😘ብቀላ😘
🔥ምእራፍ 9
✍ደራሲ ማሪኮሪሊ ቬንዳታ
.
.
.
በቀይ ጽጌረዳ ፋንታ ቀይ ደም በአናትዋ ማፍሰስ ይገባል:: ፊትዋ የሀዘን ምልክት ጨርሶ የለበትም ፍቅርን ብቻ ያመነጫል ያ ከገነት በራፍ እንደሚፈልቅ ምንጭ ይጣፍጠኝ ነበር ድምጽዋ በሰራ አካላቴ እንደመርዝ ተሰራጨ በሰፊው ስታነበንብ ሰማኋት ። የሚባባሉት አንድ በአንድ አንጐሌን እያነደደ አዳመጥኩ ።«አንተ ተላላ ጉዶ ለመሆኑ ፋቢዩ ባይሞት ምን ይውጥህ ነበር አንድቀን ነገሩ ቢታወቅስ?»
«በብልሐትሽ እንዳመሉ ትይዢዋለሽ እስከመቼም የሚታወቅ አይመስለኝም ።»
«ብቻ እንኳን ሞተ አረፍኩ ። ከእንግዲህ ግን እንደፈለግነው ልትጐበኘኝ አይገባም አሽከር ገረዱ ያወራል ። ቢያንስ ስድስት ወር አዝኜ መታየት አለብኝ ።» «ግን እንዳትዘነጊ ፋቢዩ መሞቱ ጉዳትም አለው "ለሁለታችንም የገንዘብ ምንጫችን ነበር “» እንደቆመች በኔው ፊት ከደርዘን ጊዜ በላይ ሳማት በቀጠሮ ደሙን ለማፍሰስ ወደ ኋላ እንደሚሄድ ነብር ድምጼን አጥፍቼ ማፈግፈግ ጀመርኩ የእግሬ ኮሽታ ይሁን ሌላ ኒናን ጥርጣሬ አሳደረባትና' «እሽሽ ዝም በል ። እርሱ የሞተው ገና ትናንት ነው
ጳረሞት የራሱን ግቢ ይጐበኛታል ይባላል እኮ።እንዲያውም በሕይወት ዘመኑ ይህን ቦታ ይወደው ነበር ። እዚህ በመምጣታችን አጥፍተናል » እንደመጸጸት እያለች
«ምንም ቢሆን የልጄ አባት እኮ ነው ።» «ባልሽ መሆኑን መቼ አጣሁት በሳመሽ ቁጥር ቅናት ያቃጥለኝ ነበር ።» ከእናት ልጅ የምቀርበው ጓደኛዬ መቃብሩን በገዛ እጁ ሲቆፍር ቆሜ አደመጥኩ ። ባል ሚሽቱን ሲስም ውሽማ የሚቀናበት ጊዜ መጣ? ትከሻው ላይ በተበተነው ፀጉርዋ እየተጫወተ «ለምንድነው ለመሆኑ ፋቢዩን ያገባሽው?»አላት ። «የገዳም ኑሮ አሰልችቶኝ ነው ። ከዚህም በላይ እርሱ ሀብታም ነበር። ደሀ መሆንን እንደሞት እጠላለሁ ። በዚህ ላይ ደግሞ አፈቀረኝ ።» በኩራት ወደሰማይ አንጋጣ «አዎን በፍቅሬ አብዶ ነበር ።» «አንቺስ አላፈቀርሽውም እንዴ?"
«ለአንድ ሁለት ሳምንት አፍቅሬው ነበር መሰለኝ ። ከዚያም ወዲያ ጋብቻ ሆነ ። ሀብትም ክብርም እድልም ሰጠኝ ።» «ጋብቻሽ ከኔ ጋር ቢሆን ኖሮ ግን ምንም የምታገኝው ነገር የለም ማለት ነው? «አንተን በፍቅረኝነት መያዙ በቂ ነው " ከዚህ በላይ ሌላውን እርግጠኛ አይደለሁም ። አሁን ግን ነጻ ነኝ ። ነጻነቴን ማስከበር አለብኝ ። የፈለግሁትን ማድረግ እችላለሁ ።»ንግግርዋን አላስጨረሳትም የንዴትም የፍላጐት ግፊት ይዞት ጎትቶ ደረቱ ስር ጨመቃት «ኒና ልታሞኝኝ አትሞክሪ " የሰርግሽ እለት በፍቅርሽ ተነደፍኩ ። መልአክ እንዳልሆንሽ ስለማውቅ ጊዜዬን ጠበቅሁ " ባገባሽ በሶስተኛ ወር የፍቅር ምኞቴ ነገርኩሽ " ከዚያ በኋላ በነገርም በምልክትም ፈቃድሽን ገለጽሽልኝ ። ፋቢዮ ባልሽ የሆነውን ያህል እኔም የባልሽ ያህል ነበርኩ ። በሀጥያቴ አልጸጸትም ። ፋቢዩ
አምኖኝ ከአንቺ ጋር ሊለቀኝ አይገባም ነበር ። በገዛ እጁ ለሀጥያት ዳረገኝ።
ስለዚህ በምንም ምክንያት ከእጀ ልትወጪ አትችይም » ኒና በአነጋገሩ ተቆጥታ ከእቅፉ ለመውጣት ታገለች ። «ልቀቀኝ! ትዳፈራለህ በጣም አሳመምከኝ» ለቋት
ለአፍታ ብቻዋን ፀጥ ብላ ቆም እንዳለች እንደገና ይዞ ጨመጨማት «ይቅርታ አድርጊልኝ ላስቆጣሽ አልነበረም ። ውበትሽ ነው እንዲህ የሚያደርገኝ ። ፈጣሪ ወይም ሰይጣን ውበትሽን እንዲህ አስተካክሎ የፈጠረው ተሳስቷል ። የልቤ
ልብ የነፍሴ ነፍስ ነሽ ።» ካለብዙ ትግል ተጠጋችው ። ከንፈር ለከንፈር ተጋ
ጠሙ፡ እነርሱ በተሳሳም ቁጥር እኔንም አዲስ ሾተል አእምሮዬን ወጋው ። ሀሳቤንም እነርሱንም ማዳመጡ ግራ አጋባኝና ፈዝዤ ሳለሁ «ስለዚህ ፍቅሬን አትጠራጠሪ ጊዜ እንዲህ በግላጭ አጋጥሞን የፍቅር በረከቴን ገሸሽ አታድርጊ የጀመርንበትን ጊዜ ታስታውሻለሽ?ፋቢዮ የፕሌቶ መጽሐፉ ላይ ተደፍቶ እኛ ዜማ እየተለዋወጥን ስንዘፍን «ከሁሉ ፍቅር በላይ ያንቺ ፍቅር ይበልጥብኛል ያልኩሽ ትዝ ይልሻል» አላት ተያይዘው መራመድ ሲጀምሩ ባካሄዳቸው ሕሊናቸው ንፁህ ይመስላል ። ከዐይኔ እስኪሰወሩ ተመለከትኳቸው
ጨረቃዋ የደም ብርሀንዋን አለበሰችኝ ። መሬቱን በረገጥኰት ቁጥር የከዳኝ ይመስለኛል ። ምድርም ሰማይም የሰይጣን ሥራና መጫወቻ ሆኖ ታየኝ። ዓለም ላይ የምወዳት ሕይወቴን የምሰጣት አንዲት ሴት ታማኝ ልትሆንልኝ የማትችልበት ምድር ምን ዓይነት የሰይጣን ሥራ ናት ይህች እንድሕይወቴ'የልጄ እናት' በክብር ፈንታ ውርደት የመረጠች ምን መደረግ አለባት? ይኸስ ምንም ነገር ያልነፈግ
ሁት የአንጀት ጓደኛዬ ምን ቅጣት ይገባዋል?.«ሂድና ግደላት» ያለኝ የሽማግሌው ድምጽ በጆሮዬ እስተጋባ ።«ሽማግሌው ወንድ ነው።ከመቅጽበት ተበቀለ ። ግን ስለታም በቀል ምንድነው አልኩ ። ረጅም ስቃይ የሚሰጥ በቀል መምረጥ አለብኝ ። በደም ፍላት ገድዩ ወንጀለኛ ተብዬ መጠቆም የለብኝም ።» ጊቢዬ ውስጥ አረፍ አልኩ ።አፌ ደም እንደጐረሰ ነው ። ከንፈሬ ከትኩሳቴ ብዛት ተስነጣጥቋል መመለስ የማይገባኝ ግቢዬ ተመልሻለሁ ጻረሞቴ ግን አይደለሁም ። ለበቀል የተላኩ መሆኔ ገባኝ ።የነበረኝ ሀብት አብሮኝ ባይኖርም በመቃብር ቤቴ ያለው
የሽፍታው ሀብት ከበርቴ ሊያደርገኝ ይችላል ገንዘብ ደግሞ ሊሰራ የማይችለው ስለሌለ የበቀል ዓላማዬን አሳካበታለሁ " ፍጹም ተወዳዳሪ የሌለው በቀል መጠንሰስ አለብኝ ክርስቶስ ጠላቶቻችሁን ውደዱ ያለው በሴት ፍቅር ባለመጠመዱ ነው እኔ ግን ሬትና ማር ቀምሻለሁ " በቀሌን ለኔ እንደሚጥመኝ እደግሳለሁ " በቃ ወሰንኩ ትንፋሼ ቀለል አለኝ " የሶስት ዓመት ተበዳይ ቂሜን የምወጣው ረዘም ብሎ በተሰካ ሳንጃ ነው መነኩሴው እሬሳዬ
ላይ ትተውልኝ ያገኘሁትን መስቀል አውጥቼ ስሜ ቃል ገባሁ የቂም በቀል እርምጃዬን እስክ ፈጽም ላልተኛ በአምላክ ስም ቃል ገባሁ በጨረቃና ከዋከብት ለቃል ኪዳኔ ምስክሬ ሆነው ከተቀመጥኩበት ተነስቼ በገባሁበት የጓር በር ወጣሁና ዋናውን መንገድ ተያያዝኩ ኔፕልስ ያደግሁበት ከተማ ገብቼ እንደባይተዋር በሆቴል የመኝታ ክፍል ይዤ አደርኩ::ሰማይና ምድር ወገግ ሲል ማልጄ ተነሳሁ። " ሌሊቱን ያውጠነጠንኩት የበቀል እቅዴ ተስተካክሎ በኣእምሮዬ
ቅርጽ አውጥቷል። አሁን የቀረኝ በሥራ መተርጎም ብቻ ስለሆነ ድብቅ ዓላማዬን አንድ ብዬ ለመጀመር ባትሪ ፣መዶሻ እና ሚስማር ይዤ ከተመልካች ሁሉ ተደብቄ ወደመቃብር ቤቴ ጉዞ ጀመርኩ ። እንደደረስኩ መቃብር ቤቱ አካባቢ
ብቻዬን መሆኔን እየተገላመጥኩ አረጋግጬ በዚያው የሚስጢር መግቢያ ገብቼ የሀብቱን ሳጥን ከፈትኩ። ሳላምታታ የወረቀቱን ገንዘብ በመልክ በመልኩ እየለያየሁ በኪሴ ከተትኩ። "ከብርቅ ሀብቱ በያዝኩት ከረጢት አጭቄ ባለ ብዙ ሺ ፍራንክ ሆኜ የሀብቱን ሳጥን በያዝኩት መሣሪያ ዘግቼ በገባሁበት ቀዳዳ ተመልሼ ወጣሁ።
ተቻኩዬ ስለነበር አንዲት ደቂቃም በዋዛ ሳላሳልፍ ከኔፕልስ የሚያወጣኝ ጀልባ ፍለጋ ያን ዕለቱን ወደብ ወረድኩ። ጥቂት ሰዎችን ስጠያይቅ አንዲት ወደ ፓሌርሞ የምታመራ ጀልባ መኖርዋን ሰምቼ የጀልባዋን ካፒቴን አስፈልጌ አናገርኩ። ከብዙ ማጠያየቅ በኋላ የፊቱ ቆዳ በፀሐይ ንዳድ የጠየመ ዐይኖቹ ለማሳሳቅ የሚንቀዠቀዡ ካፒቴን አገኘሁ። ካፒቴኑ የጠየቀኝን ዋጋ ከፍዬ በጀልባ ውስጥ ቦታዬን ያዝኩ። "ያስከፈለኝን ገንዘብ በኋላ ሳስላ ከመደበኛው ጋር