እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ባህልን ከመጠበቅና ከማልማት አንጻር በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተገለጸ፡፡
--------------
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከለያቸውና በትምህርት ሚኒስቴር ከጸደቁት አራት የትኩረት መስኮች መካከል አንዱ የአገው ባህል ቋንቋ እና ታሪክ ሲሆን ባህልን ለማልማትና ለመጠበቅ በዩኒቨርሲቲው በኩል በርካታ ሥራዎች እየተከናኑ እንደሚገኙ የዩኒቨርሰቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ክንዴ ብርሃን(ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ከእነዚህም መካከል በየዓመቱ የሚከበረውን የአገው ፈረሰኞች ማህበር በዓለም አቀፍ ደረጃ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ማስተዋወቅ ሲሆን አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ “የአገው ፈረስ ባህል” በሚል ብሄራዊ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ማድረግ ተችሏል፡፡
በዚህ ዓመት በተከበረው 85ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል ዋዜማ በተዘጋጀው ሲምፖዚየም ላይ የአገው ፈረሰኞች በዓል በዓለም አቀፍ ቅርስነት በማስመዝገብ ሂደት ያለበትን ሁኔታ የሚያሳይ ዳሰሳ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) የቀረበ ሲሆን “አሱሪቴ” በተሰኘው ባህላዊ ትውን ጥበብ ላይ በመ/ር ብርሃኑ አሳየ እና በመ/ር ብርሃኑ ማተቤ እንዲሁም የባኩሳ ብሔራዊ ፓርክ ያለበትን ሁኔታ የሚያሳይ ጥናት ደግሞ በመ/ር እውነቱ ታዘበው (ዶ/ር) ቀርቧዋል።
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0GTaQNkyDVVFDFd2EUe1bNveGtatMy9G961fFQVnurthTohYEfCkN7AsGC9Uwqfxxl/?app=fbl