አዲስ ምልከታ🌍


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Other


+ አዲስ የሳይንስ እይታ
+ አዲስ አስተሳሰብ
+ አዲስ እውቀት
+ ሃይማኖት
+ ፖለቲካ
+ ኢኮኖሚ
+ ሙዚቃ
# የኢትዮጵያ ትንሳኤ

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Other
Statistics
Posts filter


ስለ ሶማሊላንድ።

ከቅርብ ጊዜያት እየተካሄዱ ካሉ ክስተቶች አንጻር እና ከአንዳንዶቻችሁ ጥያቄም አንጻር ይህን ርዕስ አንስተን ማውራት ተገቢ ስለሆነ እንዳስሰው። ሶማሊላንድ ማነች? ታሪኳ ምንድን ነው? በሷ ምክንያት ኢትዮጵያና ሶማልያ ወደ ጦርነት የመግባት እድል የደረሰባቸውስ ለምንድን ነው?

ታሪኩን ለመረዳት መጀመሪያ ስለ ሶማሊ ህዝብ ማንሳት ይጠበቅብናል። ይህ ህዝብ ሰፊና ውስብስብ ታሪክ ያለው በመሆኑ በዚህ በአንድ ፖስት የምጨርሰው አይደለም። ግን በጥቂቱ እንመልከት። የሶማሊ ህዝብ የተለያዩ ጎሳዎች አሉት። ከነዚህ ጎሳዎች ደግሞ ዲር የሚባለው አንዱ ነው። ይህ ጎሳ የድሬደዋ ከተማ ስም በርሱ የተሰየመ ነው። ከሃረር እስከ ዘይላና በርበራ ማለትም የህንድ ውቅያኖስ ድረስ የተዘረጋ በሶማሊያም በኢትዮጵያም የተንሰራፋ ጎሳ ነው። ይህ ጎሳም ሆነ ሶማሊዎች በአጠቃላይ የተለያዩ ሱልጣኔቶች እና ግዛቶችን አስተናግደዋል። ከነዚህም የአዳል ሱልጣኔት አንዱ ነበር። አዳል ሱልጣኔት፣ ከፊል ሶማሊላንድን፣ የዛሬዎቹን ሃረርና ድሬደዋ አከባቢ ጨምሮ ይገዛ ነበር። በኋላ ይህ መንግስት ከወደቀ በኋላ የኢሳቅ ሱልጣኔት የሚባለው በ18ኛው ክፍለ ዘመን በርሱ ቦታ ተነስቶ ነበር። ይህንንም የመሠረቱት የሶማሊ ጎሳዎች ኢሳቅ የሚባል ከሳኡዲ አረቢያ የመጣ ሰው ከርሱ ተገኝተናል ብለው የሚያምኑ ሲሆኑ የኢሳቅ ጎሳ ተብለው ይታወቃሉ።

ወደ ኋላ ትንሽ መለስ እንበልና፣ የዲር ጎሳ፣ ኦሮሞዎች ወደ ቦታው ሲመጡ ወደ ራሳቸው አሲሚሌት ስላደረጓቸው ይህ ቅልቅል ዛሬ ላይ ሃረርጌ የምንለው ክፍለ ሀገር ውስጥ ያሉትን ህዝብ አስገኝቷል። በሌላ ስማቸውም "አፍረን ቀሎ" በመባል ይታወቃሉ። ታድያ እነዚህ የዲር ጎሳዎች በኦሮሞ አሲሚሌት የሆኑት ብቻ ሳይሆኑ በመላው የዛሬዋ ሶማሊያ፣ የኛዋ ሶማሊ ክልል፣ እንዲሁም በከፊል ጅቡቲ ውስጥም ይገኛሉ። በስራቸውም ብዙ ንኡስ ጎሳዎች አሏቸው። ከነዚህ ውስጥም የኢሳ ንኡስ ጎሳ ይገኝበታል። ይህኛው ኢሳ ቀደም ብለን ካነሳነው ኢሳቅ ጋር አንድ አይደለም። ግን ሁለቱም ሶማሊላንድ እና በከፊል ጅቡቲ ውስጥም ይገኛሉ። ኢሳዎች አሁንም ኢትዮጵያ ውስጥ አፋሮችን ጎረቤት ሆነው ይገኛሉ። አንዳንዴም በመሃላቸው ግጭት ይነሳል። ምናልባትም በሁለቱ መሃል የሚፈጠር ግጭት ለመላዋ ኢትዮጵያ —— ወረራ በር ሊከፍት ይችላል።

ብቻ የሆነ ሆኖ፣ የኢሳቅ ጎሳዎች በአሁኗ ሶማሊላንድ ውስጥ የራሳቸው ሱልጣኔት መስርተው ሳሉ ኢንግሊዞች በመምጣት ይወጓቸዋል። መጀመርያ ላይ ቢሸነፉም ያው እንደተለመደው መጨረሻ ላይ ያሸንፉና ከአከባቢው የጎሳ መሪዎች ጋር ስምምነት ተፈራርመው በኢንግሊዝ የበላይ ጠባቂነት ለመመራት ይስማማሉ። ይህ ከመሆኑ በፊት ንጉስ ምኒሊክ ቦታውን ለመቆጣጠር፤ ዘይላን እና በርበራንም በኢትዮጵያ ስር ለማድረግ ትልቅ ህልም ነበራቸው። ኢንግሊዞች ግን ይህንን በፍጹም ሊፈቅዱ አይችሉም። ለዚህ ነው አስቀድመው ቦታውን የያዙት። ከዚያም በኋላ ምኒልክ ትኩረታቸው እንዲወሰድ በቀይ ባህር በኩል ጦርነት ያስነሱት ለዚያ ነው።

ይህ በንዲህ ሳለ ከሶማሊላንድ ውጪ ያለው የሶማልያው ግዛት ከፊሉ ዛሬ ኦጋዴን የሚባለው በስምምነት ለምኒሊክ ሲሰጥ ሌላው የህንድ ውቅያኖስ ዙርያ ያለው በሙሉ ደግሞ በጣልያን እጅ ነበር። በኋላም የአፍሪካ ሃገራት "ነፃነታቸው" ሲታወጅ፣ ሶማሊላንዶች ከሶማልያ ጋር አንድ ለመሆን ተስማምተው የሶማልያ ሪፐብሊክን መሰረቱ። ነገር ግን ከደቡቡ ሶማልያ ጋር ወድያው ነበር አለመግባባቶች የተፈጠሩት። በኋላም ዚያድ ባሬ በሶማሊላንድ የኢሳቅ ጎሳዎች ላይ ከፍተኛ ጄኖሳይድ እንዳካሄደና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን እንደገደለ ይነገራል። ይህም ሶማሊላንዶች ከሶማልያ ጋር እስከዛሬም የማይስማሙበት አንዱ ምክንያት ነው። ከዚያም አስር አመት የፈጀ ጦርነት አድርገው ግዛታቸውን ነጻ አወጡ። ግን ማንም የዓለም ሀገር እውቅና ሊሰጣቸው ስላልቻለ አሁንም ድረስ በሶማልያ ስር ይቆጠራሉ። ነገር ግን የራሳቸው ፕሬዝዳንት፣ የራሳቸው ኢኮኖሚ፣ የራሳቸው መከላከያም ጭምር አላቸው።

አሁን ካለው የጂኦ-ፖለቲካ ሁኔታ ጋር ካየነው ደግሞ እነሱ እጅግ እስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ ናቸው። በቅርቡ እስራኤል የነሱን ሉዓላዊነት እንደምትቀበል አሳውቃለች። ይህ ለምን ሆነ? ስንል የመን ውስጥ ሁቲዎች እስራኤልን ፋታ ነስተዋታል። ቀይ ባህር ላይ የሚያልፉ መርከቦቿን፣ የአሜሪካ መርከቦችን ጨምሮ፣ ሁቲዎች ከኢራን ባገኙት መሳርያዎችና ሚሳኤሎች ተጠቅመው እያወደሙባት ነው። ኢስራኤል ተደጋጋሚ አየር ድብደባ ብትፈጽምባቸውም በመርከቦቿ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መታደግ አልቻለችም። እነሱም ለይተው የሷን እና የአሜሪካን መርከቦች ብቻ ይመታሉ። ስለዚህ እስራኤል አንዱ መፍትሄዋ፣ የመን ባለችበት የቀይ ባሕር መግብያ፣ ማለትም የኤደን ባሕረ ሰላጤ በሚባለው፣ ቅርብ ቦታ ላይ ጦሯን ማስፈር ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ አንዱ መልካም መፍትሄ ዘይላ ወይም በርበራ ላይ መስፈር ነው። ያ ማለት የሶማሊላንድን ሀገርነት እውቅና ትሰጣለች ማለት ነው። ታድያ አሁን ባለው አሰላለፍ፣ እስራኤል፣ ቱርክ እና አረብ ኤምሬት አንድ ጎራ ናቸው። ቱርክ ደግሞ በተመሳሳይ የራሷን ጦር ሰፈር ሶማልያ ላይ ማስፈር ትፈልጋለች። ቱርክ በቅርቡ ኢትዮጵያና ሱማልያን አስማማው ብትልም ስምምነቱ እሷና የኢትዮጵያን መንግስት ጠቅሞ፣ ሶማልያን እንደሚጎዳ አሳምራ ታውቃለች።

የእስራኤል ዋና ደጋፊ የሆነችው አሜሪካም ሶማሊላንድን እውቅና መስጠቷ አይቀርም። ትራምፕ ስልጣን ሲይዝ ያንን እንደሚያደርግ ተናግሯል። ያም ማለት፣ የኛው መንግስትም የሶማሊላንዱን ነገር ይገፋበታል ማለት ነው። ያም ማለት ከሶማልያ ጋር ሃይለኛ ጦርነት አይቀርም ማለት ነው። ምክንያቱም፣ ሶማሊላንድን መውሰድ ሲፈልጉ የሚመጣው መዘዝ አለ፣ በዚህ መሃል የኛው መንጌ የነሱን ቆሻሻ ስራ ይሰራላቸዋል፣ እነሱም ቀስ ብለው ቦታ ቦታቸውን ይይዛሉ ማለት ነው። በሶማሊላንድ ተጠቅሞ የውክልና ጦርነት ይከፍታል። ያም ጦርነት ገንፍሎ ወደዚሁ ይመጣል። ከዚያም ሲብስ ደግሞ፣ ኤርትራም ሱዳንም ግብጽም አልሸባብም ኢትዮጵያን ይወጓታል ማለት ነው። የኛ መንግስትም ሁሉም ነገር ከአቅሙ በላይ ሲሆን፣ እርዱኝ ብሎ ጥሪ ያቀርባል፣ እነሱም እሱን ለመርዳት ብለው ጦራቸውን ያመጣሉ፣ እነ ሩስያም የሱን ተቃዋሚዎች ደግፈው ይመጣሉ፣ ከዚያ መላውን የአፍሪካ ቀንድ የሚያካትት ይፈጠራል የለየለት የውክልና ጦርነት ይፈጠራል። ዝርዝሩ እንዴት ይሆናል? አሁን ላይ እንዲህ ብሎ መናገር አይቻለም። በጣም የተወሳሰበ ነገር አለው። ገና ከዚህም በላይ ይወሳሰባል። ያው መጨረሻው ግን የኛ በጦር ጀት መደብደብ፣ በአልሸባብ መወጋት፣ ወዘተ ነው የሚሆነው። ውጊያውም በጎራ በጎራ መሆኑ አይቀርም። ሰሜኑ በራሱ ውጊያ በኤርትራ እና ሱዳን በኩል ይጠመዳል፣ ኦሮሞ፣ ደቡቡ ደግሞ ከሶማሊው ጋር ይዋጋል። ብቻ ዝብርቅርቅ ያለ ነገር መፈጠሩ አይቀርም። በጣም ድብልቅልቅ ከመሆኑ የተነሳ ሁሉም ሰው "ቆይ ምን እየተካሄደ ነው?" ብሎ ይጠይቃል፣ መልስ የሚኖረው ግን የለም።

እኔም ይህን ጽሁፍ አሁን የምጽፈው፣ ቢያንስ ከአሁኑ የተውሰነ ፍንጭ እንዲኖረን ነው። ቢያንስ በጥቂቱ እንኳ አስቀድሞ ማወቅ፣ ንስሃ ገብቶ ለመጠበቅም ቢሆን ይጠቅማል።

ብቻ የሆነ ሆኖ፣ ይህ ክስተት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም እንዲበታተኑ ምክንያት ይሆናል። የአፍሪካ ቀንድን ስሪትም ይቀይራል። ወይ ኢትዮጵያ ከነ አካቴው ፈራርሳ ትጠፋለች፣ ወይም በሆነ መለኮታዊ ተአምር መላውን የአፍሪካ ቀንድ በአንድ ላይ ጠቅልላ ትይዛለች።


ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ ቀጣይ ምን ይፈጠራል የሚለው ከባድ ነው። ከዚህ በፊት ሁለት አመታትን የፈጀ አንድ መደበኛ ጦርነት፣ አሁን ደግሞ ብዙዎቻችን ባላውቀ የምናልፈው የሽምቅ ጦርነት እየተካሄዱ ነው። አሁን ደግሞ ቀጣይ የሚመጣው እጅግ አስፈሪ ይመስላል። ምናልባትም ከዚህ በፊት የነበረው ቀጥሎ ለሚመጣው ትንሽ ቅምሻ፣ ማሳያ፣ የሆነ ያህል ነው። ሃገራዊ የነበረው ጦርነት ቀጣናዊ ሆኖ፣ የአፍሪካ ቀንድን በሙሉ የሚያካትት፣ ግብጽንና የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራትን ሁሉ የሚያካትት የሚሆን ይመስላል። እጅግ ውስብስብም ግጭት ይመስላል። የኛ መንግስት በአንድ በኩል ከኤርትራ ጋር ተለያይቷል። በሌላ በኩል ደግሞ በሱማልያ በሰሜኑ የሶማሊላንዱን ግዛት፣ በደቡብ በኬንያ በኩል ደግሞ የጁባላንድን ግዛት መሪዎች እየደገፈ በእጅ አዙር የማመስ ሙከራ እያደረገ ይመስላል። ይህ ደግሞ ቀስ በቀስ የሶማሊያን መንግስት ከአልሸባብ ጋር እንዲተባበር እየገፋፋው ነው። አልሸባብ የሶማሊላንዱ ውል ከተፈረመ ጀምሮ ኢትዮጵያ ላይ የሃይል እርምጃ እንውሰድ የሚል አቋም ነበረው። የሃገሪቱ መንግስት ውስጥም ጥቂት ሰዎች የዚህ አቋም ደጋፊዎች ናቸው። በዚህም ምክንያት እስካሁን ትልቅ ጭቅጭቅ ላይ እንዳሉ አሉ። የኛ መንግስት ተግባሩን ከቀጠለ ደግሞ በራሱ እሳት ለኩሶ ራሱ ችግር ሊፈጥር ይችላል። ከዚያ ደግሞ እርትራ ከሱዳንና ሶማልያ ጋር መተባበር መጀመሯ በዙርያችን ሁሉም በኛ ላይ ጦርነት ለመክፈት ዝግጁ መሆኑን ነው የሚያሳየው።

ያ ሆኖ ሲያበቃ ደግሞ በውስጥም ከመንግስት ጋር ቅራኔ ያላቸው የሱን ማለፍ፣ መውደቅ የሚሹ ቡድኖች ታጥቀው ከርሱ ጋር መዋጋት ላይ መሆናቸው፣ ልክ በሶርያም ሆነ በሌሎች ሃገራት የነበረውን የእርስ በርስ ውግያና የውክልና ጦርነት እርሾ ይፈጥራል። ስለዚህ ነገ፣ የውጭ ሃያላን ተብዬዎች አንዱ ሰላም አስከባሪ ነኝ ብሎ፣ አንዱ አማጽያኑን ደግፋለሁ ብሎ፣ ወዘተ እኛን የውክልና ጦርነት ቀጠና ያደርጉናል። የሃገራችን የመሬት አቀማመጥ በፍጹም ለምድር ላይ ውጊያ የማይመች በመሆኑም ከፍተኛው የውጊያ መጠን በአየር ላይ ይሆናል። ስለዚህ ትላንት በሶርያ አሌፖን ወይም ደማስቆን፣ በኢራቅ ባግዳድን ወይም ሞሱልን፣ በሊቢያ ትሪፖሊን የቦምብ መአት እንዳወረዱባቸው ሁሉ፣ ነገም እኛ ላይ፣ ባህርዳርን ውይም ናዝሬትን ወይም ጎንደርን የቦምብ የሚሳኤል መሞከርያ የማድረግ ምኞት ወይም ህልም ይኖራቸዋል። በውጊያም አሳበው ምናልባት በሰበቡ ደብረ ሊባኖስን፣ ወይም ዋልድባን፣ ወይም አክሱም ጽዮንን በቦምብ፣ በሚሳኤል የሚመቱበትም ሁኔታም ሊፈጠር ይችላል።

በተለምዶ ሃገራት ላይ እንዲህ አይነት የአየር ክልልን የመዳፈር ተግባር ከመፈጸማቸው በፊት የሃገሪቱን አየር ሃይል እና አየር መቃወይሚያ ድራሹን ነው የሚያጠፉት። ሩሲያ ዩክሬን ላይ ያደረገችው ያንን ነው። እግጅ ፈጣን በሆኑት ሃይፐር-ሶኒክ ሚሳኤሎች መላውን የዩከሬን አየር መቃወሚያ ስርአት ካወደመች በኋላ ማንም ከልካይ ሳይኖራት ገብታ በርካሽ ድሮኖች እና የጦር ጀቶች የፈለገቸውን ቦታ ደብድባ ትመለሳለች። ኢትዮጵያ ግን ቀድሞውኑ ያ ስርአት የላትም። ደርግ ከሶቭየት ከገዛቸው ያረጁ ጥቂት ጀቶች እና ሚሳኤሎች በቀር ምንም የለንም። ዛሬ ላይ ደግሞ ዓለም ሁሉ እጅግ የዘመነ ሚሳኤል እስከ አፍንጫው ታጥቋል። በየጊዜው አዳዲስ መሳርያ ሁሉ ይፍለስፋሉ። የሰው ልጅ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እውቀቱን ተጠቅሞ ለሰው የሚጠቅም ፈጠራ እንደመስራት ጅምላ ጨራሽ አዳዲስ ቴክኒኮችን ይፈጥራል። ዛሬ ላይ ኢራን ብቻ ያሏት የሰራቻቸው ሚሳኤሎች ኢትዮጵያን መምታት ይችላሉ። መምታት ከፈለጉ ይችላሉ። እኛ ግን ማንም ዓለም አስቦልን ወይም ራርቶልን ሳይሆን በእግዚአብሔር ቸርነት እስከዛሬ አለን። ታዲያ የሱን ቸርነት እንደማመስገን ከሱ ጋር እንደመጣበቅ በምዕራባውያን "እውቀት" እና ፍልስፍና ተወስደን የነሱን ሰዶማዊ ባህል ተላብሰን እግዚአብሔርን፣ በቸኛው ተስፋችንን በድለናል፣ አስከፍተናል። ከአሁን ወዲህ መጠጊያችን ወዴት ነው? ንስሃ ገብተን ወደሱ ከመመለስ ውጪ ምን ምርጫ አለን?

ዓለምስ በእግዚአብሔር ቢያምጽ ያለውን ታንክ፣ ጀት፣ ኤለክትሮኒክስ ተማምኖ ነው። እኛ ምን ይዘን ነው በፈጣሪ ላይ ያመጽነው? ይሄንን ነው መጠየቅ ነው ያለብን። እግዚአብሔር አንዳች ልዩ፣ መለኮታዊ ተአምር ፈጥሮ ካላዳነን፣ ምናልባት ሊወጉን የሚመጡትን ሰራዊት፣ ስምጥ ሽለቆን ከፍሎ ባሕሩ ውስጥ ካላሰጠማቸው፣ አባይ ሞልቶ ፈሶ ጠርጎ ካልወሰዳቸው እኛ ምንም ሚሳኤል፣ ምንም ሮኬት፣ ምንም ታንክ የለንም፣ እና ያንን እያሰብን በእንባ፣ በለቅሶ፣ በንስሃ ወደሱ መቅረብ በናስብ ነው የሚሻለን።




˙       •❀• [ ስንክሳር ዘታኅሣሥ ፮ ] •❀•
                
             •• ቅድስት አርሴማ ሰማዕት ••
                              ๏-❀-๏


ይህች ዕለት ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍልሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ ናት።

እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው።

መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና" (ማቴ. 5፥11) የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል።

🌿 ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት።
🌿ቅድስት አርሴማ ይህ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት።
🌿 ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት።
🌿 ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት።
🌿 ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት።

ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦

አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ ጎርጎርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው። በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት፦

፩. ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት
፪. ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት
፫. የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት።

ቅዱሱ 3ቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ። ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት። መከራው ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ፣ ይጾሙ፣ ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር።

ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማንና ቅዱስ ጎርጎርዮስን ጻድቃን የምንላቸው። በኋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኩዋ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ።

በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ። ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው። የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ።

በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ። በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር። መከራው ግን አለቀቃቸውም። ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው።

ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሣ መታገሥ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት። ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ አይሆንም" አለችው። ሊያስፈራራት ሞከረ። ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው።

አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው። እጅግ ስላፈረ አስገረፋት፤ አሰቃያት፤ ዐይኗንም አወጣ። በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት።

ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው።

የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ። የንጉሡ እኅት ስታለቅስ በራዕይ "ጎርጎርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው። ወዲያውም ቆፍረው አወጡት።

ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም። ለ15 ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው። ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው።

የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ኢትዮጵያ እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል

ለዚህም ይመስላል ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ፍቅር ያላት። በዋናው ገዳሟ (ወሎ /ኩላማሶ/ : ስባ : ውስጥ የሚገኝ ነው) ጨምሮ ስሟ በተጠራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና።

በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል። ይህች እናት እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት፣ ታጸናት፣ ከጎኗም ትቆምላት ነበር።

ረሃቧን፣ ጥሟን፣ ስደቷን፣ መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች። በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች።

◦🌿◦🌿◦🌿◦


"የብልሃተኛ እጅ ያልሰራት በውስጧም መብራት የማያበሩባት የወርቅ መቅረዝ አንቺ ነሽ፣ ራሱ የአብ ብርሀን ያበራባታል እንጂ። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ወደ አንቺ መጥቶ አደረ በአምላክነቱም በዓለም ሁሉ አበራ። ጨለማን ከሰዎች ላይ አራቀ፤ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ በብርሃኔ እመኑ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ ብሎ በሚያድን ቃሉ አዳነን።"

ቅዱስ ያሬድ፥ አንቀጸ ብርሃን


via Mark Abyssinia:

ያው እንግዲህ ውሀብዩን ሽብርተኛ የአልቃይዳ ክንፍ በሽብርተኝነት ከሰው ካሰሩት በኋላ አሰልጥነውና አስታጥቀው መልሰው ራሳቸው በፈለሰፉት የISIS ክንፍ ውስጥ አስገብተው የራሱን አብዮት ሶሪያ ላይ እንዲጀምር አድርገው ሌላውን የአልቃይዳ ክንፍ ገርስሰው ከ15 አመት በላይ በሶሪያ ምድር የዕርስ በርስ ንትርክ ፈብርከው....ከሩሲያና ኢራን ጋር የዕጅ አዙር ጦርነታቸውን በድል አጠናቀው ይሄን ውሀብይ ዶላር አስታቅፈው እንደኢራቅ ፍርስራሹ ላይ ንጉስ ብለው ሰይመውታል።አዎ ይሄ የአሜሪካና የእስራኤል የጉልበተኝነት አለም ነው።ይሄ አለም ክፉ ነው።ሳንጣላ ያጣሉናል።ሳይቸግረን ተቸገራችሁ ይሉናል።ያልሆነውን ሆናችሁ ይሉናል።ተባብረን ሀገር ማሳደግ ስንጀምር ከፍ ማለት ስንጀምር ትንንሽ ባንዳዎችን አሰባስበው የረሳነውን የዘር DNA ያስቆጥሩናል።ይሄ ይቺ የኛ ምድር በአሜሪካውያን በባብሊዎኖቹ ምክንያት ሰላሟን እንዳጣች እስካሁን አለች።የእነዚህን አከርካሪ ተፋልሞ የሰበረው አማኙ ምኒሊክ ብቻ ነበር በታሪክ።አሁን ግን እንዲያ ያለ መሪ አጥተን ቀናችንን እየረገምን በተስፋ ፈጣሪን እንለምናለን።ምናልባት ቀጣይዋ የነሱ ታርጌት ኢትዮጵያ ናት።በርግጥ መምጣታቸው አይቀርም።መካከለኛው ምስራቅን አፈራርሰው ጨርሰዋል።የቀረች ኢራን ናት።በፍርሀት ተከባለች።.....ምናልባት ይቺ ትንሿ የምስራቋ አናብስት ምድር ኢትዮጵያችን ድጋሜ አሳፍራ ትመልሳቸው ይሆን?!!!

የሳዳሙሴ የመጨረሻ ሳቅ ትዝ አለኝ።ሞት ተፈርዶብሀል ሲባል።በሀገሩ ፍ/ቤት አሜሪካ የሰየመችው ዳኛ በገዛ ምድርህ ስለፍትህ ሲያቧርቅ አስበው።ንዴት በጨረሰው ገላህ ትሞታለህ ስትባል ሚፀፅትህን በምድር ካልሰራህ መልስህ ፈገግታ ብቻ ነው።ሰላም ከሞት ጋር!!

ወገኖቼ ዙሩ እየከረረ ነው።


Forward from: አዲስ ምልከታ🌍
#ጠፈር #firmament
ምንድነው?
ቋንቋ በተፈጥሮው ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ይሞታል። አንድ ቋንቋ የማደግ ደረጃ ላይ ባለበት ወቅት፣ አዳዲስ ቃላትን፣ ሀረጋትን አልፎም አገላለጾችን(expressions) እና አባባሎችንም ያዳብራል። ይህም የራሱን ቃላት በማርባት አዳዲስ ቃላት በመፍጠር አልያም ከሌሎች ቋንቋዎች በመዋስ ሊሆን ይችላል። አንዳንዴም ከሌሎች ቋንቋዎች የተቀበላቸውን ቃላት በራሱ ቋንቋ ውስጥ አቻ ቃል በመፈለግም ሊሆን ይችላል። እነዚህ ነገሮች ታዲያ፣ በሀገራችን ዘመናዊ ትምህርት ሲገባ የሀገራችን ሰው የውጪውን ዓለም እውቀት፣ ጥበብ፣ ፍልስፍና፣ ባህል ወደ ራሱ ለማዋሃድ ጥቅም ላይ አውሎታል። የዚህም ውጤት በየቦታው፣ በየትምህርት ዘርፉ እናያለን። ከተነሳንበት ርዕስ አንጻር ስናየውም፣ የሀገራችን ሰው የተለያዩ የአስትሮኖሚ ቃላትንና ሀሳቦችን በሀገርኛ ቋንቋ ለማቅረብ ሞክሯል። ከነዚህም የተቻለውን ያህል ቃላት በሀገርኛ አነጋገሮች ተክተናል። የዚህም ምሳሌ እንደ ስነ ፈለክ፣ ህዋ፣ ጠፈር፣ የመሳሰሉትን ቃላት ማንሳት እንችላለን። ታዲያ ይህን ስናይ፣ አንድ ሳናስተውል ያለፍናቸው ነገሮች ይኖራሉ። ይህም ለምሳሌ "ጠፈር" የሚለውን ቃል ብናየው፣ በተለምዶው በሳይንሱ የምናውቀውና የቃሉ ኦሪጂናል ትርጉም ምን ያህል እንደሚለያዩ ያስተዋልን አይመስልም።

ቃሉን በተለምዶ የምንጠቀምበት "space" ወይም "universe" የሚሉትን ሀሳቦች ለመግለጽ ነው። ይህም ከምድር ውጪ ያለውን ሰፊ አካባቢ ሲጠቁም ነው። የቃሉ የመጀመሪያ ትርጉምስ?

ይህን ቃል ከሃይማኖታዊ እይታ ስናየው የሚከተለውን ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን፦

1. ኦሪት ዘፍጥረት 1፥ 6-8
እግዚአብሔርም። በውሆች መካከል #ጠፈር ይሁን፥ በውኃና በውኃ መካከልም ይክፈል አለ። እግዚአብሔርም #ጠፈርን አደረገ፥ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኆች ለየ ፤ እንዲሁም ሆነ። ፤ እግዚአብሔር #ጠፈርን #ሰማይ ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሁለተኛ ቀን።

2. ኦሪት ዘፍጥረት 1፥14-15
እግዚአብሔርም አለ። ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት #በሰማይ_ጠፈር ይሁኑ ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ ፤ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ ፤ እንዲሁም ሆነ።

3. ኦሪት ዘፍጥረት 1:20
እግዚአብሔርም አለ። ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፥ ወፎችም ከምድር በላይ #ከሰማይ_ጠፈር_በታች ይብረሩ።

4. መዝሙረ ዳዊት 19(20)፥1
ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ #የሰማይም_ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።


ሌሎችም ቦታዎች ላይ ይህ ቃል ተጠቅሷል። ከዚህ የምንረዳው ታድያ፣ ጠፈር ማለት ከምድር በላይ ያለ፣ አካል ሲሆን ይኸውም በሌላ አገላለጽ ሰማይ ማለት እንደሆነ ይነግረናል። ጠፈር ማለት ጠንካራ፣ ምድርን እንደጉልላት የሸፈነ፣ ብርሃናት (ማለትም ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ክዋክብት) ልክ ኮርኒስ ላይ እንዳለ መብራት እርሱ ላይ ያሉት አካል እንደሆነ ይነግረናል መጽሐፉ። ይህም በሳይንስ ከለመድነው ወጣ ያለና ተቃራኒ የሆነ ነው። በሳይንስ መሠረትም ይህ አካል የለም፣ ሊኖር አይችልም ። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰዎች የተለያዩ ሙከራዎችን አድርገው ይህ አካል በርግጥም እንዳለ ለማሳየት ሞክረዋል። ይህውም አነስተኛ መንኩራኩሮችን ሰርተው ላያቸው ላይ ካሜራ ከገጠሙ በሁዋላ ማምጠቅ ነው። ከዚያም መንኩራኩሩ ከአንድ አካል ጋር ይጋጫል ወይስ አይጋጭም የሚለውን ለማየት የተለያዩ ሙከራዎችን አድርገዋል። ይህንንም በቪዲዮ የምናይ ይሆናል።

@hasabochhh


እንሆ የሶርያ መንግስት በዚህ ሁኔታ ተደምድሟል። ፕሬዝዳንቱ ከሀገር ሸሽቶ የት እንዳለ አይታወቅም፣ አንዳንዶች እሱ የነበረበት ፕሌን ተከስክሷልም ይላሉ። ሴኩላር የአረብ ሪፐብሊክ የነበረው የበአቲስቶች አይዲዮሎጂም በመጨረሻ ጠፍቷል። በምትኩም አማጺያኑ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ይጠብቃሉ። ነገር ግን አማጺያኑ በራሳቸው የተበታተኑና የየራሳቸው ጎራ ያላቸው ናቸው። እርስ በእርስም የሚዋጉ ናቸው። ይህ ማለት በአጭሩ ሶርያ ሊቢያና ኢራቅን ተቀላቅላለች ማለት ነው።

ይህ ለኢትዮጵያ ጥሩም መጥፎም ዜና አለው። ጥሩው ዜና፣ ለኢትዮጵያ መውደቅ ሲሰሩ የነበሩ፣ ኢትዮጵያን failed state ለማድረግ ሲለፉ የነበሩ ለዚህም ታጣቂ ቡድኖችንና አማጺያንን ያሰለጠኑት ሀገራት በሙሉ ራሳቸው failed state መሆናቸው ነው። ሶርያም እነዚህን መቀላቀሏ ነው። የአረብ በአቲስት ብሔርተኞች ኢራቅ ሶርያና ሊቢያም ጭምር ብዙ የኢትዮጵያ "ነፃ አውጪ" ቡድኖችን በስልጠና፣ በገንዘብ፣ በመሳርያም ጭምር ለዘመናት ሲደግፉ የነበሩ መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው። ግን እነርሱ እንዳለ ፈርሰው ኢትዮጵያ እስከዛሬ አለች። የኢትዮጵያ አምላክ ሁሌም ይሰራል።

መጥፎው ዜና ደግሞ፤ ለኢትዮጵያ ጊዜ ሲሆን ሴኩላሮቹም ጂሃዲስቶቹም አቋማቸው አንድ መሆኑ ነው። ስለዚህ በእስራኤልና ቱርክ የሚደገፈው አክራሪ ቡድን በጣም ይስፋፋል። ከሶርያ ተነስቶ ሊባኖስንም ዮርዳኖስንም ምናልባት ኢራቅንም ማመሱ አይቀርም። የማይነካው እስራኤልን ብቻ ነው😂😂 በግልጽ እስራኤል ወዳጃችን ናት ብለዋል😂😂

እናም ይህ ቡድን ቱርክ በኢትዮጵያ ባላት ተጽዕኖ፣ በሌላውም መንገድ ተጠቅመው የተለያዩ ሴሎችን እዚህም መፍጠራቸው አይቀርም። በኢትዮጵያ የጥንቱ ሱፊ እስልምና፣ ለክርስቲያኖች ክብር የነበረው፣ ታቦት ቆመን እናሳልፍ ይል የነበረው አሁን ተሸንፏል። የወደፊቱ ጊዜ እጅግ አስፈሪ፣ እጅግ አሳሳቢ ነው። ጂሃድ ኢትዮጵያ ውስጥ አይቀርም። ምክንያቱም ወሃቢስቶች አሸንፈዋል። ይኸው ነው ነገሩ።

እናም ደስ እያላቸው😂 ከግዮን እስከ ኤፍራጥስ የሚለውን ህልም ያሳካሉ😂😂 አባይን እስከ ምንጩ መቆጣጠር እየቻሉ ለምን ሲባል ግብጽ ላይ ይወሰናሉ😂😂 ይህ ግድብ ሁሉ ገና ብዙ ጣጣ ያመጣብናል። የሶስተኛው የዓለም ጦርነት አንዱ መድረክ እኛ መሆናችን አይቀርም።

ስለዚህ አሁን፣ ምንም መቀባባት አያስፈልግም፣ እውነቱን እንነጋገር።

ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ይሞታሉ፣ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ይሰደዳሉ፣ ጥቂቶች ይተርፋሉ።

በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ማስታወስ ያለብን አንድ ነገር ነው። ይህ ሁሉ የመጣብን በኃጢአታችን ምክንያት ነው። እናም ለብዙዎቻችን የንስሃው እድል ያለፈን ይመስለኛል። ቢያንስ እንኳ አንዳንዶቻችን የክርስቶስ ሰማዕት ሆነን የማለፍ እድል ተሰጥቶናል። እሱንም ቢሆን እንጠቀምበት።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
📹 ከግዮን እስከ ኤፍራጥስ


ከግዮን እስከ ኤፍራጥስ


እንደ ኳንተም ያሉ ጽንሰ ሃሳቦች የሳይንስ እድገት እና ግኝት የደረሰበት ከፍታ ተደርገው ቢወሰዱም እውነታው ግን የሳይንስ ባህሪን የማያሳዩ እና የአውሬው ሰራተኞች የሚያኑባቸውን የሚስጥር እምነቶች የሚገልጹባቸው መንገዶች ናቸው። አሁን ላይ ደግሞ በግልጽ ከማጂክ ጋር እንደሚገናኝ በዚህ መልኩ እየነገሩን ነው።


Forward from: አዲስ ምልከታ🌍
ይህ ስእል ከ "far side of the moon" የተቀረጸ ነው ይባላል። እነሱ እንደሚሉት ከሆነ ጨረቃ ሁሌም አንዱ ገጿ ብቻ ነው ወደ ምድር የሚዞረው። ሌላኛው ገጿ ሁሌም ከምድር ተቃራኒ ነው። ይህም ፎቶ የተነሳው የምድር ተቃራኒ ከሆነው ገጽ ነው።

ታዲያ ይህ ምስል ላይ ምድር ሙሉ አካሏ ይታያል። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ፀሐይ ከካሜራው ጀርባ ናት ማለት ነው። ብርሃኗ በካሜራው አቅጣጫ ቀጥታ ሲመጣ ሙሉ ምድር ላይ ያርፋል። ስለዚህ ምድርም ትታያለች ማለት ነው።

ነገር ግን ይህን ምስል ያቀናበሩ ሰዎች አንድ ስህተት ሰርተዋል። ይህም ጨረቃን ጠቆር አድርገው ነው ያስቀመጡት። ነገር ግን ጨረቃ በደምብ ደምቃ አብርታ መታየት አለባት፣ ምክንያቱም ከካሜራው ጀርባ ያለው ብርሃን ሙሉ በሙሉ እያረፈባት ስለሆነ። ነገር ግን በምስሉ ላይ የምናየው የዛን ተቃራኒ ነው።

ስለዚህ ምስሉ የተቀናበረ እንጂ እውነተኛ አይደለም ማለት ነው።

ነገር ግን አስትሮኖመሮች ከህዋ ላይ የቀረጹት ነው ተብሎ በሚዲያ ዜና ላይ የታየ ምስል ነው።


Forward from: አዲስ ምልከታ🌍
ከህዋ ተነሱ የሚባሉ ምስሎች በሙሉ በእስቱዲዮ የተቀናበሩ ናቸው። ይህንንም ማረጋገጥ ይቻላል። ሌላ ምሳሌም እንመልከት።


Forward from: አዲስ ምልከታ🌍
አንደ አካል ብርሃን ሲያርፍበት ብርሃኑ ካለበት አቅጣጫ ያለው ከፍሉ ደማቅ ብርሃን ይሆናል፣ የሱ ተቃራኒ ብርሃኑ ያልደረሰው አቅጣጫ ደግሞ ጭለማ ወይም ጥላ ይሆናል። በዚህም ምክንያት ብርሃኑ በየት በኩል እንዳለ ማወቅ እንችላለን።

በዚህም መሠረት ከላይ ያለውን ምስል ተመልከቱት። ምድር እንደሚታየው ብርሃናማ ሆና ትታያለች። ይህ ማለት ብርሃኑ እየመጣ ያለው ከላይ ነው፣ ወደታች ወደ ምድር ስለሚያበራ በብርሃኑ ትይዩ ያለው ክፍሏ ደማቅ ብርሃናማ ሆኖ እያየነው ነው።

ከዚያ ሰውየውን ደግሞ ተመልከቱት። ከታች ያለው ገጹ ደማቅ ብርሃናማ ሆኖ ይታያል። ከላይ ደግሞ ጥቁር ጭለማ። ይህ ማለት ለሰውየው ብርሃኑ እየመጣ ያለው ከላይ በኩል ሳየሆን ከታች ነው።

ግን ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ከታች ያለውን ምድር ካየን የፀሐይ ብርሃን ከላይ በኩል መኖር አለበት፣ የሰውየው አካል ግን ብርሃን እያገኘ ያለው ከላይ ሳይሆን ከታች በኩል ነው። በአንድ ምስል ላይ ይህ እንዴት ሊፈጠር ይችላል? መልሱ ምስሉ የተቀናበረ ነው። የሚለው ይሆናል። ሁለቱ ነገሮች ከሁለት ቦታ የመጡ ስእሎች አንድ ላይ ተደርገው ነው። ስለዚህ ይህ "astronaut" ህዋ ላይ የተቀመጠ የሚመስለው ትክክለኛ ምስል ሳይሆን ተቀናብሮ የተዘጋጀ ነው።


ከሰሞኑ በሶርያ የእርስ በእርስ ጦርነት በድጋሜ አገርሽቷል። ጦርነቱ የተነሳው የአይ ኤስ ቡድን ተቀጥያ የሆነው የ ኤች ቲ ኤስ አሸባሪ ቡድን የአሌፖ ከተማን በአስደማሚ ሁኔታ በሶስት ቀናት በተቆጣጠረ ወቅት ነው ተብሏል። ይህም ቡድን ከሌሎች አማፂ ቡድኖች ጋር የቱርክ ድጋፍ ያለው ሲሆን በዚህም ምክንያት ቱርክ ከኢራንና ሩሲያ ጋር ወደ ግጭት የመግባት እድሏ ሰፊ መሆኑ ነው የሚነገረው። ምናልባትም ይህ ሶስተኛውን የዓለም ጦርነት ያስነሳ ይሆን?

በሶርያ የአይ ኤስ ቡድን ከወደቀ በኋላ የእርስ በእርስ ጦርነቱ ረግቦ ነበር። ሶርያም ከኢራን ከፍተኛ ድጋፍ ያላት በመሆኑ የኢራንን ሚሳኤሎችና ጦር መሳርያዎች ወደ ሊባኖስ አስተላልፋ ለሂዝቦላህ ትሰጥ ነበር። በቅርቡ በነረበው የሊባኖስ ጦርነትም ሂዝቦላህ የእስራኤልን ከተሞችና የጦር ካምፖች ሁሉ ደብድቧል። የእስራኤል ጦር በሃይል ወደ ሊባኖስ ቢዘምትም ሂዝቦላህ ግን ከጥቂት ኪሎሜትሮች በላይ ሊሄድ አልቻለም። በዚህም ምክንያት እስራኤል የተኩስ አቁም ተፈራረማ ጦሯን መልሳለች። በዚህም ሽንፈት ደርሶባታል።

ነገር ግን ወዲያው በቱርክ የሚደገፉ የአማፂ ቡድኖች ሶርያ ላይ ጦርነት ከፈቱ። ቀድሞም አይ ኤስ ቡድን ከእስራኤል ጋር ቁርኝት አለው ተብሎ ይታማ ነበር፣ አሁንም ያንን አረጋገጡ። ምክንያቱም የሂዝቦላ ድጋፍ የነበረችው ሶርያ ላይ ውጊያ በመክፈታቸው።


በዚሁ አጋጣሚ የአይ ኤስ ቡድንን አመጣጥ እና የሶርያውን እርስ በእርስ ጦርነት ታሪክ እንዳስስ። ነገሩን ወደኋላ ከመዘዝነው ሰፊና ውስብስብ ታሪክ አለው። ግን ከአንደኛው የዓለም ጦርነት እንነሳ።

ከጦርነቱ በፊት አረቡ ዓለም በኦቶማን ቱርክ ስር ነበር። በጦርነቱም ቱርክ ስትፈርስ ግዛቶቿን አውሮፓውያን ተቀራመቱ። ኢንግሊዝ እና ፈረንሳይ አዲስ ካርታ ስለው አርቴፊሻል ሀገራትን ፈጠሩ። ሊባኖስ፣ ሶርያ፣ ኢራቅ፣ ዮርዳኖስ የሚባሉ ሀገራት፣ ሌሎችም ተፈጠሩ። ፍልስጤምም ተፈጠረችና ለእስራኤል ተሰጠች። ነገር ግን ይህ ነገር ለአረቦች አልተመቻቸውም ነበር። ከፍተኛ ተቃውሞ አድርገውም ነበር። ከዚህ ተቃውሞ ውስጥ አንዱ ትልቅ ነጥብ ደግሞ የበአቲስት ንቅናቄ ነበር። ይኸውም ሴኩላር የሆነ አንድ የአረብ ሪፐብሊክን የመፍጠር ህልም ነበር። የዚህ አይዲሎጂ አራማጅ ከሆኑት ውስጥ እነ ሳዳም ሁሴን፣ ሃፊዝ አል አሳድ እና ልጁ በሸር አል አሳድ ይገኙበታል።

ታዲያ አረቦቹ እነ ሶርያ በዚህ አይዲዮሎጂ ተመርተው የራሳቸው ዲሞክራሲን ሲፈጥሩ አሜሪካ ሰላዮቿን እየላከች ታምሳቸው፣ ተደጋጋሚ መፈንቅለ መንግስት ትፈጽም ነበር። በዚህም ምክንያት በሶርያና ኢራቅ ተደጋጋሚ መፈንቅለ መንግስቶች ይካሄዱ ነበር።

በኋላ በሶርያ ሃፊዝ አል አሳድ፣ በኢራቅ ደግሞ ሳዳም ሁሴን ስልጣን ይይዙና አምባገነን ሆነው ለአሰርት ዓመታት ይገዛሉ። በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1983 እና 1995ም አሜሪካ ሁለት ጦርነቶችን በኢራቅ ላይ ታካሄዳለች። በ95ም (በነሱ 2003) ኢሜሪካ ሳዳም ሁሴንን ትገድልና የርሱን መንግስት ሙሉ በሙሉ ታፈርሳለች። ማለትም በሱ ስር የነበረውን የመንግስት፣ የደህንነት፣ የፖሊስ፣ የመከላከያ መዋቅር ሙሉ በሙሉ ታፈርሳለች። ሰዎቹ በሙሉ ስራ አጥ ይሆናሉ። 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢራቃውያንም ይሞታሉ።

ከዚያም ሰዎቹ በዚህ ንዴት አዲስ የአል ቃይዳን ክንፍ ይፈጥራሉ። ለሚቀጥሉት ዓመታትም የአሜሪካን ጦር የእግር እሾህ ይሆኑበታል። ያላቸውን ልምድና እውቀት ተጠቅመው የመንገድ ላይ ፈንጂዎችን፣ በቤት የሚሰሩ ተቀጣጣዮችን እየተጠቀሙ፣ የሽምቅ ውጊያን እየተጠቀሙ የአሜሪካን መከላከያ አሳሩን ያበሉታል። አሜሪካም በአከባቢው ያሉ አማጺያንን ብር በመክፈል ትወጋቸውና ሊጠፉ ይደርሳሉ። ከዚያም ከፊሎቹ ሸሽተው ወደ ሶርያ ይገባሉ። በሸር አል አሳድም ይቀበላቸዋል። ባይወዳቸውም ይጠቅሙኝ ይሆናል ብሎ ያስገባቸዋል። ታዲያ ከነሱ ቀድሞ የአልቃይዳ ክንፍ በሶርያ ነበር።

ቀጥሎም በኛ 2003 በነጮቹ 2011 የአረብ እስፕሪንግ ተቃውሞ በመላው የአረቡ ዓለም ይነሳል። በሸር አል አሳድም ተቃዋሚዎቹን በአሰቃቂ ሁኔታ ይጨፈልቃቸዋል። በዚህም ጊዜ ተቃውሞ ይቀርና ትጥቅ ይዘው ይነሳሉ። በዚህም ውስጥ የተለያዩ ቡድኖች ነበሩ። በአንድ በኩል የአሳድ መንግስት አለ። ቀጥሎ የአልቃይዳ የሶርያ ክንፍ አለ፤ ቀጥሎ በአሜሪካ የሚደገፉ የሶርያ ታጣቂዎች አሉ። በመጨረሻም ከኢራቅ የመጣው የአልቃይዳ ክንፍ፣ ማለትም የሳዳም መንግስት የቀድሞ ሰዎች ቡድን አለ። ይህ ቡድን፣ አሁን ተለውጧል። እጅግ አክራሪ ጂሃዲስት ሆናል። ከዚህም የተነሳ አልቃይዳ ራሱ ደንግጦ ከኛ ተለዩ አትወክሉንም ብሏቸዋል። በዚህም ምክንያት የስም ለውጥ አድርገው ይመጣሉ።

ራሳቸውን "ዳኤሽ" ይሉታል። በኢንግሊዘኛውም አይ. ኤስ. አይ. ኤል ይሆናል። ሰዎች በስህተት አይ ኤስ አይ ኤስ ይላሉ ግን መጨረሻው አይ. ኤስ ሳይሆን አይ. ኤል ነው። ትርጉሙም እስላማዊ መንግስት በኢራቅ እና ሌቫንት ማለት ነው። ሌቫንት በአረብኛ "ሻም" ይሉታል።

ታዲያ ይህ ቡድን ሁላችንም የምናውቀውን አሰቃቂ ሽብር እየፈጸመ ይመጣል። መላውን ዓለምም አረቦቹን ሳይቀር ያስደነግጣል። ቤተክርስቲያን፣ መስጊድ ሳይል እያጋየ ይሄዳል። ሌላው ቀርቶ ሶርያ ውስጥ በሮም ኢምፓየር የነበረችን ፓልሚራ የምትባል ታሪካዊት ከተማ ሁሉ በድማሚት ያጋይ ነበር። በኋላም ወደ ኢራቅ ይመለስና ወረራ ያካሂዳል። ባግዳድና ሞሱል የተባሉትን ወሳኝ ከተሞችም ተቆጣጥሮ ወደ ኩርዶች ግዛት ይሄዳል። በዚህም ጊዜ ሁሉም ይደነግጥና በርሱ ላይ ጥቃት ይከፍታል። ኢራንም፣ ሶርያም፣ ቱርክም፣ አሜሪካም፣ ሂዝቦላም በሱ ላይ ጥቃት ይከፍታሉ። ቀስ በቀስም ቡድኑ ይፈራርሳል። ሩሲያም የአሳድን ቡድን መደገፍ ትጀምራለች። የሶርያ አማጽያንም ይደክማሉ፣ ኢራንና ሩሲያም እነ አሳድና ሂዝቦላን ከፍተኛ ድጋፍ ያደርጉላቸዋል።

ይህንን ካል ስለ አይ ኤስ የተሰወነ እንጨምር። አይ ኤስ ቡድን ከእስራኤል ጋር ንክኪ አለው። እስከዛሬ እስራኤልን ወግቶ አያውቅም። አንዳንዶች እንደውም ቀጥታ ከሞሳድ ጋር ይገናኛል ብለው ያሙታል። ሌላው ደግሞ ከኢንግሊዝ የስለላ ድርጅትና በአሜሪካ ከሚገኝ ኦርደር ኦፍ 9 ኤንጅልስ ከሚባል ሰይጣኒዝምን ከሚከተል የናዚ ቡድን ጋርም የአይ ኤስ አባላት ቁርኝት እንዳላቸው ተመልክቷል። ያው በአጭሩ የኢሉሚናቲ ፈጠራ ውጤት ናቸው ማለት ነው። ምናልባትም "ከግዮን እስከ ኤፍራጥስ" የሚለውን የእስራኤል ህልም ለማሳካት የተፈጠረ ይሆን?

ከዚህ በተጨማሪም አይ ኤስ የወሃቢ እስልምና ቡድን ተከታይ ነው። ይህም ቡድን አሰቃቂ ጂሃድን የሚደግፍና ነቢዩ ሙሃመድ ኢትዮጵያን አትንኩ ያለውን የማይቀበል ነው። የዚህ እሳቤ ተቀባዮችም ምናልባት አሁን ወደ ሀገራችን ሊመጡ ይችላሉ፣ መጥተውም ሊሆን ይችላል። አሁን ደግሞ ቡድኑ እያንሰራራ መሆኑ፣ በቱርኩም እየተደገፈ መሆኑ፣ ቱርክም ኢትዮጵያ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆኗ ነገሩን ሁሉ አሳሳቢ ያደርገዋል። ምናልባት ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በሰፊው ሰማዕትነት የምንቀበልበት ጊዜም ሊመጣ ይችላል። ነገሩ ሁሉ አሳሳቢ ነው።

ምናልባት መከራው የሚመጣብን በራሳችን ሃጢአት ይሆናል (ማስረጃ ከፈለጉ ቲክቶክን ይመልከቱ፣ ትውልዱ ምን እየሰራ እንደሚውል ይታዘቡ) ስለዚህም ይቅር በለን ብለን መጸለይ ይሻለን ይሆናል። በሁሉም ግን እግዚአብሔር የፈቀደው ይሁን። ሀገሩን አሳልፎ እንደማይሰጥ እርግጠኛ ነኝ። እኛንም ግን በዚያው ያስበን።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
The so called Solar System is a mathematically chaotic, unpredictable system. the problem of finding the "center of gravity" in a 3-body system is mathematically unsolvable. and when it's extended to a more complex system like the solar system with 100+ bodies (8 planets, 1 star, 100+ satellites), is much more complicated and even more so unsolvable. and there is no way to predict the future states of such a system using this model.

we say a mathematical model describes a natural phenomena, only if the model is properly predictable. but this simply is not possible in the solar system model, proving that we don't live in such a system. mathematicians like Newton, Laplace, Euler, Poincare have tried to solve this problem for centuries, and only succeeded in coming up with ideal solutions that are nowhere near the current complicated solar system that is proposed.


👆👆ከላይ ይቀጠለ

ሌላስ ምን ማሳያ አለ ብንል፣ በተለያየ ጊዜ ወደዚህ የመጡት እስራኤላውያን እና አረቦች ራሳቸው የያፌት ነገድ ቅልቅል ያለባቸው ናቸው። ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አረቦች በብዛት "ሌቫንት" ከሚባል ቀጠና የነበሩ ናቸው። ሌቫንት ማለት፦ የዛሬዎቹን እስራኤል፣ ሊባኖስ፣  ሶርያ፣ ከፊል ኢራቅ የሚያካትት ነው። ይህም ቀጠና እስራኤላውያን፣ ወደ አረብ "assimilate" የተረደረጉት ሶርያውያን፣ እና ሌሎችም አረቦች ይኖሩበታል።

ታዲያ ከዚህ ከሌቫንት በስተሰሜን ከፍ ብሎ፣ "ካውካሰስ" (Caucasus) የሚባል ስፍራ አለ። ይህም የዛሬዎቹን አርሜኒያ፣ አዘርባጃን እና ጆርጂያ የሚይዝ ሲሆን፣ የያፌት ነገዶች አስቀድመው የሰፈሩበት ስፍራ ነው። ከዚህ ስፍራ በስተምስራቅ የቱርክ ነገዶች ይኖሩበት የነበረው ሰፊ በረሃ ነው። የያፌት ነገዶች ከዚህ ተነስተው በቱርክና ሩሲያ/ዩክሬን በኩል ወደ አውሮፓ በመስፋፋት ዛሬ ነጮች የምንላቸውን ህዝቦች አስገኝተዋል።

ካውካሰስን የኢትዮጵያ ሊቃውንት "ቃውቃዝ" ይሉታል። ለምሳሌ የብሉይ ኪዳን ትርጓሜ መጽሐፍ ላይ እግዚአብሔር "አገልጋዬን ናቡከደነጾርን፣ የሰሜንን ህዝብም አመጣለሁ" ያለውን ሲተረጉሙ፣ ከሰሜን "የቃውቃዝ" ህዝቦች እንዳሉና፣ እጅግ ጨካኝ (barbaric) ተዋጊዎች እንደሆኑ፣ በተደጋጋሚ በእስራኤል ላይም ወረራ እንደሚፈጽሙ የታሪክ ሀተታውን አስቀምጠዋል።

የኛ አባቶች እንደነገሩን ሁሉም፣ በታሪክ የተመዘገበው እነዚህ ነጮች የያፌት ነገዶች በመካከላኛው ምስራቅ ያሉ ህዝቦችን ሁሉ እንደወረሩ፣ ከነሱም ጋር እንደተቀላቀሉ በታሪክ ተገልጿል። በዚህም ምክንያት ዛሬ እንደ ኢራቅ፣ ሊባኖስ፣ ሶርያ፣ ፍልስጤም አከባቢ ያሉ ሰዎችን ስንመለከት በአውሮፓ ካሉ ሰዎች ጋር የሚመሳሰል መልክ፣ ቀይ ወይም ወርቃማ ጸጉር ያላቸውን ሰዎች እናገኛለን።

ታዲያ እነዚህ የሴምና የያፌት ነገድ ቅልቅል ያላቸው ህዝቦች በተለያዩ ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ከኢትዮጵያውያን ጋር በሰፊው ተቀላቅለዋል። የዚህም ውጤት ሶስቱም ነገድ በኢትዮጵያ ውስጥ ውህደት መፈጸሙ ነው።

ይህ ሁሉ በማስረጃ የተደገፈ ነው። አንድ ጥናት ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ "ብሔሮችን" ያጠና ሲሆን፣ እንደ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግራይ፣ አፋር፣ ወላይታ ወዘተ ያሉት ነገዶች ከ 40-50 ፐርሰንት ከሌቫንት የመጣ የመካከለኛው ምስራቅ ዘረመል (ዲ ኤን ኤ) እንዳለባቸው አረጋግጧል። ይህም ጽሑፍ በተመሳሳይ እነዚህ የመካከለኛው ምስራቅ ዘረመሎች ከ3ሺህ ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ ይጠቅሳል። ሊንኩን በዚህ ታገኛላችሁ።

https://pubmed.ncbi.nlm.nih.gov/31827175/

ይህ ሁሉ በሳይንስ ተጠንቶ የተረጋገጠ ነው። ብዙዎች የማናውቀው ከዚህ የላቀው ምስጢር ግን የመልከጼዴቅ ምስጢር ነው። ካህኑ መልከጼዴቅ እግዚአብሔርን በብሉይ ዘመን እንኳ በወይን እና ስንዴ መስዋዕት የሚያመሰግን ነበር። ከጻድቁ አብረሃምም ጋር ተገናኝቶ ባርኮታል። ጌታችንም ኢየሱስም ጭምር "በመልከጼዴቅ ስርአት የዘለዓለም ካህን ነህ" እስከመባል ደርሶ፣ ዛሬ ክርስትና ለመላው ዓለም ሲዳረስ፣ ለዕብራውያን ብቻ የነበረው የኦሪት መስዋዕት በክርስትና ለመላው ዓለም ሲሰጥ የመልከጼዴቅ ክህነት አብሮ ተሰጥቶ፣ እስራኤላዊ ያልሆኑት የዓለም ህዝቦች በዚህ ስርአት በስንዴና ወይን መስዋዕት ያገለግላሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ ሁለቱንም የሌዊና የመልከጼዴቅ ስርአት እንዳስቀጠለች ከዚህ ቀደም ተመልክተናል፦

https://t.me/hasabochhh/6457

ታዲያ መልከጼዴቅን ልዩ የሚያደርገው ነገር አለ። ይኸውም ዘሩ ከሶስቱም የኖህ ልጆች ከሴም ካምና ያፌት የተገኘ መሆኑ ነው። በኋላም መልከጼድቅ ልጁን ኢትኤልን ወደ ኢትዮጵያ እንዳላከ፣ እርሱም ብዙ ልጆች እንደወለደና የርሱም ልጆች በዝተውና ተስፋፍተው ዛሬ በኢትዮጵያ ያሉትን ነገዶች በሙሉ እንዳስገኙ እንደ መሪራስ አማን በላይ ያሉ ታሪክ ጸሐፊዎች አስቀምጠውልናል።


ኢትዮጵያዊነት በጣም ልዩ የሆነ ምስጢር ነው።  እኛ ከምናውቀውና ከምናስበው በላይ ፍጹም የተለየ የረቀቀ ምስጢር አለው። ይህንንም ከምናውቅበት መንገዶች አንዱን እንመልከት።

ይህም፣ እኛ ኢትዮጵያውያን የሴም፣ የካምና የያፌት የዘር ሀረግ ውህድ ነን። ይህ እጅግ የተለየ ድንቅ ነገር ነው። ደግሞም እውነት መሆኑን ለማየት አስቀድመን ሳይንሳዊ ወይም ታሪካዊ ማስረጃን እንመልከት።

በመጀመሪያ እኛ ኢትዮጵያውያን የጥቁሮች የካም ዘር እንዳለብን ግልጽ ነው። ከዚህም ውስጥ የኩሽ የዘር ሀረግ አንዱ መሆኑ ይታወቃል። ብዙዎች እንደምናስበው አንዱ ብሄር ሴም አንዱ ኩሽ የሚለው ፍጹም ስህተት ነው። ለምሳሌ ሴማዊ ብለን ከምናስባቸው "ብሔሮች" ውስጥ እንመልከት። አማርኛ ተናጋሪ ህዝቦችን ብንመለከት ታሪክ አጥኚዎች ጭምር እንዳሳዩት የአማራ ነገድ የሚመጣው በከፊል ከሴማውያን ህዝቦች፣ በከፊል ደግሞ ከአገዎች ነው። ይህንንም ተድላ መላኩ ስለ አማራ መገኛና አመጣጥ በጻፈው መጽሐፉ ጠቅሶታል። ቋንቋውም በዚሁ መልኩ የኩሻውያን ቋንቋ ከግዕዝ ጋር እየተቀላቀለ ሲመጣ የተፈጠረ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህ ነው ከግዕዝ ውጪ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ውስጥ ያሉ ሴማዊ ቋንቋዎች ከሌላው ሴማዊ ቋንቋዎች የተለዩ የሆኑት። በቮካቡለሪም ደረጃ ወጣ ያሉት። ተመሳሳይ ነጥብ ስለ ጉራጊኛም ሆነ ስለ ትግርኛ ማንሳት እንችላለን።

በሌላው መልኩ ደግሞ እንደ አፋር እና ሶማሊ ያሉትን ደግሞ ስንመለከት ኩሻዊ ተብለው ቢፈረጁም ቋንቋቸው እጅግ ከባድ የአረብኛ ተጽዕኖ ያለበት መሆኑ የሚያስገርም ነው። ያ ተጽዕኖ ደግሞ እንዴት መጣ ካልን ከአረቦች ጋር የመነካካት አጋጣሚ እንደነበራቸው ያስታውቃል። ይህም የአዳል ሱልጣኔት መንግስት ስር በነበሩበት ወቅት ይሆናል። ከዚህም በላይ አረቦች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በንግድ እና ወደ አከባቢው ህዝብ በመጋባትና በመቀላቀል ስለሆነ አፋሮቹና ሱማሌዎቹ ከሴማውያኑ አረቦች ጋር የዘር መቀላቀል ነበራቸው ማለት ነው። ስለዚህ አፋሮች እና ሱማሌዎች ንፁህ ኩሻውያን ናቸው ብንል ትክክል ይሆናል?

በተመሳሳይ መልኩ፣ ዛሬ በሀረር፣ በአርሲ እና በባሌ ያሉ ሙስሊም ኦሮሞዎች፣ በአረቦቹ የስብከት ቴክኒክ ምክንያት ወደ እስልምና የመጡ ናቸው። አረብቹ ከሀገሬው ሰው እያገቡ፣ ቤተሰብ እየመሠረቱና ያንን ቤተሰብም ወደ እስልምና እያመጡ፣ እምነቱን ስላስፋፉ፣ እነዚያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦሮሞዎችም የዚህ ተጽዕኖ ውጤት ናቸው ማለት ነው። ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ንፁህ ኩሽ ናቸው ማለት እንችላለን? የምንችል አይመስልም።

ይህ አንዱ ማሳያ ነው፣ የሴም እና የካም ውህድ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖሩ። ሌላው ማሳያ ብንመለከት ደግሞ የእስራኤላውያን በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘት ነው።

የዚህ መነሻው በንጉስ ሰሎሞን ዘመን ሰሎሞን ከኢትዮጵያዊቷ ማክዳ የወለደው ልጁ ምኒልክ ቀዳማዊ አባቱን ሊጎበኝ ወደ እስራኤል በሄደበት ወቅት ነው። በዚያም አባቱ ከአስራ ሁለቱም የእስራኤል ነገድ አድርጎ በሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያንን አብሮ ወደ ኢትዮጵያ ልኳል። በዚህም እነዚያ እስራኤላውያን በከፍተኛ ሁኔታ ከኢትዮጵያውያን ጋር ተቀላቅለዋል። ይህ ታዲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብቻ የምታምነው ያልተረጋገጠ ነገር ሊመስል ይችላል። እውነታው ግን ነገሩ ፍጹም የተረጋገጠ መሆኑ ነው። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ 3ሺህ ዓመት የሚሆናቸው የኦሪት መሰዊያዎች ተገኝተዋል። ያም እስራኤላውያኑ በቦታው ከመጡበት ጊዜ ጋር ይስተካከላል። በጊዜው የኦሪት ህግን የሚከተሉት እስራኤላውያን ብቻ መሆናቸው ደግሞ በትክክልም እስራኤላውያን በጊዜው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደነበሩ ማሳያ ነው። እንዲሁም በሚገርም ሁኔታ አንድ የጄኔቲክስ ጥናት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ3 ሺህ ዓመት በፊት ከፍተኛ የሆነ ፍልሰት ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ ኢትዮጵያ እንደተካሄደ አረጋግጧል። ጥናቱ ይህንን ክስተት "back migration" ነው ያለው፣ ምክንያቱም ሳይንቲስቶች የሰው ልጅ መጀመሪያ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ ሌላው ዓለም "migrate" እንዳደረገ ስለሚያምኑ ነው። የጥናቱን ሊንክ በዚህ ታገኙታላችሁ፦

https://www.bbc.com/news/science-environment-34479905

ይህም ብቻ ሳይሆን እስራኤላውያን በቅርቡም ወደ ኢትዮጵያ እንደፈለሱ ይነገራል። ይህም በ70 ዓመተ ምህረት የሮም መንግስት ኢየሩሳሌምን ባፈረሰ ጊዜ እስራኤላውያን በመላው ዓለም ሲበተኑ፣ እንዲሁም በ1453 ቱርኮች የቢዛንቲንን መንግስት በተቆጣጠሩ ጊዜ እዚያም ተሰደው ይኖሩ የነበሩ እስራኤላውያን ወደ ኢትዮጵያ እንደፈለሱ ይነገራል።

እናም እነዚህ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ሀገራችን የመጡ እስራኤላውያን በዋናነት በሸዋ፣ ጎንደር እና የተወሰኑ የትግራይ ክፍሎች ውስጥ በሰፊው እንደተቀመጡ ይታወቃል። ይህም ብቻ ሳይሆን እነዚህ እስራኤላውያን በታሪክ አጋጣሚዎች ከሁሉም የኢትዮጵያ ነገዶች ጋር ተቀላቅለዋል። በአክሱም የአገዎቹ የዛግዌ ነገስታት ከፊል እስራኤላውያኑ የአክሱም ነገስታት ጋር ተቀላቅለዋል። የአክሱም መንግስት ተቀጥያ በሆነው የሰሎሞናዊው ስርወ መንግስት ጊዜም እንደ ከፋ እና ወላይታ ያሉት ህዝቦች በጦርነት ምክንያት ከሸዋዎቹ ከፊል-እስራኤላውያን ጋር እንደተላቀሉ በታሪክ ተገልጿል። ያም ብቻ ሳይሆን እነዚህ እስራኤላውያን በአከባቢው ከነበሩ እንደ ፈጠጋርና ደዋሮ ማለትም የዛሬዎቹ አርሲና ሀረር ውስጥ በብዛት ይኖሩ እንደነበር፣ የአከባቢው ገዢዎችም እንደሆኑ በታሪክ ተመዝግቧል።

በኋላም የኦሮሞ መስፋፋት ሲካሄድ ኦሮሞዎች የሚቆጣጠሩትን አከባቢ ህዝብ ቋንቋና ባህላቸውን ወደ ኦሮሞ ቢለውጡም ህዝቦቹ ግን ዘራቸው ቀድሞ የነበሩት ናቸው። በዚህም ምክንያት እነዚህ የእስራኤል ዘር ያላቸው ህዝቦች ከኦሮሞዎች ጋርም ተቀላቅለዋል። በዚህም ምክንያት፣ በአርሲ፣ ባሌና ወለጋ ብቻ ሳይሆን በሸዋም ጭርምር ያሉ ኦሮሞዎች ኩሻዊ ቋንቋን ይናገሩ እንጂ በዘራቸው የሴም ዘር ቅልቅል ያለባቸው ናቸው።

ከዚያ እጅግ የሚገርመው ደግሞ በግራኝ ጦርነት የአዳል መንግስት ከክርስቲያኑ መንግስት ጋር በሚዋጋ ጊዜ አዳልን ለመርዳት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አረቦች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር። በአከባቢው ካሉ ህዝቦችም ጋር ፍጹም ተቀላቅለው ነበር። በጣምም ከመቀላቀላቸው የተነሳ የኢትዮጵያ ነገስታት ጭምር ዘራቸው ከነዚህ አረቦች የሚመዘዝ አሉ። የጅማው አባጅፋር አንዱ ምሳሌ ነው። እንዲሁም የጎጃሙ ንጉስ ተክለሃይማኖት ሌላው ምሳሌ ነው። የሚገርመው የንጉስ ምኒልክ የልጅ ልጅ የሆነው ልጅ እያሱ ሁሉ የዘር ሀረጉ ወደ ኋላ ሲቆጠር፣ በግራኝ ጦርነት ጊዜ ከኢራቅ አከባቢ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ሰው እንደሆነና የዛ ሰውን ታሪክ አረቡ ታሪክ ጸሐፊ ሁሉ እንደዘገበው ይነገራል።

ይህንን ሁሉ ስንመለከት መላው ኢትዮጵያ የሴምና የኩሽ ዘር ፍጹም የተቀላቀለባት መሆኗን እና "ሴም"፣ "ኩሽ" ተብሎ የተመደበው የብሔር/የቋንቋ አመዳደብ ፍጹም የተሳሳተ መሆኑን እንመለከታለን።

ነገር ግን የያፌት ነገድስ? ከየት የመጣ ነው? የሚለውን እንይ።

አንዱ ቀላል ማሳያ የግራኝ ጦርነት ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ቱርኮች ናቸው። በትልቅ ቁጥር የመጡት ቱርኮች በወሎ አከባቢ እንደተቀመጡ ይነገራል። የቱርኮችን መገኛ ስናይ ደግሞ ከያፌት ነገድ እንደተገኙ እንመለከታለን።

ይቀጥላል👇👇


Forward from: አዲስ ምልከታ🌍
Around 2200 years ago, Eratosthenes put two sticks in the cities of Alexandria and Syene, and measured their shadows to "measure earth's circumference".

Today we take that as a proof that earth is a globe. But is it? Does different shadow lengths necessarily mean globe shape?


1፣ የጽሀይ እና የጨረቃ ግርዶሽ እንዴት ይፈጠራል?

እውነቱን እንነጋገር። ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ የለም። በትክክል ይሄ ነው የምንለው መልስ የለም። ምክንያቱም ለሁሉም ጥያቄ መልስ የለንም። ያ ደግሞ ምንም ሰህተት ወይም ችግር የለውም። በጊዜ ሂደት ነገሮችን ይበልጥ እየመረመርን ስንሄድ የምናገኘው ይሆናል። የሂደት ውጤት ነውና።

ዛሬ አስትሮኖሚ የሚሉትን እንኳ ሲጠየቁ የሚመልሷቸውን ጥያቄዎች በአንዴ አላገኙም። ክፍለ ዘመናት ወስዶባቸዋል። ለምሳሌ የጸሃይ ብርሃን ምድር ለመድረስ 8 ደቂቃ ይወስድበታል የሚለውን "ያወቁት" በ18ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ያውም ያወቁበት መንገድ ትክክል አይደለም፣ ያም ደግሞ ከዚህ በፊት በቻናሉ ላይ ሼር ያረግነው Kings Dethroned የሚለው መጽሐፍ ያሳያውል። መጽሐፉን በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ፣
https://t.me/hasabochhh/206

ሌላም ደግሞ ህዋ ማለት ባዶ ቫኪዩም ነው ያለው ምንም ዉስጡ የለም የሚለውንም "ያወቁት" በ20ኛው ክፍለ ዘመን ሪለቲቪቲ ቲዮሪ ሲወጣ ነው። ይህንንም አንዱ ሳይንቲስት የሰራው ምርምር ምድር እንደማትንቀሳቀስ ስላረጋገጠ ነው። ይህንንም ለመፍጠር የተለያዩ ሳይንቲስቶች ያመጡትን ሃሳብ አንድ ላይ አድርጎ አልበርት አንስታይን የፈጠረው ሪለቲቪቲ ቲዮሪ ነው ህዋ ባዶ "Vaccuum" ነው ያስባለው። ስለዚህ ጉዳይ ያለውን ረጅም እና ውስብስብ ታሪክ በዚህ ቻናል በተከታታይ ጽሁፍ ዳሰሳ አድርገንበታል። ከክፍል አንድ እስከ አምስት ያሉትን በሚከተሉት ሊንኮች ታገኟቸዋላችሁ፣

ክፍል አንድ
https://t.me/hasabochhh/3674

ክፍል ሁለት
https://t.me/hasabochhh/3676

ክፍል ሶስት
https://t.me/hasabochhh/3680

ክፍል አራት
https://t.me/hasabochhh/3686

ክፍል አምስት
https://t.me/hasabochhh/3720

20 last posts shown.