Gettechinfo ®️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Telegram


info about technology ስለቴክኖሎጂ መረጃ
Facebook ቻናላችንን ይከተሉን
https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Telegram
Statistics
Posts filter


ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እገዛ በሚሰሩ ሮቦቶች የመንገድ ጥገና አካሄደች፡፡

ሮቦቶች እና ሾፌር አልባ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም የተከናወነው የመንገድ ጥገና 158 ኪ.ሜ ርዝማኔ እንዳለው ተገልጿል፡፡

መንገዱ የሀገሪቱን መዲና ቤጂንግን ከደቡባዊ የቻይና ግዛቶች ጋር የሚያገናኝ የፍጥነት መንገድ ነዉ፡፡ በስራዉ ላይ ድሮኖች የመንገዱን አጠቃላይ ገጽታ በመከታተል ምስላዊ መረጃዎችን ያቀርባሉ፡፡ ምስሉ ላይ ያለዉን መረጃ መሰረት በማድረግ ሮቦቶቹ ጥገና በሚያስፈልገዉ የመንገድ ክፍል ላይ በመሰማራት አስፈላጊውን ጥገና ያደርጋሉ፡፡

በስራዉ ላይ የተሳተፉት ማሽኖች በስራ ወቅት ለሚገጥማቸዉ ችግር ምላሽ መስጠት እንዲችሉ ሆነዉ የበለጸጉ ናቸዉ፡፡ በመሆኑም ደህንነቱ የተጠበቀና ወጪ ቆጣቢ የጥገና ስራ መስራት ስለመቻሉ ሀይዌይስ ኢንዱስትሪ የተባለው ድረ-ገጽ ዘግቧል፡፡

ይህ ጅማሮ ጥራታቸውን የጠበቁ መንገዶችን ለመገንባት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ፣ ሮቦቶች እና ሾፌር አልባ ተሽከርካሪዎች ትልቅ አቅም እናዳላቸው ያሳየ ስለመሆኑ ተጠቁሟል። ════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን ወደ ናይጀሪያ ሌጎስ ያደርጋል
*************
በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን ወደ ናይጀሪያ ሌጎስ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን በቅርቡ አዲስ አበባ መግባቱ ይታወቃል።

"Ethiopia Land of Origin" የሚል ስያሜ የተሰጠው አውሮፕላኑ 400 መቀመጫዎች ያሉት ነው። ════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ቻይና ወሳኝ በተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ዓለምን መምራት ጀምራለች ቻይና ወሳኝ በተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ዓለምን መምራት መጀመሯን የአውስትራሊያው የስትራቴጂክ ፖሊሲ ጥናቶች ኢንስቲትዩት ባወጣው ሪፖርት ጠቆመ።
ተቋሙ ባወጣው ሪፖርት ቻይና ከ44 ቁልፍ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ውስጥ በ37ቱ ከምዕራባዊያኑ ቀዳሚ ደረጃን መያዟን አረጋግጧል።
ሰው ሠራሽ አስተውሎ፣ የኤሌክትሪክ ባትሪ፣ ሰው አልባ አውሮፕላን፣ የኑክሌር ኃይል፣ የሮቦት ሳይንስ እና የሕዋ ምርምር ቻይና ከፍተኛ ዕድገት ያሳየችባቸው የቴክኖሎጂ ዘርፎች ናቸው ተብሏል።
በሳይንሳዊ ምርምር ስመ-ጥር የሆኑ 10 ተቋማት ሁሉም ቻይና ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውም ተገልጿል።
አሜሪካ እና አውሮፓ በወሳኝ የቴክኖሎጂ ዘርፎች በቻይና እየተቀደሙ መሆናቸውን ይኸው የአውስትራሊያ የፖሊሲ ምርምር ተቋም አሳውቋል።
ቻይና አሁን ላይ በሚታወቁ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በሚፈጠሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችም የበላይነት ለመያዝ ሩቅ አሳቢ ዕቅድ እንዳላትም ተገልጿል።
የቻይና ግስጋሴም ሀገሪቱን በቅርቡ የቴክኖሎጂ ልዕለ-ኃያል ሊያደርጋት እንደሚችልም ተጠቁሟል።
አልጀዚራ እንደዘገበው አሜሪካ እና ቻይና በበረታ የቴክኖሎጂ ፉክክር ውስጥ ገብተዋለ። ════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


የገምቱ ይሸለሙ
ውጤቱን ቀድሞ በትክክል ለመለሰ የሞባይል ጥቅል እንሸልማለን። ኮሜንት ላይ ይፃፉልን


ማን ያሸንፋል (ይገምቱ ይሸለሙ)
Poll
  •   ማንቸስተር ዩናይትድ
  •   ቼልሲ
8 votes


5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት በወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭና ሆሳዕና ከተሞች በይፋ ጀመረ
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ከ2 ሺ በላይ የሚሆኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የአካዳሚክ ማኅበረሰብ አባላት በ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ዙሪያ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 21/2017 ዓ/ም፡ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ለሳይበር ደህንነት የሚጫወተው ሚና በሚል ርዕስ በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ ተማሪዎች እና የአካዳሚክ ማኅበረሰቡ ጋር የቪዲዮ ኮንፍረስን (Video Conference) የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን፤ በዚህም ከ43 ዩኒቨርሲቲዎችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ 30 ከሚሆኑ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የተውጣጡ ከሁለት ሺ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በቪዲዮ ኮንፈረንሱ ላይ 5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በግለሰብ፣ በተቋም እና  ሀገር ደረጃ ስለሚያስገኘው ፋይዳ፣ የባለድርሻ አካላት እና የዜጎች ሚና እንዲሁም ኢኒሼቲቩ ለሳይበር ደህንነት ስለሚኖረው አበርክቶ ገለጻ ቀርቧል፡፡ ገለጻውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሳይበር ልህቀት ማእከል ዳይሬክተር አቶ ቢሻው በየነ ያቀረቡ ሲሆን፤ ኢኒሼቲቩ በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ እና የእድሜ ደረጃ ላይ ያሉ ዜጎች ሊወስዱት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ ባለንበት የዲጂታል ዘመን ቴክኖሎጂው ይዞልን የመጣቸው መልካም አጋጣሚዎች እንዳሉ ሁሉ ከፍተኛ የስጋት ተጋላጭነትም ይኖረዋል፤ ለዚህም የዲጂታል ምህዳሩ ላይ መሰረታዊ እውቀት እና ንቃተ  ያለው ዜጋ ለመፍጠር ኢኒሼቲቩ ላይ ያሉ ስልጠናዎች ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ አቶ ቢሻው ተናግረዋል፡፡

የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የተማሪዎችንም ሆነ በአጠቃላይ የታዳጊ ወጣት ኢትዮጵያውያንን መሰረታዊ የቴክኖሎጂ ክህሎት የሚያጎለብት ስልጠና በመሆኑ ሁሉም ሰው መውሰድ እንደሚገባው  በኮንፈረንሱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ተማሪዎችና የአካዳሚክ ማኅበረሰብ አባላት ተናግረዋል፡፡ ከዚህ አኳያ በዛሬው እለት የተካሄደው ኮንፍረንስ ተማሪዎችም ሆነ የአካዳሚክ ማኅበረሰቡ በስልጠናው ላይ በስፋት እንዲሳተፉ የሚያነቃቃ ነው ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፤ በኢኒሼቲቩ አጠቃላይ  አተገባበር፣ ኢኒሼቲቩን ተግባራዊ ለማድረግ  ሊኖሩ በሚገቡ የፖሊሲ አቅጣጫዎች ዙሪያ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በኢኒሼቲቩ ላይ ከቀረቡት ስልጠናዎች በተጨማሪ መሰረታዊ የሳይበር ደህንነት ስልጠና በሚካተትበትና በሚሰጥበት አግባብ ዙሪያ  ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል ፡፡

በቪዲዮ ኮንፈረንሱ ማብቂያ ላይ የመዝጊያ ንግግር ያደርጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነተ አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ  አርአያሥላሴ እንዳሉት 5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢንሼቲቭ የኢትዮጵያ ወጣቶችን ከመጻኢው ዘመን ጋር የሚያስተሳስር መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸው፤ ይህን ወርቃማ እድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
#5_Million_Ethiopian_Coders #Digital_Ethiopia #INSA  
http://www.ethiocoders.et
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የቴክኖሎጂ ዕውቀት ለማላቅና በዘርፉ ተፈላጊነታቸውን ለማሳደግ የሚሰራውን ተቋም ተዋወቁት፤

ድርጅቱ አመኒም ሶሉሽንስ ይባላል።

የድርጅቱ መስራቾችም እዛው አሜሪካ ነዋሪና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የሆኑት ጀሚላ ተሰማና ጸጋዬ ሽንብር ናቸው።

ድርጅቱ ወደ ስራ በገባባቸው ባለፉት አራት አመታት በቴክኖሎጂ ዘርፍ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ስኬታማ መሆን የሚያስችላቸውን ክህሎት ተኮር ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

በ19 ዙሮች የተቋሙን ስልጠና የወሰዱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በቴክኖሎጂ ዘርፍ በመንግስታዊና የግል ተቋማት ተፈላጊ ባለሙያዎች መሆን የቻሉ ሲሆን፣ ገቢያቸውንና ኑሯቸውን በማሻሻል ላይ ይገኛሉ።

ተቋሙ ከሚሰጠው ስልጠና ባሻገር በወሰዱት ስልጠና ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ልምዳቸውን የሚያጋሩበትና ወጣቶችም ትስስር የሚፈጥሩበትን መድረክ ያመቻቻል።

በቅርቡ በአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ባዘጋጀው ተመሳሳይ መድረክ ላይም የተቋሙ የቀድሞ ሰልጣኞች ስኬት የተከበረ ሲሆን፣ በሥራ ገበያ ውስጥ አስፈላጊ ስለሆኑ ክህሎቶች የባለሙያዎች ምክርና የልምድ ልውውጥም ተካሂዷል።

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በቴክኖሎጂው መስክ ከተሻሉ የሥራ አማራጮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያግዙ መሰል የስልጠና ተቋማት በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ እየተበራከቱ በመምጣት ላይ እንዳሉ ከቪኦኤ አማርኛ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፦

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et

በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። #MoE ════❁✿❁════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ቴስላ ሮቦቫን የተሰኘ አዲስ ሾፌር አልባ ተሽከርካሪ አስተዋወቀ፡፡

ሮቦቫን የሚል መጠሪያ የተሰጠዉ ሾፌር አልባ መኪና በትናንትናዉ ዕለት ቴስላ ባዘጋጀዉ የትዉዉቅ መድረክ ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡ 20 ሰዎችን የመጫን አቅም ያለዉ መኪናዉ 30ሺህ ዶላር መሸጫ ዋጋ ተተምኖለታል፡፡ 

መኪኖቹ በዋናነት የታክሲ አገልግሎት እንዲሰጡ ታስበዉ እንደተሰሩ ቴስላራቲ በድረ ገጹ አስታዉቋል፡፡ የቴስላ ባለቤት ኤለን መስክ በትውውቅ መርሓ ግብሩ ወቅት እንደተናገሩት ከአውሮፓውያኑ 2027 በፊት ተሽከርካሪዎቹን ለገበያ ለማቅረብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል ፡፡

ሮቦቫን ወደ ስራ ሲገባ የትራንስፖርት ዋጋ በመቀነስ ብሎም የመንገድ ላይ ቆይታን በማሳጠር ምቹ የሆነ የትራንስፖርት ሥነ ምህዳርን ለመፍጠር እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

በፈረንጆቹ 2003 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን ለመስራት የተቋቋመዉ ቴስላ አሁን ላይ ትኩረቱን ሾፌር አልባ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ማምረት ላይ አድርጓል ፡፡

════❁✿❁ ═══════
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፦
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


በመጀመሪያ ቀን የፓንአፍሪኮን ኤ.አይ 2024 ውሎ 15 የሚሆኑ የጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዋል፡፡

በሦስት የትኩረት መስኮች ላይ የቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፎቹ በተለያዩ ጥናት አቅራቢዎች ተዳሰዋል፡፡ ጽሁፎቹ ኤ.አይ በሳይበር ደህንነት (AI in Cybersecurity) ፣ የተፈጥሮ ቋንቋ ቅንብር (Natural Language Processing) እንዲሁም የኤ.አይ ትግበራ(AI Application) ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

ጥናታዊ ጽሑፎች በቀረቡበት ወቅት ከተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄዎች በጥናት አቅራቢዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይካሄዳል
*

5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር "የቁልፍ መሰረተ ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ሃሳብ ከጥቅምት 1 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ወሩ የተቋማትንና የማህበረሰቡን የሳይበር ግንዛቤ በማጎልበት ለሳይበር ደህንነት ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጥ በማስቻል ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት መቀነስ ማስቻል አላማ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

ጥቅምት 1/2017 በሳይንስ ሙዚዬም የሚጀመረው ፕሮግራሙ የተለያዩ የውይይት መድረኮችና የተማሪዎች ውድድር ይቀርብበታል ሲሉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ገልፀዋል፡፡

በፕሮግራሙ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እና ተማሪዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ የተገለጸ ሲሆን ህብረተሰቡም በፕሮግራሙ እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ የሳይበር ደህንነት ወር በአለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ እንደሚከበር ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ etv
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ይህንን የቴሌብር ጫወታ እየተጫወታችሁ ከሆነ የምትፈልጉትን ፊደል ጠይቁን እንልክላችኋለን


ከአጠቃላይ ተፈታኞች 36 ሺህ 409 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አልፈዋል- ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 684 ሺህ 205 ተማሪዎች ያለፉት 36 ሺህ 409 መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን እና ተማሪዎችም ከሌሊቱ 6 ሠዓት ጀምረው ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች የነበረው የደንብ መተላለፍ ከአለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ እንደነበርም አንስተዋል፡፡
አዳሪ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን በመግለጽ÷ 1 ሺህ 363 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም ብለዋል፡፡
ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ሀገራዊ አማካኝ ውጤት 29 ነጥብ 76 መሆኑን ጠቅሰው÷ የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት ከ700ው 675 መሆኑን እና ይህም በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ ከፍተኛ ውጤት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
እንዲሁም ከ600 ከተፈተኑት ውስጥ 575 ከፍተኛው ውጤት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።
ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ.ም


ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ይፋ ይደረጋል::

1. በዌብሳይት https://eaes.edu.et/
2. በ6284 - SMS
3. በቴሌግራም - @eaesbot

መልካም ዕድል! Gettechinfo


Programming Languages and Their Creators

Gettechinfo


የቴሌግራሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓቬል ድሮቭ ማን ነው? ለምን በቁጥጥር ሥር ዋለ?
***

ሩስያዊውና ባለ ሶስት ዜግነት ባለቤቱ ፓቬል ዱሮቭ የቴሌግራም መስራች ሲሆን በአውሮፓውያኑ 2013 ነው ይህንን ድርጅት ያቋቋመው።
በፈረንሳይ በእስር ላይ ይገኛል። ግለሰቡ ለእስር የተዳረገው ከመተግበሪያው ጋር በተያያዙ ወንጀል ለመስራት የሚተገበሩ አጠቃቀሞችን ለመግታት እርምጃዎችን ባለመውሰዱ ነው ተብሏል።
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


አስቸኳይ የቅጥር ደብዳቤ

ከስራና ክህሎት ሚንስቴር የተፃፈ ነው።



20 last posts shown.