውን ዜና አልሰማሁም» እየተጠራጠረና በሀሳቡ እየተጨነቀ «የትናንቱን ጉድ እንዴት አልሰማህም? የባለፀጋውን ጌታ ሮማኒን በኮሌራ አሟሟት አልሰማህም?» አለማወቄን ጭንቅላቴን አወዛውዤ ገለጽኩለት «ምን ያደርጋል ወንድሜ እንደ ንጉሥ ይከበር የነበረው ባለፀጋ ጌታ ሮማኒ ዛሬ የለም ። ትናንትና የአጥቢያችን ትልቁ መነኩሴ ጐትተው እዚሁ ቤት አምጥተው እግርህ አጠገብ ያለው ቦታ አስተኝተውት ነበር ። አንሱኝ
መልሱኝ ሳይል ፣ ሀጥያቱንም ሀብቱንም ሳይናዘዝ በአንድ ቀን ጀምበር በተስቦው ተለክፎ ሞተ ። ጥቂት ከተከዘ በኋላ «ምን ይኸ ብቻ መሰልዎት ጉዱ ። እኒያ ቅዱስ መነኩሴ እስከመጨረሻው ሳይለዩ አስከሬኑን ሲከፍኑ በሽታው ያዛቸውና ዛሬ ጠዋት እርሳቸውም እንደሱው አፈርቀምሱ» በሀዘንና በድንጋጤ የቀረበልኝን ቡና እየመረረኝ ቀመስኩ ። ሀዘኔ ግን እንዳይታወቅ ተረጋግቼ ማድመጥ ጀመርኩ ።
«መነኩሴው የራሳቸውን የደረት መስቀል ደረቱ ላይ አድርገውለት አባቶቹ መቃብር አስተኙት ሰዓቱንና የሲጃራ መያዣውን ለባለቤቱ ሰጥተው መርዶውንም እርድተው በበሽታው በስለው ተመለሱ ኒናዬ ትዝ አለችኝና ጥያቄዬ ከአፌ አምልጦ ወጣ።
«የሟቹ ባለቤት ሀዘንዋን እንዴት ቻለችው መቼም አብዳ ይሆናል" ሴቶች እንኳ በሁሉ ነገር ያብዳሉ እንኳን ለባል ሞት ለበግና ፍየል ሞት ያብዳሉ ብቻ ቄሱ ተይዘው ስለ ነበር ይኽን ሁሉ አልተናገሩም ። » ይህን ስንነጋገር በበሩ እንድ ሰው በዝግታ እርምጃ አለፈ ። ጓደኛዬን ጉዶፈራሪን መሰለኝ ። ዘልዬ ልጠመጠም
በት ከጀልኩ ። የሆነ ነገር መለሰኝና በዐይኔ ተከተልኩት ፒፓውን ያጨሳል ከፊቱ ፈገግታ ይታያል ። እኔው ቅጽር ግቢ የሚበቅል የጽጌረዳ አበባ ኮሌታው ላይ ሰክቷል ።
ስሜቴ ሁሉ በአንድ ጊዜ አመድ ትቢያ ነከሰ ። ያየሁትን ማመን አቃተኝ ። የመጨረሻው ውድ ጓደኛው ገና ትናንትና ሞቶ የእርሱ ገጽታ ግብዣ ቤት የሚሄድ ደስተኛ ይመስላል እንዴት ሊሆን ይችላል? ከንዴቴ ብዛት ሳቄ መጣ ።ሌላም ሀሳብ በተቃራኒው መጣብኝ ። እኔ ጓደኛው የሞትኩት ገና ትናንት ነው ። የሀዘን ሥርዓት የሚጠይቀውን ገና ሳያሰላስል ይችላል ። ጽጌረዳውም ቢሆን ልጄ ስቴላ አድርጋለት እርስዋን ለማስደሰት ኮሌታው ላይ ትቶት ይሆናል ። ብቻ ለሁሉም ማምሻዬን ቤቴ ስገባ እረዳለሁ ብዬ ልከተለው የነበርኩትን ትቼ ሂሣቤን ከፍዬ በሌላ
አቅጣጫ መንገዴን ቀጠልኩ ።ሞትን አሸንፎ ወደ ፍቅርና ደስታ የሚመለስ ድል አድ
ራጊየሚሄደውን እርምጃ እየተራመድኩ ምሽትን እጠባበቅ ጀመር ትእግስቴ ሲያልቅ ጀንበርዋ ጠለቀች በጣም የተጠበቀው ምሽት መጣ።ንፋሱ ቀዝቀዝ ብርሀኑም ደብዘዝ እለ።ወደ ቪላ ሮማኒ የሚወስደውን ዋና መንገድ ይዤ ሳዘግም ፀሐይዋ
ትታው ያለፈችውን አድማስ ጨረቃዋ ዝግ እያለች ተረከበች የልቤ ትርታ እየጨመረ ጉልበቴ በደስታ ብዛት መደነቃቀፍ ጀመረ መንገዱ ግን ያለወትሮው ረዘመብኝ ። መድረስ አይቀር በመጨረሻው ዋና በር ደረስኩ
የግብዬ በር ግጥም ብሉ ተቸንክሮአል ። የቤቱ ጠረኑ አወደኝ ፈገግታዬ ሁሉ ተመለሰ።የሁኔታዬ መለዋውጥ ዋናውን በር አስከፍቶ የሚያስገባ ስላልሆነ በብርቱካን አጸድ