Forward from: N£xt Dr€amer$🔱
•
ምነው አትመጪም ወይ?
#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
ዘወትር እያለምኩ
ለወሰደሽ መንገድ ድርሳን እያነበብኩ
አምና ብትቀሪ ለዘንድሮ እያልኩ
ይኸው ስንት ሌሊት ይኸው ስንት ንጋት
በስቃይ ያለፉ ጨለማ ዘመናት
ስጋዬን አራቁተው አጥንቴን አሳስተው
በናፍቆትሽ ሰበብ ህልሞቼን ቀምተው
ይኸው እከፍላለው
የማይታመን ሰው የማመኔን እዳ
በተስፋ ስካሬ
ምሽቱን ስትቀሪ ስጠብቅ ማለዳ
መቅረጥሽ ሲገርመኝ
አሻግሬ እያየው ሰፋ ካለው ሜዳ
ይኸው እኖራለው
ከሚኖሩት በታች ከሞተ ሰው በላይ
ግ'ዝት ተገ'ዝቼ
አትሜው እንድኖር ምስልሽን ካይኔ ላይ
ምነው አትመጪም ወይ?
ጠብቄሽ ደከመኝ
ትዝታሽ ልቤ ውስጥ
ረመጥ ሆኖ ፈጀኝ
ሳስብሽ መኖሩ ማለም ቢታክተኝ
ቢደርስ እርግማኔ
እነደዚህ እያልኩ መራገም አሰኘኝ
ካለሽበት ቦታ
ከባድ አውሎ ንፋስ ይዞሽ በነጎደ
እያወዛወዘ እያንገዳገደ
ደራሽ ጎርፍ ይውሰድሽ
ግንድ እያላተመ ስርቅ ስርቅ እስኪልሽ
ውሃውም ንፋሱም ምናልባት ወደኔ
አምተው ቢጥሉሽ!
ብስራቴ ቢያረጉሽ!
✍ @Lanchisel
join as👉 @Berukpoem
join as👉 @Berukpoem
join as👉 @Berukpoem
ምነው አትመጪም ወይ?
#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
ዘወትር እያለምኩ
ለወሰደሽ መንገድ ድርሳን እያነበብኩ
አምና ብትቀሪ ለዘንድሮ እያልኩ
ይኸው ስንት ሌሊት ይኸው ስንት ንጋት
በስቃይ ያለፉ ጨለማ ዘመናት
ስጋዬን አራቁተው አጥንቴን አሳስተው
በናፍቆትሽ ሰበብ ህልሞቼን ቀምተው
ይኸው እከፍላለው
የማይታመን ሰው የማመኔን እዳ
በተስፋ ስካሬ
ምሽቱን ስትቀሪ ስጠብቅ ማለዳ
መቅረጥሽ ሲገርመኝ
አሻግሬ እያየው ሰፋ ካለው ሜዳ
ይኸው እኖራለው
ከሚኖሩት በታች ከሞተ ሰው በላይ
ግ'ዝት ተገ'ዝቼ
አትሜው እንድኖር ምስልሽን ካይኔ ላይ
ምነው አትመጪም ወይ?
ጠብቄሽ ደከመኝ
ትዝታሽ ልቤ ውስጥ
ረመጥ ሆኖ ፈጀኝ
ሳስብሽ መኖሩ ማለም ቢታክተኝ
ቢደርስ እርግማኔ
እነደዚህ እያልኩ መራገም አሰኘኝ
ካለሽበት ቦታ
ከባድ አውሎ ንፋስ ይዞሽ በነጎደ
እያወዛወዘ እያንገዳገደ
ደራሽ ጎርፍ ይውሰድሽ
ግንድ እያላተመ ስርቅ ስርቅ እስኪልሽ
ውሃውም ንፋሱም ምናልባት ወደኔ
አምተው ቢጥሉሽ!
ብስራቴ ቢያረጉሽ!
✍ @Lanchisel
join as👉 @Berukpoem
join as👉 @Berukpoem
join as👉 @Berukpoem