ሂዳያ መልቲሚዲያ | ʜɪᴅᴀʏᴀ ᴍᴜʟᴛɪᴍᴇᴅɪᴀ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


- አንዳንድ ማስታወሻና ምክሮች
- ዳዕዋዎች እና ፈታዋዎች
- ምርጥ ግጥሞች
- አጫጭር የዳዕዋ ቪድዮዎች
- የተለያዩ ደርሶችና ታሪኮች
-ጥያቄና መልስ ፕሮግራሞች የሚጋሩበት የሆነ ቻናል ነው።
Join እና Share በማድረግ አጋርነታችሁን ግለፁ!!
🔘በተጨማሪም የዩቱብ ቻናላችን ይቀላቀሉ!
https://www.youtube.com/@hidaya_multi
🗳ለአስተያየት @annafiabot ይጠቀሙ!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter




የመካ እና የመዲና ሱራዎች
ጥቂት ስለ ቁርኣን

~
ቁርኣን ነብያችን ﷺ መካ እያሉ በሚወርድ ጊዜ የሙስሊሞች ቁጥር አናሳ ነበር። አጋሪዎች ብዙሃን ነበሩ። መዲና ውስጥ በነበሩ ጊዜ ደግሞ የሙስሊሙ ኃይል ተጠናክሯል። መካና መዲና የነበሩት ተቃራኒ ኃይሎች በብዛት ከእምነትም፣ ከንቃተ ህሊናም አንፃር ልዩነት አላቸው። በነዚህና መሰል ልዩነቶች የተነሳ በሁለቱ ዘመኖች የወረዱ ሱራዎች ትኩረትና ይዘት ልዩነት ይታይበታል። ይሄ የተወሰነ ሰፋ ያለ ትንታኔ ይፈልጋል።
ከወረዱበት ዘመን አንፃር ሲታይ ከ114 የቁርኣን ምእራፎች ውስጥ 20ዎቹ መደኒያ ናቸው፣ በዘመነ መዲና የወረዱ። 12ቱ ኺላፍ አለባቸው። ቀሪዎቹ መኪያ ናቸው። ስለዚህ ከቁጥር አንፃር አብዛኞቹ የቁርኣን ምእራፎች መካ የወረዱ ናቸው ማለት ነው።

በነገራችን ላይ የመካ እና የመዲና ሱራዎች የሚታወቁባቸው መለያዎች አሉ።

1 - የመካ ሱራዎች፦

⓵ - "ከልላ" (كلا) የሚለው ቃል ያለባቸው ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው።
⓶ - ሰጅደተ ቲላዋ ያለባቸው ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው። እነዚህም 14 ሱራዎች ናቸው።
⓷ - በመሀላ የሚጀምሩ ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው። እነዚህም 14 ሱራዎች ናቸው።
⓸ - በሑሩፉ ተሀጂ (ሑሩፉል ሙቀጠዐ) የሚጀምሩ ሱራዎችም ከበቀረህ እና ኣሊ ዒምራን ውጭ መኪያ ናቸው። በቀረህ እና ኣሊ ዒምራን መደኒያህ ናቸው። ሱረቱ ረዕድ ኺላፍ አለባት።
⓹ - በውስጣቸው "ያ አዩሀ ናሱ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ) የሚል ያለባቸው እና "ያ አዩሀለዚነ ኣመኑ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟) የሚል የሌለባቸው ሱራዎች መኪያ ናቸው።
⓺ - በ "አልሐምዱ" የሚጀምሩ ሱራዎች መኪያ ናቸው። እነሱም አምስት ሱራዎች ናቸው።
⓻ - ከሱረቱል በቀረህ ውጭ "ቀሶሱል አንቢያእ" የያዙ ሱራዎች መኪያ ናቸው።

2 - የመዲና ሱራዎች፦

❶ - በውስጣቸው "ያ አዩሀለዚነ ኣመኑ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟) የሚል ያለባቸው እና "ያ አዩሀ ናሱ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ) የሚል የሌለባቸው ሱራዎች መደኒያ ናቸው።
❷ - ስለ ሙናፊቆች የተወሳባቸው ሱራዎች ሁሉ መደኒያ ናቸው። አልዐንከቡት ስትቀር። እሷ ግን መኪያ ነች። ይሁን እንጂ በውስጧ ስለ ሙናፊቆች የሚያወሳው ክፍል መደኒይ ነው።
❸ - ሑዱድ እር ፈራኢድ የተወሳባቸው ሱራዎች ሁሉ መደኒያ ናቸው።

ምንጭ፦ ዲራሰህ ፊ ዑሉሚል ቁርኣኒል ከሪም፣ ፈህድ አሩሚይ

© IbnuMunewor


🌾ተክልን መትከል🍃▲▲▲

© ሂዳያ መልቲሚዲያ


◉...ከአስር በኋላ መተኛት ▲▲▲

t.me/hidaya_multi

🦈 ሼር & ሴቭ


የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
"ሱጁድ ላይ ተስተካከሉ። አንዳችሁ እንደ ውሻ ክንዶቹን አያንጥፍ።"

[ቡኻሪይ ዘግበውታል።]


🍂ሰዒድ ኢብን ጁበይር🍃

«አብደላህ ኢብን አባስ ምላሱን ይዞ እንዲህ አለ:- መልካምን ተናገር ታተርፍለህ፣ ወይ ዝም በል ሰላም ትወጣለህ ከመቆጨትህ በፊት» (ዙህድ ሊአህመድ 237)
┈┈┈┈••◉🌹◉●••┈┈┈
Telegram» https://t.me/hidaya_multi


قال رسول صلى الله عليه وسلم:

«ومن فرج عن مسلم كربة، فرج الله عنه بها كربة من كرب يوم القيامة» رواه مسلم


عن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما أن النبي صلى الله عليه وسلم قال : (مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلَاةً صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا). رواه مسلم

አብደላህ ቢን አምር ቢን ወቃስ እንዳስተላለፈው:-
ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:-
«እኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ እሱ ላይ አስር ሰለዋት ያወርድበታል።»ሙስሊም ዘግቦታል


ሪዝቅህ በአላህ እጅ ነው!!
~
ኢብራሂም ኢብኑል አድሀም አንድ ጊዜ ከፊት ለፊታቸው የተጠበሰ ስጋ ሊበሉ አስቀምጠው... አንዲት ድመት ከፊታቸው ትመጣለች። እናም ከዛ ስጋ ቆርጠው ሲሰጧት ይዛ ሄዳ... የአንድ ጉድጓድ አፍ ላይ ታስቀምጠዋለች። ወዲያውም አንድ ዘንዶ ይወጣና ከዛ ውስጥ  ያንን ስጋ በልቶ ወደ ጉድጓዱ ይመለሳል። ዘንዶውን ሲያዩት አይን የለውም... እንዲያው ዝም ብሎ ስለሸተተው እንጂ የወሰደው ይሄንን ስጋ... አይን የለውም። ከዛ ምን ብለው ተናገሩ ¿¡

«سُبحَانَ مَن يَرزُقُ الأَعدَاء، بَعضَهُم مِن بَعض»

«ጠላቶችን አንዳቸውን ከአንዳቸው የሚረዝቅ የሆነ ጌታ ጥራት ይገባው»


አላህ; እንኳን ከወዳጅ፤ እርስ በእርሳቸው ከሚበላሉ እንስሳት እራሱ አንዱ ለአንዱ አምጥቶ እንዲሰጥ ያደርጋል።

ያንተ ሪዝቅ ከሆነ የትም ሚሄዴብህ ነገር የለም።

© Hidaya Multi

https://youtu.be/jsDac7tbT6E?si=RkK9vDTayLD5_PXD


📌 ቁርአን ላይ ያሉ ምልክቶች ትርጉም!!

© Hidaya_Multi


سُئِلَ الطَّنْطَاوِي رحمه الله عَن أجملِ حِكمَةٍ قَرأهَا فِي حَياتِهِ فقَال:

لقد قَرأتُ لِأكثرَ مِن سبعين عامًا، فما وَجَدتُ حِكمَةٍ أجمل من تلكَ التي رواها إبن الجوزي رحمه الله : «إنَّ مشقةِ الطاعةِ تذهبْ ويبقى ثوابُها .وإنَّ لذةِ المعاصي تذهب ويبقى عقابُها. كُن مع الله ولا تُبالي، ومُدّ يَدَيْكَ إليه في ظُلُماتِ اللّيالي، وقُل: يا رب ما طابتِ الدّنيا إلاّ بذِكرِك، ولا الآخرة إلاّ بعَفوِك، ولا الجنّة إلاّ برُؤيتِك. صافِح وسامِح، ودع الخَلْقَ لِلْخالق. فَنَحنُ وهُمْ راحِلُون، افعَلِ الخَيرَ مَهمَا استَصغَرتَهُ، فإنَّك لا تَدرِي أيُ حسنةٍ تُدخلُكَ الجَنَّة.


Forward from: ሂዳያ መልቲሚዲያ | ʜɪᴅᴀʏᴀ ᴍᴜʟᴛɪᴍᴇᴅɪᴀ
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🕋ከቁርአን ጋር🕋
🌄የምሽት ስንቅ!!!🌄


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🔍 ውለታ ቢስ አንሁን ! !

🎙 ኡስታዝ አብዱልዋሲዕ (አቡ የህያ)

◉ ክፍል ሁለት(2)

∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞∞
© ሂዳያ መልቲሚዲያ
----------------------‑--------
🔊በቴሌግራም
https://telegram.me/hidaya_multi
🎶 ቲክ ቶክ
https://www.tiktok.com/@hidaya_multi
⭕️ ዩቲዩብ
https://www.youtube.com/@hidaya_multi
ላይ ያግኙን


«አንደኛቹ ከሰዎች የሚከልለው በሆነ ነገር ሲሰግድ፤ አንዱ በፊቱ ሊያልፍ ቢፈልግ፤ይግፋው። እንቢ ካለ ይጋደለው ፤ እሱ ሸይጧን ነውና።»

📚ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

© ሂዳያ መልቲሚዲያ


አስተንትኚ + አስተውዪ ➝ ምረጪ !

قِيلَ لَهَا ادْخُلِي الصَّرْحَ ۖ فَلَمَّا رَأَتْهُ حَسِبَتْهُ لُجَّةً وَكَشَفَتْ عَن سَاقَيْهَا ۚ [النمل:٤٤]

«ሕንጻውን ግቢ ተባለች፡፡ ባየቺውም ጊዜ ባሕር ነው ብላ ጠረጠረችው፡፡ ከባቶችዋም ገለጠች፡፡» [አን-ነምል:44]

⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻⁻

በልቂስ(ንግስት ሳባ) ወደ ሕንፃው ግቢ በተባለች ጊዜ ከውሐ የተሰራ መሰላት። ባቷንም ለመሻገር እንዲያመቻት ገለጠችው። ይሄ ልብሷ ረጅምና የሚሸፍን እንደነበረ ጠቋሚ ነው። ከበፊት ጀምሮ የሚሸፍን ልብስ የንግስታት ልብስ ነው። መገላለጥና ፈታኝ አካላትን ማሳየት ደግሞ ወንድን ለማበላሸት የሚታትሩ ዝሙተኞች አለባበስ ነው።

አለባበስሽን ተመልከቺ! ከዛም ራስሽን መድቢ፦
ወይ ከንግስቶች እንደ በልቂስ....
ወይ ከነዛ ፈታኝ አበላሺዎች!!!


©ሂዳያ መልቲሚዲያ

ተቀላቀሉ ➤ @hidaya_multi


«አላህ በዱንያ ላይ ሰዎችን ሲቀጡ የነበሩትን ይቀጣል!»

📚ሶሂህ ሙስሊም

© ሂዳያ መልቲሚዲያ


وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَكَأَنَّمَا خَرَّ مِنَ السَّمَاءِ فَتَخْطَفُهُ الطَّيْرُ أَوْ تَهْوِي بِهِ الرِّيحُ فِي مَكَانٍ سَحِيقٍ [ الحج: ٣١]

በአላህም የሚያጋራ ሰው፤ ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው፣ ወይም ነፋስ እርሱን በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ብጤ ነው፡፡ [አል ሐጅ: 31]




عن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما أن النبي صلى الله عليه وسلم قال : (مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلَاةً صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا). رواه مسلم

አብደላህ ቢን አምር ቢን ወቃስ እንዳስተላለፈው:-
ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:-
«እኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ እሱ ላይ አስር ሰለዋት ያወርድበታል።»ሙስሊም ዘግቦታል


🤲ከሰላት በኋላ ዱዐ ስለማድረግ🤲

🔺ሸኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አልዑሰይሚን

📌ጥያቄ:

«አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከፈርድ ሰላት በኋላ ሰጋጆች ለዱዐ እጃቸውን ያነሳሉ። ይህ እንዴት ይታያል?»

📌ምላሽ:

❝ ከሰላት በኋላ ዱዐ ነብያዊ ሱና አይደለም። አላህም በቁርአኑ (ሰላትን ባጠናቀቃችሁም ግዜ አላህን አስታውሱ) ነው ያለው። ከሰላት በኋላ ዱዐ ሱና የሚሆነው በአንድ አጋጣሚ ብቻ ነው። እሱም ከሰላተል ኢስቲኻራ በኋላ ነው። ሰላተል ኢስቲኻራን አስመልክቶ ነብዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋልና ( አንዳችሁ በአንድ ጉዳይ በተጨነቀ ግዜ ሁለት ረከዐ ይስገድ ከዛም ዱዐ ያድርግ) አሉ። ዱዐን ከሁለቱ ረከዐ ሰላት በኋላ አዘዙ። ግን ከዚህች ሰላት ውጪ ያለን ሰላት አገባዶ ዱዐ ማስከተል ሱና አይደለም። እጁን አንስቶም ይሁን ሳያነሳ፣ ከፈርድ ሰላት ኋላም ይሁን ከሱና። አላህም ያዘዘን እርሱን በማስታወስ (በዚክር) ነው። (ሰላትን ባገባደዳችሁም ግዜ አላህን አስታውሱ) ብሎ። በሱረቱል ጁሙዐህ ደግሞ (ሰላትም በተጠናቀቀች ግዜ በምድር ላይ ተበተኑ: የአላህ ችሮታንም ፈልጉ) ብሏል።

📚ሊቃኡ_ባቢል_መፍቱህ 82

20 last posts shown.