“የገና ስጦታ ለየኔታ” በሚል መሪ ቃል ከኅዳር ፲፭ እስከ ታኅሣሥ ፴ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያና የስጦታ ዘመቻ በመካሄድ ላይ እንደሆነ ተገለጸ::
የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ወልደ እግዚአብሔር ፍጹም ሰው ሆኖ ዓለሙን ለማዳን መምጣቱን አሕዛብ ዓይተው ያመኑበት ዕለት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሰብአሰገል ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤ እጅ መንሻ ያቀረቡት በዚህ ታላቅ ዕለት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ምእመናን በጾመ ነቢያት “የገና ስጦታ ለየኔታ” በሚል ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶችን ይደግፉ ዘንድ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ተሰናድቷል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን በገዳማት እና በአብነት ትምህርት ቤቶች ላይ የሚያከናውናቸውን ፕሮጀክቶች ለማጠናከር “የገና ስጦታ ለየኔታ” በሚል መሪ ቃል ከኅዳር ፲፭ እስከ ታኅሣሥ ፴ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ድረስ የሚቆይ መርሐ ግብር እያካሄደ እንደሆነ ማስተባበሪያው ቀደም ሲል ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
የስጦታ መርሐ ግብሩም ከ፳፻፲፬ ዓ.ም ጀምሮ እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን የ፳፻፲፯ ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል “ስጦታዬን ለእራሴ” ሳይሉ ሁለ ነገራቸውን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰጥተው ለሚያገለግሉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና ገዳማውያን እንድናበርክት ማስተባበሪያው ጥሪ ያስተላልፋል፡፡
ማኅበሩ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር የሚኖሩ ምእመናንን በማስተባበር በገዳማትና በአብነት ትምህርት ቤቶች ላይ ከመቶ ስልሳ አምስት በላይ ፕሮጀክቶችን መተግበር እንደቻለና በዚህም በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን ማፍራት እንዲሁም ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች እንዲጠናከሩ ማድረጉ ይታወቃል።