አሸናፊ ፊዳ ፣ወንድማገኝ ማዕረግ፣ ይሁን እንዳሻው እና ነፃነት ገብረመድህን የጨዋታ እገዳ ሲጣልባቸው እንዲሁም በክለቦች ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ፣ ወላይታ ድቻ እና አዳማ ከተማ ቅጣት ተላልፎባቸዋል - ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
የዲሲፕሊን ውሳኔዎች 1. አሸናፊ ፊዳ (አርባምንጭ ከተማ) : ማከሰኞ ጥር 27 2017 ዓ.ም. ክለቡ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ባደረገው የ18ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 62 ኛ ደቂቃ ላይ የተጋጣሚን ተጫዋች በመማታት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 በተቁ 1 (ሠ)