"ልጄ 2 ወር ነበር አረንጓዴ ነገር በጣም ያስታውከው ነበር። ከ 3 ቀን በኋላ ወደ ሆስፒታል ወሰድኩት። በአፋጣኝ ቀዶ ጥገና ተደረገለት። ነገር ግን አንጀቱ በመጠምዘዙ አብዛኛው አንጀት ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ምንም ልናደርግለት አንችልም አሉኝ። ልጄ በሚቀጥለው ቀን ሞተብኝ።
ሌሎች እንዲማሩበት እባክዎን ስለዚህ ችግር ይንገሩን።" (የወላጅ ጥያቄ)
😢ውድ ጠያቂያችን በደረሰብዎት ሐዘን በጣም አዝኛለሁ።
✍ልጅን ማጣት የማይረሳ ከፍተኛ ህመም ነው እና ሌሎች እንዲማሩበት የእርስዎን ልምድ ለማካፈል ፈቃደኛ መሆንዎ በእውነት የሚደነቅ ነገር ነው።
🩺እርስዎ የገለጹት ችግር እንደ እርሶ አገላለፅ ከሆነ የአንጀት መጠምዘዝ (Midgut Volvulus) ሲሆን አዲስ በተወለዱ ሕፃናት እና ትናንሽ ሕፃናት ላይ ለሕይወት አስጊ የሆነ ድንገተኛ የአንጀት አደጋ ነው።
🌡🌡ከዚህ በታች :
🩺🩺ችግሩ ምን እንደሆነ፣
🩺🩺 ለምን እንደሚከሰት፣
🩺🩺እንዴት እንደሚታከም እና ለምን አስቸኳይ ሕክምና(ቀዶ ጥገና) አስፈላጊ እንደሆነ ለማብራራት እንሞክራለን።
🥇Midgut Volvulus ምንድን ነው?
🌡Midgut Volvulus ማለት አብዛኛው ትንሹ አንጀት እና የተወሰነ ትልቁ አንጀት በሚጠመዘዝበት (Twisting) ጊዜ የሚፈጠር አደገኛ ችግር ነው።
🌡ይህ ችግር የሚከሰተው በተፈጥሮ የአንጀት አቀማመጥ ትክክል በማይሆንበት በህክምና ቃል Malrotation ባላቸው ህፃናት ላይ ነው።
💊በመደበኛ አፈጣጠር በፅንሱ እድገት ወቅት አንጀት ትክክለኛውን አቀማመጥ ለመያዝ ይዞራል (Rotation) እንዲሁም በሆድ እቃ ውስጥ ተስተካክሎ ይቀመጣል (Fixation)።
💉ነገር ግን ከላይ የተጠቀሰው ችግር ያለባቸው ሕፃናት አንጀት በትክክል ስለማይስተካከል ለአንጀት መጠምዘዝ በከፍተኛ መጠን ይዳርጋቸዋል።
🩺አንጀቱ በሚጠመዘዝበት ወቅት የደም አቅርቦቱ ይቋረጣል ይህም ወደ ጋንግሪን (የመበስበስ ) አደጋን ያስከትላል።
🌡💊ይህም በፍጥነት አንዳንድ ጊዜም በሰዓታት ውስጥ ሊከሰት ይችላል እና በጊዜ ካልታከመ ለሞት ሊዳርግ ይችላል።
🥈የMidgut Volvulus ምልክቶች ምን ምን ናቸው?
✏️በጣም አስፈላጊው እና ከሁሉም ምልክቶች ቀደሞ የሚከሰተው ምልክት በድኖገት የሚከሰት አረንጓዴ ነገር ማስታወክ (Bilious Vomiting) ነው።
✒️ይህም ለአንጀት መዘጋት የሚጠቁም አደገኛ ምልክት (Red flag sign) ነው።
✍ሌሎች ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
• ከባድ የሆነ የሆድ ህመም (በጨቅላ ህጻናት ላይ ከመጠን በላይ ማልቀስ ሊያስከትል ይችላል)
• የሆድ መነፋት
• መፍዘዝ እና መድከም
• የአንጀት እንቅስቃሴ መቀነስ ወይም ሰገራ ወይም አየር አለማስወጣት።
😳ብዙ ወላጆች አረንጓዴ ትውከትን አደገኛ ምልክት መሆኑን ላያውቁ ይችላሉ።
😳ይህም ወደ ሆስፒታል ለመውሰድ ይዘገያሉ።
🌡እንደ አለመታደል ሆኖ እርስዎ እንዳጋጠሙዎት መዘግየት አስከፊ እና ለሞት የሚዳርግ ሊሆን ይችላል።
🥉ቀዶ ጥገና ከተደረገ ግን ለምን ምንም ነገር አልተሰራም?
🩺ይህ ችግር ያለባቸው ህፃናት ዋናው ህክም ቀዶ ጥገና(Surgery) ነው።
🩺በቀዶ ሕክምናው ጊዜ የአንጀቱን የደም ዝውውር ጤነኛ ወይም ሕያው (viable) መሆኑን ወይም የበሰበሰ (Gangrene) እንደሆነ ለማወቅ ይረዳል።
🌡በጣም ብዙ አንጀት ከሞተ የመዳን እድል ላይኖራቸው ይችላል።
ምክንያቱም:
1. አጭር የአንጀት ሲንድሮም (Short Bowel Syndrome)
💊አብዛኛው አንጀት ከተወገደ ህፃኑ በሕይወት ለመቆየት በቂ ምግብ እና ንጥረ ነገሮችን መውሰድ አይችልም።
በዚህም ምክንያት የመትረፍ እድሉን አደጋ ውስጥ ይከተዋል።
2. ከባድ ኢንፌክሽን (Sepsis) -
💊የሞተ አንጀት ወደ ደም ውስጥ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ፣ባክቴሪያዎችን ይለቃል።
💊ይህም ለሕይወት አስጊ የሆነ ኢንፌክሽን ያመጣል።
🩺ቀዶ ጥገናውን የሚሰሩት ሐኪሞች አብዛኛው አንጀት መሞቱን ከተረዱ ልጁን ለማዳን ምንም ዓይነት የቀዶ ጥገና አማራጮች ላይኖር ይችላል።
😭ይህ ልብ የሚሰብር ውሳኔ ነው።
😭ዘግይተው ከመጡ ምንም ለማድረግ አለመቻል ለሐኪሙም ቢሆን ልብን የሚሰብር እውነታ ነው።
✍ሌሎች ወላጆች ከዚህ ምን ይማራሉ?
👉ከዚህ ተሞክሮ ወላጆች መማር ያለባቸው ዋናው ትምህርት ቀድሞ መረዳትና እና አስቸኳይ ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ ነው።
👉ወላጆች ልጃቸው አረንጓዴ ትውከት ካለበት ወዲያውኑ አስቸኳይ ሕክምና ማግኘት አለባቸው።
😳ለጥቂት ሰዓታት እንኳን መዘግየት አንጀትን በማዳን እና በማጣት መካከል ያለውን ልዩነት ሊያመለክት ይችላል።
😳😳😳ማስታወስ ያለብን ቁልፍ ነጥቦች፡-
✓ ጨቅላ ሕፃናት አረንጓዴ ነገር ካስታወኩ ሁልጊዜ የድንገተኛና ቀዶ ጥገና የሚያስፈልገው የአንጀት ችግር ምልክት ነው።
✓ የአንጀት አቀማመጥ ችግር ያለባቸው ህፃናት ምንም ምልክት ሳያሳዩ ጤናማ ሆነው ቆይተው ድንገት የአንጀት መዞር ችግር ሊከሰትባቸው ይችላል።
✓ አፋጣኝ ቀዶ ጥገና ቶሎ ከተሰራ አንጀትን ሊያተርፍ ይችላል።
✓ መዘግየት ወደ አንጀት መበስበስ (ጋንግሪን) ሊያመራ ይችላል። ይህም መዳን የማይቻል ያደርገዋል።
ይህንን ታሪክ ለማካፈል ያለዎት ድፍረት እና ተነሳሽነት ሌሎች ወላጆች ምልክቶቹን ቀደም ብለው እንዲያውቁ እና ተመሳሳይ አሳዛኝ ሁኔታዎች እንዳይከሰቱ ለመከላከል ሊረዳቸው ይችላል እና ላመሰግንዎ እፈልጋለሁ።
ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን ለመግለፅ እፈንፈልጋለን ፣ መፅናናትን ያድልልን ።
ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!
አዘጋጅ: ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም
Dr. Saleamlak Tigabie: MD, Pediatric Surgeon
👉ለበለጠ መረጃ እና ነፃ የምክር አገልግሎት :
📱0911441651
👉Gmail: saleamlaksati@gmail.com
👉
@DrSaleamlak(በግል ለማናገር እና ምስል ለመላክ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ)
https://t.me/DrSaleamlakThttps://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/@HakimEthio