❤️ ከምርጦች ማህደር


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Other


📍በዚህ ቻናል :
የተመረጡ አዝናኝ 😂✔ አስተማሪ ✔ ነገሮችን ያገኙበታል።
በዚህchannal የተመረጡ oldies❤ and new music በ #kb size
አስተማሪ ታሪኮች♨
ግጥሞች 💟 ያገኛሉ🙏
እየተዝናናን እራሳችንን የተሻለ ሰው እናድርግ!
ተቀላቀሉን

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Other
Statistics
Posts filter


​​🙇🙇🙇ስህተቴ🙇🙇🙇
        ክፍል ሁለት (2)

ከካፌዉ እንደወጣን ቦርሳዋን ይዤላት እያወራንና በየመሀሉ እየዘፈነችልኝ ወደ ቤቷ ሸኘኋት። ከሷ ጋር ስጨርስ ሚኪ ጋር ደወልኩለት። ፑል ቤት እየተጫወተ እየጠበቀኝ ነበር። ተገናኝተን ወደ እማዬ ምግብ ቤት ሄድን። እማዬ ምግብ ካቀረበችልን በኋላ "ከኛ ቤት ጎን የተሰራዉ ትልቁ ቤት እኮ ተሸጠ። ዛሬ ሰዎቹ ገቡበት።" አለችን።
እኔና ሚኪ ትምህርት በመሄዳችን እቃ አዉርደን የምናገኘዉን ብር ስላጣን ተበሳጨን። ለነገሩ ጎረቤት መቦጨቅ ደሞ አይነፋም። እማዬ ለሌላ ተስተናጋጅ ምግብ እያቀረበች "ደሞ ጥሩ ሰዎች ይመስላሉ። ሰዉየዉ ቁልፉን እንድሰጣቸዉ ደዉለዉ ሄጄ አይቻቸዉ ነበር።" አለች። እማዬ ቤቱ እስኪሸጥ ደላላ ሲመጣ እንድታሳይ አደራ ተብላ ቁልፉ እሷ ጋር ነበር።
.
ማታዉን እናቴ ቡና አፍልታ አዲሶቹ ጎረቤቶቻችን ጋር ሄድን። እኔ እንኳ ጀበናዉን እና ሽንብራዉን አድርሼላት ለመዉጣትና ከፌቪ ጋር ፌስቡክ ላይ ለመጀናጀን አስቤ ነበር። ሰዎቹ ጋር ስናንኳኳ አንድ ጠይም የሆነች፣ ረዥም ቀሚስ የለበሰች፣ ሂጃብ የጠመጠመችና ጥርሷ በብሬስ የታሰረ ወዛም ልጅ በሩን ከፈተችልን። እቃ አድርሶ የመመለሱን ሀሳብ ሰረዝኩት። ይህቺን የመሰለች ልጅ ያለችበት ቤት መቀመጡ ራሱ ደስ ይላል። እኔ ሴት ላይ ችግር አለብኝ። ያየሁት ሁሉ ያምረኛል። ለነገሩ ይህቺ እንኳ ትገባኛለች። የሰፈሬን ሴትማ ማንንም አላስበላም። እማዬ ሴቶቹ ጋር ገባች። እኔን ልጅቷ ወደ ሳሎን ወሰደችኝ።
ሳሎን ስገባ ምግብ ቀርቦ ነበር። አንድ ሸምገል ያሉ ሰዉዬ ስገምት አባቷ ይመስሉኛል "አምሪያ እጅ መታጠቢያዉን አሳይዉ ይቀላቀለን!" አሉ። አሀ ስሟ አምሪያ ነዉ ማለት ነዉ አልኩ በልቤ። ምናለ ስልኳንም በዛዉ ቢጠሩት። ፈገግ ብላ መታጠቢያ ቤት ወሰደችኝ። እየታጠብኩ "ስንተኛ ክፍል ነሽ?" አልኳት። ድፍረቴ ሳይገርማት አይቀርም። "ከወር በኋላ ኢንትራንስ እፈተናለሁ። አስራሁለተኛ ክፍል ነኝ።" አለችኝ በትህትና። ስለራሴ ትንሽ ነገርኳትና የአባቷን ስም ጠየቅኳት። "ራህመቶ" አለችኝ ፈገግ ብላ። ልጅቷ ፈገግታ ታበዛለች።  እኔ የአባቷን ስም የጠየቅኳት አባቷን መተዋወቅ ፈልጌ ሳ ይሆን ፌስቡክ ላይ ልፈልጋት ስላሰብኩ ነዉ።
ታጥቤ እየተመለስኩ ቆም አልኩና "ወንድም ምናምን የለሽም?" አልኳት። "ሶስት አሉኝ። ሳሎን ያሉት ሁለቱ ወንድሞቼ ናቸዉ። አንደኛዉ ልጁ ታማ ሄዷል። ሶስቱም አግብተዉ ወጥተዋል።" አለችኝ። የቤቱ ታናሽ መሆኗ ነዉ እንግዲህ! ለዛሬ ከበቂ በላይ መረጃ እንደሰበሰብኩ አሰብኩ። ነገ ለነሚኪ ይተረካል። ሳሎን ገብቼ በልተን ከጨረስን በኋላ አባቷ የጥያቄ መዓት አወረዱብኝ። ብዙዉ የሀይማኖት ትምህርት ለምን እንዳልተማርኩ ምናምን ነዉ። ሲጠይቁኝ ስወዛገብ አለመማሬ ገባቸዉ መሰለኝ። ሰዉየዉ ሀይማኖተኛ ነገር ናቸዉ።
ፌቪ አስሬ ትደዉላለች። ስልኬን ዘጋሁት። ደሞ በመጀመሪያ ቀን ልጠቆር እንዴ?
.
ሰዉየዉ አንድ በአንድ ሳሎን የነበሩትን ልጆች ካስተዋወቁኝ በኋላ አምሪያን ጠርተዉ ሰፈሩን እንዳላምዳት አደራ አሉኝ። ተመስገን! እንኳን አደራ ተብዬ ወትሮዉንም እንዲሁ ነኝ። አንገቴን ስደፋ ምንም የማላዉቅ መስያቸዋለሁ።
.
ከነአምሪያ ቤት እንደወጣሁ ፌቨን ጋር ደወልኩ። ፌቪ በጣም ተጨንቃ ነበር። ሁሌም ከሶስት ሰዓት በኋላ ስለምናወራ ስልክ አላነሳ ስላት ደንግጣለች። ድንጋጤዋ ሲበርድላት "አንድ አንድ እንዝፈን!" አለችኝ። ፌቪ ስዘፍን ድምፄን ትወደዋለች። አንድ አንድ ተዘፋፍነን ስልኩን ዘጋሁት።
ቤት ከገባሁ በኋላ አምሪያን ፌስቡክ ላይ አሰስኳት። መጨረሻ ላይ አንድ ፎቶ የሌለዉ አካዉንት የሷ ይሆናል ብዬ ገመትኩና ሪኳየስት ላኩኝ። ወዲያዉ ተቀበለችኝ። ትንሽ እንዳወራኋት እሷ አለመሆኗን አወቅኩ። ተበሳጨሁ።
.
ልተኛ ስል ሚኪ ደወለ "ኧ ሚኪ" አልኩ ስልኩን አንስቼ
"ሀቢቤ ያበደ እቅድ አለ ቸከሶቹን በተመለከተ! አሁን አያቴ ሰዉ ሲመክር ሰምቼ ነዉ። ጠዋት በሰፊዉ እተነትንልሀለሁ።" አለኝ። ሚኪ የሌለ ጓጉቷል። እኔም እስኪ ይንጋና ለነሚኪ ስለ አምሪያ ልተርተርላቸዉ።

share your channal
    
#Share


90/100 አለም ላይ አስመሳይ አፍቃሪዎች ነው ያሉት ፣እንዴት ካልክ የሴቷ ወይም የወንዱ ተገዢ ናቸው።

✍አቤል


ስህተቴ

      ክፍል አንድ (1)
🙇🙇🙇🙇🙇🙇🙇🙇🙇🙇
የጠዋቷ ፀሀይ በየት በኩልም እንደወጣች እንጃ! ተፈጥሮን የማድነቅ ልምድ የለኝም። ብቻ ዋናዉ ነገር መዉጣቷ ነዉ። እኔም ሰዉነቴ ላይ የተለጠፈ የሚመስለዉን ስኪኒ ዩኒፎርሜን ለብሼ ፣ፀጉሬን ፈርዤና አንድ ደብተር አንጠልጥዬ ወደ ትምህርት ቤት እሄዳለሁ። እንደሌላዉ ተማሪ ቦርሳ ሙሉ ደብተርና መፅሀፍ ተሸክሞ መሄድ በጣም ነዉ የሚሸክከኝ። ቦርሳ የያዙ ልጆችን ሳይ ፋራ ነዉ የሚመስሉኝ። እነሱ ቦርሳ እየተሸከሙ እኔ በወጉ እንኳ ሳልፅፍ ይኸዉ ኩረጃ ዕድሜዉ ይርዘምና አስራአንደኛ ክፍል ደርሻለሁ። ጓደኞቼ አብነት ፣ ሚኪያስ እና ከሪም ይባላሉ። የትምህርት ቤታችን ጭሶች እኛ ነን። እኔ ፍቅረኛ ሳይኖረኝ አንድ ለሊት ካለፈ በጣም ነዉ የሚደብረኝ። ከአንዷ ጋር ስደባበር ሌላኛዋን ወዲያዉ ጠብ አደርጋታለሁ። ሚኪያስም የኔ ቢጤ ነዉ። ከሪም እና አብነት ግን የኛን ወሬ ከመስማት እና በአለባበስ ከመመሳሰል በዘለለ ብዙም ቺክ ማዉረድ አይቀናቸዉም። "ያለሙያችን አንገባም!" ይላሉ። እኛም የቺኮቻችንን ጓደኞች ልናስበላቸዉ እንሞክራለን። ግን እስካሁን አልቀናቸዉም።
.
ጠዋት አስራሁለት ሰዓት እንደደረሰ የማዉቀዉ እናቴ ቤት ዉስጥ መንጎዳጎድ ስትጀምር ነዉ። "ሀቢቤ ተነስ መቼስ ገና እስክትኳኳል መከራ ነዉ!" አለች። እኔ አልጋ ላይ ተጋድሜ በፌስቡክ ከፌቨን ጋር እጀናጀናለሁ። ፌቪ አዲሷ ፍቅረኛዬ ናት። ሁሌም ጠዋት ጠዋት እናቴ ለሊት የጋገረችዉን እንጀራ ከቤታችን ትንሽ ራቅ ብሎ ያለዉ የላስቲክ ምግብ ቤቷ ሳላደርስላት ወደ ትምህርት ቤት አልሄድም። አባቴ ከሞተ በኋላ በቻለችዉ ሁሉ እኔን ለማኖር ትለፋለች። ቤታችን ቢሸጥ ብዙ ብር የሚያወጣ ቢሆንም እማዬ "የከማሌን ማስታወሻ አልሸጥም!" ብላ ግግም አለች። ከማል የአባቴ ስም ነዉ። ያለኋት ልጅ እኔዉ ብቻ ስለሆንኩ በቻለችዉ መጠን ከማንም እንዳላንስባት ትጥራለች። የምይዘዉ ስልክ ፣ ልብሶቼ እና ኪሴ ዉስጥ የሚገኘዉ ብር የላስቲክ ምግብ ቤት ያላት እናት ያለችኝ አይመስልም። ለኔ ያላትን ከመስጠት ወደ ኋላ ብላ አታዉቅም። እናቴ ሁሌም "ሱስ የሚባል ላይ ትወድቅና አይኔን አታያትም!" ብላ ስለምታስፈራራኝ ሱስን በሩቁ ነዉ የምሸሸዉ። ጓደኞቼም እኔን ስለሚከተሉ ሱስ ሰፈር የሉበትም። ምድር ላይ ሁሉ ነገሬ እናቴ ናት። በጣም እወዳታለሁ። አዛኝ እምቢ ማለት ይከብደኛል። እየተነጫነጭኩም ቢሆን ያለችኝን እፈፅማለሁ።
.
ከአልጋ ላይ ተነስቼ ከተጣጠብኩና ፀጉሬን ከፈረዝኩ በኋላ ደብተሬን እናቴ ይዛልኝ፣ እንጀራዉን ፍሪዜ እንዳይበላሽ በእጆቼ አየር ላይ ተሸክሜ ወደ ምግብ ቤት አድርሼ ፤በዛዉ ሚኪያስን ጠርቼዉ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ። አብነት እና ከሪሜ እኛ ሰፈር ስላልሆኑ ትምህርት ቤት ነዉ የምንገናኘዉ። ከክፍላችን ተማሪዎች በእድሜ ትንሽ ከፍ የምንለዉ እኛ ነን። ሰልፍ እስኪያልቅ ድረስ ዉጪ ላይ ያለዉ ሻይ ቤት ጮርናቄ በሻይ እየበላን እናረፍዳለን። ሰልፍ ሲያልቅ እንገባለን። ሚኪ ከቺኩ ጋር ሲዛዛግ ይቆይና ካሰናበታት በኋላ አብረን እናሳልፋለን። ከትምሮ ስንለቀቅ የኔዋ ፌቨን ከኛ ትምህርት ቤት አቅራቢያ ያለ የግል ትምህርት ቤት ስለምትማር አብሬያት እስከ አስራአንድ ሰዓት ቆይቼ ሸኝቼያት ወደ ቤት እመለሳለሁ። እኛ የምንማረዉ የመንግስት ትምህርት ቤት ነዉ። 
.
ፌቨን እዉነት ካወራን ቆንጆ አትባልም። ግን የሆነ የደስ ደስ አላት። ቅብጥብጥ ትላለች። ከሷ ጋር ፍቅረኛ ከሆንን ወር አልፎናል። ጓደኞቼ ፌቨንን ጠብ ሳደርጋትእዉነቱን የሌለ ነዉ የኮሩብኝ። ምዕራባዊያንን ያንበረከክኩ ያህል! እሷ ትንሽ የሀብታም ልጅ ነገር ስለሆነች ጓደኞቼን ሳይቀር ትጋብዛቸዋለች።  ለመናገር ግን ከሶስት ወር በላይ ከአንድ ሴት ጋር መቆየት አይሆንልኝም። ከዚህ በፊት ሶስት ሴቶች ፍቅረኛዎቼ ሆነዉ ነበር። ሰላማዊት ፣ ሜሮን እና ሰሚራ ይባላሉ። ከሰላም እና ከሰሚራ ጋር ተኝቻለሁ። ከተዉኳቸዉ በኋላ ሁለቱም በጣም ተጎድተዋል። ሜሮን ስትገግምብኝ ነዉ የጫርኳት። ከዛ በኋላ ምን ትሁን ምን አላዉቅም። ብቻ ግን ከፍቅር ግንኙነቶች መቋረጥ በኋላ በጣም የሚጎዱት ሴቶቹ ናቸዉ። ሁለ ነገራቸዉ ብልሽትሽት ነዉ የሚለዉ።
.
ከፌቨን ጋር ዛሬ ከተገናኘን በኋላ አንድ ሰፈራችን ዉስጥ ደፍሬ ገብቼ ወደማላዉቅበት ካፌ ወሰደችኝ። ካፌዉ ግርማ ሞገስ አለዉ። ገብተን አንዱ ጥግ እንደተቀመጥን ፌቪ አይን አይኔን እያየች "የእዉነት ትወደኛለህ?" አለችኝ። ወዲያዉ ፈገግ ብዬ "አንቺን አለመዉደድ እንዴት ይቻላል?" አልኳት። ምላሴ እኮ ጤፍ ይቆላል።
"ግን እኮ እኛ ትምህርት ቤት ስላንተ ደስ የማይል ነገር ይወራል።" አለችኝ።
"ምን?" አልኳት ትኩር ብዬ እያየኋት
ፍርሀት አይኖቿን እኔን ከመመልከት እየሰበራቸዉ "ሴት አሯሯጭ ነዉ ፣ ብዙ ሴት ያተራምሳል! ምናምን" አለችኝ።
እንደመቆጣት እያልኩኝ "እሱ ትናንት ነዉ። ዛሬ አንቺ መጥተሽ ህይወቴን ሙሉ ለዉጠሽዋል። ተስተካክያለሁ። አታምኚኝም እንዴ?"  አልኳት።
ፈጥና እጆቼን በእጆቿ ጭምቅ እያደረገች "ኧረ አምንሀለሁ። ተዋቸዉ በቃ!" አለችኝ። የፌቪ ፍቅር ሁሉ ነገሯ ዉስጥ ይታያል። ጀንጅኜ ያሰመጥኳት እኔዉ ነኝ ግን እሷ ፎንቃዬ የሌለ ገብቶላታል። ፌቪ ስትዘፍን ድምጿ በጣም ያምራል። ብዙ ጊዜ ደዉላ ትዘፍንልኛለች። የልቧን የምትነግረኝ በዘፈን ነዉ። ዛሬም ዘፈነችልኝ። ድምጿ ዉስጥ የሆነ ለቅሶ አለ። እንዳታጣኝ ሰግታለች።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
💓💓ነገ💓ይቀጥላል💓💓💓
🌺🌺ከወደዱት ሼር ማድረጉን አይዘንጉ🌺🌺🌺🌺🌺🌺

        
#Share @melkamliiboch


አንድ ኢትዮጲያዊ አንድ ህንዳዊና አንድ ቻይናዊ ሬስቶራንት ውስጥ ምሳ እየበሉ ሳለ አንዲት ዝንብ ትመጣና ህንዳዊው እጅ ላይ ታርፋለች ህንዳዊውም ያባርራታል ቀጥላም የኢትዮጲያዊው እጅ
ላይ ታርፋለች እሱም ሲያባርራት ወዲያው ቻይናዊው እጅ ላይ
ታርፋለች ቻይናዊውም ቀ……ስ አለና ያዛት ቀጠለናም በላት፡፡🙈

ህንዳዊው እና ኢትዮጵያዊው በጣም ተገረሙ


ትንሽ ቆየና ደግሞ ሌላ ዝንብ መጣች አሁንም በጀመሪያ ህንዳዊው ላይ አረፈች አባረራት

ቀጥሎ ኢትዮጲያዊው እጅ ላይ አረፈች ኢትዮጲያዊውም ልክ
እንደ ቻይናዊው ቀ……ስ ብሎ ያዛትና ወደ ቻይናዊው ዞሮ ምን ቢለው ጥሩ ነው







"ስንት ትገዛኛለህ?"
😂😂😂😂😂😂😂😂

ስራ ፈጠራ ይሏቹሀል ይሄ ነው😜 እና ደግሞ
ቀልዶቻችንን  በየግሩፑ Forward በማድረግ ይተባበሩ


♥️🥰
ጨረቃ ስትወጣ ከጎኔ ቁጭ ብለሽ
በዓይኔ አይሻለው……
ከዋክብት ሲጓዙ ከነሱ መካከል
አንቺን ፈልጋለው……😊
ከፀሃይ ጋር ብትወጪ ብዬ
ሁል ጊዜ ጠዋት እጠብቅሻለው
አንዳንዴም በህልሜ
#አቅፌሽ አድራለው።🤗
ዝም ብለሽ በሀሳቤ ሁሌ ትመጪያለሽ
ምክንያቱን ባላቅም ትናፍቂኛለሽ
#ያነጫንጨኛል ላገኝሽ እሻለው…☹️
በሰበብ አስባቡ
#ስላንቺ አወራለው♥️
የፅድቄ ሽልማት የኔ ገነት ውዴ
ኧረ ጉዴ ፈላ…ፍቅር
#ያዘኝ እንዴ 😳


ሼር አደራ


ታውቃለህ ??

የተደገፍከው ያ እንዳንተ ስጋ ለባሽ ሰው የህይወትህን መንገድ ያካሂድህ (አብሮህ ይጏዝ) ይሆን ይሆናል እንጂ ... ያንተን ጉዞ አይጏዝልህም!!

ልበ-ቀና ከሆነ መንገድህ ያዛለህ ጊዜ ያበረታሃል!! ... የወደቅህ ሰዓት ደግፎ ያነሳሃል!! ....

የፍቅር ሰው ከሆነ በመንገድህ ስታነክስ ትከሻውን አስደግፎህ በምትጎትተው እግርህ ልክ የራሱን መንገድ ፍጥነት ገትቶ አብሮህ ይጏዛል::

በጣም ለፅድቅ የቀረበ ከሆነ እስከሚችለው ድረስ ያዝልህ ይሆናል:: .... (አንተ ጀርባው ላይ ሀሳብህንም ክብደትህንም ጥለህ ለሽ ብለህ እያንቀላፋህ ... ፈሱ እስኪያመልጠው አይሸከምህም!! ... 🤷🏽‍♀️🤷🏽‍♀️)

በተረፈው ሁሉም ልክ እንዳንተው የራሱ ሩጫ.. የራሱ መውደቅ እና መነሳት ... የራሱ ጉድለት አለው እና የራሱን አቁሞ እንዲያቋቁምህ መጠበቅ የዋህነት ነው!!!

ወደቅህም ተነሳህም .. ፈረጥክም ... ቀደምህም ... ዘገየህም ...ህይወቱኮ ያንተ ነው!! እገሌ እንዲህ አላደረገልኝም ... እገሊት ትታኝ አለፈች... ታምሜ ሳይጠይቁኝ ... ሞቼ ሳያለቅሱልኝ ... እያልክ የምታላዝነው ምን ሆነህ ነው??

ለራስህ ህይወት ሀላፊነቱን ራስህ ውሰድ እንጂ 🙄ምን ሆነህ ነው ቤተሰብ .. ጎደኛ .. ፍቅረኛ ... ደርበው ያንተን ስንክሳር እንዲኖሩልህ ቁጭ ብለህ የምትጠብቀው??

እንኳን ሰው አምላክ ራሱ ሲረዳህኮ የምትጏዝበትን ጉልበት እና ጥበብ እንጂ የሚሰጥህ በአስማት ነገር እንደንፋስ አያስወነጭፍህም!!

እንዳልኩህ ነው!! ማንም ቢሆን አብሮህ ይሮጥ ይሆናል እንጂ ያንተን ሩጫ አይሮጥልህም!! ...

ሰው እንዲረዳህ ከመጠበቅህ በፊት በራስህ የምትችለውን አድርግ !!! ሰው እንዲወድህ ከመጠበቅህ በፊት ራስህን ውደድ !! ሰው እንዲያከብርህ ከመጠበቅህ በፊት ራስህን አክብር!!)

(ሄዋንዬ ለአዳም ነው ብለሽ አላለፍሽማ?? 🤣🤣🤣 ለኛም ነው እህትዬ❤️❤️❤️❤️ )


በዚች በጉድ አገር፣

ጉልበተኛው ሲነጥቅ፣ላብ-አደር አፍኖ

መንገደኛው ያልፋል፣

በምን-ገዶኝ ግርዶሽ ፣ማያውን ሸፍኖ፡፡

በዚች በጉድ አገር፣

ጥራዝ-ነጠቅ ሲያኝክ፣የቅልለትን ቅጠል

ትውልድ አሰልፎ፣ልሂቁ ያጠምቃል፣የፍርሃት ጠበል፡፡፡

#_ከወደዱት_ሼር_ያድርጉ


ታ ስ ፈ ል ጊ ኛ ለ ሽ !
(መላኩ አላምረው)

በተለይ በክረምት ፡ ሙቀት ሲያስፈልገኝ
በተለይ በምሽት ፡ የብቻየን ስገኝ !
.
ብርድና ባዶነት ፡ ተባብረው ሲመጡ
ባንች ተገፍትረው ፡ ፈጥነው እንዲወጡ
.
ከላየ ቁጭ በይ ፡ ግርማየ ሞገሴ
እቅፍፍፍ ስታደርጊኝ ፡ ትሞቃለች ነፍሴ
.
ጌጤ ነሽ ለአካሌ ፡ ክብርና ውበቴ
በይ ነይ ልደርብሽ ፡ ከታናሿ ቤቴ
.

...ስ
......ፈ
..........ል
..............ጊ
.................ኛ
.....................ለ
.........................ሽ !
....
.
ወፍራሟ ጃኬቴ!


💔🥹
#_አደራ_ሼር_አድርጉ


የሰውነት መብራት
(ተስፋሁን ከበደ)

እግዚአብሔር . . .

ምን መኾን ቢችል : አካል መልኩን ስሎ :

ዐይኑን ያየው ዘንዳ :

የሰውን ፊት ሰራ ! መስታወት ነው ብሎ።


💔🥺 #_አደራ_ሼር_አድርጉ

9 last posts shown.

33

subscribers
Channel statistics