🧁ማራኪ ምግብ አሰራር🍔


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


Do you want to cook something different today ? Or do you want to give a spicy twist to your daily boring recipes? Then you are at right place .Enjoy our channel and learn the art of cooking foods and recipes.
Admin: 👉[ @leulprince ]
አጣጥሙት


Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


ልብሶችን በታላቅ ቅናሽ የምያገኙበት ምርጥ የቲክቶክ ቻናል ይቀላቀሉ ሼር ያድርጉ
👇👇👇👇👇👇

https://vm.tiktok.com/ZML7jXCFX


​​የአታክልት ኦሜሌት
vegetable omelet
አስፈላጊ ግብአቶች እና መጠናቸው
• 1 ½ ኩባያ ጥቅል ጎመን
• 1 ½ ኩባያ ብሮኮሊ
• ½ ሽንኩርት
• 1 ቲማቲም (12 ቼሪ ቲማቲም)
• 2 ትንሽ ቃርያ
• 2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
• ½ ማንኪያ እርድ
• ½ ማንኪያ የኩመን ዱቄት
• ½ ማንኪያ ነጭ ሽንኩርት ዱቄት -
• ¼ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
• ¼ ማንኪያ ጨው
• 5 እንቁላል
አዘገጃጀት
• -በመጀመሪያ እትክልቶቹን በሙሉ በትንንሽ መክተፍ
• -ዘይቱን የሞቀ መጥበሻ ላይ ጨምሮ ሽንኩርቱን መጨመርና ትንሽ ማቁላላት
• -ቲማቲሙን ጨምሮ መጥበስ (ለ 1 ደቂቃ ማብሰል)
• -ጥቅል ጎመኑን ጨምሮ መጥበስ (ለ 3 ደቂቃ ማብሰል)
• -ሁሉንም ቅመሞች መጨመር (ጨው ሲቀር)
• -ለ ትንሽ ደቂቃ መጥበስ ( 1 -2 ደቂቃ ማብሰል)
• -ብሮኮሊውን መጨመር ( 1 ደቂቃ ማብሰል)
• ጨውንና ቃርያውን ጨምሮ እሳቱን ማጥፋት
• እንቁላሎቹን ሰብሮ ትንሽ ጨውና ቁንዶ በርበሬ መጨመር
• -የማይዝ መጥበሻ ላይ (non-stick pan) ትንሽ ዘይት እድርጎ ማሞቅ
• -መጥበሻው በደንብ ከጋለ በሁዎላ እንቁላሉን መጨመርና በመሃከለኛ እሳት ማብሰል
• -በማማሰያ ጥግ ጥጉን እየከፈቱ ያልበሰለውን እንቁላል ማዳረስ (እላዩ መጠጥ እስኪል)
• -የበሰለውን እትክልት የመጥበሻው ግማሽ ላይ መነስነስና የቀረውን ግማሽ እንቁላል እጥፎ አትክልቱን ማልበስና ከእሳት ላይ ማውጣት
• -መጥበሻውን ከድኖ ለ 2 ደቂቃ በእንፋሎቱ ማብስል


#ብጉርን_ከፊትዎ_ለማጥፋት_ይህን_ይጠቀሙ

♻️እርድ

በህንድ ሀገር ቆዳን ለመንከባከብ እንዲሁም ብጉርን ለማከም እርድ ተመራጭ ነው። ከመጠን በላይ የሆነን ዘይት ከቆዳዎ ላይ ለማስወገድ ይረዳል በዚህም ምክንያት ብጉር እንዳይፈጠር ይከላከላል። ከማር ጋር አዋህደው ቢጠቀሙት ደሞ ይበልጥ ውጤታማ ይሆናል።

✳️አጠቃቀሙም

ግማሽ የሻይ ማንኪያ እርድ ከ 1 የሾርባ ማንኪያ ማር ጋር ይቀላቅሉ።ከዛም ፊትዎን መቀባት በመቀጠል ለአስር ደቂቃ በማቆየት በቀዝቃዛ ውሃ ይታጠቡ።

📌ብጉሩ እስኪጠፋ በሳምንት 2 ጊዜ ይህን ውህድ ይጠቀሙ።

Join @MARAKIRECIPES


​​የእንቁላል ትራሜዚኒ
Egg tramezzini

ግብዓቶች እና መጠናቸው፤

4 እንቁላል
8 የሾርባ ማንኪያ ማዬኔዝ፤
2 የሻይ ማንኪያ ፐርስሊን፤
8 ስላይስ ዳቦ፤
ጨውና ቁንዶበርበሬ፤


አዘገጃጀት


# እንቁላሉን ቀቅሎ መላጥ፤

# እንቁላሉን በጣም በደቃቁ
መክተፍ፤

# ጎድጓዳ ሰሀን ውስጥ እንቁላሉን ጨምሮ ፐርስሊን ጨውና

# ቁንዶበርበሬ ጨምሮ በደንብ ማደባለቅ፤

# ሁለት ስላይስ ዳቦ አዘጋጅቶ በሁለቱም በኩል ማዬኔዝ መቀባት፤

# የተከተፈውን እንቁላል በዳቦ በአንድ በኩል ላይ አስቀምጦ እንቁላሉን ማዳረስ፤

# ሁሉም ሳንዱች ተሰርቶ ካለቀ በኃላ እስከሚበላ ድረስ ዳቦው እንዳይደርቅ በጥቂቱ ረጠብ ያለ የኪችን ፎጣ ላይ ማስቀመጥ ይመረጣል፡፡

Join @MARAKIRECIPES


✍ #ንጹህ #ማር #በውሃ #በጥብጦ #በባዶ #ሆድ #መጠጣት #ያለው #አስገራሚ #ጥቅሞች

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥

⏩ #አዘገጃጀት ፡-

አንድ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሃ እና አንድ የሾርባ ማንኪያ ንጹህ ማር ማዘጋጀት። በመቀጠልም ማሩን ውሃው ውስጥ በመጨመር ሁለቱ ተዋህደው የሚያስገኙት የቀለም አይነት እስኪመጣ ድረስ በደንብ ማማሰል እና በአግባቡ መቀላቀል፤ በጣም ያልቀላ የቀለም አይነትእስኪያመጣ ድረስ። ከዛም ያዘጋጁትን የማር እና የውሃ ቅልቅል ምንም አይነት ምግብ ሳይቀምሱ በባዶ ሆድ ከቁርስ በፊት መጠጣት፥ ከቻሉም ይህን ውህድ ማታ ላይ ከእራት በፊት ቢደግሙት እና ቢጠጡት መልካም ነው።

⏩#ውህድ #በመጠጣት #ጥቅም ፡-

📌 ሳንባ ላይ የሚከማችን አክታ ያስወግዳል፤

📌 የጉሮሮ ቁስለትንና አደገኛ ጉንፋንን በመከላከል እና በማስወገድ

📌 የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅምን ያዳብራል፤

📌 የሆድ እቃ እና የውስጥ ቁስለትን
በማስወገድ ለበሽታ የሚያጋል

📌 ጥገኛ ህዋሳት እንዳይራቡ ያደርጋል፤

📌 የሆድ ድርቀትን በመከላከልና በማለስለስ ለተስተካከለ የሰውነት ሽግግር ይረዳል። ከዚህ መፀዳጃ አካባቢ የሚፈጠር ድርቀትንም መከላከል ያስችላል፤

📌 አጠቃላይ ሰውነትንና አንጀትን ንጹህ እና ፅዱ በማድረግ መርዘኛ ነገሮችን ከሰውነት ለማስወገድ ይረዳል፤ ፈንገስን ፣ ባክቴሪያን እና ቫይረስ በሰውነት ውስጥ እንዳይከሰትና እንዳይከማች ያደርጋል፤

📌 የሚከሰትን የሽንት አለመቆጣጠር ስርአትን ማስተካከልም የዚሁ ውህድ ሌላው ጠቀሜታ ነው።

📌 ማር የኩላሊትን የማጣራት ተግባር በእጅጉ በማገዝ እና ስራውን ቀልጣፋ በማድረግ የሚፈጠረውን የጤና ጠንቅ የማስወገድ አቅም አለው።

📌 ማራኪና ፅዱ የቆዳ ገጽታንም ያላብስዎታል።

Join @MARAKIRECIPES


Forward from: ISPOORTII
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ይፍጠኑ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ቅናሽ አድርገናል 5 in 1 Beauty Care Massager

ዋጋ 550ብር ብቻ

🚀ብጉር፣ ማዲያት ፣ ሽፍታ ፣ የፊት መጨማደድ ፣ ቶሎ የፊት ቆዳ መበ ላሸት የመሳሰሉትን በአጭ ር ጊ ዜ ማ ጥፍት የሚ ችል (በባትሪ የሚሰራ ማሳጅ)

*ለስላሳ እና ውብ ፊት ያላብሳል የደም ዝውውርን ውጤታማ በሆነ መንገድ ያሻሽሉ። ለአጠቃቀም ቀላል

📥 Inbox👉 @leulprince
📞ለማዘዝ +251910991744

🚚ያሉበት በነፃ እናደርሳለን🚚
🛍️ @MARAKIFASHION 🛍️
ሱቅ ጀሞ ሚካኤል ሚና ሞል 2ኛ ፎቅ


​​በምጣድ ላይ የሚሰራ ፓንኬክ
የሚያስፈልገን
1, 2 እንቁላል
2, 1 ሲኒ ከግማሽ ስኳር
3, 1/4 ወተት
4, 5 የሾርባ ማንኪያ ዱቄት
5, 2 የሾርባ ማንኪያ baking powder

አሰራሩ
1 እንቁላሉን እንመታለን
2 ስኳሩን እንመታለን
3 ወተቱን ጨምረን በደንብ እንመታዋለን
4 ዱቄቱን እና baking powderun ኣንድ ላይ እናዋህዳለን
5 ቫኔላ (የቀረፋ) ዱቄት ጨምረን ምጣዱን አግለን በዘይት አስሰን በጭልፋ እየጨለፉ መጋገር ።

Join @MARAKIRECIPES


ካሮት ካፕ ኬክ

• ግብዓቶች
• 3 ካሮት (የተፈቀፈቀ)
• 250 ግራም ፍርኖ ዱቄት /5 የቡና ስኒ/
• (1/2) ሩብ የሾርባ ማንኪያ ጨው
• 50 ግራም ዘቢብ (1 የቡና ስኒ)
• 2 የሾርባ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
• 100 ሚሊ ሊትር ዘይት (2 የቡና ስኒ)
• 150 ግራም ስኳር (3 የቡና ስኒ)
• 1 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ ቀረፋ
• 4 እንቁላል

• አሰራር
1. በቅድሚያ ኦቨኑን በ180°c ሴንቲ ግሬድ ማሞቅ፤
2. በትልቅ ጎድጓዳ ሰሀን ፍርኖ ዱቄት፣ ቤኪንግ ፓውደር፣ የተፈጨ ቀረፋ እና ጨው በደንብ ማደበላለቅ፤
3. በሌላ ጎድጓዳ ሰሀን ውስጥ እንቁላል እና ስኳሩን በደንብ መምታት፤
4. ዘይቱን እንቁላል ውስጥ ጨምሮ በደንብ መምታት፤
5. ሶስቱን ካሮት ልጦ በመፈቅፈቂያ በደቃቁ መፈቅፈቅ፤
6. የተመታውን እንቁላል የፍርኖ ዱቄት ውህድ ውስጥ መቀላቀል፤
7. ካሮትና ዘቢቡን ጨምሮ በደንብ ማደበላለቅ፤
8. የካፕ ኬክ መስሪያውን ዘይትና ዱቄት ቀብቶ በጭልፋ እኩል እየከፈሉ እያንዳንዱ የካፕ ኬክ ዕቃ ውስጥ መጨመር፤
9. ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ኦቨን ውስጥ ጨምሮ መጋገር፤
10. ከኦቨን ውስጥ አውጥቶ 30 ደቂቃ ያህል ማቀዝቀዝ።

JOIN @MARAKIRECIPES


​​የዶሮ አሩስቶ በድንች 🥔🍗

የሚያስፈልጉን ግብዓቶች
1ቲማቲም🍅
1 ሽንኩርት
1 ፍልፍል ሮሚ(የውጭ ቃሪያ)🌶
ይበቃል የምትሉት አቃል ድንች ልጣችሁ አጥባችሁ በክብ ቅርፅ ከትፎ ማዘጋጀት🥔
1 ዶሮ በደንብ የታጠበ ቆዳው ያልወጣ ማንሳትም ትችላላችሁ ግን ባታነሱት ምርጥ ነው 🍗
3 ማንኪያ እርጎ
ዘይት ዘይቱን (ዘይቱ)🍶
ዝንጅብል የተፈጨ ትንሽ
2 ማንኪያ የሚሆን የቲማቲም ሳልሳ(ማጅን ጥማጥም)
ለምግብ የምትጠቀሙት ማንኛውም ቅመም ቁንዶ በርበሬ(ፍልፍል አስወድ)፣ከሙን ፣የነጭ ሽንኩርት ፓውደር ፣ እርድ ፣ ጨው 🧂🥫
ሎሚ ካለ የሎሚ ጭማቂ ጨምሩ ከሌላቹ ደግሞ አንድ ማንኪያ አቼቾ (ኸል)🍋

አሰራር

በመጀመሪያ ዶሮውን በደንብ ካጠብን በኃላ ውሃውን በንፁህ ነገር ማድረቅ ወይም ጠፈፍ እስኪል ጠብቀን ያዘጋጀናቸውን ቅመሞች ፣ዘይት ፣ዝንጅብል ፣ቲማቲም ሳልሳ፣አቼቾ ሁሉንም በአንድ እቃ እናደርግ እና ማዘጋጀት
ከዛም ዶሮው እና ድንቹ ላይ አድርገን ማዋሀድ ከዛም ለ1-2 ሰዓት በፍሪጂ ማቆየት
የምንሰራበት እቃ ላይ ጊስቲር አድርገን ዘይት እንቀባና ሽንኩርት ፣ቲማቲም፣የውጪ ቃሪያ በክብ ከትፈን እናረጋለን ከዛም ያዘጋጀነው ድንቺ ከላይ በመጨረሻም ዶሮውን አድርገን ከላይ የምንሸፍነውን ጊስትር በውስጥ በኩል ዘይት እንቀባለን ምክንያቱም ዶሮውን እንዳይልጥብን ከዛም ኦቨን ውስጥ ከታችም ከላይም በ180⁰ አድርገን ለ1 ሰዓት ማብሰል ከ1 ሰዓት በኃላ ከበሰለ ከላይ ጊስትሩን አንስቶ ማቅላት ከዛም ለመመገብ ማቅረብ

Join @MARAKIRECIPES


ክለብ ሣንድዊች

• ግብዓቶች
• 1 ኪሎ ግራም ዳቦ
• 3 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ
• 4 የሾርባ ማንኪያ (100 ግራም) ማዮኔዝ ሶስ
• 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) ተቀ ቅሎ የተከተፈ የዶሮ ሥጋ
• 1 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተከተፈ ቲማቲም
• 2 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተከተፈ የሠላጣ ቅጠል
• 1 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
• 3 በቁመቱ የተከተፈ ቃርያ
• 4 ተቀቅሎ በቁመቱ የተከተፈ ዕንቁላል
• 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) በቁመቱ የተከተፈ ለስላሣ የበሬ ስጋ
• 1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
• 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
• 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) በቁመቱ የተከተፈ ሞርቶዴላ

• አሰራር
1. ጥሬ እቃዋቹን በሙሉ ከዳቦ በስተቀር ጋር ቀላቅሎ መለወስ፤
2. ካሬ ዳቦውን በጎኑ በስሱ መቁረጥ፤
3. የያንዳንዱን ቁራጭ ጠብሶ አንዱን ገፅታ በቅቤ ማውዛት፤
4. ሦስት የሾርባ ማንኪያ ዉሁድ ባንድ ቁራጭ የወጣ ገፅታ ላይ አድርጎ በቢለዋ እየተጫኑ ማስተካከል ፤
5. በላዮ አንድ ቁራጭ ዳቦ መደረብና ከውሁዱ ሦስት የሾርባ ማንኪያ ጨምሮ ማስተካከል ፤
6.ተጨማሪ አንድ ቁራጭ መደረብና ጫን ፡ጫን አድርጐ ማስተካከል ፤
7.ዙሪያውን በቀጭኑ በቢለዋ እየከረከሙ ማስተካከል፤
8.የተደራረበውን ዳቦ ከላይኛው ግራ ማእዘን ጫፍ በመጀመር ቀኝ ማዕዘኑ ድረስ በቢለዋ መቁረጥ፤
9.ቀጥሎ ከላይኛው ቀኝ ማዕዘን ጫፍ በመጀመር ግራ ማዕዘኑ ድረስ በቢለዋ መቁረጥ፤
10.በዚሕን ጊዜ አራት ባለ ሦስት ማዕዘን ሳንድዊች ስለሚኖሩን እያንዳዳቸዉን በስቴኬኒ ወግቶ ማያያዝ፤
11.በለሣሕን ለይ አራቱንም ሳንዲዊቾች ካንድ ዝንጣፌ ሰላጣና ከድንች ጥብስ ጋር አድርጎ ማቅረብ፤
12.በዚሕ መልኩ የቀረበዉን ወሁድና ዳቦ እያዘጋጁ መቀጠል ይቻላል።
( ለክለብ ሳንዲዊች ማዘጋጃነት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዋች ከተለወሱ በኋላ መቀመጥ አይችሉም ። ሳይለወሱ ለየብቻ ማቀዝቀዣ ዉስጥ አስቀምጦ ሲፈልጉ ለውሶ መጠቀም ይገባል።)

@MARAKIRECIPES


​​የኸልያ ወይም የማር እንጀራ ጣፋጭ

አዘገጃጀት

/ደረጃ አንድ ፉርኖ ዱቄት
/እርሾ
/ወተት ለብ ያለ
/ውሀ ለብ ያለ
/ትንሽዬ ዘይት
/ትንሽዬ ጨው
/ቤኪንግ ፓውደር
/ስኳር ሳይበዛ
የሁሉም ግብአቶችን መጠን ያልፃፍኩት ሁሉም በፈለገው መጠን ይስራ በሚል እሳቤ ነው !

አዘገጃጀት

1. ልክ ለድፎ እንደምናቦካው በደምብ አሽተን ማቡካት ከዛ ቢያንስ ለአርባ አምስት ደቂቃ ኩፍ እንዲል መተው ኩፍ ሲል በእጃችን እየቆነጥርን 2.መሀሉ ላይ ቤት ያፈራውንቺዝ እየከተትን እያድበለበልን መጋገሪያችንን ላይ ልክ ፎቶው ላይ በሚታየው መልኩ መደርደር (ይበልጥ ጣፍጭ የሚሆነው ግን ቺዝ ኬሪ ብንጠቀም ነው)
3.ከዛ እንቅላል ወይም ወተት ቀብተን ከላይ ሰሊጥ ወይም ጥቁር አዝሙድ በትነን ኦቭን ማስገባት ከስር ቢያንስ ለሰላሰ ደቂቃ ከበሰለ በኃላ ከላይ ቀላ እንዲል ከፍተን ማብሰል ነው !
4. ከወጣ በኃላ ማር ወይም የስኳር ሴሮም ወይም ቤት ያፈራውን የተገኘውን ፍሌቨር ከላይ ማፍሰስ እና ማቅረብ ! በጣም ነው ሚጥመው😘


​​Ricotta cheese cake
የሪኮታ ቺዝ ኬክ

• ግብዓቶች
• 600 ግራም ሪኮታ(ቺዝ)
• (1/2) ሩብ የሾርባ ማንኪያ ጨው
• 80 ግራም የተፈጨ ስኳር (1 የቡና ስኒ እና 3 የሾርባ ማንኪያ)
• 5 የሾርባ ማንኪያ ፍርኖ ዱቄት
• 20 ግራም ዘቢብ (2 የሾርባ ማንኪያ)
• 3 እንቁላል
• የቀለጠ ማርማላት
• አሰራር
1. በቅድሚያ ኦቨኑን በ180° ሴንቲግሬድ ማሞቅ፤
2. ሪኮታውን በደንብ ውሃውን እስከሚጨርስ ድረስ ማጥለል፤
3. በጎድጓዳ ሰሀን የእንቁላል አስኳሉንና ነጩን መለየት፤
4. ነጩን እንቁላል ጨው ጨምሮ ነጭ እስከሚሆን ድረስ በደንብ መምታት፤
5. አስኳሉን፣ ስኳርና ቫኒላ ጨምሮ በደንብ መምታት፤
6. በትልቅ ጎድጓዳ ሰሀን ሪኮታውን፣ ዱቄቱንና ዘቢቡን ጨምሮ በደንብ ማደበላለቅ፤
7. የተመታውን የእንቁላል አስኳል እና ነጩን ቀላቅሎ በደንብ ማዋሃድ፤
8. የተዋሃደውን እንቁላል፣ ሪኮታና ዱቄት ውስጥ በደንብ እያዋሃዱ መቀላቀል፤
9. ክቡን የኬክ መጋገሪያ ፓትራ ዘይትና ዱቄት መቀባት፤
10. የተደበላለቀውን (የተዋሃደውን/ ሊጥ መጋገሪያ ውስጥ በመጨመር ለ35 ደቂቃ መጋገር፤
11. አውጥቶ ማቀዝቀዝ።
12. ማርማላታውን ጨምረው መመገብ

Join @MARAKIFASHION


​​ለስላሳ የህንዶች ቂጣ አሰራር
Soft Indian chapati

በጣም ቀላል ና ፈጣን ና ብዙ ወጪ የሌለው ምርጥ ለቁርስ ለምሳ ለራት ለፈለጋችሁት የሚሆን ነው ሞክሩት : የሞከራችሁትን picture ግሩፕ ላይ ሼር ልታደርጉ ትችላላችሁ::

ግብአቶች

1. 100ግ ዱቄት
2. 50 ml ለብ ያለ ውሀ
3. 1 ሾርባ ማንኪያ ዘይት
4. 1 ቁንጫ ጨው


አዘገጃጀት
1. ዱቄቱን ጎድጓዳ ሰሀን ውስጥ መጨመር ውሀውን ጨው ና ዘይቱን ጨምረው ማቡካት

2. በመቀጠል ሊጡን 4 ቦታ ከፍለው በየተራ ሳሳ እያደረጉ መዳመጥ

3. ከዛም ማብሰል መጥበሻችን ወፍር ያለ መሆን አለበት አለበለዚያ ደግሞ በበእንጀራ ምጣድ መጋገር እንችላለን::

4. እየገለበጥን ማብሰል ንፍትፍት ብሎ እጋም ሲመስል ማውጣት

ይህንን ቻፓቲ ለጨጨብሳ ማርማላት በለውዝ ቅቤ እንዲሁም በሻይ መመገብ ይቻላል::

መልካም ቀን🌞🌞🌞🌞🌞🌞
Share share
@MARAKIRECIPES @MARAKIRECIPES
​​የካካዋ ብስኩት

• ግብዓቶች
• 200 ግራም የፍርኖ ዱቄት (4 የቡና ስኒ)
• 200 ግራም ስኳር (4 የቡና ስኒ)
• 200 ግራም የገበታ ቅቤ ወይም ማርጋሪን
• 1 እንቁላል
• 2 የሾርባ ማንኪያ ካካዋ
• 2 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ
• 2 የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
• (1/2) ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው

• አሰራር
1. በቅድሚያ ኦቨኑን በ180° ሴንቲግሬድ ማሞቅ፤
2. በጎድጓዳ ሰሀን እንቁላል፣ ቫኒላ፣ የገበታ ቅቤ ወይም ማርጋሪን እና ስኳሩን ጨምሮ በደንብ መምታት፤
3. በሌላ ጎድጓዳ ሰሀን ዱቄቱን፣ ካካዋ፣ ቤኪንግ ፓውደሩንና ጨው ጨምሮ በደንብ ማዋሃድ፤
4. እንቁላሉን ወደ ዱቄቱ አደባልቆ በእጅ ማሸት፤
5. ሊጡ ከወፈረ በኋላ ንጹህ ጠረጴዛ ላይ አድርጎ በመዳመጫ ወይም በጠርሙስ መዳመጥ፤
6. የብስኩት ቅርጽ ማውጫ ወይም የቡና ስኒ በመጠቀም በክብ በክብ አድርጎ ማውጣት፤
7. ዘይት የተቀባ የብስኩት መጋገሪያ ትሪ ላይ አድርጎ ለ20 ደቂቃ መጋገር፤
8. ዙሪያው ቡናማ እስኪሆን ማብሰል፤ አውጥቶ ማቀዝቀዝ።

Join. @MARAKIRECIPES


Banana cake
ባናና ኬክ

• ግብዓቶች

• 5 እንቁላል
• 3 የሾርባ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
• 100 ሚሊ ሊትር ወተት
• 50 ሚሊ ሊትር ዘይት
• ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው
• 1 የሻይ ማንኪያ ቫኒላ
• ግማሽ ኪሎ ግራም የፉርኖ ዱቄት
• 3 የቡና ስኒ (300 ግራም) ስኳር
• ግማሽ ኪሎ ግራም ሙዝ

• አሰራር
1. ሙዙን ልጦና ከትፎ ከስኳሩ ጋር በዕንቁላል መምቻ እስኪወፍር ለረጅም ጊዜ መምታት፤
2. እንቁላሉን በዝግታ እየጨመሩ መምታት፤
3. ወተቱንና ዘይቱን ጨምሮ በደንብ ማዋሃድ፤
4. ጨዉን፣ ዱቄትና ቤኪንግ ፓውደር ጨምሮ ትንሽ ከመቱ በኳላ ቫኒላውን መጨመር፤
5. የኬክ መጋገሪያ ትሪ ላይ ቅቤ ቀብቶ ዱቄት በላዩ ከነሰነሱ በኋላ ዱቄቱን አራግፎ ውሁዱን መጨመር
6. የሞቀ የዳቦ መጋገሪያ ውስጥ በ220°c ለ45 ደቂቀ መጋገር ፤
7. ሲቀዘቅዝ እንደ አስፈላጊነቱ መጠቀም ።

Join @MARAKIRECIPES


Lemonade

• ግብዓቶች
• 6 ሎሚ
• 1 ¼ ኩባያ ነጭ ስኳር
• 5 ኩባያ ቀዝቃዛ ውሃ

• አሰራር
1. የአትክልት ማጽጃን በመጠቀም ሎሚዎችንይጠቡ እና ሁሉንም ፍሬዎች ይላጡ ፡፡ የተላጡ ሎሚዎችን ወደ ጎን ያስቀምጡ ፡፡ የሎሚ ጣዕምን ወደ ሳህኑ ውስጥ ይጨምሩ እና በስኳር ይሸፍኑ ፡፡ከዛን ማዋሃድ ሲቸርሱ ፡፡ ይሸፍኑ እና ቢያንስ ለ 2 ሰዓታት ይቀመጥ ፣ ወይም ማታ ያሳድሩ ፡፡
2. በከፍተኛ እሳት ላይ ድስት ውስጥ ውሃ ያፈሉ ; እሳቱን ያጥፉ እና በሎሚ-ስኳር ድብልቅ ውስጥ ይቸምሩ ፡፡ ለ 5 ደቂቃዎች ያህል ስኳሩ ሙሉ በሙሉ እስኪፈርስ ድረስ ያማስሉ እና ከዛ ለ 5 ደቂቃ ያስቀምጡ ፡፡
3. እንደገና ወደ ተመሳሳይ ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ በማጣሪያ ማጣሪያ ውስጥ ያፈስሱ እና ቴራፊን ይጣሉት ፡፡ ከ 20 እስከ 30 ደቂቃዎች አንድው እንዲቀዘቅዝ ያድርጉ ፈረጅ ያሳስገቡ ፡፡
4. ሎሚ በግማሽ ይቁረቱና እና ወደ ሳህኑ ውስጥ ይጨመቁ ፡፡ በሌላ እቃ ይቀንሱ እና ፡፡ በፕላስቲክ መጠቅለያ መጠቅለል እና በረዶ ቸመረው ከማክረቦ በፊት በደንብ ማቀዝቀዝ ፣ ቢያንስ ለ 2 ሰዓታት ፡፡

SHARE @MARAKIRECIPES


​​Guacamole 🥑

የሚየስፈልጉን

• 3(4) የበሰለ አቮካዶ 🥑(በደቃቁ የተከተፈ)
• 1 ቲማቲም🍅 (በደቃቁ የተከተፈ)
• ግማሽ ቀይሽንኩርት (በደቃቁ የተከተፈ)
• 2 ንጭሽንኩርት (በደቃቁ የተከተፈ)
• 2 የሾርባ ማንኪያ ፐርሲል ,parsley 🌿(በደቃቁ የተከተፈ)
• 1 የሎሚ ጭማቂ 🍋
• ጨው
• 1/2 የሻይ ማንኪያ ከሙን (cumin powder)

አሰራር

• ከላይ የተዘረዘሩትን በሙሉ በአንድ የጎድጉዋዳ እቃ ውስጥ በሚገባ ቀላቅሎ ወዲያውኑ ማቅረብ 👌

•• ይሄንን የአቮካዶ ቅልቅል በድንች ጥብስ 🍟,በርገር🍔,ቶስት በተደረገ ዳቦ 🍞,....መጠቀም

••use your Guacamole with potatoes chips,French fries 🍟,toast bread ,deep fried fish,....or Use cucumbers, carrots, celery, or any other veggie as your dipping stick 😉

Join @MARAKIRECIPES


Forward from: abuja
‼️እንዳያማልጥሽ ታላቅ ቅናሽ‼️

⚪የቦንዳ ልብስ ለሴቶች (2nd hand cloths)
⚪የ አውሮፓ እስታንዳርድ የሆኑ ኳሊቲ እና ለየት ያሉ ልብሶችን በታላቅ ቅናሽ👗 ማግኘት ከፈለጉ ከታች ካሉት የምትፈልጊውን መጫን ብቻ ነው
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇


ተሰብሮ በውሃ የተቀቀለ እንቁላል
1 እንቁላል
1 በቅቤ የተጠበሰ ዳቦ
2 ኩባያ ውሃ
1/2 የሻይ ማንኪያ ጨው
1/2 የሻይ ማንኪያ ኮምጣጤ

----አሰራር----
1. ውሃ በብረት ድስት ማፍላት
2. ጨውና ኮምጣጤ የፈላ ውሃ ውስጥ መጨመር
3. እንቁላሉን ሰብሮ የፈላው ውሃ ውስጥ ጨምሮ አምስት ደቂቃ ማብሰል።
4. የበሰለውን እንቁላል በቅቤ ከተጠበሰ ዳቦ ጋር ማቅረብ።
--መልካም ምግብ--

20 last posts shown.