"ዜጎች የሕጎች ሁሉ የበላይ ለሆነው ህገ መንግስት ተገዢ ሊሆኑ ይገባል"
--- አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ---
(ዜና ፓርላማ) መጋቢት 26 ቀን፣ 2017 ዓ.ም፣ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ዜጎች የህጎች ሁሉ የበላይ ለሆነው ህገ መንግስት ተገዢ ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የተከበሩ አፈ ጉባዔ "ህገ መንግስትና ህገ መንግስታዊነት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ የተጀመረው ሶስተኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም የውይይት መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ዜጎች የህጎች ሁሉ የበላይ ለሆነው ህገ መንግስት ተገዢ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።
ህገ መንግስት የመንግስትንና የህዝብን ግንኙነት የአስተዳደር ስርአት የሚደነግግ ሰነድ መሆኑንም ተናግረዋል ።
ሀገሪቱ የምትመራባቸው ፖሊሲዎችና ሌሎች ህጎች የሚመነጩት ከህገ መንግስት መሆኑን የተከበሩ አፈ ጉባዔ አንስተው ፤ ተቋማት የሚገነቡት የህገ መንግስቱን ድንጋጌ መሠረት በማድረግ መሆኑንም ገልጸዋል ።
የህግ አውጪው፣ህግ አስፈጻሚው እና የህግ ተርጓሚው ስልጣንና ተግባር የስራ ግንኙነት ህገመንግስቱን መሰረት ያደረገ መሆኑንም የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በመክፈቻ ንግግራቸው አንስተዋል።
በህገ መንግስቱ አንቀጽ 9 ላይ ተቋማትና ዜጎች ህገ መንግስቱን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነት እንዳለባቸው የሚደነግግ መሆኑንም ገልጸዋል ።
ህገመንግስቱ የሚሻሻልበት ስርአት ስለመኖሩም በአንቀጽ 105 ላይ የተደነገገ መሆኑን ጠቁመዋል ።
በውይይት መድረኩ ሶስት የመወያያ ጽሑፎች ህገ መንግስት፣ ህገ መንግስታዊነት፣ የህገ መንግስት ታሪክ በኢትዮጵያ ፣ የህገ መንግስት ቅቡልነትና ተግዳሮቶች በኢትዮጵያ እና የህገ መንግስት ሪፎርምና ሀገራዊ መግባባትን በተመለከተ በዘርፉ ባለሙያዎች እየቀረበ ነው ።
ዜና ፓርላማ እንደ ዘገበ!
Paralama News wabeeffannee!
Oduu parlama hordofuufis👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/LawStudentsUnionhttps://t.me/LawStudentsUnionhttps://t.me/LawStudentsUnionhttps://t.me/LawStudentsUnionhttps://t.me/LawStudentsUnion