አሜሪካዊቷ የጠፋባትን መልዕክት ስትፈልግ የ3 የሚሊዮን ዶላር ሎተሪ ማሸነፏን አወቀችየማይፈለጉ ኢሜይሎች መካከል የጠፋባትን ሌላ መልክት በመፈለግ ላይ ሳለች ነበር ላውራ የሦስት ሚሊዮን ዶላር ዕጣ የያዘ ሎተሪ ማሸነፏን የሚያበስረውን መልዕክት ያገኘችው።የ55 ዓመቷ ላውራ ስፓርስ በመንግሥት የሚዘጋጀው ይህ የእድል ጨዋታ ዕጣ ወደ መቶ ሚሊዮኖች ከፍ ማለቱን ከተመለከተች በኋላ ነበር በኢንተርኔት ላይ እድሏን ለመሞከር ሎተሪውን የገዛችው።
"ሎተሪውን ከገዛሁ ከጥቂት ቀናት በኋላ ከአንድ ሰው ተልኮልኝ የነበረ ኢሜይል እየፈለግኩ ነበር። በማይፈለጉ የኢሜይል ፎልደር ውስጥ አፍጥጬ ነበር" ስትል ላውራ ለሎተሪ ባለሥልጣናት ተናግራለች።
"ከዚያም ይህንን ሽልማት ማሸነፌን የሚገልጽ ኢሜይል ተመለከትኩ" ስትልም አክላለች።
"ያነበብኩትን ማመን ስላልቻልኩ በኢሜል የተላከልኝን ለማረጋገጥ ወደ ሎተሪ አካውንቴ ገብቼ ለማመሳከር ሞክሬአለሁ። አስደንጋጭ ነበር" ስትል ገልጻለች።
ከእድሜዋ ቀደም ብላ ጡረታ ለመውጣት ማሰቧን እና ለወደፊቱም ኢሜሎቿን በቅርበት ለመከታተል ማቀዷን በቀልድ አዋዝታ ተናግራለች።
"ምን አልባት የሌላ ትልቅ ሽልማት ባለዕጣ ከሆንኩ በሚል የሚቺጋን ሎተሪን ቅድሚያ የምሰጣቸው ኢሜይሎች ዝርዝር ውስጥ አስገብቼዋለሁ" ብላለች።
በአሜሪካ ከፍተኛው የሎተሪ እድል የተያዘው እ.ኤ.አ. በ 2018 በደቡብ ካሮላይና አንድ አሸናፊ በ1.6 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ሎተሪውን ይዞ ወደ ቤቱ መሄዱን ተክትሎ ነው
https://t.me/lottery_service01#national_lottery #ethiopian_national_lottery #lottery_service #admas_digital_lottery #admas_lottery #የኢትዮጵያ_ብሄራዊ_ሎተሪ #የብሄራዊ_ሎተሪ_አገልግሎት #ሎተሪ_አገልግሎት #አድማስ_ሎተሪ #ዲጂታል_ሎተሪ #ሎተሪ