ማኅበረ መድኀኔዓለም መዝሙር ጥናት


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


✝️ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮን ስርዓትን የጠበቁ መዝሙሮች እና ግጥሞችን ከነዜማቸው እንለቃለን ✝️
🙏🙏🙏 (መዝሙር ጥናት) 🙏🙏🙏

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


" በፍልሰቴ ቀን አባቴ አባቴ የሚለኝ ሁሉ ይምጣ ያኔ እኔ ወዳጄ ሚካኤል እና ልጄ ፊሊጶስ አብረን መጥተን እንባርካለን "   

#ደብረሊባኖስ_አብነ_ተክለ_ሃይማኖት

መንፈሳዊ የንግስ ጉዞ ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም

መነሻ ቀን እሁድ ግንቦት 11
መመለሻ ቀን በ 12 ከንግስ በኃላ


❗️ውስን ቦታ ስላለን ቀድመው ቦታ ያሲዙ

CBE : 1000353773187

❗️ክርስቲያናዊ አለባበስ እንዳይለዮት

☎️
0966037164
0963004353


#ነበርኩ_መች_ያድናል

ሀጢያትን ስትሰራ አምላክን እረስተህ
ቅዱሱን ሰውነት በሀጢያት አርክሰህ
ትእዛዝን ሳትፈጽም መልካምን ሳትሰራ
ዘይት ሳታዘጋጅ መብራትህ ሳይበራ
በተጠራህ ጊዜ መልዐከ ሞት ሲመጣ
ለማያልፈው አለም ሲወጣልህ እጣ
ለሚዛን ስትቀርብ አገልጋይ ነበርኩኝ እያልክ መናገሩ
መዝሙር ዘምሬያለው ሄጃለው ከበሩ
ብሎ መከራከር ያኔ መች ይጠቅማል
ይዞ መገኘት ነው ነበርኩ መች ያድናል !!!

🙏🏼


✞ #የሚያዚያ_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

ሰኞ ሚያዝያ 7 - ቅዱስ እያቄም - እረፍቱ - በኮተቤ ሐና ማርያም ቤተክርስቲያን

ረቡዕ ሚያዚያ 9 - አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ  እረፍታቸው - በቤተል ሚካኤል ቤተክርስቲያን በቀበና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን - በወይራ ሰፈር ቅድስት አርሴማ ወአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን

ማክሰኞ ሚያዝያ 15 - መጥምቁ ዮሐንስ - አንገቱ ለ15 ዓመት ያስተማረችበት መታሰቢያ በዓል - በቤላ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን

እሁድ ሚያዝያ 20 - በለቡ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን

ማክሰኞ ሚያዝያ 22 - ቅዱስ ዑራኤል - ቅዳሴ ቤት ጎፋ መብራት ሀይል

ረቡዕ ሚያዝያ 23 - ቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ እረፍቱ

እሁድ ሚያዝያ 27 - ቸሩ መድኃኔዓለም በ 6 ኪሎ ምስካየ ኃዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ብቻ

ረቡዕ ሚያዝያ 30 - ቅዱስ ማርቆስ - በዓለ እረፍቱ -በ6 ኪሎ ቅዱስ ማርቆስ

🚨!!! ማሳሰቢያ !!!🚨

ሚያዝያ 22 እና ሚያዝያ 23 ሕማማት
ላይ ስለዋለ ለሌላ ጊዜ ተላለፏል።
ሚያዝያ 27 ደግሞ ትንሣኤ ስለሆነ
በጌታ በዓል ላይ ሌላ በዓል አይከበርም
እና እሱም ለሌላ ጊዜ ተላለፏል።

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


ድንቅ አድርጎልኛል

ድንቅ አድርጎልኛል የሠራዊት ጌታ (2)
አልረሳኝም አምላክ አነሳኝ ከትቢያ (2)

ድንቅ አድርጎልኛል በደሌን ሳይቆጥር
ድንቅ አድርጎልኛል ወደቤቱ ጠራኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ረክሼ ሳለሁ
ድንቅ አድርጎልኛል ልጄ ሆይ ና አለኝ
ድንቅ አድርጎልኛል በዳግም ምፅዓቱ
ድንቅ አድርጎልኛል መንግስቱን ሊያወርሰኝ

ድንቅ አድርጎልኛል ከአንበሳ መንጋጋ
ድንቅ አድርጎልኛል ከጉድጓድ አወጣኝ
ድንቅ አድርጎልኛል በጠላቶቼ ፊት
ድንቅ አድርጎልኛል ግርማ ሞገስ ሰጠኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ምን እመልሳለሁ
ድንቅ አድርጎልኛል እንዲ ለወደደኝ

ድንቅ አድርጎልኛል ጠላቶቼ ሁሉ
ድንቅ አድርጎልኛል ሲጓደዱብኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ማን ይደርስለታል
ድንቅ አድርጎልኛል እያሉ ሲሉኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ፈጥነህ ደረስክልኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ከሞት አዳንከኝ


@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
።።።🙏🙏🙏።።


እንኳን ደስ አለን ደስ አላችሁ
ወንጌላዊው ፍቁረ እግዚእ ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በደብራችን በደብረ መድኀኒት መድኀኔዓለም ቤ/ክ ፅላታቸው ገብቷል እንኳን ደስ አላችሁ 🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼

ዘወትር በ 4 ቅዱስ ዮሐንስ
ዘወትር በ 13 ቅዱስ ሩፋኤል ይታሰባሉ


አልተወኝም ጌታ ለካስ ይወደኛል /2/
ዛሬም ስበድለዉ ልጄ ነህ ይለኛል
ዛሬም ስበድለዉ ልጄ ነሽ ይለኛል

አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥

በበደል ጉራንጉር በኃጢአት ጫካ
ብጠፋበት እንኳን አልተወኝም ለካ
/ ዛሬም ልጄ ብሎ ዳግም ይጠራኛል
ለካስ አልጠላኝም ጌታ ይወደኛል / 2

አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥

ለሥልጣን ለክብር ብዬ ስክደዉ
ለገንዘብ አድልቼ እኔ ስረሳዉ
ለእኔ ያለዉ ፍቅር አልቀነሰብኝም
ዛሬም ይወደኛል ጌታ አልጠላኝም
ለእኔ ያለዉ ፍቅር አልቀነሰብኝም
ዛሬም ይወደኛል ጌታ አልተወኝም

አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥

ታዲያ ለዚህ ፍቅሩ ለሌለዉ ወሰን
ከጭንጫ መቃብር ላወጣኝ እኔን
/ በሕይወቴ ሁሉ ፍጹም ለመራኝ
ክብርና ምስጋና አቀርባለሁኝ / 2

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


#ሰው_ለሰው

ሰው ለሰው/2/ ቢፋቀር ምነው /2/

ለሰው ይመስለዋል ብዙ የሚቆይ
ግን በድንገት ያልፋል ሁሉንም/2/ ሳያይ
ሀብትን ያከማቻል ቀኑን ሳያውቀው
በድንገት ሲጠራ/2/ ላይከተለው

#አዝ

የሰው ልጅ በተራው መጠራቱ ላይቀር
ምነው አንዱ ለአንዱ መቃብር/2/ ባይቆፍር
አይጠቅምም መጨነቅ እንዲያው ለውበት
ይረግፋል ይጠፋል ሁሉም/2/ ከመሬት

#አዝ

ዋ! ቁንጅና ከንቱ ማማርም ብላሽ
አፈር ትቢያ ሲሆን ሲጨለም/2/ ሲመሽ
ደሀ ባለጸጋ አንድ ነው መንገዱ
በጨርቅ ተገንዞ በሳጥን/2/ መሄዱ

#አዝ

ሰው ዙሪያውን ቢያጥር መዝጊውን ቢሠራ
በሕንፃ ላይ ሕንፃ ቢያስመስል ተራራ
አይቀርም መሄዱ ሁሉም/2/ በየተራ

ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


#ዛሬስ_ተይዣለሁ

ዛሬስ ተይዣለሁ በፍቅርህ ስጦታ
ውለታህ ማርኮኛል የሠራዊት ጌታ
ከአመድ ያነሳኸኝ በትቢያ ተጥዬ
ውለታህ ከበደኝ ማረከኝ ጌታዬ
ማረከኝ ጌታዬ


ያልሰጠኸኝ ነገር በዚህ ምድር የለም
ፍቅርህ ወሰን የለው ድንቅ ነው ዘላለም
እኔነቴን ሳስብ ምንድን ነኝ እላለሁ
ፍቅርህን ሳስተውል ሁልጊዜ አለቅሳለሁ
ሁልጊዜ አለቅሳለሁ

አዝ

ለብቻዬ ሆኜ አምላኬን ሳስበው
ከሕሊና በላይ ውለታህ ብዙ ነው
የተጣለውን ሰው ማንሳት ያውቅበታል
ምስኪንን ሲያጽናና ከሁሉም ይበልጣል
ከሁሉም ይበልጣል

አዝ

ሰው ነህ ተብያለሁ አንተ ሰው ስላልከኝ
ማን ያስታውሰኛል አንተ ባታከብረኝ
አትጣለኝ አንተ ሁሉም ያከብረኛል
ሐጢአቴን ባትቆጥር ለእኔ ይበቃኛል
ለእኔ ይበቃኛል


🌺ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ🌺


@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


 ወንበዴ ነበርኩኝ



ወንበዴ ነበርኩኝ ሀገር ያስለቸው 
በመስቀል ላይ ሆኖ ታሪኬን ለወጠው 
አስበኝ ስላልኩት በኋላ ስትመጣ 
ገነትን ለማየት የመጀመሪያው ሰው ሆነኩኝ ባለእጣ
 
አቤት ፍቅሩ የእግዚእሔር/2/ 

       ግሩም ፍቅሩ ›› ›› 
        ኃያል ፍቅሩ ›› ›› 
        ግሩም ፍቅሩ ›› ›› 
አስበኝ ስላልኩት አሰበኝ ጌታዬ 
ወንበዴ ነበርኩኝ ስርቆት ነው ሙያዬ 
በመስቀል ላይ ሆኖ ሕዝቡን ያስብ ነበር 
እኔስ አላየሁም /2/ እንዲህ ያለ ፍቅር 

አልታይም ብዬ ኃጢአትን ስሠራ 
ተመለስ ይለኛል ስሜን እየጠራ 
እንዳልሞትበት ነው በኃጢአት ታስሬ 
ፍቀሩን አልዘልቀውም/2/ እንደዚህ ዘርዝሬ 

መከራ ሲከበኝ መጥቶ ያጽናናኛል 
በሐዘኔ ጊዜ እግዚአብሔርም ያዝናል 
ዓይኑ ከእኔ አይርቅም ጥበቃው አይጠፋም 
ስሙን እጠራለሁ/2/ በጌታዬ አላፍርም 

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyale
m
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏


✞ #የመጋቢት_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

እሁድ መጋቢት 1 - ቤተል ማርያም - ህንፃ ቤተክርስቲያን ምርቃት

አድራሻ ቤተል አደባባይ ወረድ ብሎ በግ ተራው አካባቢ

ሐሙስ መጋቢት 5 አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ - ዕረፍታቸው

ቅዳሜ  7 ቅድስት ሥላሴ  - ቤተክርስቲያኑ የተመሰረተበት(ጠሮ ሥላሴ)

ማክሰኞ 10 መስቀለ ኢየሱስ - በቀጨኔ መድኃኔዓለም በዕንቁ ልደታ በዘነበ ወርቅ አቡነ አረጋዊ በማንጎ ገብርኤል

አርብ 27 ቸሩ መድኃኔዓለም - ጥንተ ስቅለት

እሁድ  29 የኢየሱስ ክርስቶስ ፅንሰት -በ4 ኪሎ በዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን እና እኩለ ፆም ደብረዘይት በገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመካኒሳ አቦ በቃሉ አቡነ ሀብተማርያም

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


✞ #የየካቲት_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

አርብ የካቲት 1 - ቶታል ፈለገ ህይወት ቅድስት ኪዳነምህረት እና መድኃኔአለም ቤ/ክ - ቅዳሴ ቤት

አርብ የካቲት 8 - በዓለ ስምዖን አምላካችን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበት መታሰቢያ በዓል - በቦሌ ቡልቡላ አባ ሳሙኤል ቤተክርስቲያን

ቅዳሜ የካቲት 9 እና 10 - ለቡ መርጦ ለአርሴማ - ምርቃቷ

-ካዛንቺስ ቅዱስ ዑራኤል - ህንፃ ቤተክርስቲያን ምርቃቱ

ሰኞ የካቲት 11 - አቡነ ሐራ ድንግል - በጣፎ

ማክሰኞ የካቲት 12 - ቅዱስ ሚካኤል - ቅዳሴ ቤት በ 6 ኪሎ ማርቆስ ቤተክርስቲያን (አካፋው ሚካኤል)

ቅዳሜ የካቲት 16 - ቅድስት ኪዳነምህረት የምህረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት

ረቡዕ የካቲት 20 - ቅዱስ ፊልጶስ - ቅዳሴ ቤት- አጠና ተራ

ቅዳሜ የካቲት 23 - ቅዱስ ጊዮርጊስ በአደዋ ጊዜ  የተራዳበትን ምክንያት በማረግ በገነተ ፅጌ (ፒያሳ)

አርብ የካቲት 29 - ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ - እረፍቷ - በአንቆርጫ መድኃኔዓለም ፈረንሳይ ጉራራን አልፎ

ቅዳሜ የካቲት 30 ቅዱስ ዮሀንስ - አንገቱ በሸክላ ዕቃ የተገኘችበት መታሰቢያ በዓል - በቀርሳ ሚካኤል ወ ቅዱስ ዮሀንስ ቤተክርስቲያን ከኮተቤ መምህራን ኮሌጅ አለፍ ብሎ አዋሽ ጋር እዛው ቀርሳ ሚካኤል (ዮሐንስ ) የሚሄድ ታክሲ አለ

ቅዳሜ የካቲት 30 እና መጋቢት 1 - ቤተል ማርያም - ህንፃ ቤተክርስቲያን ምርቃት

አድራሻ ቤተል አደባባይ ወረድ ብሎ በግ ተራው አካባቢ

✞ መምጣት የማትችሉ #Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ✞


@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


UPDATED ⁉️


በሰርጋችን እለት

በሰርጋችን እለት እንድትባርከን
ጌታ ጠርተንሃል በእምነት ሆነን
ከእናትህ ጋራ ከእመቤታችን
ከመላእክትህ ጋር ና በሰርጋችን
ከሐዋርያት ጋር ና በሰርጋችን
ከወዳጆችህ ጋር ና በሰርጋችን

በገሊላ መንደር እንደተገኘህ
ና በእኛ ድንኳን ጌታ ስንጠራህ
የጥሪ ወረቀት ልከናል እንዳትቀር
አንተነህ ክብራችን የቤታችን ፍቅር

ነይ ከልጅሽ ጋራ እመቤታችን
እንድታሟይልን የጎደለውን
ንገሪው ለልጅሽ ባዶው እንዲሞላ
በረከት የእርሱ ነው ቤታችንን ይሙላ

በጎደለው ሁሉ እየጨመርሽልን
ቤታችንን ሁሉ ሙይው እናታችን
ለአገልጋዮቹ ድንግል ንግሪያቸው
ጠርተን እንዳናፍር ጋኖቹን ይሙላቸው

==================

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


ተፈሥሒ ቤተክርስቲያን

ተፈሥሒ ቤተክርስቲያን ተፈሥሒ ቤተ ሥላሴ
ያሳደግሻቸው ልጆችሽ አብርሃም ሣራን ሲሆኑልሽ
ያሳደግሻቸው ሙሽሮችሽ አብርሃም ሣራን ሲሆኑልሽ

ትምህርትሽ ገብቶአቸው የወንጌሉ ቃል
በኑሮ ሊያበሩ ይኸው ወጥተዋል
በክርስቶስ ትምህርት በቃሉ ተመርተው
ለዓለም መሰከሩ ተራራ ላይ ቆመው
ተፈሥሒ

ከእንቅቡ በታች አይደለም መብራቱ
በራ እንጂ ለሁሉ ከእነበረከቱ
ጢስ የሌለው ሻማ ደምቀው የከበሩ
ልጆችሽ ሙሽሮች እንደጧፍ አበሩ ተፈሰሒ

ሰላም ላንቺ ይሁን ደስ ይበልሽ በጣም
የዘራሽው ማሳ ፍሬውን ሲሸከም
ካባ ደረብሽለት ለወንዱ ሙሽራ
አክሊል ደፋሽለት ከምርቃት ጋራ
ተፈሰሒ

ቃልሽ ይለውጣል ግሩም ነው ኃያል
አመንዝራዎቹን ድንግል ያደርጋል
ተገለጠ ክብርሽ በሙሽሮች ዛሬ
መከር ሆኖልሻል ባፈራሽው ፍሬ
ተፈሥሒ

ሰላም ላንቺ ይሁን ደስ ይበልሸ በጣም
የዘራሽው ማሳ ፍሬውን ሲሸከም
ካባ ደረብሽላት ለውዷ ሙሽራ
አክሊል ደፋሽላት ከምርቃት ጋራ
ተፈሥሒ


=================
የሰርግ መዝሙሮች
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


#የክብሯ_መግለጫ


የክብሯ መግለጫ የድንግልናዋ/2/
ይኸው ዛሬ ታየ በተክሊሉ ደምቃ
ይኸው ዛሬ ታየ ካባዋን ደርባ

የክብሯ መግለጫ ከሆኑት ነገሮች
የክብሯ መግለጫ ቅዱስ ጋብቻ ነው
የክብሯ መግለጫ ክብሯን መጠበቋ
የክብሯ መግለጫ ከወንድ መራቋ
የክብሯ መግለጫ አክሊል ተጭኖላት
የክብሯ መግለጫ የድንግልናዋ
የክብሯ መግለጫ ኮራን በልጃችን
የክብሯ መግለጫ በአዲሷ ሙሽራ

የክብሯ መግለጫ ከእናት ከአባቷ ቤት
የክብሯ መግለጫ አሸብቃ ወጣች
የክብሯ መግለጫ ረዳት ልትሆነው
የክብሯ መግለጫ ወደ ባሏ ሔደች
የክብሯ መግለጫ ዛሬስ በዓይናችን
የክብሯ መግለጫ ሁላችን አየነው
የክብሯ መግለጫ ቀድሞም መኩራታችን
የክብሯ መግለጫ ይህንን አውቀን ነው

የክብሯ መግለጫ በስርዓት ማደጓን
የክብሯ መግለጫ ዓለም መሰከረ
የክብሯ መግለጫ አለል ዘለል ሳትል
የክብሯ መግለጫ መኖሯ ታወቀ
የክብሯ መግለጫ እንግዲ ሙሽራው
የክብሯ መግለጫ ኩራ ደስ ይበልህ
የክብሯ መግለጫ ደግ ጨዋ መርጦ
የክብሯ መግለጫ እግዚአብሔር አደለህ

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem


እመቤታችን በአንቺ ምልጃ (በማየ ቃና)

እመቤታችን በአንቺ ምልጃ (2)
ድንግል ማርያም በአንቺ ምልጃ (2)
መድኃኔዓለም ተአምር ሠራ በማየ ቃና(2)

ለጌታችን ተአምር >>> በማየ ቃና
ተመርጣ ታድላ >>> በማየ ቃና
መጀመሪያ ኾነች >>> በማየ ቃና
ቃና ዘገሊላ >>> በማየ ቃና

ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

አዝ ---------------

ታውቋት ስላለችው >>> በማየ ቃና
ወይንኬ አልቦሙ >>> በማየ ቃና
ውኃ ወይን ሲሆን >>> በማየ ቃና
ኹሉ ዓዩ ሰሙ >>> በማየ ቃና

ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

አዝ -------------

አሳላፊዎቹ >>> በማየ ቃና
ግራ ቢገባቸው >>> በማየ ቃና
የድንግል ማርያም ልጅ >>> በማየ ቃና
ከጭንቅ አወጣቸው >>> በማየ ቃና

ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ

አዝ --------------

እኛም እናምናለን >>> በማየ ቃና
በርሷ ትንብልና >>> በማየ ቃና
ስለ ቃልኪዳኗ >>> በማየ ቃና
ሁሉ እንደሚቃና >>> በማየ ቃና

ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ስፍራ
የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ


መዝሙር: ቀሲስ እስክንድር ወ/ማርያም
=================


ሰኞ ጥር 27 - ቸሩ መድኃኔዓለም - ቅዳሴ ቤት - በአለምባንክ ጀሞ ተራራ መድኃኔዓለም

አድራሻ : ከአለምባንክ የሻቦ ባጃጅ ይዞ መጨረሻ ላይ ወርዶ ከልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን ትንሽ ከፍ ብሎ ይገኛል ።

ታዲያ ለቤተክርስቲያኑ የሚሆን ጧፍ ምፅዎት አስራት በኩራት ሌላም የቻላቹትን በመያዝ እንድትሄዱ ።

🙏🏼🙏🏼🙏🏼
#Share
#Share


#ሞትሰ
ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ
ሞታ ለማርያም/2/ የአፅብ ለኩሉ
#ትርጉም
ሞት ለሚሞት ይገባል
የማርያም ሞት ግን /2/ ከሁሉ ይደንቃል


@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
።።።🙏🙏🙏።።


ማን ያድነኛል እያልኩኝ አማኑኤል መቶ ፈወሰኝ/፪/
ማን ያድነኛል እያልኩኝ አማኑኤል መቶ ፈወሰኝ/፪/
አማኑኤል መቶ ፈወሰኝ/፪/

ምህረት ይዛለች በቀኝ እጇ ኪዳነምህረት ለወዳጇ/፪/
ምህረት ይዛለች በቀኝ እጇ ኪዳነምህረት ለወዳጇ/፪/
ኪዳነምህረት ለወዳጇ/፪/

ለያዕቆብ ነገድ ለእስራኤል ጠባቂያቸው ነው ሚካኤል/፪/
ለያዕቆብ ነገድ ለእስራኤል ጠባቂያቸው ነው ሚካኤል/፪/
ጠባቂያቸው ነው ሚካኤል/፪/

ከእሳት ያወጣል ከነደደው ቅዱስ ገብርኤል ለወደደው/፪/
ከእሳት ያወጣል ከነደደው ቅዱስ ገብርኤል ለወደደው/፪/
መላኩ ገብርኤል ለወደደው/፪/

ተክለሃይማኖት ፀሀይ ነፍሴን አደራ በሰማይ/፪/
ተክለሃይማኖት ፀሀይ ነፍሴን አደራ በሰማይ/፪/
ነፍሴን አደራ በሰማይ/፪/

አቡነ ሀብተማርያም ፀሀይ ነፍሴን አደራ በሰማይ/፪/
አቡነ ሀብተማርያም ፀሀይ ነፍሴን አደራ በሰማይ/፪/
ነፍሴን አደራ በሰማይ/፪/


✞ ምስክርነቱን ገለፀ ✞

ምስክርነቱን ገለጸ ቂርቆስ ህጻን/2/
በእሳት ተፈትኖ አለፈ ፈተናውን
በእሳት ተፈትኖ አለፈ ኧኸ
ፈተናውን ደስ ይበለን
      
ቂርቆስ ኢየሉጣ ሁለቱም
በአንድ ልብ ምንኛ ጨከኑ/2/
ተቃቅፈው ሲገቡ ወደ እሳት ጋኑ/2/

      /አዝ * * * * *

ህጻኑና እናቱ በእሳት ውስጥ
ሲዋኙ ያለ ምንም ፍርሃት /2/
ገብርኤል ተላከ እነርሱን ለማውጣት/2/

      /አዝ * * * * *

በርዶ እና አቀዝቅዞ የእሳቱ
ነበልባል በጌታችን መስቀል
ሁሉቱም ስማዕታት ተጎናጸፉ ድል /2/

@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
@mahberemedhaniyalem
         ።።።🙏🙏🙏።።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ይሄን አረኩ ብለህ የምትመካ ወጣት አትመካ መዳን በቅዱስ ስጋው እና በክቡር ደሙ ነው ። በምድር ምን ሰራክ ሲባል ዘመርኩ, ምንጣፍ አነጠፍኩ አደባባይ አሳመርኩ መልስ አይሆንም ።

ማስተዋልን ያድለን🙏🏼

20 last posts shown.