#ከዜናዎቻችን| ዶናልድ ትረምፕ እና አፍሪካ ከፕሮጀክት 2025 አንፃር ሲታይ
(መሠረት ሚድያ)- የዶናልድ ትረምፕ ፕሬዝደንት ሆኖ መመረጥ በኢትዮጵያ እና በጠቅላላው ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሊኖረው እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል።
በርካታ የኢትዮጵያ የመንግስት ሚድያዎች የትረምፕን መመረጥ በደስታ እንደተቀበሉ በሚመስል መልኩ ሲያሞካሹ እና የጆ ባይደን አስተዳደርን ሲኮንኑ እየታየ ይገኛል።
የቀጠናው ተንታኞች ግን እውነታው ከዚህ የራቀ እና ምናልባትም ከጆ ባይደን አስተዳደር በባሰ የዶናልድ ትረምፕ አስተዳደር ጎጂ ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን እያስቀመጡ ይገኛሉ።
ይህን ለማስረዳትም "ፕሮጀክት 2025" የተባለውን የድብቅ እቅድ ያነሳሉ።
በዚህ እቅድ መሰረት ፕረምፕ ግብፅን እና እስራኤልን ያቀፈ ጠንካራ ትብብር ለመመስረት እቅድ እንዳላቸው ተደጋግሞ ይነሳል፣ ይህ ደግሞ ከኢትዮጵያ ጋር ቅራኔ ላይ ላለችው ግብፅ ከፍተኛ እድል ሊከፍት ይችላል ተብሏል።
ትረምፕ የግብፁን መሪ አል ሲሲን "የምወደው አምባገነን መሪ" ብለው ከዚህ በፊት ሲያሞካሹ እንደነበር ይታወሳል።
በሌላ በኩል የትረምፕ አስተዳደር አፍሪካ ውስጥ ከቻይና ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላቸውን ሀገራት በእቀባ ሊቀጡ እንደሚችሉ ምልክቶች አሉ።
ትረምፕ ከቻይና ጋር የንግድ ጦርነት ሊጀምሩ እንደሚችሉ በምርጫ ቅስቀሳቸው ላይ ሲጠቅሱ ተሰምተዋል፣ ታድያ የዚህ ጦስ ለቻይና የአፍሪካ አጋር ሀገራት እንዳይተርፍ ስጋት አለ።
በዚህም በተጨማሪ ትረምፕ ጦርነት በሚነሳባቸው ሀገራት ጣልቃ በመግባት ለማርገብ ሙከራ ከማድረግ ይልቅ "አያገባንም፣ የራሳችሁን ችግር ራሳችሁ ፍቱ" የሚለው አካሄዳቸው ለአፍሪካ አምባገነን መሪዎች የተመቸ፣ ለሚጨቆነው ህዝብ ግን የሞት ፍርድ ሆኖ ሊታይ እንደሚችል ተንታኞች እያነሱ ይገኛሉ።