❤️ሰላም ጤና ይስጥልኝ የጥበብ አፍቃሪያን እንዴት ሰነበታችሁ እንዴት አመሻችሁ እኔ ደና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን !!!!!!!
❤️ዛሬ ስለ ደላሹት፣ ልበ ምድር ፣የሴት ልብ፣አእጋረ ፀሐይ ፣ደመ መለኮት፣ ዕፀ ደማኮል፣ አውታረ ፀሐይ
..ወዘተ በመባል የምትጠራው ድንቅ ዕጽ ገቢር እና አነጋገስ እንሆ!
📕አንቲ ውእቱ ዕፅ ቡሩክ፡ዕፀ:ሕይወት፡ወዕፀ መድሀኒት፡ዕፀ፡ሐድሶ፡ወአንግሶ፡በቃለመለኮት፡ዕፀ፡ደለሹት፡ከመ፡ዕፀ፡ኮሞል፡ኩኒ፡ወከመ፡ንጉሥነ፡እገሌ፡ንገሢ፡ወከመ፡ጳጳስነ፡እገሌ፡ተጰጰሲ፡ወከመ፡ታቦተ፡ማርቆስ፡ወኤልያስ፡ተቀደሲ፡እደ፡መሠርያን፡ደምስሲ፡ወልበ፡ጠቢባን፡ሐድሲ፡ወሊተኒ ፡እገሌ፡
(ስም አግባ)
አነግሲ፡ሙታነ፡አንስኢ፡ወሕሙማነ፡ፈውሲ፡ሰንተው፡ቀንተው፡ቀርነው፡ቀርነለው፡ዱኤል፡ጉኤል፡ኢያኤል፡አማኑኤል፡ኤራን፡ቄራን፡መፍርሐን፡በከመ፡አንገስኮሙ፡ለአዳም፡ወለሔዋን፡በውስተገነት፡ከማሁ፡አንግሣ፡ለይእቲ፡እጸ፡ደለሹት፡ለከዊነ፡መፍትሔ፡ሀብት፡ወመክሥተ፡ጥበባት፡በላዕሌየ፡ሊተ፡ለገብርከ፡እገሌ፡ (ስም አግባ)
ቡታኤል፡ዱታኤል፡ዱክታኤል፡ንሂል፡ሕዮብ፡ደሂብ፡ሄራብ፡በእሉ፡ቃላት፡በከመ፡አንገሦኮ፡ለሰሎሞን፡በፈለገ፡ግዮን።ከማሁ፡አንግሣ፡ለይእቲ፡እጸ፡ደለሹት፡ለከዊነ፡መፍትሔ፡ሀብት፡ወለመክሥተ፡ሲመት፡በላዕሌየ፡ እገሌ (ስም አግባ)
❇️ገቢሩ ❇️
ከላይ ያለው ጾሎቱን ቁመህ ፯ ጊዜ፡ደግመህ፡እጸዋቷን፡እየዞርክ፡በምስራቅ፡በምዕራብ፡በሠሜን፡በደቡብ፡በአራቱ፡ማእዘን፡እፍ እያልክ፡ንፁህ ማር እና ወተት ቀላቅለህ ወደ ዕፅዋ እየረጨህ በፈጣሪሽ በንጉስሽ ኃይል እና ስልጣን አዝዤሻለሁ።
ለክ እንደዚህ ማር እና ወተት ፈጣሪሽን በሰጠሽ ፀጋ በሰጠሽ የሀብት ጥበብ አጣፍጪኝ ሀብቱም ሲሳዩም አምጪ የሚገረግረኝ ዓይነጥላየም ቁረጪ ብለህ ቀንድ ካራ ይዘህ የዕፅዋን ጫፍ በአንዱ እጅህን ይዘህ!
🌿አይነጥላ።ገርጋሬ፡ሀብት፡ምቀኛ፡ተንኮለኛ፡ከራሴ፡እስከ እግሬ ያለውን ሀብት የሚገረግረኝን፣ጤና የሚገረግረኝን፣ ስራ የሚገረግረኝን፣ ትዳር የሚገረግረኝን፣ እንደዚሁ ቁረጪ ብለህ በቀንድ ካራ ከስሯ ቁረጥ መላ አካሏን ያዝ።
ወደ ምስራቅ ዙረህም ዓይነ ጥላየን እንዲህ ቅበሪ ብለህ ከተቆፈረበት ውስጥ ጥሬ ጨው እና ቅጠሏን ቀብረህ በአፈሩ አዳፍን።
🌿በስተ መጨረሻ ወደ ምስራቅ ዙረህ መዝሙረ ዳዊት መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞንን ሙሉውን ምዕራፍ ስምህን በስተመጨረሻ እያስገባህ ጸልይ። ዕጽዋንም ይዘህ ወደ ቤትህ ሂድ።
🌿ይህ የአንጋገስ ስርዓት ከአንድ ዕፅ ላይ ካከናወንክ አልያም ካነገስክ በኃላ በርከት አድርገህ ያለምንም ማንገሻ ዕፀ ደለሹት ቆፍረህ መሰብሰብ እና ማድረቅ ነው።
👉፩ኛ,ለመፍትሔ ሀብት፦ሥሯን እና አበባዋን በእርጥቧ በንፁህ ጨቅጭቀህ በጣዝማ ማር ማክሰኞ ቀን በባዶ ሆድ በትንሹ መብላት መልካም ነው።
👉፪ኛ,ሀብት፣ ገበያ ለሚገረግር፦የደለሹት ዕጽ በብዛት በማሰባሰብ ከ ከርቤ እና ከዕጣን ጋራ ቀላቅሎ ቤት ውስጥ እንዲሁም ስራ ቦታ ጧት ጧት ማጨስ ገርጋሪ ክፉ መንፈስን ታባርራለች።
👉፫ኛ,ለፍቅረ ሰብእ፦ይህ ማለት ሰዎች እናንተ ዘንዳ መልካም አመለካከት እንዳይኖራቸው የሚያደርገውን የዓይነጥላ መንፈስ ማራቅ ነው። የደለሹት ሥር በደንብ አድርቀው አልመው ትዳር ለሚገረግራቸው ሴቶች ከንፁህ ቅቤ ጋር ቀላቅለው ለ ፫ ቀን ይቀቡ።
ለወንዶች ከሚቀቡት ቅባት ሁሉ በመቀላቀል እየተቀቡ መውጣት ይችላሉ።
👉፬ኛ,ለመፍትሔ ሥራይ፦በሰዎች የተሰራቦት ተንኮል መተት ሥራይ ወዘተ ካለ።
ስሯን እና ቅጠሏን በብዛት በማሰባሰብ ጨቅጨቅ አድርገን በአዲስ ቅል በዕለት ውኃ በመዘፍዘፍ ጧት ጧት በባዶ ሆድ ለ ፯ ቀናት ያክል መላ ሰውነትን በደንብ አድርጎ መታጠብ ነው። እሙን ነው።
👉፭ኛ,ለማይድን ቁስል ለለምጽ የደለሹት ሥር በብዛት አሰባስበን አድርቀን በመደቆስ በንጹህ ቅቤ እስኪድን ድረስ በተደጋጋሚ መቀባት ያድናል። ለለምጽ ሲሆን ውኃ በየ ፫ ቀን ይታጠቡ ረዘም ላለ ጊዜም ይጠቀሙ።
👉፮ኛ ሀብት ለሚልከሰከስበት (ለሚበተንበት)
የደለሹት ሥር እና የጊዜዋ ሥር አንድ ላይ በማቀላቀል ማታ ማታ ለ ፯ ቀን ያክል እየታጠኑ መተኛት።
👉፯ኛ,ለሆድ ሥራይ የደለሹት ሥር በንፅህና አድርቀው ነፍተው በማዘጋጀት ፫ የሾርባ ማንኪያ የደለሹት ሥር ከአንድ የሾርባ ማንኪያ የወይራ ሥር ቅርፊት ጋር በማቀላቀል በግማሽ ኪሎ ጣዝማ ማር ለ ፫ ቀን ለውሰው በማቆየት ከዛ በኃላ ለ አስራ አራት ቀን ያክል ጧት ጧት በባዶ ሆድ በትንሿ ማንኪያ አንድ አንድ እየቀመስክ ውጣ።
👉፰ኛ,ሥራ አልሳካ ላለው ሰው፦የደለሹት ሥር በንፅህና አድርቀው በማዘጋጀት በቅብዓ ቅዱስ ለውሰው እጅ እና ግንባር እየተቀቡ መሄድ እንዲሳካ ይሆናል።
👉፱ኛ,ለድከመተ ወሲብ፦የደለሹት አበባ እና ሥር፣የችፍርግ ሥር፣የፍየለፈጅ ሥር፣እነዚህን አንድ ላይ በማቀላቀል በአንድ የሾርባ ማንኪያ እየለኩ በግማሽ ሊትር ወተት ጨምረው በማፍላት ማታ ማታ ቀዝቀዝ አድርገው ይጠጡ።
👉፲ኛ,ለመፍትሔ ሀብት፣ለግርማ ሞገስ፣ለፍቅረ ሰብእ፦የደለሹት ሥር አድርቀው ከቀረጽ ተቀጽላ እና ከዋርካ ተቀጽላ አንድ ላይ ቀላቅለው ከትበው ይያዙ።
🌿ከላይ የተጠቀሱት የደለሹት ገቢር አሰራር እና አነጋገስ ከፈጣሪ ስራ ያልወጣ መሆኑን እንድትገነዘቡት እሻለሁ።
🌿ይህ ማለት በሂወታችን እየገቡ ሀብታችን ፍቅራችን ጤንነታችን የሚረብሹ ክፉ አጋንንትን የማራቅ ሥራ ነውና።
🌿ይህ የአነጋገስ ስርዓት ከተቻለ ለዕጽዋት አቆራረጥ ግንዛቤ ያለው ሰው ቢቆርጣት የተሻለ ይሆናል።
ካልሆነ ደግሞ በንጽህና ቢቆርጧት ይመረጣል።
🌿የደለሹት ገቢር ከዚም በላይ በየሊቃውንቱ የተለያየ ስርዓት ያላት ከዚህም በላይ ብዙ ገቢር ያላት ስትሆን አንደኛው እሄው እንሆ በእንደዚሁ መልክ አቅርቤላችኃለሁ።
❤️#መሪጌታ አምደ ብርሃን !!!
👉የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
👉0918487073
👉0920253444
👉0918834904
መልእክት ለማስቀመጥ
@merigetaamedeberhan 👈
@mergetaam 👈
እናመሰግናለን