መህምሩ ለተማሪዎች ወደፊት ማሳካት የምትፈልጉትን ነገር በሙሉ ጽፋችሁ በነገው ዕለት እንድትመጡ ብሎ አዘዘ..
“በዚያ ምሽት ተማሪው ሕልሙን እና ማሳካት የሚፈልገውን ሁሉ ጻፈ እናም እንዲህ ይል ነበር በመጪው 10 ዓመታት የፈረስ እርሻ ባለቤት እንደሚሆን፣ አራት ሕንጻዎች እንደሚኖሩት፣ 200 ሄክታር የእርሻ መሬት እና 4,000 ካሬ ቤት እንደሚኖረው ጻፈ ለዚህም ዝርዝር የወለል ፕላን አዘጋጀ። እና በሚቀጥለው ቀን ለአስተማሪው አስረከበው። ከሁለት ቀናት በኋላ ወረቀቱን መልሶ ተቀበለ።
አስተማሪው ወረቀቱ ላይ ጉልህ "ኤፍ"አድርጎበታል። ልጁም ተበሳጭና መምህሩን ሄዶ አናገረ።
አስተማሪውም ይህ እንደ አንተ ላለው ወጣት ልጅ ከእውነታው የራቀ ሕልም ነው። ገንዘብ የለህም፣ የድሃ ቤተሰብ ልጅ ነህ፣ ምንም ሀብት የለህም። የፈረስ እርሻ ባለቤት መሆን ብዙ ገንዘብ ይጠይቃል። 4ሺህ ካሬ እና ትልቅ እርሻ ላንተ "ላም አለኝ በሰማይ ነው" ብሎ ተዛባበተበት። እናም እንዲህ አለ "ማታ እንዳዲስ ሊሳካ የሚችል እቅድ ጻፍና ውጤትህን አስተካክልልሃለው"
"ልጁ ወደ ቤቱ ሄዶ ብዙ አሰበበት። አባቱንም ምን ማድረግ እንዳለበት ጠየቀ። አባቱም "ተመልከት ፣ ልጄ፤ እዚህ ጋር የራስህን ሐሳብ መወሰን አለብህ። እኔ ግን በጣም አምንብሃለውና ልብህን ስማ" አለው።
በነገታው እቅዱን ምንም ሳይቀይር መልሶ ለአስተማሪቅ ሰጠ አስተማሪውም በ"ኤፍ ግሬዱ" ጸና።
ከዓመታት በኋላ ያ መምህር አርጅቶም እያስተማረ ሳለ አንድ ቀን ማለዳ ላይ በቴሌቭዥን የአንድ ወጣት ቃለመጠይቅ ይቀርብ ነበር... ወጣቱ ልጅ እያለ አሳካዋለሄ ካለው አንድም ያልቀረው የናጠጠ ሀብታም ሆኖ ነበር። እንዲህ አለ "ሕልሜን አስተማሪዬ ሊሰርቀኝ ሲታገል እንደምንም ነበር የተረፍሁት... እኔም ህልሜን እሱም ኤፉን ወሰደ"
የዛኑ ቀን መምህሩ ለተማሪዎቹ ወደፊት ማሳካት የምትፈልጉትን ጻፉልኝ ብሎ አዘዘ በነገታው መለሱለት ለሁሉም የሰጠው ውጤት "ኤ"ነበር።
*
ሞራል፡ መምህራን የጠቀሙ መስሏቸው የስንቱን ሕልም ሰረቁ። በሕልማችሁ አትደራደሩ ለማሳካት የምታስቡት ሁሉ የሚደረስበት እና የተደረሰበት ነው።
*
ይህ ጽሑፍ ላይ ያላችሁን ሐሳብ በኮሜንት አጋሩን
ከተስማማችሁም ሼር አድርጉት
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ