🤝
ስለ ድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ካለን ልምድ እናካፍላችሁ👉ፈተናው ከሚጀምርበት ሰዓት ከ30 ደቂቃ ቀድማችሁ NGAT Exam Entry Ticket ፕሪንት ያደረጋችሁትን ይዛችሁ በተመደባችሁበት መፈተኛ ክፍል መገኘት። ይህ ማድረጋችሁ አርፍዳችሁ መታችሁ ከምትረበሹ ይልቅ እንድትረጋጉና ፈተናው ላይ ትኩረት እንድታደርጉ ይረዳችኋል።
👉ፈተናውን በምትፈተኑበት ጊዜ አለመጨነቅ ይሄ እንኳን ባይሳካ ቀጣይ መፈተን ስለትምችሉ አብዝታችሁ በመጨነቃችሁ ምክንያት መስራት የምትችሉትንም ጥያቄዎች ሳትሰሩ ትቀራላችሁ።
👉ምንም እንኳን ፈተናው ቀድም ብሎ በቂ ዝግጅት ማድረግ የሚፈልግ ቢሆንም እስከዛሬ ያደረጋችሁት ዝግጅት በቂ እንደሆነ በራሳችሁ ሙሉ መተማመን ሊኖራችሁ ይገባል። ጥያቄው ጠቅላላ እውቀትን የሚጠይቅ ስለሆነ መስራት የምትችሉት ነው በፈተና ጊዜ አትጨነቁ።
👉ፈተና ላይ በጋራ መስራትን ተማምናችሁ አለመግባት። ፈተናው በኮምፒውተር የታገዘ ስለሆነም በጣም ብዙ ኮድ ነው ያለው። ይሄ የማይቻል ነው እራሳችሁ መስራት የምትችሉትንም ጊዚያችሁን የሚያባክንባችሁ ነው።
👉በምትፈተኑበት ጊዜ በስህተት ኮምፒውተራችሁን እንዳትዘጉት መጠንቀቅ። ምክንያቱም እስኪ ከፍት ድረስ ጊዚያችሁን ያባክንባችኋል።
👉ፈተና ላይ ሆናችሁ ጥያቄ በምትሰሩ ሰዓት የከበዳችሁን ጥያቄ ለመስራት በመታገል ብዙ ጊዜ አትግደሉ፤ እሱን ለመስራት ስትታገሉ ሌሎች ቀላል ጥያቄዎችን ሳትሰሩ ሰዓት ሊያልቅባችሁ ይችላልና። ከባዱን ጥያቄ #Flag_Question በማድረግ ዝለሉትና ቀለል የሚሉትን ሰርታችሁ ስትጨርሱ ሰዓት ስለሚተርፋችሁ ወደ ከበዳችሁ ጥያቄ ትመጡና ትሰሩታላችሁ። ነገር ግን ሰአት እንዳያንሳችሁ የምትዘሉት ጥያቄ ብዙ እንዳይሆን።
ለወቅታዊ መረጃ ይቀላቀሉን
👉ቴሌግራም ቻናላችን: @GATExams
👉ቴሌግራም ግሩፓችን: @GATSquad