ኢብኑ ሀሰን


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Blogs


ኑ የረሳነውን እናስታውስ
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ በነዚህ ቻነሎች በየቀኑ የሚለቀቁ ፕሮግራሞች
🔰በየቀኑ ከሁለት በላይ አስተማሪ ሃዲሶች
🆚አስተማሪ መጣጥፎች
🆚ኢስላማዊ ግጥም
አስተያየት ካለወት
- @ibnuhasenadvice_bot
- @ibnuhasenadvice_bot

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Blogs
Statistics
Posts filter


Forward from: ◔͜͡◔ mustefa ◔͜͡◔
Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Forward from: ◔͜͡◔ mustefa ◔͜͡◔
Video is unavailable for watching
Show in Telegram




Tap On My Link Start The Bot Join All Channels And Reffer To Friends And Get Netflix Premium Account Now... https://t.me/NetflixArenaXbot?start=user86606


Forward from: ◔͜͡◔ mustefa ◔͜͡◔
Video is unavailable for watching
Show in Telegram




አዲስ አስተማሪ ቻነል ከፍተናል
እባክወን ይቀላቀሉን ይጠቀሙበታል እንጂ አይጎዱም
https://www.youtube.com/channel/UCpkMp2gtQkdm3gkI5LnVN7w?sub_confirmation=1












አታላይ የኔ ቢጤዎች ወይም ለማኞች እንዴት ነው እሚያጭበረብሩት?!
እንዴትስ ተያዙ?! እሚለውን ለማግኘት ቪድዮውን ይመልከቱ


https://youtu.be/og2vo64kKwY


🚨ማሳሰቢያ🚨

ይህ ቻነል ከዛሬ ቀን ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ያቆማል።

ባለፉት ጊዚያት ለታዳሚወቻችን ይጠቅማሉ ብለን ያሰብናቸውን ነገሮች ስናቀርብ ነበረ። ሆኖም ግን ነገራቶች እዳስብነው ሆኖ መቀጠል ስላልተቻለ ሁላችሁም ይህን የቴሌግራም ቻነል ለቅቃችሁ እንድትወጡ እንጠይቃለን።

ከምስጋና ጋር
@ibnuhasen

ለአስትያየት
@ibnuhasenadvice_bot


የሆነ ትልቅ ሰው ገብያ ላይ ተገናኝተን ማውራት ጀመርን።
ሰውየው ጋር ትንሽ ካወራን በኋላ እንዲህ አለ ፡- "እኔ ወደ ሻሸመኔ የሄድኩት በ 67 (1967) ነው። የዛኔ ወታደር ነበርኩ። ለግዳጅ በዛው እንደሄድኩ ኑሮየን መሰረትኩ። ልጆች ወልጃለሁ አካባቢው ላይ ሰላም ነበርን ግን ድንገት ነገሩ ሁላ ተቀያየረ አፈራውት ያልኩት ሀብት እና ንብረቴ ወደመብኝ። ለብዙ ግዜ በእርዳታ መኖር ቻልኩ ግን መዝለቅ አልቻልኩም። አሁን ይሄው እንደምታየኝ እዚህ መጥቼ እንደ አዲስ ኑሮ መስርቼ መኖር ጀምሪያለሁ። ግን ከብዶኛል። አእምሮየ ረፍት አጥቷል። በቃ ጭንቃላቴ ላይ የተቀረፀው ረብሻ እና ማፈናቀሉ። " ሰውየው መቀጠል አቃተው።


እኔም "እኔም ጂማ ነበርኩ ። የጅማ ሰው ጥሩወች ናቸው። አንዴ በብሄር ምክንያት ግቢውን ለቅቈ እንድወጣ ተደርጌ ነበር። እና እሚሰማህ ያለውን ነገር በትንሹም ቢሆን ይገባኛል የሆነው ነገር ያሳዝናል አይዞን ጋሼ!" ብየ ሸኘኋቸው።
ሙሉ ኢትዮጵያ በዘረኝነት የተበከለች ያህል ይሰማኛል። "የተፋዋ ምድር" እየተባለች ስሰማ ያደግኩት ነገር ሁሉ ውሸት እንደሆነ አወቅኩ። አንዳንዴማ "ኢትዮጵያ የተስፋዋ ሳይሆን የክፋት ምድር ናት" እያልኩ አስባለሁ።

@ibnuhasen


እናስተነትን ዘንድ

ክፍል ሶስት

እነሆ አላህ በስሟ ቁርአንን ምእራፍ የተሰየመላትን ሌላኘዋን በራሪ ነፍሳት የሆነችውን ንብን በዛሬው 'እናስተነን ዘንድ' ፕሮግራማችን ልናነሳ ወደድን።

ብዙወቻችን ስለ ንቦች እናውቃለን። ማራቸውን ማን ያልበላ አለ☺️።

ንቦች ብዙ አይነት ዝርያ ያላቸው ናቸው። ከነዛ ውስጥ ግን የማር ንቦች ዝርያ ሰባት ወይም ከዛ በላይ ናቸው። እንዲህ ያልኳችሁ 'ጢንዚዛ' በመባል እሚታወቁትም የንብ ዝርያ ናቸው ተብሎ ስለሚታመን ነው።

ንቦች ሶስት አይነት መደብ አላቸው። ሰራተኛ፣ ንግስቷ እና ድሮን ተብለው እሚታወቁት ናቸው።
እስኪ አሪፍ ጥያቄወችን እናንሳ

ንቦች ለምንድን ነው ማር እሚያመርቱት?!
እኔ ልንገራችሁ ንቦች የክረምት ጊዜ ወይም አበቦች እማይገኙበት ጊዜ ሲመጣ እሚመገቡት እንዳያጡ ነው እሚያከማቹት። ማር ለንቦች ምርጥ የምግብ ምንጭ ይሆንላቸዋል። ማር በ nutreient የበለፀገ ከመሆኑ በተጨማሪ ብዙ ስኳር ስለሚኖረው ሀይል ሰጭ ምግብ ሁኖ እንዲያገለግላቸው ነው።

ሰራተኛ ንቦች በጠቅላላ ሴቶች ናቸው። ደሮን ተብለው እሚታወቁት ደግሞ ወንድ ናቸው። ስራቸው ንግስቲቱን መገናኘት ብቻ ነው። ግን ንግስቲቱም ከሀዲ ናትና ከግንኙነት በኋላ ልትገድላቸው ትችላለች።
እነዚህ ወንድ ንቦች አይናደፉም። ሰራተኛ ንቦች ደግሞ ሴት ቢሆንም መራባት አይችሉም። መራባት እምትችለው ንግስቲቱ ብቻ ናት። ንግስቲቱ ለቀናት ማየት የተሳናት ሁና ልታሳልፍ ትችላለች።ሰራተኛ ንቦች ከተናደፉ በኋላ ይሞታሉ።

አሁንም እንጠይቅዎ ንቦች ከተናደፉ በኋላ ለምን ትሞታሉ?!

መልሱ ቀላል ነው እሚናደፉበት ሰንኮፋቸው በመቀመጫቸው አካባቢ ነው ያለ። በሚናደፉበት ጊዜ ሰንኮፉ ሆዳቸው ውስጥ ያለውንም ነገር ይዞባቸው ይወጣል። ያ ማለት እሚናደፉበት ሰንኮፍ ሆዳቸው ውስጥ ያለውን ለማዋሀድ እሚጠቅማቸው እና ሆዳቸው ውስጥ ያለውን ነገር አብሮ ስለሚያወጣው መትረፍ አይችሉም።


ንቦች እሚያዘጋጁት ማር ብዙ የጤና ጥቅሞች አሉ። ከነዛ ውስጥ health line ያስቀመጣቸውን እንንገራችሁ አንቲኦክሲዳንት፣ባክተሪያን እና ፈንገስን ለማጥፋት፣ ቁስልን ለማከም፣ በሽታን የመከላከል አቅም ማሳደግ፣ ለአንጀት ጤንነት እና ለውህደት ፣ እንዲሁም የተዘጋ ጉሮሮን ለመጥረግ ይጠቅማል።

ግን በቅርብ ደግሞ የ አውስትራሊያ ዶክተሮች ከንብ መርዝ አዲስ ግኝት አግኝተናል ይላሉ።

BBC እንደዘገበው ከሆነ ተመራማሪወች ከንብ ሰንኮፍ የጡት ካንሰር ሴሎችን እንደሚገድል አስታውቀዋል። ምን ይሄ ብቻ ሜላኖዋ ተብሎ እሚታወቀውን ካንሰርም እንደሚከላከል አስታውቀዋል።

ሰራተኛ ንቦች በሚናደፉብት ጊዜ ሰውነታችን ላይ ያብጣል። ግን ሊገለን ይችል ይሆን?!
አንድ የንብ መርዝ ሊገለን አይችልም ግን እስከ አንድ ሽህ የሚደርሱ ንቦች ከተነደፍን ግን መሞታችን አይቀሬ ነው።

@ibnuhasen

t.me/ibnuhasen


እናስተነትን ዘንድ

ክፍል ሁለት

እነሆ ትላንት እንቅልፍ እንዳልተኛ በ ጩኸታቸው እና በንክሻቸው አላስተኛ ያሉኝ ትንኞች ነበሩ። እስኪ ስለ ቢምቢዎች ልንገራችሁ።

ቢምቢ ከ 3000 በላይ ዝርያወች ያሏት ትንኝ ናት። ከነዚህ ውስጥ ትንሾቹ ብቻ ናቸው ከ ሰው ልጅ ደም እሚመጡት። ግን ለምንድን ነው እሚመጡት?!

ደም መጣጭ የሆኑት ቢንቢወች ሴቶች ብቻ ናቸው። ወንድ ቢምቢዎች ምግባቸውን ከአበባ ብቻ ነው እሚፈልጉት። ታድያ ሴቷ ደም ምን ይሰራላታል?!ካላችሁኝ ለ እንቁላሏ እድገት ስትል ነው።

ምን አለ መሰላችሁ የ ሰው ልጅ ደም በ ፕሮቲን እና አሚኖ አሲድ የበለፀገ ስለሆነ ለእንቁላሎቻቸው እድገት ያስፈልጋቸዋል። ለዚያም ሲሉ ሴት ቢምቢወች ደም ይመጣሉ። በነገራችን ካይ ቢምቢወች ከ 1.6 - 2.3 ኪሎ ሜትር በሰአት መብረር ይችላሉ።

ታድያ ከነዚህ ውስጥ anopheles የተባሉት የቢምቢ ዝርያወች ናቸው ወባን እሚያስተላልፉት። ግን ቢምቢወች ሲነክሱን ቆዳችን ላይ እብጠት ይከሰታል ለምንድን ነው?!

መልሱ ቢምቢወች ከሰው ልጅ ደም ለመምጠጥ ቆዳችን እንደበሱ ምራቅ ነገራቸውን ወደ ውስጥ ይለቁታል! በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ሰውነት ወደ ውስጥ ለገባው ምራቅ ነገር ምላሽ ይሰጣል በዚህ ጊዜ እብጠት ነገር ይከሰታል።ቢምቢወች ድምፅ እሚፈጥሩት በ ክንፋቸው ውልብልብታ ነው።

እነዚህ ቢምቢወች መብራት ጠፍቶ እንኳን ሊያገኙህ ይችላሉ። ምክኒያቱ ደግሞ ቢምቢዎች ለ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ (CO2)፣ ለሙቀትና ለጥቁር ቀለም ልብሶች የተሳቡ መሆናቸው ነው።

እንደ healthline ገለፃ ከሆነ ቢምቢወች O blood group (የደም አይነት) ያላቸውን ሰወች ነው በደምብ እሚመገቡት። ደማችሁን እየመጠጡ ዝም ብላችሁ ብትከታተሏቸው እስከ አራት ደቂቃ ሊቆዩ ይችላሉ።

እንደ national institute of health ገለፃ ከሆነ የቢምቢ ትንኞች ከመጠን በላይ ጨውና ፈሳሽ ነገሮችን እሚያስወግድ #ኩላሊቶች አላቸው። ይህንን ቆሻሻም በሽንት መልክ ያስወግዱታል።

ወንዱ ቢምቢ ከ ሴቷ ጋር ግንኙነት ካደረጉ በኋላ በሂወት የመኖር እድል የለውም። ሴቷ ግን ብዙ ጊዜ ልታደርግ ትችላለች በሁሉም የግንኙነት ጊዜ የዘር ፈሳሹን ታጠራቅምና አንዴ ትጠቀምበታለች። ወንዶች ለጉልምስና ጊዜ በኋላ በዛ ቢባል አንድ ወይም ሁለት ሳምንት ይኖራል ሴቷ ግን እስከ መቶ ቀን መኖር ትችላለች።

ለዛሬ ይህን ይመስላል ሌላ ጊዜ በሌላ ነገር እንገናኛለን

@ibnuhasen


እናስተነትን ዘንድ

እነሆ ተፈኩር እናድርግ ብለን ሀሳቡን ጀምረን አሁን ማስቀጠልን ወደድጅን። እንደ ሙስሊም አካባቢያችን ያሉ ነገሮችን እንስተነትን ዘንድ የተወደደ ነውና አካባቢያችን ስላሉ ነገሮች እያነሳን እንወያያለን።

ለዛሬ የመረጥንላችሁ አላህ በስሟ አንድ የቁርአን ምእራፍ የሰየመላትን አንድ የነፍሳት ዝርያ የሆነውን ጉንዳንን ነው።

ጉንዳን በጣም ጠንካራ ከሆኑ ነፍሳት እሚመደብ ነው። የክብደቱን 20 እጥፍ መሸከም ይችላል። ይህ ማለት አንድ ወጣት እንደ ጉንዳን ጠንካራ ቢሆን አንድ የቤት መኪናን ሊሸከም ይችላል ማለት ነው።

ጉንዳን በዳይነሶሮች ጊዜ ጀምሮ የነበረ እንደሆነ ሳይንቲስቶች ያትታሉ። ይህም ማለት ከ 100 ሚልዮን አመት በፊት ማለት ነው። ይህ ነፍሳት ከ 12,000 አይነት በላይ ዝርያወች ያሉት ነው ። ምድር ላይ እሚርመሰመሱ ብዙ ጉንዳኖችን አይተው ይሆናል። እስኪ እንጠይቅወ ምድር ላይ እሚሄዱት ጉንዳኖች ሴት ወይስ ወንድ ?!

ብዙ አያስቡ ምድር ላይ እሚያዩኣቸው ተራማጅ ጉንዳኖች በሙሉ ሴቶች ናቸው። ወንድ ጉንዳኖች ሁሉም መብረር እሚችሉ ናቸው።ቤትዎ ቁጭ ብለው ከየት መጣ ሳትሉት አንድ መንጋ ጉንዳን በሰልፍ ቤትወን ሊወሩት ይችላሉ። "ይህ ሁሉ ጉንዳን ከየት መጣ?" ብለው ከተገረሙ እንንገርዎት ። ጉንዳኖች በየቦታው ምግብ እሚፈላልግ ወታደር ይልካሉ። ጉንዳኖች ጣፋጭ ነገርን ይወዳሉ። በርግጥ እማይበሉት ነገር የለም ። ጣፋጭ ነገር ግን ምርጫቸው ነው። ያ ወታደር ቤት ውስጥ ምግብ ካገኘ ሌሎች ወታደሮችንም ይጠራና ወደ ቤትወ ዘመቻ ይከፍትበዎታል ማለት ነው።

እዚህ ምድር ላይ እስከ አስር ኳድሪሊዮን የሚደርሱ ጉንዳኖች አሉ። በቀላሉ መራባት ይችላሉ። ሴቷ ጉንዳን ወይም ንግስቲቱ ብዙ አመት መኖር ስትችል በሚልዮን የሚቆጠር ጉንዳኖችን መፈልፈል ትችላለች።

ከሰወች ጋር በ ratio ስናስቀምጥ ለአንድ ሰው አንድ ሚልዮን ጉንዳን ማለት ነው። ጉንዳኖች ይታመማሉ። ባውቨሪያ ባሲያና የተሰኘውን የፈንገስ ዘር ከነኩት ዘሩ ሰውነታቸው ላይ ተራብቶ ህመም ላይ ይጥላቸዋል። በርግጥ ጉንዳኖች ሀኪም አላቸው። ይህን ፈንገስ ግን ፈንገስን እሚገድል ጥቂት ኬሚካል ከጠጡ ይድናሉ።

ጉንዳኖች በግዛት ጦርነት ይገጥማሉ። በጦርነቱ ወቅት የቆሰሉት ጉንዳኖች የእርዳታ signal (ምልክት) ይልካሉ። ወዲያው ሀኪም ጉንዳኖች ደርሰው ያክሟቸዋል። መዳን እማይችሉ ከሆኑ ግን ሀኪሞች አይረዷቸውም።

እንደ reddit ገለፃ ከሆነ ጉንዳኖች ሲሞቱ የሰው ልጅ ሊሰማው የሚችልን ጩኸት ይጮሀሉ ወይም ድምፅ ያሰማሉ።

ለዛሬ በዚህ እናበቃለን ሌላ ጊዜ በሌላ ፍጥረት እንገናኛለን።

@ibnuhasen

T.me/ibnuhasen


እነሆ ጊዚያችን ጠብቀን ተከስተናል☺️

#Reading_challenge

ዛሬ ደሞ ለየት ያለ መፅሀፍ ነው ምጋብዛችሁ


የመፅሀፉ ስም - ጀነት መግባት ትፈልጋለህ? እና ሌሎች ኢስላማዊ ፅሁፎች

ፀሀፊ - ፀሀፊወቹ ብዙ ስለሆኑ አሳታሚውን ብናገር ይሻላል😂

አሳታሚ- ነጃሺ ማተሚያ ቤት

የመፅሀፉ ይዘት -

መፅሁፉ ሶስት የተለያዩ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ፤ ሁለቱ የትርጉም ስራወች ሲሆን አንዱ የጥንቅር ስራውን የሰራው ሙሀመድ ሰኢድ(ABX) ነው።
በመጀመሪያ ላይ እምታገኙት "ጀነት መግባት ትፈልጋለህ?" እሚሰኘው በ ማጂድ ኢብን ኸንጀር አልባንካኒ ፤ አቢ አነስ አል ኢራቂይ የተዘጋጀ ሲሆን አብዱልፈታህ ሙሀመድ ወደ አማርኛ መልሶታል። እዚህኛው ክፍል ላይ ጀነት ምን እንደሆነ በማብራራት እሚጀምር ሲሆን ሙስሊሞች ጀነት ውስጥ ቤት ይገነባላችኋል ተብለው የተላለፉትን ሀዲሶች እና ትንተናወችን ሸክፎ የያዘ ነው።

ሁለተኛው ደግሞ ሙሀመ ሰኢድ ያጠናቀረው ሲሆን ፤ ንፁህ ቀልብ ያስፈልገናል ሲል ሰይሞታል። ቀልባችን ንፁህ ለማድረግ እሚጠቅሙ ፅሁፎችን "ፌርማታ" ብሎ በመሰየም አስራ አራት ፌርማታ ፅሁፎችን አቅርቧል።

የመጨረሻው የኢብነል ቀይምን ኪታብ በአቤል ሀይሌ ወደ አማርኛ መልሶ ስሜትን መከተል ብሎ አቅርቦታል። ስሜትህን ለምን መከተል እንደሌለብህ እያብራራ ብዙ ነጥቦችን ያነሳል።

የገፅ ብዛት - 123

ከመፅሀፉ የተወሰደ -

" እንደ አቢ ደምደም መሆን እሚችል ማን ነው?

የሚለው የብዙወቻችን ጥያቄ እንደሆነ እገምታለሁ። ተከተሉኝማ ልንገራችሁ ። አቡዳውድ እና ጦበራኒ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ ረድየሏሁ አንሁ እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) አንድ ቀን ለሰሀቦቻቸው 'ከናንተ መካከል እንደ አቢ ደምደም መሆን እሚችል ማን ነው!' በማለት ጠየቋቸው። ሰሃቦችም 'የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አቢ ደምደም ማን ነው?' በማለት በግርምት ጠየቋቸው 'እሱማ' አሉ ነብያችን 'እሱማ ባነጋ ቁጥር ጧት ላይ በመነሳት የሚል ሰው ሲሆን የሚሰድቡትን መልሶ አይሳደብም፤ የበደሉትን አይበድልም፣ የመቱትንም አይመታም' አሏቸው።" ገፅ ፥55


@ibnuhasen

T.me/ibnuhasen


የምር መናገር አልፈልግም ነበር ግን አልቻልኩም

ሰሞኑን world hijab day ደረሰ እያሉ ፖስት ሲያደርጉ አየሁ። ገረመኝ። "እንዲህ እሚባልም ቀን አለ" እያልኩ ተገረምኩ። ግን የታዘብኩት ነገር ቢኖር አንዳንድ ሰወች ይሄን ፖስት እሚያደርጉት ሂጃብ በትክክል እማለብሱ አሉ። እነዚህ ሰወች ምን ነካቸው አመቱን ሙሉ ሂጃብ አስተካክለው ሳይለብሱ የሂጃብ ቀን ብለው ሊያከብሩ ነው☺️። ከአላህ ጋር እምንቀርበው ትእዛዙን አስተካክለን ስንፈፅም እንጂ በአመት አንድ ቀን ሂጃብን ቀን ብለን ስላከበርን አደለም😒።
አንዳንዴ ለምንድን ነው ፀጉራቸውን እሚገልጡት እያልኩ አስባለሁ።ደሞኮ ፀጉራቸውን እያሳዩ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ይለጥፋሉ።

እስኪ ልጠይቃችሁ ምክንያታችሁ ምንድን ነው?!
(ከዚህ በታች እሚመለከተው እዚህ facebook መንደር ፀጉራችሁን ገለጥ አድርጋችሁ ፎቶ ለምትለቁት ነው)

- እንደሚከለከል አላወቅኩም ነበር ! ካላችሁ እንግዲያውስ እህቴ አላህ ይዘንልሽና እወቂ ሴት ልጅ ለሷ ያልተፈቀዱ የሆኑ ወንዶች ተገላልጣ ልትታይ አይፈቀድላትም(ሱረቱ አል ኑር 24፥31)


-ሂጃብ አስተካክሎ መልበስ ስራ ሆኖባችሁ ነውን?! ፎቶ ለምትነሺበት ስታይል ስትቀያይሪ ምንም ያልመሰለሽ ሂጃብ አስተካክሎ መልበስ ስራ ሆነብሽ¡

- ሂጃብ የጨቆናችሁ፣ ነፃነታችሁን የቀማ መስሎ ከተሰማችሁ ! ከነጅማሮው አውልቁት። እንዴት ጭቆና መስሎ የተሰማችሁን ነገር ታደርጋላችሁ።

-ውበታችሁን ማሳየት ፈልጋችሁ ከሆነም!
ወላሂ ነው እምላችሁ ፀጉራችሁን ከምታሳዩበት ፎቶ ይልቅ በሂጃብ ጥቅልል ብላችሁ እምትታዩበት ምስል ውበት አለው።

-በድንገት ፎቶ ስነሳ ነው እንጂ ፈልጌ ያደረግኩት ነገር የለም! ካላችሁ ፎቶውን ስታዩት ፀጉራችሁ የሚታይ መሆኑን አስታውላችሁ እዚህ ማህበራዊ ሚድያ ላይ አትለጥፉት
በነገራችን ላይ እንዲህ ስል ለምንድን ነው አይባችን እምትከታተል! አንተ ምን አገባህ?! ትሉ ይሆናል
Well እንግዲህ እምላችሁ ነገር ቢኖር ጥፋታችሁን ለመሸፋፈን እኔን "ምን አገባህ" ማለት የለባችሁም። እኔን "ምን አገባህ" ስላላችሁ ስራችሁ ትክክል አይሆንም አላህ ዘንድ ተፅፎ ይቀርባልና።

ሲቀጥል እኔ የናንተን ጥፋት አልተከታተልኩም ጥፋታችሁ ነው እኔን የተከታተለኝ☺️(ቀልዴን ነው)።

በነገራችን ላይ እኔ hijab day ይቻላል አይቻልም እያልኩ አደለም።

አላህ ሁላችንንም ቅኑን መንገድ ይምራን።

@ibnuhasen
T.me/ibnuhasen

20 last posts shown.

243

subscribers
Channel statistics