🩸
አል-ፉርቃን ጥፋቷ ምንድን ነው?✍️ بسم الله الرحمن الرحيم ሚቅዳድ ኢብኑ አስወድ ባስተላለፈው የታወቀው ሓዲስ ላይ ነብዩﷺ እንዲህ ይላሉ፦
📚
«إن السعيد لمن جنب الفتن إن السعيد لمن جنب الفتن إن السعيد لمن جنب الفتن ولمن ابتلي فصبر فواها»
«ደስተኛ ማለት ፊትና የራቀ ነው፤ ደስተኛ ማለት ፊትና የራቀ ነው፤ ደስተኛ ማለት ፊትና የራቀ ነው: በፊትና ተሞክሮ የታገሰ (የፀና) ሰው ምንኛ የታደለ ነው።» ከአፋቸው ሐቅ እንጂ ባጢል የማይወጣ፤ በስሜት ሳይሆን በወሕይ የሚናገሩት ውዱ ነብዩﷺ በትክክል ደስተኛ እና በእውነት እድለኛ የሆነ ሰው ማለት
«ፊትናን የራቀ ነው» በማለት ሦሥት ጊዜ ደጋግመው አረጋገጡ።
ተመሳሳይ በሆነ ትርጉም ከትልቁ ሰሀብይ አቡ ሁረይራ በተላለፈው እንዲህ ይላሉ፦
📚
«ستكون فتن القاعد فيها خير من القائم والقائم فيها خير من الماشي والماشي فيها خير من الساعي ومن يشرف لها تستشرفه ومن وجد ملجأ أو معاذا فليعذ به»
«ፊትናዎች ይከሰታሉ: (በዚህ ጊዜ) የተቀመጠው ሰው ከቆመው ሰው ይሻላል፤ የቆመው ሰው ከሚራመደው ሰው ይሻላል፤ የሚራመደው ሰው ከሚሮጠው ሰው ይሻላል። ለእሷ ብቅ ያለላት ብቅ ታደርገዋለች፤ ከእሷ መጠበቂያ ወይም መከለያ ያገኘ ሰው በእሱ ይጠበቅ ይከለል።» አይቀሬ ነው: ቂያማ በተቃረበች ልክ ፊትናዎች ይከሰታሉ ይደራረባሉ። በዚህ ሰዓት ነጃ ለመውጣት፣ ሰላም ለማግኘት፣ አኼራህን እና ማንነትህ ለመጠበቅ ብቸኛው አማራጭ መልእክተኛውﷺ ባመላከቱት መልኩ በተገኘው አጋጣሚ ከፊትናው መራቅ እና መሸሽ ነው።
አቡ ሰዒድ አል_ሁድሪይ ያስተላለፈው ቀጣዩን ሐዲስ እንመልከት፦
📚
«يوشِكُ أن يَكونَ خيرُ مالِ المسلِمِ غنمًا يتبعُ بِها شَعَفَ الجبالِ ومواقعَ القطرِ يفرُّ بدينِهِ منَ الفتنِ»
«የአንድ ሙስሊም ምርጥ የሆነው ሀብቱ: የተራራ ጫፍ እና የዝናብ ጠብታ ወዳለበት ይዟቸው የሚሰደድ በጎች የሆንበት ዘመን ይደርሳል፤ ይህ የሚያደርገው በዲኑ ከፊትና እየሸሸ ነው።»
ፊትናን በመራቅ፣ ፊትናን በመሸሽ ዙሪያ የመጡ ሓዲሶች እዚህ ቦታ ተዘርዝረው ሚያልቁ አይደሉም። አላህ ግልፅም ይሁን ድብቅ ከሆኑ ፊትናዎች ይጠብቀን!!
ተወዳጁ
"አል-ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱድዮ"ም ይሁን በስሩ የሚንቀሳቀሱ ቻናሎች: ከላይ የተጠቀሱት የረሱል(
ﷺ) አደራዎች በመያዝ አላህ ባስቻለው ልክ ከፊትና ርቀውና ተጠብቀው ይገኛሉ። ቢሆንም ግን
"ዝሙተኛዋ ሴት ሴቶች በአጠቃላይ ዝሙተኛ እንዲሆኑ ተመኘች" እንደተባለው ስራቸው እና መሰረታቸው ፊትና የሆኑ ቻናሎችም ይሁን ግለሰቦች
"አል-ፉርቃን"ም ወደዚህ ደባሪ ጨዋታ ለማስገባት ቀን ማታ ሳይሉ በመወትወት እና በመጣራት ላይ ይገኛሉ።
⭕️
ውድ የአልፉርቃን ቤተሰቦችና አንባቢያን……… ሁላችሁም እንደ ምታውቁት እና እንደምታዩት ስቱድዯአችን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ አላህ ባስቻለው መልኩ ሸሪዐው ከሚቃረኑ ከሆኑ ከየትኛውም የብሄር፣ የቡድን፣ የወገንተኝነትና ከተለያዩ ሸሪዐው ከሚፃረሩ የመጥፎ አመለካከቶች ነፃ በሆነ መልኩ ለህዝበ ሙስሊሙ ይጠቅማሉ ብሎ ያመነባቸው ሸሪዐዊ ትምህርቶች በማሰራጨት ላይ ይገኛል። የአላህ መሺዐ(ፍላጎት) እስከፈቀደው ጊዜ ድረስ በዚሁ መልኩ የሚቀጥል ይሆናል።
⭕️
በምድር ላይ የአላህ ሱና ሆነና……… ኸይር ለመስራት ዲን ለመርዳት በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ከቅርብም ይሁን ከሩቅ ተቀናቃኝ ጠላት አያጣቸውም።
"አል_ፉርቃንም" በተመሳሳይ መልኩ ከወቃሽ ወቀሳ መትረፍ አልቻለችም።
⭕️
እነዚህ በባጢል ወቃሾች እነማን ናቸው? ከተባለ……🫵ከዚህ በፊትም
"አል_ፉርቃን" ላይ የሚተላለፈውን ኸይር በመጥላት የነበሩ ሲሆኑ: አሁንም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በሰዎች ልብ ላይ የ
"አል_ፉርቃን" ጥላቻ ለማስገባት የሚደክሙ፣
🫵
"አል-ፉርቃን" ላይ ከፊትና እና ከጭቅጭቅ በራቀ መልኩ እየተላለፈ ያለውን ኸይር በመከታተል ላይ ያሉ ቤተሰቦች: ከዚህ አስወጥቶ ወደ ሌሎች የፊትና እና የጭቅጭቅ ቻናል ለመጋበዝ የሚጥሩ፣
🫵 ከድሮም ጀምረው
"አል_ፉርቃን" ሲቃረኑ የነበሩ አካላት ሆነው ሳለ: አሁን ላይ ግን ከዚህ በፊት የ
"አል-ፉርቃን" አባል እና ደጋፊ የነበሩ ሆነው አሁን ነገሩ ደብሯቸው የሚቃወሙ የሚያስመስሉ አስመሳይ ቀጣፊዎች ፤
🫵 አንዳንዱ በረቀቀ መንገድ ዐረቦች እንደሚሉት ተቃረን ትታወቃለህ በሚሉት ቀመር በጥሩ የሚታወቁትን በመቃረን ራሳቸውን ለማሳወቅና የቻናላቸው ተከታዮች ቁጥር ለማሳደግ ፈላጊ የሆኑ እና መሰሎቻቸው ናቸው።
⭕️
መታወቅ ያለበት ነገር………… ከቅርብም ይሁን ከሩቅ ሆነው
"አል-ፉርቃንን" በማውገዝ ላይ ያሉ ሰዎች ትልቁ ፍላጎታቸው እና ብሶታቸው: እነርሱ ገብተው እየዋለሉበት ያለው የፊትና ጋጋታ
"አል-ፉርቃን" ላይ እነርሱ በሚፈልጉት ልክ ስላላስተጋባንላቸው እና
ፊትናውን እንዲደርስ የፈለጉበት ቦታ ከአላህ እገዛ በኋላ በ
"አል_ፉርቃን" ዝምታ ምክንያት መድረስ ባለመቻሉ ብቻና ብቻ ነው።
"አል-ፉርቃንም" እንደ ሌሎች ቻናሎች በዚህም በዝያ እያለች የፊትና ነፋስ ብታራግብ እና ቤተሰቦቿም በዚህ ግርግር ቢጦዙ ኖሮ ዛሬ ላይ የሚተቿት ሰዎች ባወዳደሷት ነበር።
ይህ የታወቀ አካሄዳቸው ነው!!⭕️
እንጂማ………… የ
"አል-ፉርቃን" መስራቾችም ይሁን አድሚኖች የሚታወቁ የሆኑ ወንድሞች ናቸው። ቅሬታም ይሁን ሀሳብ ሲኖር ቀርቦ መጠየቅም መውቀስም እየተቻለ: ከዚህ ተቃራኒ በሆነ መልኩ በግልፅም በድብቅም የ
"አል_ፉርቃን" ጥላቻ ብቻ መንዛት በጠላት ሴራ ካልሆነ በምን ሊተረጎም ይችላል??
⭕️
እንድታውቁት……… ከሙኻለፋም ይሁን ከሙኻሊፎች ማስጠንቀቅ እና የሙኻሊፎች ማንነት መግለፅ የዲናችን የዳዕዋችን አንዱ አካል ነው። ስለሆነም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ፣ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ከዚህ በፊት እንደሚደረገው የሚደረግ ይሆናል። የዚህን ዓይነት መልዕክቶች ቋሚ ከሆኑ ፕሮግራሞች ጋ እንዳይጨናነቅ በሚል ራሱን የቻለ
"የሰለፍዮች ረድ በሙኻሊፎች ላይ" የሚል በ
"አል_ፉርቃን" የሚንቀሳቀስ ቻናል አለ። የፈለገ ሰው በዝያ መከታተል እንደሚችል ለማሳወቅ እንወዳለን።
⭕️
የተከበራችሁ የአል_ፉርቃን ቤተሰቦች!! ምድር ላይ ያለው ተጨባጩ እውነታ በዚህ ልክ ከተረዳችሁ እና የችግር ፈላጊዎች ፍላጎት ምን እንደሆነ ከተገነዘባችሁ: ለምቀኛም ይሁን ለጠላት ወሬ ጆሮ ሳትሰጡ ሰላማዊ የሆነውን የመማር ማስተማሩ ፕሮግራም እንድትከታተሉ በአል-ፉርቃን ስም በድጋሚ ግብዣችን እናቀርባለን።
💻ይህ የሰለፍዮች ልሳን የሆነው "አል-ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱድዮ" ነው!!📎
https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio