ሃምሳ አለቃ ሀብታሙ አስራት በ29ኛው ዙር የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ በ4ኛው ዕጣ የ 700ሺህ ብር ቼካቸውን ተረከቡ ፡፡ ሃምሳ አለቃ ሀብታሙ በጅግጅጋ ነዋሪ ሲሆኑ ከመደበኛ ስራቸውም በተጓዳይ የዲጂታል ሎተሪ የመሞከር የቆየ ልምድ አላቸው ፡፡ መቸም ዘወትር ሎተሪን የሞከረ ከዕድል ጋር ተማከረ እንዲሉ በ4ኛው ዕጣ የ700 ሺ ብር ዕድለኛ ሆነዋል ፡፡ በደረሳቸውም ገንዘብ ላይ በመጨመር ቤት የመግዛት ዕቅድ እንዳላቸው ገልጸውልናል ፡፡