ሌሊት ነበር፤ አንድ ሰው በመንገድ ላይ እየነዳ መኪናው በገዳሙ አቅራቢያ ይበላሽታል። እናም ወደ ገዳም ሄዶ በሩን አንኳኳ። መነኩሴው ወደ ውጭ ወጥቶ በሩን ሲከፍት “መኪናዬ ተበላሸ። እዚህ ለአንድ ሌሊት መቆየት እችላለሁን?” አለ። መነኩሴውም ጥያቄውን ተቀበለ። መነኮሳቱንም ማቆየት ብቻ ሳይሆን መገቡት አልፎ ተርፎም መኪናውን አስተካከሉለት።
ሰውየው ለመተኛት ሲሞክር እንግዳ የሆነ ድምጽ ሰማ። በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ስለዚያ ድምጽ መነኩሴውን ጠየቀ ነገር ግን መነኩሴው “መነኩሴ ስላልሆንክ ልንነግርህ አንችልም” አለው። ሰውየው ቅር ቢሰኝም አመስግኖት መንገዱን ቀጠለ።
ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ፣ ያው መኪና በተመሳሳይ ገዳም ፊት ለፊት ይበላሻል። አሁንም እንደበፊቱ ሁሉ መነኮሳት ተቀብለው መግበውት መኪናውን አስተካከሉለት። እናም ለመተኛት ሲሄድ ያኛው ሰውዬ ከዚህ ቀደም የሰማውን ተመሳሳይ እንግዳ ድምጽ ይሰማል።
በማግስቱ ጠዋት ስለዚያ ጫጫታ መነኩሴን ይጠይቃል፤ ግን መነኩሴም ተመሳሳይ መልስ ሰጡት “መነኩሴ ስላልሆንክ ልንነግርህ አልችልም" ሰውዬውም "ስለዚያ ድምጽ ለማወቅ መነኩሴ መሆን ግድ ከሆነ፤ እንዴት መነኩሴ መሆን እችላለሁ?” መነኩሴም መለሰ ፣ “መነኩሴ ለመሆን ከፈለክ የምድርን አሸዋ መቁጠር እና ቁጥሩን ለኔ መንገር አለብህ ይህን ስታገኝ መነኩሴ ትሆናለህ ”አለው።
ሰውየው ለዚህ ተግባር ተነስቶ ከአርባ ዓመታት በኋላ ተመልሶ የገዳሙን በር አንኳኩቶ “መላውን ምድር ተዘዋውሬ 222,345,323,954,110,958,203 የአሸዋ ጠጠር በምድር ላይ እንዳለ አገኘሁ” አለ።
መነኩሴ ሰውየውን በማመስገን “አሁን ወደ ድምጹ የሚወስደውን መንገድ እናሳይሃለን” አለው። መነኩሴ ወደ አንድ የእንጨት በር እየመራው “ሰውየው የሚፈልገው ድምፅ ከዚያ በር በስተጀርባ ነው” ሲል ሰው ተደሰተ። በሩን ለመክፈት ሲሞክር ግን ያ በር እንደተዘጋ ተረዳ። ስለዚህ በሩን ለመክፈት ቁልፉን እንዲሰጠው መነኩሴውን ጠየቀ። መነኩሴ ቁልፉን ሰጠው። ሰው በሩን ከፍቶ ከዚያ በር ጀርባ ከድንጋይ የተሠራ ሌላ በር አየ። ዳግመኛ ሰው በሩ እንደተቆለፈ ስላየ የዚያ በር ቁልፍ ጠየቀ። ሰው የድንጋይ በር ሲከፍት ከወርቅ የተሠራ ሌላ በር አገኘ ግን ተቆልፏል።
መነኩሴ የዚያን በር ቁልፍም ሰጠው። እንደገና ከሩቢ የተሠራ ሌላ በር ነበር። በሌላ ተከታታይ በር እስኪያልፍ ድረስ ይህ ይቀጥላል። በመጨረሻ መነኩሴ “ይህ የመጨረሻው በር እና እዚህ የዚህ በር ቁልፍ ነው” አለ። ሰውየው በመጨረሻ እፎይታ አግኝቶ በሩን ከፍቶ ገባ እና ከዚያ በር በስተጀርባ የድምፅ ምንጭ በማግኘቱ ተገረመ ግን ምን እንደ ሆነ ልነግራችሁ አልችልም .. ምክንያቱም እናንተ መነኩሴዎች አይደላችሁም።
*
ኃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን። ሌሎች ታሪኮችን እና የመጻሕፍት ጥቆማዎች ለማግኘት ገጻችንን ላይክ፤ ለሌሎች እንዲደርስ ደግሞ ሼር ያድርጉ። እናመሰግናለን!
*
ሁሉንም ነገር ማወቅ አለብን ብላችሁ ታስባላችሁ?
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንበብ ለንባብ
***