«በጨለማ ኩራዝ ለኩሼ ልብሴን እየሰፋሁ ሳለ ድንገት ኩራዙ ወደቀ'ና ክፍሉን ፅልመት ሞላው፤ መርፌዬም ወደቀች....» ስትል ትርክቷን ጀመረች ዓኢሻ (ረ.ዐ)
በዚህ ሁኔታ ሆኜ የወደቀብኝን መርፌ በዳሰሳ በመፈለግ ላይ ሳለሁ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ብቅ አሉ። የክፍሉን ፅልመት የፊታቸው ኑር ገፈፈው።
ወላሂ ክፍሉ በፊታቸው ፍካት አብርቶ የጠፋብኝን መርፌ ለማግኘት አስቻለኝ።
ወደሳቸው ዞር ብዬ፦ « አባቴምእናቴም መስዋእት ይሁኑልዎ፤ ፊትዎ ምንኛ ያበራል!!!» አልኳቸው።
«ወየውላቸው የቂያማ እለት ይህን ፊቴን ለማየት
ለማይታደሉት!» አሉኝ።
«ማን ነው ይህን ፊት የቂያማ እለት የማያየው? » ስል ጠየቅኳቸው።
እሳቸውም፦ «ስሜ በሱ ዘንድ ተወስቶ ሰለዋት የማያወርድ ሰው ነው» ሲሉ መለሱልኝ።
❣اللهُم صلِ وسلم على نبينا مُحمد!💚
"ከሩቅ ሲያይዋቸው በጣም ውብና ቆንጆ ናቸው፤ ቀርበው ሲመለከቷቸው ደግሞ በጣም ለስላሳና ጣፋጭ ናቸው።" ትላለች ኡሙ ማዕበድ ረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ስትገልፅ!🥰
ከናቴ እቅፍ በላይ ካባቴም ዳበሳ፣
ምቾት አገኛለሁ ስላንቱ ሲወሳ፣
እዝነት ፈገግታዎን አትሜ ከልቤ፣
ላኖር እደክማለሁ ገፅዎን በምናቤ።
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱለሏህ!!!
ሰሉ አለል ሀቢብ❤️❤️❤️
❤️❤️❤️አብዝተን ሰለዋት የምናወርድበት ፣አላህን ይበልጥ የምናጠራበት፣ በሩቋ ሀገር ያሉትም ከአላህ የሆነ እርዳታ እና ድል የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣ ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን የሚወፈቁበት፣ በሰለዋት፣ በካህፍ እና በዱዓ የደመቀ እና የተዋበ ጁምዓ ይሁንልን💚💚💚
@Islamisthis