Habesha sport


Channel's geo and language: Ethiopia, English
Category: Sport


በ ሐበሻ ስፓርት ስፓርት ትኩስ ስፖርታዊ መረጃዎችን ከቻናላችን ያገኛሉ! በተጨማሪም ፦
፨ የሀገር ውስጥ ትኩስ ስፓርታዊ መረጃዎች
፨የ አውሮፓ ታላላቅ ሊጎች መረጃዎች
፨የስፓርት ሰዎች ግለታሪኮች ይፈተሻሉ

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Category
Sport
Statistics
Posts filter


አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት የሚያቆየውን አዲስ የሁለት አመት ኮንትራት ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል።

[JBurtTelegraph]

https://t.me/habeshasportnews1


አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ቪኒስየስ ባላንዶርን ያሸንፋል ሲል ተደምጧል።

https://t.me/habeshasportnews1


" ያነጋገረኝ ክለብ እንኳን ባለመኖሩ አዝኛለሁ " ሳሪ

ከላዚዮ ጋር ከተለያዩ በኋላ ያለ ሀላፊነት የሚገኙት ጣልያናዊው አሰልጣኝ ማውሪዝዮ ሳሪ በዚህ ክረምት ምንም የጣልያን ክለብ ለአሰልጣኝነት እንዳልፈለጋቸው ገልፀዋል።

" ከጣልያን ክለቦች ምንም አይነት የአሰልጣኝነት ጥያቄ ስላልቀረበልኝ ትንሽ አዝኛለሁ " ያሉት አሰልጣኝ ማውሪዝዮ ሳሪ " ለማነጋገር እንኳን የፈለገ ክለብ የለም ይህ እንኳን ይገባኝ ነበር ብለዋል።

አሰልጣኝ ማውሪስዮ ሳሪ በንግግራቸው በዚህ አመት ኤስ ሚላን ወይም ፊዮረንቲናን የማሰልጠን ፍላጎት እንደነበራቸው ተናግረዋል።

https://t.me/habeshasportnews1


አርሰናል በቅርብ ወራት ውስጥ መልማዮችን ልከው ዩሱፍ ፎፋናን ሲመለከቱት ነበር ።

የሚጠበቀው ፎፋና በዚህ ክረምት ከሞናኮ እንደሚለቅ ነው። [ Fabrizio Romano ]
https://t.me/habeshasportnews1


ላውረንት ኮስሎኒ በሀላፊነት ተሾሟል !

ከአመት በፊት በይፋ ራሱን ከፕሮፌሽናል እግርኳስ ያገለለው የቀድሞ ፈረንሳዊ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ላውረንት ኮስሎኒ በአዲስ ሀላፊነት መሾሙ ተገልጿል።

የቀድሞ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ተከላካይ ላውረንት ኮስሎኒ የፈረንሳዩ ክለብ ሎርየንት ስፖርቲንግ ዳይሬክተር በመሆን በሀላፊነት መሾሙ ይፋ ተደርጓል።

የ 38ዓመቱ ላውረንት ኮስሎኒ ከዚህ በፊት የሎርየንት ታዳጊ ቡድንን በማሰልጠን ላይ ይገኝ ነበር።

https://t.me/habeshasportnews1


የ ሚጌል አልሚሮን የወደፊት እጣ ፈንታ የተረጋገጠ አይደለም እና ኒውካስትል ከፋይናንሺያል ፌር ፕሌይ ጋር በተያያዙ ችግሮች ምክንያት የክንፍ አጥቂውን ለመሸጥ ፍላጎት አለው።

(Fabrizio Romano)
https://t.me/habeshasportnews1


ቲያጎ ሞታ የጁቬንቱስ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ኮንትራቱን ዛሬ ተፈራርሟል።

አሰልጣኙ እስከ ሰኔ 2027 ድረስ የሚያገለግል የሶስት አመት ውል ፈርሟል።በቀጣዮቹ ቀናት ይፋዊ የክለቡ መግለጫ ይወጣል።

(FabrizioRomano)
https://t.me/habeshasportnews1


ማን ዩናይትድ ለአዳዲስ ዝውውሮች መንቀሳቀስ ከመጀመራቸው በፊት የቴንሀግን ሁኔታ ለመፍታት እየጠበቁ ነው ።

( Fabrizio Romano )

https://t.me/habeshasportnews1


ክርስቲያኖ ሮናልዶ: 🗣

"ብዙ ማውራት አልወድም ግን ማን እንደሆንኩ ማሳየት እወዳለሁ ።

"በ 6 ዩሮ ውድድሮች ላይ የተጫወተ የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል፣ ብሄራዊ ቡድናችን አላማውን እንዲያሳካ ለማድረግ እዚህ በመገኘቴ ደስተኛ ነኝ በድጋሜ ኩራት ይሰማኛል"።

https://t.me/habeshasportnews1


፨ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ አዲሱ የማንቸስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ እንዲሆኑ ግፊት እያደረጉ ነው።
[x/GraemeBailey]
https://t.me/habeshasportnews1


ቪክቶር ኦሲምሄንን ለማስፈረም Al_Ahli €12Om ለተጫዋቹ አዘጋጅተዋል። ምንም እንኳን ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመዛወር ፍቃደኛ ባይሆንም ።

[Il Matino]

https://t.me/habeshasportnews1


ቪኒ ጁኒየር የዘረኝነት ጥቃት ያደረሱበት ሰዎች ላይ ውሳኔ ከተላለፈ በኋላ ያስተላለፈው መልዕክት፡

“ብዙዎች ችላ እንድል ጠይቀውኛል፤ ሌሎች ብዙዎች ደግሞ ፍልሚያዬ ከንቱ እንደሆነ እና “እግር ኳስን ብቻ መጫወት” እንዳለብኝ ተናግረዋል።”

“ ግን ሁሌም እንደምለው እኔ የዘረኝነት ሰለባ አይደለሁም፤ ዘረኞችን የማሰቃይ ነኝ እንጂ። ይህ በስፔን ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው የወንጀል ክስ ስለእኔ ብቻ አይደለም ለሁሉም ጥቁር ህዝቦች ነው።”

“ሌሎች ዘረኞች አሁን ላይ ማፈር፣ መፍራት እና መደበቅ ያለባቸው ጊዜ ነው፤ ያለበለዚያ ልይዛቸው እመጣለሁ።”

“ ላሊጋ እና ሪያል ማድሪድ ለዚህ ታሪካዊ ፍርድ ስላገዙን እናመሰግናለን፤ ተጨማሪ ሌላም ለውጥ ይመጣል። 🙏🏾✊🏿”

@ETHIO_REAL_MADRID_15

https://t.me/habeshasportnews1


ኒኮላስ ጃክሰን ባለፈው ሳምንት ለሴኔጋል ሲጫወት በቁርጭምጭሚቱ ላይ ጉዳት ከደረሰበት በኃላ ለቼልሲ የቅድመ ውድድር ጅማሮ ሙሉ በሙሉ ብቁ ላይሆን ይችላል ተብሎ ተሰግቷል ።
https://t.me/habeshasportnews1


ፓትሪክ ቪዬራ ወደ አሰልጣኝ ስራው ከሄደ በኋላ የማን አሰልጣኝ ተፅዕኖ እንዳደረገበት ሲጠየቅ ፦

" የአርሴን ቬንገር የአሰለጣጠን መንገድ እወድለታለሁ ፤ ከቬንገር ጋር ከዘጠኝ አመት በላይ አሳልፌያለሁ እናም ልዩ አሰልጣኝ ናቸው ፤ በተለይም ለወጣት ተጫዋቾች ላይ ያላቸው በራስ መተማመን ያስደንቃል ፤ በጭራሽ ስለ ተጫዋች መጥፎ ንግግር አያወሩም ።"

" ሞሪኒዮ ጋርም በኢንተር ሰርቻለሁ ፤ እሱ ጨካኝነት ያስተምርሃል ፤ ዋንጫ ስለማሸነፍ እና ውድድር ስለማሸነፍ ነው የሚያስበው ፤ ከሞሪኒዮ ርህራሄ የለሽነት ተምሬያለሁ ።"

" ፔፕ ጋርዲዮላ ? የእሱ አሰለጣጠን ለእኔ ምንም ተፅዕኖ አላሳደረብኝም ምክንያቱም እንደፔፕ ለመጫወት ጥራት ያለው ተጫዋች ያስፈልግሃል ።" ሲል ተናግሯል ።

@ETHIO_ARSENAL
https://t.me/habeshasportnews1


አርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ ሆላንዳዊ የቦሎኛ አጥቂ ጆሹዋ ዚርክዜን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው።
https://t.me/habeshasportnews1


ባርሴሎና ለኮቢ ማይኖ ዝውውር 8.5m እና ራፊንሃ ማቅረቡ ተዘግቧል ሀንሲ ፍሊክ የመሃል ክፍሉን በዙሪያው ማጠናከር ይፈልጋል።
[ elnacionalcat]
https://t.me/habeshasportnews1


ማንቸስተር ዩናይትድ ከሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ወኪል ጋር ተገናኝቷል። 

[ Graeme Bailey ]
https://t.me/habeshasportnews1


ቤንጃሚን ሴስኮ በቅርቡ ውሳኔውን ያሳውቃል::

FABRIZIO ROMANO
https://t.me/boost/habeshasportnews1


ዋልያዎቹ ነጥብ ተጋርተዋል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአቻነቷን ግብ ምንይሉ ወንድሙ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በማጣሪያ ጨዋታው እስከአሁን ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች የመጀመሪያ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

በምድብ አንድ የሚገኙት ዋልያዎቹ በምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሰበሰቧቸውን ነጥቦች ሶስት በማድረስ  አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

የማጣሪያ የመጀመሪያ ነጥቡን ያሳካው የጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ በአንድ ነጥብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዘዋል።

https://t.me/boost/habeshasportnews1


አል አህሊ ኪሚቺን ለማስፈረም 90ሚሊየን አቅርቧል ሲል ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ዘግበዋል።

https://t.me/boost/habeshasportnews1

20 last posts shown.