አሜሪካ በሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳ ለተከሰተው ድርቅ እና የምግብ እጥረት ምግብ እየተላከ መሆኑን አስታወቀች
(መሠረት ሚድያ)- አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የተከሰተውን ድርቅ እና የምግብ እጥረት ተከትሎ እርዳታ ወደ ስፍራው እየተላከ መሆኑን አስታውቋል።
ኤምባሲው በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፁ እንዳስታወቀው በወረዳው ድርቅ እንደተከሰተ ከሰሞኑ እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች ላይ ክትትል አድርጓል።
"የኢትዮጵያ ህዝብን ለመደገፍ አጋሮቻችን ምግብ እና አልሚ ምግቦችን ወደተጠቁት ስፍራዎች እየላኩ ነው" ያለው ኤምባሲው ሁኔታውን በቀጣይም በመከታተል ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሰራ አስታውቋል።
መሠረት ሚድያን ጨምሮ አንዳንድ ሚድያዎች ከሰሞኑ በሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳ ስለተከሰተው ድርቅ ሲዘግቡ ቆይተዋል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው እና በርሀብ እጅግ የተጎዱ ህፃናት ምስልም በማህበራዊ ሲዘዋወር ነበር።
መረጃን ከመሠረት!
@MeseretMedia