እንዲህ.... ነበርኩ ያኔ... ጥንት ያኔ ድሮ
መድኔ የሌለበት መራራውን ኑሮ
በጢቂት በጥቂቱ ላስቃኛችሁ
ስለ ኢየሱስም ላጭውታችሁ
እንዲህ.... ነበርኩ
በሀጥያት የሞሽሽኩ
የመርገም ጨርቄ ከርፍቶ
ስንከላወስ መንገዴ ጠፍቶ
ለጥያቄ ጥያቄ መልሱም ጥያቄ
ከሆኑ መላምት እራሴን ደብቄ
አንድ ሁለት የሌለውን እማነባ
ከለላ የሌላት ከእቅፉ የሚያገባ
እንዲህ ...ነበርኩ
እምነቃ ከሞት እየተፋለምኩ
ህይወት የሆነብኝ መና የሰመመን የጣር
እምል አልብሰኝ ከፈኑን ይጫነኝ አፈር
እምናፍቅ በምፃት መዳን አሊያም ሞት
ሁነቴን በቅጡ የማልለይ ሆኖብኝ ትንግርት
እምተነፍስ ቁና
ሆኜ ኦና
እር ብዙ... እንዲህ እንዲያ
አጀብ ..እልፍ ወዲህ ወድያ...
ተረሱ እንደ ዋዛ የሆኑብኝ ትንግርት
አሁንማ ዳንኩ ጌታን ያገኜሁ እለት
አልልም እንዲያ በማያጠግብ ቃል አፌን ሞልቼ
በገዛ እጄ ከጠፋሁበት በእርሱ በፍለጋ ተገኝቼ
ወዳጆቼ የተጣልን ሳለን ያገኘን ጌታ ይባረክ
ተባረኩልን🙋🙋
✍️Siyana
ማንባችሁን
በreaction ግለጹልኝ ❤ 👍 😍 🙏 🥰
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
|
@GITIM_ALEM |
|
@GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me
@abu_ND8