💙 ምኞቴ 🔸
#ክፍል_ 1️⃣3️⃣
ረድኤት እናቷን ፈራቻቸዉ፡፡ ንግግራቸዉ ወደ ቁጣ እየተቀየረ ይመስላል፡፡
..."አይ አታዉቅም" አለች
..."የኔ ልጅ!" አሉ እማማ "ባለፈዉ ያባትሽ ሚስት በእኔ ምክንያት እንደሞተች
ነግሬሻለኃ?"
..."አዎ እማዬ ነግረሽኛል"
..."ስለዚህ የኔ ልጅ ኤዲም ባንቺ ምክንያት መጎዳት የለባትም፡፡ አንቺና ቢኒያም እንደሆናችሁ ሳጨርሱ አቀሩም፡፡ እኔ ለቢኒያም የምድርሽ የእናንተን መስማማት አይቼ ሳይሆን የኤዲን ፍቃደኝነት ጠይቄ ነዉ!"አሉት፡፡ ረድኤት ደስም አላት ግራ ተጋባችም፡፡ ቢኒያምን ልታገባዉ ነዉ ግን ደግሞ ኤዲ ባትፈቅድስ
..."እና ለኤዲ ልትነግሪያት ነዉ እማዬ?"
..."አዎ ቀስ ብዬ እነግራታለሁ፡፡ አንቺ አታስቢ የኔ ልጅ" ብለዋት ከተቀመጡበት ተነስተዉ
ወደ ዉስጥ ገቡ፡፡ አባባ ሀብታሙ ከዘራቸዉን ይዘዉ ዉጭ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ እንደ አጋጣሚ ኤዲ ከቤት ስትወጣ ፊት ለፊት አየቻቸዉና "አባባ ሀብታሙ ሰላም ኖት" አለቻቸዉ፡፡ እርሳቸዉም "ደህና ነኝ ፈጣሪ ይመስገን ሰላም ነሽ ወይ ኤዲ" ብለዉ መለሱላት፡፡
ከዚያም አጠገባቸዉ ቀረበችና ስለ ረዲ አንዳንድ ነገር ለማወቅ "አባባ ረዲን አትድሯትም እንዴ እድሜዋኮ እየሄደ ነዉ፡፡"አለቻቸዉ፡፡አባባ ሀብታሙም የሷን ጥያቄ ወደ ጎን አሉና "አንቺና ቢኒያም ከተጋባችሁ ምን ያህል ጊዜ ሆናችሁ?" ብለዉ ጠየቋት፡፡ኤዲ ይሄን ጥያቄ ከመለሰች ቡኋላ ቀጣዩ ጥያቄ ምን እንደሚሆን አዉቃለች፡፡ ለጥያቄያቸዉ
መልስ መስጠት ስላለባት ብቻ "አራተኛ አመታችንን ይዘናል" አለቻችዉ፡፡"ታዲያ ልጃችሁን ቤተሰቦችሽ ዘንድ አርጋችሁት ነዉ?" ብለዉ ጠየቋት፡፡
..."አይይ አባባ..." አለቻቸዉ በረጅሙ የብሶት ትንፋሽ እየተነፈሰች፡፡ ተራርቀዉ
መቀመጣቸዉ እንጂ ትንፋሿ እንደ በርሃ ወበቅ ይጋረፋል፡፡
..."ምን ነዉ? የኔ ልጅ?" አሏት ጭንቀቷን ሲያዩ
..."አይ ምንም" አለችና አቀረቀረች ኤዲ፡፡ አባባ የሆነ ነገር እንዳለ ጠረጠሩ፡፡እሳቸዉም የልጅ ፍቅር ስላላቸዉ ጭንቀቷ ይገባቸዋል፡፡
"ልጅ አልወለድኩም አባባ..." አለቻቸዉ፡
አባባ ሁኔታዋን ሲያይዋት ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይታይባታል፡፡ እሷ ግን እንደምንም እየታገለች ፈገግ ለማለት ትሞክራለች፡፡ ምክንያቱም ልጃቸዉን ለባሏ ልትጠይቃቸዉ ነዉና፡፡ ከረጅም ዝምታና ፀጥታ ቡኃላ አባባ ተንፈስ አሉና "ባልሽ ቢኒያም ግን በጣም ጎበዝ ነዉ አደነቅኩት" አሏት፡፡ እሷም ለምን? እንዴት? በምን ምክንያት አደነቁት? ብላ አልጠየቀቻቸዉም፡፡ ቢኒ የሚደነቅ ጥሩ ሰዉ እንደሆነ ታዉቃለችና፡፡ አንድ ነገር ግን እርግጠኛ እየሆነች ነዉ፡፡ የረድኤት ቤተሰቦች ቢኒያም ረድኤትን ለትዳር ቢጠይቅ እምቢ እንደማይሉና በደስታ እንደሚድሩት
ከአባባ ሀብታሙ ሁኔታ መረዳት ችላለች፡፡ የረድኤት ቤተሰቦች ቢኒያምን ይወዱታል፡፡ ደስ
አላት፡፡ ባሏን እሷዉ ልድረዉ ነዉ፡፡...ቢኒ ከስራ እንደመጣ ጊዜ ማባከን አልፈለገችም፡፡
"ቢኒ ለረድኤት ቤተሰቦች ሽማግሌ መላክ አለብህ" አለችዉ፡፡
..."እንዴ ፈጠንሽሳ?" አላት ቢኒ
..."አዎ ፍቅሬ ሌላ የኔን ቢጤ ደሃ ካገባህኮ እኔን መፍታትህ አይቀርም፡፡ እኔ ደግሞ አንተ
እንድትፈታኝ አልፈልግም፡፡ ሁሌም በፍቅርህ መኖር እፈልጋለሁ" አለችዉ እየተቅለሰለሰች፡፡
ይሄን ከማለቷ ብዙም ሳይቆዩ የቢኒያም ስልክ መልዕክት (ሜሴጅ) ገባ "ጢጢጥ
ጢጢጥ" ሜሴጁ ሲገባ የቢኒ ስልክ ያሰማዉ ድምፅ ነበር፡፡ ቢኒ ስልኩን አነሳና
የላኪዉን ስም ሲያይ በማማ በለጡ ስልክ ነዉ የተላከዉ "ረድኤት መሆን አለባት" አለ
በዉስጡ፡፡ ኤዲ እያየችዉ ነበር፡፡ ደንገጥ ብሎ ስታየዉ ፊቷ ክስም ይላል፡፡ እንደገና ፈገግ
ሲል እሷም አብራ ትፈካለች፡፡ ኤዲ ሁሌም ቢሆን በቢኒያም ደስታ ደስ ይላታል፡፡
"የኔ ፍቅር ምንድን ነዉ መልዕክቱ?" አለችዉ....ኤዲ ቢኒ ፈገግ ስላለበት ጉዳይ ለማወቅ ጓጓች፡፡ ቢኒ አሁንም እንደፈገገ ነዉ፡፡
" ንገረኛ ዉዴ?" አለችዉ፡፡ በአይኖቿ እየተማጸነች፡፡ ቢኒያም ሊነግራት ነበር ነገር ግን
ከረድኤት ጋር ከዚህ በፊት እንደተደዋወሉና በስልኩ መልዕክት እንደላከችለት ቀድሞ ለኤዲ
አልነገራትም ነበር፡፡ ትቆጣ ይሆን እንዴ? ፈራ፡፡ ከሷ መደበቅ ስላልፈለገና ኤዲ ብትቆጣም
ብታኮርፍም ልትንሽ ሰዓታቶች እንደሆነ ስላወቀ ስልኩን ለኤዲ አቀበላት፡
#ክፍል 14 ይቀጥላል... LIKE ❤️ & Share✅ በማድረግ ታሪኮቹን በፍጥነት ያግኙ።ዮሀንስ...🤌🤍
@Jo_21_19🥀ᴊᴏɪɴ & ꜱʜᴀʀᴇ🥀
🔔
@Kurach_kalat💭
📣
@Kurach_kalat💬