ከ"ሙኒክ ባሻገር" መፅሐፍ የተቀነጨበ...
"...ሁለቱ ሰዎች ለዘመቻው የምሥጢር ስያሜም ሰጥተውታል፡፡ ኦፕሬሽኑ ‹‹ዘመቻ ኢቅሪት እና ቢሪም›› የሚል ስያሜ የነበረው ሲሆን ስሞቹ የእስራኤል ጦር በ1948 ዓ.ም. ‹‹የደኅንነት ስጋት አለ›› በሚል ሰበብ ያፈናቀላቸው የጥንታዊያኑ የዐረብ ክርስቲያኖች መኖሪያ መንደሮች መጠሪያ ስሞች ነበሩ፡፡
እነዚህ የዐረብ ቤተሰቦች ከትውልድ ትውልድ፣ አያት ቅድመ-አያቶቻቸው ከኖሩባቸው የመኖሪያ መንደሮች እንዲወጡ ሲገደዱ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ትመለሳላችሁ ተብለው ነበር፡፡ ይሁን እና ከዐሥርት ዓመታት በኋላም ፍልስጤማዊያኑ ወደ ቀዬያቸው መመለሳቸውን እየተጠባበቁ ነበር፡፡ ምንም እንኳ አብዛኞቹ እስራኤላዊያን ስለዚህ አሳዛኝ ሁኔታ እውቀቱ ባይኖራቸውም ሁኔታው ለዐረቦቹ የሚጠዘጥዝ ቁስል ነበር፡፡..."
ጥላሁን ግርማ የቁጥር ሰው ነው። ፈረንጅ አገር ሄዶ ተምሮ "እናት አገር ትኑር ለኛ" በማለት በአፍም በመጽሐፍን አገሩን ያገልግላታል። ከዚህ ቀደም የትሬቨር ኖሃን "Born a crime" የአመጻ ልጅ ብሎ በጥራት አቅርቦልን ነበር። አሁን በአዲስ መጽሐፍ በድጋሚ ተከስቷል " One day in September "ን ከሙኒክ ባሻገር ብሎ። ግዙ፣አንብቡ፣ ጋብዙ... መጽሐፉን በሁሉም መጻሕፍት ቤት ውስጥ ታገኙታላችሁ።
***
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ