የስንኝ ቋጠሮ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Books


የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው።
ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Books
Statistics
Posts filter


ለምን ቀረሽ
ሳልኖር ካንቺ ጋር፣
ሳላቀው ስሜቱን ሳልኖር በቅፍሽ ውስጥ፣
ሳለየው ጠረንሽን ሳይቀር ልቤ ውስጥ።
ላክሽኝ ተስፋ ሞልተሽ ከማላቀው ሰው ጋር።
ጉንጮቼን ደባብሰሽ አቅፈሽ ስትስሚኝ፣
እንባዬን ጠራርገሽ በስስት ስታይኝ፣
መች ገባኝ እማዬ ቻው እንደምትይኝ፣
እመጣለሁ ልጄ መሸት ሲል ቀኑ ነበር እኮ ያልሽኝ።
ቀኑም መሸት ሲል ጀንበር አዘቅዝቃ ወደ ቤቷ ገባች፣
ተረኛ ጨረቃም በከዋክብት መሀል አሸብርቃ ወጣች።
እኔም ወጣሁ ከቤት መምሸቱን አይቼ፣
ከበራፉ ቆሜ እጠብቅሽ ጀመር እስካይሽ ጓጉቼ፣
አቅፌ ልስምሽ አጆቼን ዘርግቼ።
        ግን ግን ግን
     አልመጣሽም እማ
ለምን እንደቀረሽ ሚነግረኝ አጣሁ፣
የኔንም መጠበቅ ላንቺ የሚነግር ተላላኪም አጣሁ።
ታዲያ ለምን ቀረሽ እመጣለሁ ብለሽ?
ምን እንቅፋት ያዘሽ ልጅሽ እንዳታይሽ።

                                          MW
          @gitmv                          13-07-2015


Forward from: Unknown


ቶሎ ና🏃💨

ቆሜያለው ከደጁ 🏠ናፍቆትን አርግዤ😔
ትመጣለህ👣 የሚል ትንሽ ተስፋን ይዤ
ከብርዱ እንድሸሸግ እቅፍን ናፍቄ
ከጉያዬ ውስጥ ፍቅርን ❤አምቄ
     
   እየጠበኩህ ነው👤
           .
           .
    ብርዱ  ሳይጠናብኝ እባክህ ቶሎ ና
     ብቻዬን እንዳልሆን ስጎዝ በጎዳና
ትመጣልኛለህ ከቅፍህ እንድኖር
ከአለም እርቀን በፍቅር እንድንበር💓
                  አሰብከው አለሜ💑
                          .
                          .
አነስ ባለ ጎጆ በእሳት በሞቀ
በ'ቅፍህ ውስጥ ሆኜ ፍቅርን ባመቀ
ልባችን ታድሞ ከጣፋጩ ዜማ
ከእሳቱ ዳር🔥 ሆነን መውደድን ስንሰማ
              ለማይደገመው ለዚ ጣፋጭ🍯 ጊዜ
              ዝናብ ☔ብርዱን ችለህ ቶሎ ና በጊዜ⏳ Be Mahi


Human Hair የሚፈልግ በ ውስጥ መስመር ያናግረኝ 👉 @mogea


አትሳቅ
 
መክነፌ ሳያንሰኝ በአይኖችህ 👀ውበት
መድከሜ ሳይበቃኝ ውሉን ሳላውቅበት
በፍቅርህ ቀንበር ውስጥ የተያዘ ልቤን 🫀
ላስመልስ ሰታገል የወሰድከው ቀልቤን
         ትቼህ እንዳልተውህ በሀሳቤ 🧠እንዳልፀና
          ስቀህ አታለልከኝ ጥርስህ ይርገፍና😁
በ ማህሌት


#ለሀጥያት_ሙት
ሞትም የት አባቱ ገዳይ ብቻ ሆኖ ዘመን ያስቆጠረ
በ ሃጢአት ስር ሽፋን የሰውን ዘር ሁሉ ሲቀጣ የኖረ
ከዘመናት ሁአላ ከዘመናት በፊት ነባር የነበረ
ሞግዚትነት ሽሮ ነፃነት አብስሮ ሞትንም ያሰረ
ሞትበሞት ተገድሎበመስቀልተቀጥቶ ሰላምከተገኘ
አሸናፊው እሱ ነው ለፅድቅ ለመኖር ሞቶ የተገኘ
@mogea @gitmv


መደጋገፍ
ያስተምራል ጎዳናው እውቀት ነው መንገዱ
ማስተዋል ለሚሹ አይተው ለሚረዱ
ተሸካሚ ናቸው እንዲያው መወጣጫ
ለአይን መነፅር ጆሮ እና አፍንጫ
@mogea @gitmv


ድል ነው
ያመደ ቢወዛ ድፍርሱ ቢጠራ
ያለቀሰ ቢስቅ ፅልመቱ ቢበራ
እድል ሳይሆን ድል ነው የ አምላኩ ውጊያ
የጭንቅ ቀን ፀሎት መልስ ነው ማብሰሪያ
@mogea


ትዝታ ሲናፍቅ



እውነት አንዳንዴ ትዝታ ምንም ክፋት የለው፣
ከዛሬ ይሻላል ድንቅ ቀለም አለው ፣
ትናንት የሆነውን ወደሗላ እያዩ፣
ስንት ደስታ አለው ትዝታ ከላዩ፣
ከላይ ካፋፍ ካፋፍ፣
ትዝታ ሲገዝፍ ፣
ትዝ ትዝ የሚለኝ ፍቅራችን ነበረ፣
በደስታ ተገምዶ በጥብቅ የታሰረ ፣
አሁን ግን ትዝታ የነበር ቃል ድርሳን ፣
ልባቺን ሊነደል ቀስ በቀስ  ያሳሳን ፣
ውል የነበረበት ቃል የተፃፈበት ፣
አሁን በትዝታ ነበር የሆነበት ።።


  ዝ
      ታ
                  

ትዝታ   ክፋትም አለበት

ላይመለስ ነገር ህመም ሆኖ ያልፋል፣
ትዝታ ህመም አለበት ውስጠት ልብ ያቆስላል፣
በትላንት ላይ እሾህ ይተክላል፣
ሰርክ እየታሰበ ደስታን  ያሳድፋል ፣
ንፉግ ሀሳብ የማይመለስ ተስፋ ጥሎ ፣
ህመምን ከደስታ እኩል አስከትሎ፣
ግና ምን ይደረግ
ህይወት ነው አቀበት፣
ተራራ ቁልቁለት ፣
ሜዳ ደልዳላ ነው ስቃይና ድሎት፣

ክፉ ነው  ትዝታ


✍️አቤል አረጋ 
(አቡ)  @son_abu


ውርደትሽ አንሷቸው ውርደት ሊጨምሩ
ይኧው አየናቸው
መጥፎ ያልናቸውን መርቀው ሲምሩ
በገዛ ራሣቸው ትውልድ እየገዙ
ጥሩ ያሉት ሥራ መጥፎ እየሆነ ስንቴ ተወገዙ
በቀል ያረገዘን የህማማት ሥቃይ
እንድንሸከመው አረጉን መርቀው አውራጅና አሰቃይ
ማነው ያደረጋቸው ነፋጊና ከልካይ
ማነው ያደረጋቸው ነቃይና ተካይ
ሁሉም በየድርሻው
ሁሉም በየእርሻው ላብ አለኝ እያለ
የማይጠፋ አሻራ ጠማማ ችግኝን አፍልቶ ተከለ

ዝቅታሽ አንሷቸው ይባሱን
ሊያዘቅጡሽ
ይኸው አየናቸው፣
መላቅጥ ጠፍቷቸው መላቅጥ ሲያሳጡሽ
ከፍ ካለ ቦታ ዝቅታውን መርጠው
የተቀጠለውን ከመሐሉ ቆርጠው
እኔ ነኝ እያለ ፎካሪም ቀራሪም
እኔ ነኝ እያለ ጨራሽ አስጀማሪም
አተኳኮስ ማያውቅ አያነጣጥርም
ምላሠ ኮልታፋ አያቀጣጥርም
ወትሮስ ዘሩን እንጅ ስንዴውን አይቆጥርም

ሕመምሽ አንሷቸው ሕማም ሊደርቡ
ይኸው ታዘብናቸው፣
ከህማም ጎተራ ሰበዝ ሲሸርቡ
ማነው የሚያቅተው ጥያቄ ማነብነብ
ማነው የሚከብደው ሠማይን ማዘነብ
ሁሉም እየሆነ አቧራ አራጋቢ
ሁሉም እየሆነ በቁስል አንገብጋቢ
ፈዋሽ ነው ያጣነው የተራበ አጥጋቢ
መሆን ቢያቅታቸው ለችግርሽ ደራሽ
እንዴት ይሆናሉ እንቅፋትን አውራሽ
መሆን ሲገባቸው ሕመምሽን ጠጋኝ
እንደምን ይላሉ የናቴ አጥር ወጋኝ
እናም

በተቆራረጠ ባረጀ ዘመን ላይ ዓመታት ያልፋሉ
እነዚያ ዓመታቶች መቼም የማይጠፋን ታሪክ ይጽፋሉ
እነዚያ ታሪኮች ዘመን ያስቀራሉ
እነዚያ ታሪኮች፣
ለአንዳንዱ ሕይወትን
ለአንዳንዱ ሞትን ይመሰክራሉ
በተበጣጠሰ ባልተቀጣጠለ
የታሪክን ሊያፋልስ ማን የኑሮ ለጠለ
ባልታከመ ሥጋ ባልደነደነ አንጀት
እንዴት ይታሰባል እየዋሉ ማርጀት
እንደምን ይሆናል የዕድሜ ጣራን መፍጀት

✍Eyuel


ልንገራት?ንገራት!!

የኔ ፍቅር ላላጣት እራሴን ጎዳሁ ሳልነግራት
ወይ ነግሬአት አላረፍኩ ፍቅሬን አልተነፈስኩ
እንዲሁ ጭንቀት እራሴን እየወቀስሁ

ነግሬአት እህትነትዋ ከማጣ ከምትርቅ ካጠገቤ
ወይ ደግሞ እሺ ብላኝ ገደብ የለሽ ደስታ ላዘነላት ልቤ

አውይ አሁንማ ሲቃዬ በዛ ልጥራት ካለችበት
እሷን ሳይሆን ሌላ እንዳፈቀርኩ ላማክራት እንዳልኩ

አንተኮ ጥሩ ሰው ብላ እንደጀመረች አለችኝ ንገራት
እኔም እሺ ብዬ እሷ መሆናን ስነግራት እኔን ለመውገር ድንጋይ ነው የቀራት

  ወይ ልንገራት?ንገራት!
   Sam💝 to Mar 💝
@gitmv


😭😭😭😭😭😭😭😭😭
😪😪መታመን ሞቷል😪😪
😢😢😢😢😢😢😢😢😢


🌷🌷🌹መታመን ሞቷል🌹🌷🌷
             ቀበርኩት ብቻዬን

              ትናንትና ማታ
☹️☹️☹️አፍስሼው እምባዬን☹️☹️

                 🌷🌹ልቤ እየሳሳለት🌹🌷
                 🌷🌹ሆዴ እየራራለት🌹🌷

😓😓😓ትናንት እሁድ ለታ😓😓😓
😥😥😥ሸኘሁት በማታ😥😥

😞አንቺ ና ብለሺኝ😞😞
☹️ጥለሺኝ ስትጠፊ😟😟

             የገላዬን ሙቀት
             ወደዛ ስትገፊ

              ብከብደኝም ቅሉ
              ጨከነና ልቤ
😩😩😩😩😩😩😩
የመቃብር ወጉን
ስዬው በምናቤ

እምነትን ቀበርኩት
ሸኘሁት ባሳቤ
😭😭😭😭😭😭

by Gutu.Z


አንተ እዚህ የለህም

አንተ እዚህ የለህም፣
ሰርክ አመት አትጣም፣
ቤቴም ይለምደዋል ያላንተ መኖሩን፣
አይኔም ይጠግበዋል ሳያይህ መዋሉን፣
ገላየም ይለምዳል ለብቻ ማደሩን ፣
   ግን ይህን ያልቻለ አንድ ነገር አለ፣
     ሳያስብህ ውሎ ሳያስብህ ማደር ፍጽሱም ያለመደ፣
ልቤ አንተን በማለም በትዝታ ብቻ ዘመናት ነጎደ፣
        ሊረሳህ አልቻለም ፈጽሞ ሊተውህ፣
      ከልቤ ቦታላይ በደማቅ ታትመህ፣
       ለመርሳት ያልቻልኩት ምንድነው ጥበብህ፣
        እርግጥ ነው ደርሶኛል የላከው ደብዳቤ፣
        ግን ከፍቶ ለማንበብ አልደፈረም ልቤ፣
        መልክቱ መሰለኝ የያዘ ይህንቃል፣
        ወዳንች ላልቀርብ ርቂያለው በሃይል፣
         ሆኖ ብመጣ እንኩዋን አይንሽ አላይም፣
         ደግሜ  ላገኝሽ ላይሽ አልፈልግም፣
         እናም የኔ አበባ፨
ባገኝ ይህን ፅሁፍ ከመልክትህ ጋራ፣
የቆሰለው ልቤ እንዳይደማ ፈራ፣
  እርግጥ ነው አውቃለሁ አንተ እንዲ አትልም፣
   ቢሆንም የኔ ውድ ባንተ መከፋትን መቆጣት አልሻም፣
   ስትመጣ በአካል ታነብልኛለህ፣
    በርቱዕ አንደበት ትገልጽልኛለህ፣
  ባስተዋይ አእምሮ ታብራራልኛለህ፣
   እስከዛ የኔ አለም…
ባለህበት ሰናይ ሰላምህ ይብዛልኝ፣
ለወደደህ ልቤ ዝንት አለም ኑርልኝ ፣

Hawlet.A


የጅምሬ መጀመሪያ የእቅዴ ውጥን፣ የሐሣቤ ማሥቀመጫ የቅዠቴ ጓዳ ሣጥን፣ ተፈጽሞ ሣይጀመር ከሌላውጋ ቢወዳደር፣ ጌጥ ኣሥውቦት ላዬ ቢያምር ለካ ልቤ ባዶ ነበር። ታቹ ቅጠል ላዩ እንጀራ፤ ውጪው ለምለም ውሥጡ በራ፣ የሐዘን መነሻ የጭንቀት ጎተራ፤ የትካዜ ሻማ የጽልመት ደመራ፣ ከውሥጤ ኣጣልቶ ከራሤ ያለያየኝ፣  የሖነ ግዜ ላይ ዕኔም ልብ ነበረኝ።፤ ለራሡ የገባዉን ቃልኪዳን የጣሠ፤ ግማሽ ጎኑ ከድቶት በ1 እግሩ ያነከሠ፣ ከሐሠት ኣእዛምዶ ከእውነት ያለያየኝ፤ የእሬሣ ክፋይ ልብ እንኳ ነበረኝ። የጸብ ተጎራባች የደሥታ ባላንጣ፤ የሓዘን ተጠሪ የሥኬት ጋሬጣ፣ እድለቢሥ ቁልቋል ከአጋም የተጠጋ፤ በእሾሕ ተወግቶ ሌላውን የወጋ፣ በምግባር ያነሠ በምሥል የገዘፈ፣ በኢሕግ ያመነ ሊያውም ባልተጻፈ፣ የበረደ እሣት ፍሙ የከሠመ፤ በማይድን በሽታ ከጥንት! የታመመ፣ ከቁጥቋጦ ቅጠል መሐል የተዋጠ፤ ከኣለም ውቅያኖስ ገብቶ የዘቀጠ፣ ከጉድጓድ የገባ ርቆ ከተማሠ ልብ እንኳ ነበረኝ ከሰው ያላነሠ። ታድያ ምን ያደርጋል፣ የኣኗኗር ፈሊጥ የሒወት ምእራፍ፣ የልፋት ጉልላት የእሩጫችን ጫፍ፣ በድንገት ተቋጭቶ ሣይታይ ካለቀ፤ ኣጽሜ ሢመነምን ጥርሤ እየሣቀ፣ አርፌ ቁጭ ብዬ እድሜዬ እሥኪጠባ፣ ከ2 ክንድ ምድር ልቀበር ልገባ፣ ቃሌን ሠጥቻለሑ በኖረኝ ልመካ፤ በሌሎች መሥፈሪያ የራሤን ላልለካ።✍️@eyader24 @eyader24


ስንት ጊዜ ወድቀናል ስንቴ ተነስተናል
ስንት ጊዜ አልቅሰን ስንት ጊዜ ስቀናል
ቢፈራረቅብን ብርሃን ከጨለማ
ምድርም ፍሬዋን ብትሰጥም ብትቀማ
ማለቂያ የሌለው ቁጥር እንኳን ያልቃል
የምድር ውጣ ውረድ ተጠቃሎ ያልፋል
የቀራኒዮ ፍቅር እርሱ ግን ይልቃል!!
@mogea @gitmv


ድሩን ከማጉ ጋር ወስፌውን ከክሩ
ፈረሱን ከሜዳው በልክ ካሰማሩ
ተማሪዎች ዘርፉን ፈልገው ቢማሩ
በስኬት ጎዳና ህልማቸውን በኖሩ!!

@mogea @gitmv


ለምን ይገርመናል....?
ለምን ይገርመናል የሄደው መሄዱ፣
ሰአቶች ያለ አፍታ በፍጥነት ቢነጉዱ፣
ጊዜው ቢገሰግስ ሳንሆንም ካንዱ፣
ለምን ይገርመናል.....
ስለ ትላንቱ ቀን ሀሳብ ስናቀና፣
እየተብሰለሰልን በከንቱ ጎዳና፣
ለምን እንላለን በመጣ እንደገና።
የአምናው አይድነቀን ሌላ አለም አለና፣
ዛሬን ሳናስተውለው ሄደን ወደ ሁዋላ፣
እንድህ ቢሆን እያልን ሂሳብ ስናሰላ፣
ልክ እንደ በፊቱ እንደ ትላንትና፣
ትዝታ ይሆናል ዘንድሮም ያልፍና።
K.W
@gitmv


ልፅፍልሽ ነበር በቀለም አድምቄ
ልፅፍልሽ ነበር ብራናየን ስየ ፊደላት አጥብቄ
ልፅፍልሽ ነበር ያለችሎታየ ውስጤን አስጨንቄ
ግና ምን ያደርጋል አንችን የሚመጥን ቃላት አጣሁልሽ
አፌ ተያያዘ ኮልታፋ ሆንኩልሽ
ጣቶቸም ራዱ ሰባራ ሆኑልሽ።
✍Hawlet Ali
@gitmv


ትቻለሁ ስላንቺ  
መስሎኝ ምታፈቅሪኝ
        ተሳስተሽ ማትዋሺኝ
ልብሽን ደብቀሽ
           ከንፈርሽ ሰጠሽኝ
እኔም ተታልዬ
          ፍቅርሽ እውነት መስሎኝ
ጥበብ ባጠራኝም
           ገጣሚ ሆኛለሁ የማገኝሽ መስሎኝ

አሁንማ ውዴ
           ሁሉም ሳይሆን ቀረ
መግጠሙም ይቅርብኝ
                  አንቺን ካልቀየረ
ትቻለሁ ከንግዲህ
          ህልሜ መና ቀረ
አንቺም ገደል
          ግቢ መሞቴ እስካልቀረ 😀
👉 ጥበብ ባጠራኝም እጋፈጣታለሁ 😂
@gitmv


የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው።
ግጥሞችን ለመላክ @Abebekasu @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!! @gitmv ስንኝ ቋጠሮ ብቻ!!

20 last posts shown.

1 982

subscribers
Channel statistics