⚖Ethiopian law by Daniel Fikadu Law office⚖


Channel's geo and language: Ethiopia, English
Category: Law


ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ
ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559
Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia.
Email- nurotekore@gmail. Com
⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Category
Law
Statistics
Posts filter


Forward from: Ethiopian Legal insight
የማይንቀሳቀስ ንብረት የመተላለፍ መብት እና አፈፃፀሙ
በፍ/ህ/ቁ 1221 መሠረት መሬቱ የተዘጋበት ወይም በመሬቱ ለመጠቀም ለህዝብ በሚያገለግለው መንገድ ላይ በቂ ያልሆነ መውጫ ያለው ባለሀብት ሊያደርስ በሚችለው ጉዳት መጠን ግምቱን ከከፈለ አስፈላጊውን መተላለፊያ እንዲሰጠው ጎረቤቱን ለማስገደድ እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ይህም ማለት አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ያለው ሰው በቂ መውጫ መግቢያ ከሌላው አስፈላጊ መተላለፊያ እንዲሰጠው አጠገቡ ያለውን ጎረቤቱን አስፈላጊውን ካሳ ከፍሎ መውጫ መግቢያውን እንዲያሰፋ የሚደረግበት አሰራር ነው፡፡በመሆኑም የመተላለፊያ መብት ጠያቂው ኪሳራ ወይም ካሳ የመክፈል ተነፃፃሪ ግዴታ ፈፅሞ የመተላለፊያ መንገድ የማግኘት መብት እንዳለው ከድንጋጌው መገንዘብ ይቻላል፡፡የፌ/ጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም በቅፅ 10 በሰ/መ/ቁ 48783 ላይ የመተላለፈያ መንገድ እንዲሰጠው ለአስተዳደር መስሪያ ቤት ጠይቆ ከሰበር ተጠሪው 1.10 ሜትር ተቀንሶ መንገድ እንዲሰጠው ከተወሰነለት በኃላ የኪሳራ ክፍያውን ለመክፈል ፈቃደኛ ያልሆነው የሰበር አመልካች በፍ/ህ/ቁ 1221 መሰረት የሰበር ተጠሪው ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ተገቢውን ካሳ ሳይከፍሉ ተጠሪ መንገድ እንዲሰጣቸው ሊገደዱ እንደማይችሉ ነው፡፡አመልካች በአስተዳደሩ የተወሰነው የመካካሻ ግዴታ ሳይወጡ ተጠሪን ማስገደድ አይችሉም ሲል የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔን ያፀናው ሲሆን ነገር ግን አሁንም ቢሆን አመልካች በአስተዳደሩ ውሳኔ መሠረት ግዴታቸውን ከተወጡ በኃላ የመተላለፊያ መንገድ የማግኘት መብት አላቸው ሲል ፍርድ ሰጥቷል፡፡

www.ethiopianlegaltech.com
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Ethiopianlegalinsight


በኢሜል የደረሰኝ መልእክት ነው

ሰላም አቶ ዳንኤል እንዴት ነህ።
*** እባላለሁ ጠበቃ ነኝ።የቴሌግራም ደግነትህ ተገልጋይ ነኝ አመሰግናለሁ።
አንድ ነገር አሳሳቢ ሆኖ ታየኝ እና በሚዲያው ሆነ በማህበራዊ ድህረ ገፅ በማጋራት ፈጣን መፍትሄ መሰጠት ይኖርበታል።
ጉዳዩ በከተማ ነክ ስልጣን የሆኑ ክሶችን ለማቅረብ ከሳሹ የቀበሌ ዲጂታል መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ ነው በማለት ግለሰቦች ከነሀሴ ወር ጀምሮ እየተንገላቱ ይገኛል። ይባስ ብሎ ጉዳዩ በጠበቃ ቢቀርብም ጠበቃው የከሳሾችን የቀበሌ ዲጂታል መታወቂያ ይዞ መቅረብ አለበት ተብሏል።ፍትህ ለማግኘት ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጥ ሰብአዊ መብት ጥሰት ነው የምትችለውን እንድታደርግ ነው።አመሰግናለሁ።


የጦር መሳሪያ የጫነ ተሽከርካሪ ስለሚወረስበት አግባብ የሰ/መ/ቁ. 241787 /Daniel Fikadu Law Office/
ቁጥሩ ብዙ የሆነ ህገወጥ የጦር መሳርያ ሲያዘዋውር የተገኘ ተሽከርካሪ የመኪናው ባለቤት ስለድርጊቱ እውቀት ይኑረውም አይኑረውም ተሽከርካሪው ይወረሳል።
/አዋጅ 1160/11 አንቀፅ 143 ና 147(3)፣1177/2012፣ 1160/2011፣859/2006/


























Forward from: TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia

ከፍተኛ ክርክር የተደረገበት የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ ከነማሻሻያ አዋጁ ትላንትና ፀድቋል።

የምክር ቤቱ አባላት ረቂቅ አዋጁንና ማሻሻያ ሪፖርቱን አስመልከተው የተለያዩ የድጋፍና የተቃውሞ ሐሳብና አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡ 
የምክር ቤት አባልት ምን አሉ ?

- ማሻሻያው ከአሁን ቀደም ከሥራ ባህሪያቸው አንፃር ለየት ባለ የአደረጃጀትና የአሠራር መዋቅር ተደራጅተው የነበሩ የፍርድ ቤቶችን መሰል አዋጆችን መሻሩን የወቀሱ ነበሩ፡፡

- ማሻሻያ አዋጁ ልክ ለገቢዎችና ለጉምሩክ ኮሚሽን ሠራተኞች እንደሰጠው ሁሉ፣ ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች ተገቢውን ትኩረት ሊሰጥ ይገባ እንደነበርም ተገልጿል።

- ሥራ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በየትኞቹ የአገሪቱ አካባቢዎች በሚወጡ የሥራ ማስታወቂያዎች በእኩልነትና በፍትሐዊነት ሊወዳደሩ የሚችሉበት አስገዳጅ ሁኔታ በግልጽ በረቂቅ አዋጁ ማሻሻያ አለመቅረቡ ተነስቷል።

- የውስጥ ዝውውርን በተመለከተ አንድ የተቋም ኃላፊ ለውጤታማነት በሚል ሠራተኞችን ወደ የሚፈልግበት ቦታ አዛውሮ ማሠራት፣ ይህንን የማይቀበሉ ሠራተኞች ደግሞ መልቀቅ ይችላሉ መባሉም ጥያቄዎችን አስነስቷል፡፡ የአሠራር ክፍተቶችን የሚፈጥር እንደሆነም ተመላክቷል።

የአብን የምክር ቤት አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ፦

" እንዲህ ዓይነት አዋጆች ሲዘጋጁ ሰፊ ዝግጅትና ውይይት ይፈልጋሉ። እንዲሁም የሠራተኞችን ሥጋት ማካተት ይገባል።

የረቂቅ አዋጁ መንደርደሪያ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ኢትዮጵያን የሚመስል የሠራተኞች ስብጥር እንዲኖር ነው በሚል መገለጹ ችግር አለበት።

' ሲቪል ሰርቪሱ በአንድ ብሔር የበላይነት ተይዟል ' በሚል የቀረበ ነው። ያን ለማለት ደግሞ በሚያስችል መንገድ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

ሲቪል ሰርቪሱ ብቃትንና አቅምን መሠረት አድርጎ ሊገነባ ይገባል። ኮታን ወደ ማከፋፈል አይወስደንም ወይ ? ሥራን በኮታ ማደላደሉ ማቆሚያው የት ነው ?

አንድ ሠራተኛ አፈጻጸሙ ምንም ይሁን ምን ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እስከፈለገ ድረስ አንስቶ ሌላ ተቋም ላይ በተመሳሳይ ደረጃና ደመወዝ መመደብ ይችላል። ያን የማይፈልግ ከሆነ ሠራተኛው መልቀቅ ይችላል መባሉ የሠራተኞችን መብት የሚጋፋና ዕጣ ፋንታቸውን በአለቆቻቸው እንዲወሰን የሚያደርግ ነው።

እንዲሁም ከሥራ እንዲለቁ የሚገፋፋ ነው።

የሠራተኞች የትርፍ ሰዓት ጉዳይ ከ39 ወደ 48 ሰዓታት እንዲያድግ መደረጉም አግባብነት የሌለው ነው " ብለዋል።


የኢዜማ አባል አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" በረቂቅ አዋጁ ' ዘመናዊና ኢትዮጵያን የሚመስል ' መባሉ በዘወርዋራው የኮታ ሥርዓትን የሚመለከት ነው።

' ዘመናዊ አገርና ዘመናዊ ቢሮክራሲ እንፈጥራለን ' እያልን የመንግሥት ሠራተኞችን ከችሎታና አቅም ይልቅ በብሔር ኮታ እንቅጠር ማለት እርስ በርሱ የሚቃረን ሐሳብ ነው።

ማይክሮሶፍትን መሰል ዓለም አቀፍ ተቋማት በአሜሪካውያን ሳይሆን በህንዳውያንና በቻይናውያን የሚመሩና የሚተዳደሩ ናቸው።

የመንግሥት ተቋማት የሃይማኖት የስብከት ቦታዎች እየሆኑ ነው። ይህ በጥብቅ ሕግ ጭምር ሊከለከል ይገባል።

አንድን ሠራተኛ መሥሪያ ቤቱ ወይም የበላይ ኃላፊው በፈለገው ቦታ መድቦ ማሠራት ይችላል የሚለው ሰው በሙያ (ፕሮፌሽን) እንዳያድግና የካበተ ልምድ እንዳይኖረው እንደሚያደርግ፣ ይህ ደግሞ በተቃራኒው ቢሮክራሲውን የበለጠ የሚጎዳ ነው።

የበላይ አመራሩ የመጨረሻ ወሳኝ መሆኑ ከሕግና ከሥርዓት የሚፃረርና ሰብዓዊ መብትንም የሚጋፋ ነው።

ይህ ከሆነ ባርነትን እንደገና በሕግ እያፀደቅን ነው ማለት ነው ? ውሳኔውን ፍርድ ቤት መስጠት አለበት " ብለዋል።


የምክር ቤት አባል አቶ ለማ ተሰማ ምን አሉ ?

" ረቂቅ አዋጁ ሠራተኞች በትምህርት መስክና ደረጃቸው እንዲሁም በልምዳቸው እንጂ፣ ከዚያ ውጪ የሚመደቡበትን አሠራር አይፈጥርም።

የሚነሱ ሥጋቶች ቀጥለው ሊወጡ በሚችሉ ደንቦች ሊመለሱ ይችላሉ።

በረቂቅ አዋጁ የተካተቱ አንዳንድ ጽንሰ ሐሳቦች በጥርጣሬ ሊታዩ አይገባም። ሲቪል ሰርቪሱ መለወጥ አለበት። ትናንት የነበረው አግላይ ነበር። ዕድልንም አይሰጥም ነበር።

ረቂቅ አዋጁ ሁሉንም ጠርጎ የሚያስወጣ ሳይሆን፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በብቃቱ ተወዳድሮ ሠራተኛ መሆን የሚችልበትን ዕድል የሚፈጥር ነው። "


ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የሰው ሀብት ልማት ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

🔴 ብዙዎቹ ጥያቄዎች በውይይት ወቅት ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸው ነበር።

🔴 ፍርድ ቤቶች በልዩ ሁኔታ መታየት ነበረባቸው መባሉ በረቂቅ አዋጁ በሚቋቋመው በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው የሜሪትና የደመወዝ ቦርድ በኩል ራሱን ችሎ ምላሽ ሊያገኝ ይችላል።

🔴 በረቂቅ አዋጁ ውስጥ ኮታ የሚል ነገር የለም። ኮታ ተቀባይነት እንደሌለው በረቂቅ አዋጁ ውስጥ ተቀምጧል።

🔴 ረቂቅ አዋጁ የሥራ አመራር ኢንስቲቲዩትን እንደ አዲስ የብቃትና ሥራ አመራር ኢንስቲቲዩት በሚል ስያሜ አቋቁሞ ሠራተኞችን በብቃታቸውን ለመመዘን ያስችላል።

🔴 ሠራተኞችን የማዘዋወሩ ኃላፊነት በማኔጅመንት እንጂ በበላይ ኃላፊዎች ብቻ አይወሰንም። የሠራተኛው ምክንያት የሚደመጥበትና መብቱ የሚጠበቅበት አሠራር በረቂቅ አዋጁ ተካቷል።

ከፍተኛ ክርክር የተደረገበት ይህ ረቂቅ አዋጅ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 ሆኖ በ3 ተቃውሞ በአራት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡#ሪፖርተር

@tikvahethiopia


Forward from: TIKVAH-ETHIOPIA


Forward from: Ethiopian Legal insight
ኢትዮጵያን ሌጋልቴክ ሶፍትዌር የተገነባው የጉዳዮች አስተዳደርን፣ የሰነድ ዲጂታላይዜሽን እና የደንበኛ ግንኙነትን ለማስተናገድ ነው፣ ስለዚህ ጠበቆች ጉዳዮችን በማሸነፍ እና ተግባራቸውን በማሳደግ ላይ እንዲያተኩሩ ማገዝ ፍላጎታችን ነው
በኢትዮጵያ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ዲጅታል የሕግ ላይብራሪና ኬዝ ማኔጅመንት ሲስተም ለሁሉም የሕግ ባለሙያዎች ፣ ለሕግ ተማሪዎች ፣ ለነጋዴዎችና ለቢዝነስ ተቋማት ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።
www.ethiopianlegaltech.com በሚለው አዲሱ አድራሻ መግባትና መመዝገብ ትችላላችሁ
#share #lawyer #legalsupport #legaladvice
#ethiopianlaw #legalcounsel #legalhelp
#ህግ #የህግምክር #የኢትዮጵያ

ፈር ቀዳጅ የሆነውን ይህን ዲጂታል የሕግ ሶፍትዌር እንዴት በተሟላ ሁኔታ መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳዩ የቪዲዮ ማሳያ ቱቶሪያሎች አዘጋጅተን በዩትዩብ ቻናላችን
አስቀምጠናል

ሊንኩ ከታች ይገኛል

https://youtube.com/@ethiopianlegaltech
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Ethiopianlegalinsight


ሰ.መ.ቁ 248877 ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ . ም- የወራሽነት ማስረጃ የወሰደ ሰው በሕግ በታወቀ ጋብቻ ውስጥ ወይም እንደ ባልና ሚስት ግንኙነት ወይም ከሁለቱ በአንዱ በሕግ በሚታወቅ ግንኙነት ውስጥ እንዳልተወለደ ከተረጋገጠ የሟች ልጅ እንደሆነ በመግለጽ ከአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሟች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ነው ተብሎ የተሰጠ ማስረጃ ጸንቶ ሊቀጥል የሚችለው ሟች ልጄ ነው በማለት የተቀበሉት ስለመሆኑ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 131 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሠረት እና በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 143 እና ተከታዮቹ መሠረት አባትነት በፍርድ ቤት ውሳኔ የሚታወቅባቸው ሁኔታዎች መኖራቸውን በመግለጽ በማስረጃ የተደገፈ ክርክር ሲቀርብ መሆኑን: ሰዎች የወራሽነት ማስረጃ የሚወስዱት መብት ለማቋቋም በማሰብ እንደመሆኑ ይህን ማስረጃ በመጠቀም በሚደረግ ተግባራት የሶስተኛ ወገኖች መብቶች ሊነካ የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ከግምት በማስገባት ማስረጃውን የሚሰጠው ፍርድ ቤትም የወራሽነት ማስረጃ ሲሰጥ ጠያቂዎቹ ከሟች ጋር አለን የሚሉትን ግንኙነት በተገቢው ማስረጃ እንዲያረጋግጡ ማድረግ እንደሚኖርበት: በዚሕ አግባብ ተረጋግጦ የተሰጠ የወራሽነት ማስረጃ መሆኑን ማስረጃው የተሰጠው ሰው ባላስረዳበት ሁኔታ ማስረጃውን በመቃወም ክስ ያቀረበ ሰዉ ክስ የማቅረብ መብቱ በይርጋ የታገደ ነው የመካድ ክስ እንዲያቀርብም ሊፈቀድለት አይገባም በሚል የሚሰጥ ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት መሆኑን በመግለጽ አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡


የመንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ.pdf
744.5Kb
የፌዴራል መንግሥት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ ፀደ
*
**

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል የመንግሥት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል፡፡

በዚህም መሰረት የፌዴራል መንግሥት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ተሻሽሎ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1353/2017 በምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

The final Draft 👆👆👆

20 last posts shown.