ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


በዚህ ቻናሌ ላይ የኦርዶክስ ተዋህዶ መንፈሳዊ ትምህርቶች፣መዝሙሮች፣እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ያገኛሉ። ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter






❗#ህዳር_12 #ቅዱስ_ሚካኤል❗
🔷 #ለምን_ይከበራል??🔷
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ህዳር 12 የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓላት ከሚከበሩበት ቀናቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በዚህ ዕለት ለምን እንደምናከብር እና በዕለቱ ምን ምን የተደረገበት ዕለት እንደሆነ በአጭሩ እንመለከታለን።

1 👉 በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል❗

🔷👉 ህዳር 12 በዚህ እለት መላእኩ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመበት ዕለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡

🔴👉 እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ ተሹሟል፡፡ (ይህንም አክሲማሮስ በሚባለው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡)

2 👉 ቅዱስ ዱራታዎስ ቴዋብለት(ቴውብስታ) ቤት የተገለጠበት እና ቤታቸውን የባረከበት ዕለት ነው።❗

🔷👉 የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዋብለት ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያረጉ ነበር፡፡ ከዚህምወ በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ በዚህም የተነሳ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን አጡ፡፡ ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡

🔴👉 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት፤ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስን ወደ በጎች እንዲሔድና በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ አዘዘው፤ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሔዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ አዘዘው፡፡ መልአኩም ወደ ቤት ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አስጠነቀቀው፡፡ ወደ ባለ ስንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በእርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ፡፡

🔷👉 ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው፤ እጅግም አደነቀ፤ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደው አደረገ፡፡ የተራቡ ድሆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደ ቤታቸው አሰናበታቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠላቸው ዱራታዎስንም የዓሳውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፤ በሰነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሳው ሆድ ተገኘ፡፡

🔷👉 ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዋብስታን እንዲህ አላቸው፡፡ ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ ለባለ ዓሳውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ፤ እግዚአብሔር አስባችኋልና በጎ ሥራችሁን መስዋዕታችሁን ምጽዋዕታችሁን በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፡፡ በኋላኛውም መንግስት ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል፡፡›› ብሎ ባርኳቸው ከእንርሱ ተሰወረ።

3 👉 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በባህር ሲጓዙ የተጨነቁትን የተራዳበት ዕለት ነው።❗

🔴👉 በአንድ ዘመን ብዙ ሰዎች ከግብፅ አውራጃ መጥተው ወደ ባሕር ማዶ ሄዱ፡፡ ከባሕሩም በደረሱ ጊዜ በመርከብ ላይ ተሳፍረው ከየብሱ ጥቂት በራቁና ወደ ባሕሩ መካከል በደረሱ ጊዜ ጽኑ ነፋስ ተነሳባቸው ለመስጠም እስኪ ደርሱ ድረስ፡፡
የማዕበሉ ሞገድ እየጨመረ እየጸና ከፍ አለ፡፡ ታላቅም ማዕበል መጥቶ ሊገለብጣቸው ደረሰ፡፡ ፍጹም ጥፋትና ክፉ ሞት እንደ መጣባቸው ባዩ ጊዜ ጽኑ ሐዘን ያዛቸው፡፡ የሚያድናቸው የሚያጽናናቸው አጥተው ተስፋ ቆረጡ፡፡ ያን ጊዜ እንዲህ ብለው ጮኹ፡፡ ‹‹የመላእክት አለቃቸው ግሩም ገናና የምትሆን ሚካኤል ሆይ የተአምራትና የይቅርታ መልአክ ነህና፡፡ ልዑል ቸርነቱን የሚገልጥብህ መልአክ ሆይ! እግዚአብሔር ፍቅሩን የሚያስታውቅብህ መልአክ ሆይ ወደኛ ተመልከት እርዳን፡፡ የተጨነቅን እኛን አድነን፡፡ ከመጣብን ሞትና ጥፋት እንድን ዘንድ ስለኛ ወደ ፈጣሪህ ወደ ፈጣሪያችን ወደ እግዚአብሔር ለምንልን፡፡ አሁን የሞት መጋረጃ ዓይናችንን ሸፍኖታልና፡፡ ፍጹም የጥፋት ጥላንም አይተናታልና›› ብለው በፍጹም ልቦናቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡

🔷👉 በመርከብ ውስጥ ያሉት ሁሉ ጽኑ ለቅሶ እያለቀሱ መራራ እንባ እያፈሰሱ ጮኹ፡፡ ከባሕር ጽኑ ማዕበል ከሞት ያድናቸው ዘንድ ያን ጊዜ በዚያች ሰዓት እግዚአብሔር የልቦናቸውን ሐዘንና ልመናቸውን ሰማቸው፡፡ ያን ጊዜም ይገዳቸው ዘንድ ቸር መልአኩን ሚካኤልን ላከላቸው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወረደ መርከቡን በእጁ ይዞ ሳበው፡፡ በመርከቡ ውስጥ ያሉትንም ወደ የብስ አወጣቸው፡፡ በደኅናቸው ተሻገሩ፤ ክፉ ነገር ጥቂትስ ስንኳ ፈጽሞ አላገኛቸውም፡፡

4 👉 እስራኤልን ከግብፅ እየመራ ወደ ሀገራቸው ያስገባበት ዕለት የሚታሰብበት እለት ነው❗

🔴👉 ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጡትን ሕዝብ እግዚአብሔርን ቀኑን በደመና ዓምድ ሌሊቱን ደግሞ በብርሃን ዓምድ መርቷቸዋል እስራኤል ዘሥጋን በመንገዳቸው ሁሉ የጠበቃቸው መና ከሰማይ ያወረደላቸው ተአምራትን ያደረገላቸው ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ርስታቸው የመራቸው በደመና መጋረጃ የጋረዳቸውበክንፎቹም የሸፈናቸው መጋቤ ብሉይ የተባለ ቅዱስ ሚካኤል ነው።

🔷👉 ስለዚህም እኛ የተዋህዶ ልጆች ህዳር 12 ቀን በየዓመቱ በማኅሌት እና በቅዳሴ የምናከብረው በዓለ ሹመቱን በማሰብ ቴዎብስታ ዱራታዎስ ያደረገው ታምረ እና በባህር የተጨነቁትን ያዳነበትን እና ሌሎችም በቀኑ የተደረጉትን ለመዘከርና ለማሰብ ነው። በተጨማሪም ከገናናው መልዓክ ከቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከቱን ለማግኘት ነው።

የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ሚካኤል ምልጃና ፀሎት ከሁላችን ጋር ይሁን በዓሉም የሠላም የፍቅር ያድርግልን። አሜን

❗ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ❗

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 11/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16








❗#ታላቅ_የንግስ_ክብረ_በዓል_ጥሪ❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ታላቁ እና ጥንታዊው የወልመራ ደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ነው ፡፡

🔷👉 ይህን መልዕክት ያነበባችሁ ሁላችሁም ሼር በማድረግ ጐደኞቻችሁን ጋብዛችሁ መጥታችሁ ነገ ማለትም ህዳር 12 የቅዱስ ሚካኤልን ዓመታዊ ክብረ በዓል በወልመራ ደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንድታከብሩና ከታላቁ መልአክ ከቅዱስ ሚካኤል በረከትን ትቀበሉ ዘንድ ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን ታስተላልፋለች ።

🔴👉 እኛም ቤተ ክርስቲያኗ ባቀረበችልን ጥሪ መሠረት በቦታው ተገኝተን መምጣት ለማትችሉ በዩትዩብ ክብረ በዓሉን በቀጥታ ስርጭት ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

🔶ህዳር 12 እንገናኝ ባላችሁበት ሁሉ አምላከ ቅዱስ ሚካኤለ ይጠብቃችሁ አሜን።🔶

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 11 /2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16




❗ #ህዳር"11" #ቅድስት_ሐና❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 በዚች ዕለት አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች የቅድስት ሐና የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው።

🔷👉 ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት። ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት።

🔴👉 ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥመቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት። ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት እሊህም ሰሎሜና ኤልሳቤጥ ለቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው።

🔷👉 የዚችንም የቅድስት ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ጸጋ ባልተገባት ነበር።

🔴👉 ይህችም ጻድቅት ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትማልድ ነበር እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት።

🔷👉 ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባናል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

ምንጭ :- ስንክሳር ዘወርኃ ህዳር

❗ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ❗

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 11/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia1


❗ህዳር 12 የቅዱስ ሚካኤልን ዓመታዊ ክብረ በዓል❗
🔷👉 በወልመራ ደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ን
🔴አይቀርም

በዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 10/2017 ዓ.ም
ሆለታ

🔴ለሁሉም እንዲደርስ ሼር አድርጉ!

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia1








❗#ጻድቁ_አባታችን_አባ_ኪሮስ ❗
................................................................
🔴👉 አባታቸው ንጉሥ ዮናስ
እናታቸው አንስራ ይባላሉ።

🔷👉 የቀደመ ስማቸው ዲላሶር የተሰኘ ሲሆን
ሁለተኛ ስማቸው ደግሞ ❖ #ኪሮስ ❖

🔴👉 በታህሳስ 8 ቀን ተወልደዋል
በ8 ዓመታቸው ያላቸውን ገንዘብ ከወንድማቸው ጋር በመካፈል ወደ አባ በብኑዳ ገዳም ገብተዋል።

❗👉 እስከ 17 ዓመታቸው ረድዕ ሆነው እያገለገሉ ስርዓተ ምንኩስናን ከተማሩ፤ ከተረዱ በኋላ የምንኩስናን ማዕረግ ተቀብለዋል።

🔵👉 ስለ እግዚአብሔር ፍርድ እንዲሁም ስለ ሰው ልጆች ይቅርታ 40 ዓመት በመሬት ላይ ተኝተው ስጋቸው ከመሬት ጋር ተጣብቆ ሣር እስኪበቅልባቸው ድረስ ጸልየዋል።

🔵👉 ጌታችንም ስለ መታመናቸው እና ስለ ተጋድሏቸው አክብሯቸዋል ።

❗👉 ቃል ኪዳናቸውም ፡- መካኖች ልጀ የሌላቸው ገድሉን አቅፈው ቢያለቅሱ ጸበሉን ቢጠጡ ስምህን ቢጠሩ፤ የመካኒቱን ማህጸን እከፍታለሁ፡፡ የሚሞትባቸውን እንዳይሞተባቸው አደርጋለሁ፡

🔷👉 በንጹ ገንዘቡ ቂምና በቀል ሳይዝ በህግ በስጋውና በደሙ የጸና ሰው በስምህም በተሠራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ አሰጠዋለሁ፡፡ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ከዚም በኋላ ሐምሌ 8 አርፈዋል።

የጻድቁ አባታችን አቡነ ኪሮስ ምልጃና በረከታቸው አይለየን

❗በዕለተ ቀናቸው ይህንን የበረከት ስራ ተሳተፉ❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ። ሐዋ, 20፥35

🔴👉 ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች መፅሐፍ እንደሚለው ስንቶቻችን ከመቀበል ይልቅ ለመስጠት ዝግጁዎች ነን ? ስንቶቻችንስ በምፅዓት ቀን ለምንጠየቀው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሳይመሽብን ተዘጋጅተን ይሆን ?

🔵👉 በውኑ በምፅዓት ቀን ምንድን ነው የምንጠየው ትሉኝ ይሆናል እስቲ ከነ ፍርዱ መፅሐፍ የሚለውን እንመልከት 👇👇

🔴👉 ማቴዎስ 25
³⁴ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
³⁵ ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥
³⁶ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።
³⁷ ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?
³⁸ እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?
³⁹ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
⁴⁰ ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።

🔴👉 ⁴¹ በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
⁴² ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥
⁴³ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።
⁴⁴ እነርሱ ደግሞ ይመልሱና፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።
⁴⁵ ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።
⁴⁶ እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።

🔴👉 ወዳጆቼ እኛ የትኛውን ይሆን የምንፈልገው ? የአባቴ ብሩካን ኑ የሚለውን ነው ወይስ እናንተ ርጉማን ከኔ ሂዱ የሚለውን ነው ? እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም የአባቴ ብሩካን ኑ መባልን መንግስቱን መውረስን ነው የምንፈልገው !

🔵👉 ታዲያ ይህንን እንድንባል የተራበ አብልተን ይሆን የተጠማ አጠጥተን ይሆን የታረዘ አልብሰን ይሆን የታሰረ ጠይቀን ይሆን ? የታመመ ጠይቀን ይሆን ? መቼስ ነው ይህንን የምናደርገው ? ወዳጆቼ መጠሪያችን አይታወቅምና ሳይመሽብን ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንስራ !

🔴👉 እግዚአብሔር ፈቅዶልን ከዚህ በፊት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተቸገሩትን እቤታቸው ድረስ በመሔድ ለበዓሉ የሚያስፈልገውን አድርገናል ነዳያንንም አንድ ቦታ ሰብስበን መግበናል። አንዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ደግሞ ከ700 በላይ የሚሆኑ የታሰሩ ወገኖቻችን ጠይቀናል በዓሉን አብረናቸው አክብረናለ ! ይህ የሆነው ደግሞ እናንተው አነሰ በዛ ሳትሉ ከ100 ብር ጀምሮ በሰጣችሁት ገንዘብ ነው ይህንንም በቪዲዮ ወደ እናንተ አድርሰናል። በዚህም ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንድሰራ የፈቀደልን አምላክ ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁንልን ። አሁንም እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከፊታችን የሚመጣውን የጌታችንን የልደት በዓል (የገና በዓል) ምክንያት በማድረግ ታምሜ አልጠየቃችሁኝም ይላልና ቃሉ በየ ሆስፒታሉ በህመም ምክንያት ከሚሰቃዩ እህት ወንድሞች ጋር ለማሳለፍ ፕሮግራም ይዘናል ! ወገኖቼ ስንቱ ወየ ሆስፒታሉ ጤና አጥቶ መታከሚያም አጥቶ የሚሰቃይ አለ ።

🔵👉ስለዚህ እኛ በዓሉን በቤታችን ሁሉ ሞልቶልን ስናከብር ቃሉ እንደሚለው የታመሙ ወንድም እህቶቻችንም ማሰብ ተገቢ ነውና ሁላችሁም አነሰ በዛ ሳትሉ እዚህ የበረከት ስራ ላይ ልትሳተፉ ያስፈልጋል ! ቢያንስ እዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ ከ60 ሺ ሰው በላይ አለ ሁሉም መቶ መቶ ብር እንኳን ቢያዋጣ ትልቅ የበረከት ስራ መስራት ይቻላል እናንተ የምትሰጡት መቶ ብር ትልቅ ስራ መስራት ይችላል ስለዚህ ይህንን ያነበባችሁ እዚህ የበረከት ስራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ በ 0902829657 በኢም, በዋትስአፕ , በቴሌግራም , አናግሩኝ ! ቃል መግባት የምትችሉም ቃል መግባት ይቻላል !

🔴👉 እንዲሁም ለዚሁ አላማ ተብሎ በሶስት ሰው ስም በተከፈተው ንግድ ባንክ አካውንትም ማስገባት ትችላላችሁ 👇👇
1000614809683 ደሳለኝ እጅጉ & በረከት & ዋሲሁን

❗በሚጠፋው ገንዘባችን የማይጠፋውን ሰማያዊ ቤታችንን እንስራ❗

በዚህ ቻናላችን ላይ በአመት ሶስት ቋሚ የነብስ ስራዎችን አብረን እንሰራለን ።
👉 ለአዲስ ዓመት :- የተራቡ ማብላት
👉 ለገና በዓል :- የታመሙ መጠየቅ
👉 ለፋሲካ በዓል :- የታሰሩ መጠየቅ

❗ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ❗

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 8/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w




❗❗#ህዳር_8 #አርባዕቱ_እንስሳ❗❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ህዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው #የአርባዕቱ_እንስሳ በዓላቸው ነው፣

🔵👉 እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።

🔶👉 የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።

🔷👉 የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።

🔴👉 ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።

🔵👉 የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።

❗👉 ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።

🔵👉 በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።

🔴👉 እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።

🔷👉 ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።

🔷👉 ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።

🔵👉 በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።

🔴👉 ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው።

🔷👉 ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።

🔵👉 ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።

❗መንፈሳውያን አመስጋኞችና መዘምራን የምትሆኑ አራቱ እንስሳት ስለ አኛ ለምኑ❗

❗አርባዕቱ እንስሳ መንፈሳውያን ሰባሕያን ወመዘምራን ሰዐሉ በእንቲአነ❗
( አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ሰዓታት )

🔷👉 ቅዱስ ጄሮም እንዲህ አለ ፦
አርባዕቱ እንስሳት የድኅነታችን ምሥጢር የሆኑትን አራት ደረጀዋች ያስረዳሉ ።

🔷👉ገጸ ሰብእ ፦ ሥጋዌውን ( ቃል ስጋ መሆኑን )
🔷ገጸ አንበሳ ፦ ትንሣኤውን
🔷ገጸ ላህም ፦ ንጹሕ መሥዋዕት ( ቤዛ ) መሆኑን
🔷ገጸ ንሥር ፦ ዕርገቱን

🔴የእግዚአብሔርን ባሕርያት ያመለክታሉ።
ገጸ ሰብእ ፦ ጥበቡንና ዕውቀቱን
ገጸ አንበሳ ፦ ግርማውንና ኃይሉን
ገጸ ላህም ፦ ትዕግስቱን ፈታሒነቱን
ገጸ ንሥር ፦ ክብሩን ልዕልናውን

🔴አንድም አርባዕቱ እንስሳት
በአራቱ ወንጌላውያን ይመሰላሉ።

🔵#አርባዕቱ_እንስሳት #በእመቤታችን_ድንግል_ማርያም_ይመሰላሉ። እነሱ መንበሩን ለመሸከም እንደተመረጡ ፤ ሰማይና ምድር የማይችሉትን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ ተሸክማዋለችና ።

፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

🙏⏩ሼር አድርጉ አይከፈልበትም

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 8/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16






❗#ሚስጥረ_ስላሴ ❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴.1 ማን ፈጠረን?
መልስ 👉 ቅድስት ስላሴ።

🔵.2 ስላሴ ስንት ናቸዉ?
መልስ 👉 አንድም ሶስትም ናቸዉ።

🔴.3 ሶስትነታቸዉ በምን በምን ነዉ?
መልስ 👉 በስም በአካል በግብር።

🔴.4 አንድነታቸዉስ በምንድነዉ?
መልስ 👉 በባህሪይ በህልዉና በመለኮት በፈቃድ ሰዉን በመፍጠር አለምን በማሳለፍ በዘለአለማዊ ስልጣን!

🔵.5 የስም ሶስትነታቸዉ እንዴት ነዉ?
መልስ 👉 አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ።

🔴.6 የአካል ሶስትነታቸዉ እንዴት ነዉ?
መልስ
👉ለአብ ፍፁም ገፅ ፍፁም አካል ፍፁም ሰዉነት አለዉ!
👉ለወልድም ፍፁም ገፅ ፍፁም አካል ፍፁም ሰዉነት አለዉ!
👉ለመንፈስ ቅዱስም ፍፁም ገፅ ፍፁም አካል ፍፁም ሰዉነት አለዉ።

🔵.7 የግብር ሶስትነታቸዉ እንዴት ነዉ?
መልስ 👉 አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሰራፂ ነዉ።

🔴.8 አብ ማለት ምን ማለት ነዉ?
መልስ 👉 አባት።

🔵.9 ወልድ ማለት ምን ማለት ነዉ?
መልስ 👉 ልጅ።

🔴.10 መንፈስ ቅዱስ ማለትስ?
መልስ 👉 ሰራፂ
🔵.11 ከማን የሰረፀ?

መልስ 👉 አብን አክሎ ወልድን መስሎ ከአብ የተገኘ ወይም የሰረፀ።

❗ሚስጥረ_ስላሴ አይመረመርም ጥልቅና ሰፊ ነዉ ከረጅሙ በአጭሩ ከብዙ በጥቂቱ ከመለኮታዊ ስፋቱ የገለፀልን የአቦቶቻችን አምላክ ልኡል እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን አሜን❗

🔵👉ለሌችም እንዲደርስ በቅንነት
ሼር አድርጉ !

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 7/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia1


❗ኑ የጀመርነውን እንፈፅም❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉 ታላቅ መንፈሳዊ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር የመናገሻ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ዓመታት ሲያስገነባ የነበረውን ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ከፍፃሜ ለማድረስ "የጀመርነውን እንፈፅም" በሚል መሪ ቃል በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ የፊታችን ህዳር 8 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ልዩ ጉባኤ አዘጋጅቷል።

🔴👉 በመሆኑም እናንተም ላልሰሙት በማሰማት በዕለቱ በቦታው በመገኘት የበኩላችሁን በመወጣት የበረከቱ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ ህንፃ ቤተ ክርስቲያኗንም ከፍፃሜ እናደርስ ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

🔷👉 እኛም ቤተ ክርስቲያኗ ባቀረበችልን ጥሪ መሠረት በዕለቱ በቦታው በመገኘት በአካል መገኘት ለማትችሉ ባላችሁበት ሆናችሁ መርሃ ግብሩን ትከታተሉና የበረከት ስራው ላይ ትሳተፉ ዘንድ በYoutube እና በ facebook በቀጥታ ስርጭት ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

🔷👉 የደብሩ አካውንት :- 1000033842434 ንግድ ባንክ

❗ለሁሉም እንዲደርስ ሼር አድርጉ አይከፈልበትም❗

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 6/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

20 last posts shown.