ጋዜጠኛ እና ደራሲ ዜናነህ መኮንን አረፈ
(መሠረት ሚድያ)- አንጋፋዎቹ መገናኛ ብዙሀን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን በ70ዎቹ እና 80ዎቹ ሲታወሱ ዛሬም ድረስ ስሙ በጉልህ ይነሳል። የታሪክ ተመራማሪ፣ የመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካ ተንታኝ እና የጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ልዩ እና ተወዳጅ ዘጋቢ ነበር።
ዜናነህ መኮንን ከጋዜጠኛነቱ በተጨማሪ ደራሲ፣ ገጣሚና ሃያሲም ነበር። ከግርማ ሞገሱ ጋር ግርማ ሞገስን የሚያላብስ ልብስ ለብሶ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሸቱ ሁለት ላይ “ጤና ይስጥልኝ እንደምን አመሻችሁ ከሰዓቱ ዜና ጋር ዜናነህ መኮንን ነኝ” በማለት እጅ ሲነሳ የብዙዎች ትዝታ ሆኖ አልፏል።
በበርካታ የቲቪ እና የሬድዮ ተከታታዮች ዘንድም የሚወደድ ነው፡፡ የጀርመን ድምጽ (ዶቼ ዌሌ) የጣቢያው መክፈቻና መዝጊያ ድምፅ የዚሁ አንጋፋ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ዜናነህ ኑሮውን በእየሩሳሌም ካደረገ ዘመናት ተቆጥረው ነበር።
Via Tewedaje Media
#መሠረትሚድያ #MeseretMedia
@MeseretMedia