#ከዜናዎቻችን| ባንዲራ ይዘው የኢትዮጵያን ብሄራዊ መዝሙር ሲዘምሩ የነበሩ ታዳጊዎች ከትምህርት ቤታቸው ታፍሰው ተወስደው እንደተደበደቡ ታወቀ
(መሠረት ሚድያ)- ጀሞ 1 የሚገኘው የሳውዝ ዌስት አካዳሚ ተማሪዎች የሰንደቅ አላማ ቀንን ለማክበር እያንዳንዳቸው አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ለየብቻ፣ ማለትም አንዱ ተማሪ አረንጓዴ ሌላው ቀይ ሌላው ቢጫ ለብሰው እና የጥላሁን ገሰሰን "ኢትዮጵያ" መዝሙር ሲዘምሩ ቆይተው ኋላ ላይ ግን ለምን ይህን ቀለም ያለበት ልብስ ለበሳችሁ ብለው የፀጥታ አካላት የጅምላ እስር እንደፈፀሙባቸው መሠረት ሚድያ ያሰባሰበው መረጃ ያሳያል።
በሶስት መኪናዎች ተጭነው የመጡት የፖሊስ አባላት ባለ ኮከቡን የኢትዮጵያ ባንዲራ ጭምር ይዘው ሲዘምሩ የነበሩ 30 ገደማ ታዳጊ ተማሪዎችን ጭነው በመውሰድ በቁጥጥር ስር ካዋሉ በኋላ ድብደባ እንደፈፀሙባቸው ታውቋል።
ከተደበደቡት ተማሪዎች መሀል ቢያንስ ሁለቱ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
እነዚህ የ10ኛ ፣የ11ኛ እና የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲሁም ዳይሬክተሩ ሀሙስ እለት ካሰሩዋቸው በኋለ አርብ የተወሰኑትን ከፈቱዋቸው በኋላ ዳይሬክተሩን እና የተወሰኑ ተማሪዎች አስረው አቆይተዋል ተብሏል።
"የራሱን የመንግስት በአል ማክበር ያሳስራል ወይ? በጣም ነው ያዘንነው" ያሉት አስተያየት ሰጪዎች የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆቻችን ላይ የደረሰውን ግፍ እና በደል ይወቅልን ብለዋል።
ባንዲራ ከመልበሳቸው ጀርባ የሆነ አላማ አለ በሚል ጥርጣሬ እስሩ እና ድብደባው እንደተፈፀመ ምንጮቻችን ጠቅሰው የወረዳ አመራሮች የልጆቻቸውን ከእስር መፈታት ሊጠይቁ ሲሄዱ "የፈለገ በክላሽ መግጠም ይችላል፣ ምላሽ እንሰጣለን" የሚል አሳዛኝ ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።
ማርያም ሰፈር በሚገኘው ፖሊስ ጣብያ በታዳጊዎቹ ላይ የተፈፀመው ድብደባ ልባቸውን የሰበረው ወላጆች "ፖለቲካ ምንድን ነው ቢባሉ እንኳን ምላሽ የሌላቸውን የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች አጉሮ መደብደብ የግፍም ግፍ ነው" ብለው በምሬት ተናግረዋል።
(#ከዜናዎቻችን በሳምንቱ በቪድዮ ዩትዩብ ላይ ያቀረብናቸውን የተመረጡ መረጃዎች ቆየት ብለን በድጋሜ በፅሁፍ የምናቀርብበት አምድ ነው)
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia