የዳኝነት ክፍያን እስከ 500 ፐርሰንት የሚጨምረው ህግ ዛሬ ፀደቀ
(መሠረት ሚድያ)- የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣው ረቂቅ ደንብ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀ ሲሆን መሠረት ሚድያ የተመለከተው ይህ የክፍያ ወሰን እስከ 500 ፐርሰንት ጭማሪ ተገልጋዮች ላይ ይጥላል።
ደንቡን ማሻሻል ያስፈለገው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከዚህ ቀደም የሚጠቀሙበት የዳኝነት ገንዘብ አከፋፈል ለ72 ዓመታት ማሻሻያ ሳይደረግበት የቆየ መሆኑ የተገለፀ ቢሆንም እስከ 500 ፐርሰንት ጭማሪ ማድረጉ በተለይ አሁን ላይ ካለው የኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ለብዙዎች አስገራሚ ሆኗል።
መሠረት ሚድያ የተመለከተው እና በቅርቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እንደሚወጣ የሚጠበቀው ዛሬ የፀደቀው የዳኝነት ክፍያ ከዚህ በፊት ለሁለት ሚልዮን ብር የክስ ገንዘብ መጠን ይከፈለው የነበረው 23,000 ብር ወደ 82,000 ብር ጨምሯል።
ይህ የተጋነነ ክፍያ ሰዎች ፍትህ ለማግኘት ወደ ፍትህ ተቋማት እንዳይሄዱ እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ እየተጠቆመ ይገኛል።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia