•
ሂወት ውል የሌላት
#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
ሂወት ትሰጣለች
ደግሞም ትነፍጋለች
አንዱን ስታነሳ
አንዱን ትጥላለች
ኩራዟን ለኩሳ እድል እያዜመች
ሲያሻት ከብርሃን
ስትፈልግ ከጭሱ ታከፋፍላለች
ሂወት እንደዚ ነች
ከቶ ማትገመት ውሏ ያልታወቀ
ድንገቴነቷ ሰው እያሳቀቀ
ጥቁር ስታለብስ ነብስ እየማቀቀ
ያደለች እንደሆን
በሠጠችው ፀጋ ውስጥም እየሳቀ
ግፋ በለው ስትል
ተስፋ እየሰጠች ሆድ የምታባብል
ትንሽ እያሳየች ልብ የምታማልል
ከዚያኛው ቀምታ ለዚኛው መስጠትን
ደርሶ ማደላደል ሁሉን የታካነች
ሂወት እንደዚ ነች
ሂወት እንዳሻት ነች
አዎ በትክክል ቃሉን እመንበት
በሰጠችህ ዛባያ ሳታቆም ዙርበት
ከቶ አታፈግፍግ
ጀርባህን ግረፊኝ ብለህ አታሳያት
ጀግነህ ቁምና ከፊት ተጋፈጣት
ክፉውን ካልወጣህ
ደግን ላታገኘው
ጠንክር ወንድም አለም
አይዞኝ እህት አለም
በርችልኝ እናቴ በል ግፋው አባቴ
ግርፋቷን ፈርቶ ከሩቅ ለሚሸሻት
ገፍታ ብትጥለው ወድቆ ለቀረላት
ቦታ እንኳ የሌላት……………
ሂወት እንደዚ ናት
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel
ሂወት ውል የሌላት
#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
ሂወት ትሰጣለች
ደግሞም ትነፍጋለች
አንዱን ስታነሳ
አንዱን ትጥላለች
ኩራዟን ለኩሳ እድል እያዜመች
ሲያሻት ከብርሃን
ስትፈልግ ከጭሱ ታከፋፍላለች
ሂወት እንደዚ ነች
ከቶ ማትገመት ውሏ ያልታወቀ
ድንገቴነቷ ሰው እያሳቀቀ
ጥቁር ስታለብስ ነብስ እየማቀቀ
ያደለች እንደሆን
በሠጠችው ፀጋ ውስጥም እየሳቀ
ግፋ በለው ስትል
ተስፋ እየሰጠች ሆድ የምታባብል
ትንሽ እያሳየች ልብ የምታማልል
ከዚያኛው ቀምታ ለዚኛው መስጠትን
ደርሶ ማደላደል ሁሉን የታካነች
ሂወት እንደዚ ነች
ሂወት እንዳሻት ነች
አዎ በትክክል ቃሉን እመንበት
በሰጠችህ ዛባያ ሳታቆም ዙርበት
ከቶ አታፈግፍግ
ጀርባህን ግረፊኝ ብለህ አታሳያት
ጀግነህ ቁምና ከፊት ተጋፈጣት
ክፉውን ካልወጣህ
ደግን ላታገኘው
ጠንክር ወንድም አለም
አይዞኝ እህት አለም
በርችልኝ እናቴ በል ግፋው አባቴ
ግርፋቷን ፈርቶ ከሩቅ ለሚሸሻት
ገፍታ ብትጥለው ወድቆ ለቀረላት
ቦታ እንኳ የሌላት……………
ሂወት እንደዚ ናት
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel