ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6

" አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን
አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም
ለእግዚአብሔር እልል በሉ።"
(መዝሙረ ዳዊት 47:1)

ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧


Forward from: ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
መልካም ዜና ለአእላፍት ዝማሬ ቤተሰቦች ❤️‍🔥

የአእላፍት ዝማሬ መዝሙሮችን በነፃ የምታገኙበት አዲስ ቻናል ተገኝቷል፣ በቀላሉ ቻናሉን ለማግኘት
👇


እስጢፋኖስ ሰማዕት

እስጢፋኖስ ሰማዕት ሊቀ ዲያቆናት
ለምዕመናን የተሾምክ❨፪×❩
የአምላክህን ትዕዛዝ በስራ የፈጸምክ❨፪×❩

የስምህ ትርጓሜ የክብር አክሊል ነው
እስጢፋኖስ ፀሐይ ገድልህ የሚያበራው
ስድብና ዛቻ በድንጋይ መወገር
አንተን አይለይህም ከክርስቶስ ፍቅር
       /አዝ = = = = =
ሕዝብን እንድትመራ በወንጌሉ ፋና
የስምንት ሺህ ነፍስ ምግባር ልታቀና
አምላክ ከፍ አረገህ በከበረው ሹመት
ጸጋን ተጎናጸፍክ መንፈሳዊውን ሀብት
       /አዝ = = = = =
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በጥበብ ተሞልተህ
አንገትህን በማቅናት ወደ ሰማይ አይተህ
ከሙታን ተነሥቶ በክብር ያረገውን
በአብ ቀኝ ቆሞ አየህ ኢየሱስ
       /አዝ = = = = =
በኩረ ሰማዕታት ሊቀ ዲያቆናት
የቤትህ መሰረት ታንጿል በዐለት
አይፈርስም አይወድቅም በመከራ ዋዕይ
ዋጋውን ስላየ ያለውን በሰማይ
/አዝ = = = = =
ብድራትን ሁሉ እስጢፋኖስ አይቶ
ለፍቅር የሞተውን አከበረው ሞቶ
አትቁጠርባቸው ይህን እንደ ኃጢአት
እያለ ለመነ ለጠላቶች ምህረት

👉ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

 ╔✞════●◉❖◉●════✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
@enamsgn @enamsgn
@enamsgn @enamsgn
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞════●◉❖◉●════​✞╝
✍ ወድሰኒ


Forward from: ወድሰኒ ​​
​​​​​​ቅዱስ እስጢፋኖስ

በሐዋርያት ስብከት ቤተ ክርስቲያን ስትስፋፋ በትምህርታቸውና በተዐምራታቸው ተስበው ወደ ክርስትና እምነት የተመለሱ ከአይሁድና ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ክርስቲያኖች መሬታቸውንና ጥሪታቸውን በመሸጥ  ያላቸውን ሀብት አንድነት በማድረግ በኢየሩሳሌም የአንድነት ኑሮን ይኖሩ ነበር፡፡ በሕብረትም የሐዋርያት ትምህርትን በመስማትና በጸሎት ይተጉ እንዲሁም ማዕድን በመባረክ በጋራ ይመገቡ ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም “አንድ ልብና አንዲት ነፍስ አላቸው በማለት (የሐዋ.4፡32) ስለአንድነታቸው ፍጹምነት ይነግረናል፡፡

ነገር ግን በቁጥር እየበዙ ሲመጡ በመካከላቸው በማዕድ ምክንያት ልዩነት ተፈጠረ፡፡ ከይሁዲነት ወደ ክርስትና የተመለሱ ክርስቲያኖች በምግብ ክፍፍል ወቅት ከግሪክ የመጡትን ይጸየፉዋቸው፣ በተለይ ባልቴቶቻቸውን ቸል ይሉባቸው ስለነበር በማኅበሩ መካከል አለመስማማት ተፈጠረ፡፡ ይህም በሐዋርያት ዘንድ ተሰማ፡፡

ሐዋርያትም “የእግዚአብሔርን ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ አይደለም” (የሐዋ.6፡2) በማለት ማዕዱንና በውስጥ ያለውን አገልግሎት ያስተናብሩ ዘንድ ሰባት ሰዎች እንዲመረጡ የክርስቲያኑን ኅብረት ጠየቁ፡፡ ምዕመናኑም በአሳቡ ደስ ተሰኝተው መንፈስ ቅዱስና ጥበብ የሞላባቸውን ሰባት ክርስቲያኖችን መረጡ፡፡ ሐዋርያትም እጆቻቸውን ጭነው ረድእ ይሆኑአቸው ዘንድ ዲያቆናት አድርገው ሾሙአቸው፡፡

ከእነዚህም ዲያቆናት መካከል በቅድስና ሕይወቱ ለክርስቲያኖች ዓብነት የሆነው ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ይገኝበታል። እስጢፋኖስ የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “አክሊል” ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ግእዝ በኋላም ወደ አማርኛ የመለሱት አባቶች በቀጥታ የግሪኩን እስጢፋኖስ የሚለውን ቃል ተጠቅመዋል፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ምንም እንኳ ስሙ የግሪክ ስም ይሁን እንጂ በትውልዱ አይሁዳዊ ነው፡፡ ወላጆቹ ይህንን ስም ሊሰጡት የቻሉት በፍልስጤም ጠረፋማ ከተሞች ይኖሩ ስለነበር የግርክ ባሕልና ቋንቋ ተጽእኖ አድሮባቸው ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡

ቅዱስ እስጢፋኖስ በሐዋርያት ጥበቃ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ከአምላክ ዘንድ ባገኘው የማስተማርና የፈውስ ሀብት ያገለግል ነበር፡፡ በእርሱም ታላላቅ ተኣምራት ይፈጸሙ ነበር፡፡ ስለዚህም ሕዝቡ ከፊት ይልቅ እጅግ እየበዛና በትምህርት እየጠነከረ መጣ፡፡ አይሁድም ይህን ተመልክተው በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ በቅናትና በጠላትነት ተነሡበት፡፡ ነገር ግን ከመንፈስ ቅዱስ ባገኘው ጥበብና ኃይል እነርሱን በቃልም በድርጊትም ይቃወማቸው ነበርና ሊረቱት አልተቻላቸውም፡፡

ስለዚህም እግዚአብርሔርን፣ ሙሴ ሲሳደብ ሰምተነዋል፣. ሙሴ የሠራልንን ሥርዐት ይለውጣል፣ በዚህ ቤተ መቅደስና በሕጉ ላይ የስድብን ቃል ይናገራል፣ ይህንንም ቤተ መቅደስ የናዝሬቱ ኢየሱስ አፍርሱ ብሎአል እያለ ያስተምራል አያሉ፣ ሕዝቡን፣ ሽማግሌዎችንና ጸሐፍትን በማናደድ ይዘው ከሸንጎ ፊት አቆሙት፡፡

ቅዱስ እስጢፋኖስን በሸንጎ ፊት ባቆሙት ጊዜም ፊቱ ልክ እንደ መልአክ ፊት ሆኖ በርቶ ነበር፡፡ እርሱም ለተከሰሰበት ነጥብ መልስ ሰጠ፡፡ ከአብርሃም እስከ ክርስቶስ ለእነርሱ የተሰጣቸውን በረከት በመቃወማቸው ከተስፋ ቃል እርቀው እንደተወገዱ ገለጠላቸው፡፡ ክርስቶስንም ባለመቀበላቸው ወቀሳቸው፡፡ በዚህም ምክንያት በቁጣ ተነሣስተው ከከተማ ውጭ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡

ቅዱስ እስጢፋኖስ አይሁድ በድንጋይ እየወገሩት ሳለ ሰማያት ተከፍተው ክርስቶስን በአብ ቀኝ ቆሞ ተመለከተ፡፡ ይህንን ራእይ የክርስቶስን ትንሣኤን ለማይቀበሉት አይሁድ አሰምቶ ተናገረ፤ እነርሱ ከፊት ይልቅ በእርሱ ጨከኑ በድንጋይም ወገሩት፡፡ ነገር ግን ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታውን ክርስቶስን መስሎ ነበርና ልክ እንደ መምህሩ ክርስቶስ “አቤቱ ይህን ኀጢአት አትቁጠርባቸው” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኾ  ነፍሱን ሰጠ፡፡ በቤተክርስቲያንም ታሪክ ስለክርስቶስ መስክሮ ሰማዕትነትን የተቀበለ የመጀመሪያው ዲያቆን ሆኖአል፡፡

በደማስቆ መንገድ ላይ ክርስቲያኖችን ያሳድድ የነበረ ሳውል በኋላም ቅዱስ ጳውሎስ ተብሎ ስያሜ የተሰጠው ሐዋርያ  ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ በሚወግሩበት ወቅት በእርሱ ሞት ተስማምቶና ድንጋይን በእስጢፋኖስ ላይ ያነሡትን የአይሁድ ልብስ ይጠብቅ የነበረ ብላቴና ነበር፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ከሆነ በኋላ የእስጢፋኖስን ቤተሰቦች አጥምቆአቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ ድንቅ ነው፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ይህን ቅዱስ የመታሰቢያ ቀን በመስጠት ጥቅምት 17 የዲቁና ማዕረግን በአንብሮተ ዕድ በሐዋርያት የተቀበለበትን፥ ጥር 1 ደግሞ ዕረፍቱን ታስባለች፡፡

የቅዱሱ በረከት በሁላችንም ላይ ይደርብን!


ወንድ ልጅ ተሰጠን

ወንድ ልጅ ተሰጠን ህፃን ተወለደ❨፪×❩
በለቢሰ ሥጋ ኮነነ ዘመደ❨፪×❩
               ኧኸ
በለቢሰ ሥጋ ኮነነ ዘመደ❨፪×❩

ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ የተባለው አዳም
ይኸው ተወለደ ኪዳኑን አልረሳም
በሞት ጥላ ላለን ጨለማን አራቀ
አማናዊው ፀሐይ እም ድንግል ሰረቀ
          /አዝ = = = = =
ተመኝቶ ነበር ሙሴ ገፁን ሊያየው
አይተኸኝ አትቆምም ብሎ ከለከለው
እርሱ ጀርባውን ሲያይ አዘልሽው በጀርባሽ
ከሁሉ መረጠሽ ትውልዱ ፊት በራሽ
          /አዝ = = = = =
ፊታቸውን ጋርደው መላእክት ሲቆሙ
እናቱ ነሽና ክንድሽ ላይ ነው ፍህሙ
ይህ እሳት ወረደ ቤተልሄም ግርግም
በእጆችሽ ዳሰስነው አላቃጠለንም
          /አዝ = = = = =
በአባቱ እቅፍ ያለው እስከሚተርከው
አንድስ እንኳን የለም እግዚአብሔርን ያየው
ቢለንም ዮሐንስ በቃለ ወንጌሉ
ዓየነው በአንቺ እቅፍ በተለየ አካሉ
          /አዝ = = = = =
በአባቱ እቅፍ ያለው እስከሚተርከው
አንድስ እንኳን የለም እግዚአብሔርን ያየው
ቢለንም ዮሐንስ በቃለ ወንጌሉ
ዓየነው በአንቺ እቅፍ በተለየ አካሉ

👉ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

 ╔✞════●◉❖◉●════✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
@enamsgn @enamsgn
@enamsgn @enamsgn
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞════●◉❖◉●════​✞╝
✍ ወድሰኒ


🗣 የበግ ቆዳ ያለው?

ለገና በዓል በቤትዎ ወይም በአካባቢዎ ከሚከናወኑ እርዶች የበግ እና የፍየል ቆዳን ለሐመረ ብርሃን በመስጠት የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ፣ ትውፊት እና ታሪክ ያስቀጥሉ።

የመቀበያ ቦታዎች ፦

📍ፒያሳ አሮጌው ፖስታ ቤት
📍ሰአሊተ ምሕረት
📍አየር ጤና ኪዳነ ምሕረት
📍መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል
📍ጀሞ መድኃኔዓለም
📍ገላን ልደታ ለማርያም


ለበለጠ መረጃ፦

09 66 76 76 76
09 44 24 00 00
09 09 44 44 55
09 44 17 61 26


ሀሌ ሀሌሉያ

ሀሌ ሀሌሉያ❨፪×❩በሠማይ በምድር
ምህረት ሆኗልና ሀሌ ሀሌሉያ
አሜን ሀሌሉያ

መላዕክት ዘመሩ አመሠገኑት
እየተደነቁ በአምላክ ቸርነት❨፪×❩
ስብሐት ለእግዚአብሔር በሠማያት አሉ
እረኞችም አብረው እርሱን አከበሩ❨፪×❩
       /አዝ = = = = =
ዓለምን ለመፍጠር ከተጠበበበት
ይበልጣል ከሁሉም እኛን ያዳነበት❨፪×❩
ከዳግማዊት ሄዋን ከእመቤታችን
በረቂቅ ጥበቡ ተወልዶ አዳነን❨፪×❩
       /አዝ = = = = =
ሁላችሁም ሂዱ ከቤተልሔም
ታገኙታላችው በከብቶች ግርግም❨፪×❩
ኢየሱስ ክርስቶስ ወሃቤ ሠላም
ሞታችንን ወስዶ ሕይወቱን ሠጠን❨፪×❩
       /አዝ = = = = =
ሁላችሁም ሂዱ ከቤተልሔም
ታገኙታላችው በከብቶች ግርግም❨፪×❩
ኢየሱስ ክርስቶስ ወሃቤ ሠላም
ሞታችንን ወስዶ ህይወቱን ሠጠን❨፪×❩

👉ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

 ╔✞═══●◉❖◉●════✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
@enamsgn @enamsgn
@enamsgn @enamsgn
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
╚✞════●◉❖◉●════​✞╝
✍ ወድሰኒ


በጎል_ሰከበ

በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ
ቤዛ ከሉ ዓለም❨፪×❩ዮም ተወልደ
በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ
የዓለም መድኀኒት❨፪×❩ ዛሬ ተወለደ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖
@mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ


ኖሎት_ርእይዎ

ኖሎት ርእይዎ መላእክት አእኩትዎ
ዮም ሰማያዊ❨፪×❩ ሰከበ በጎል

     #ትርጉም
እረኞች አዩት መላእክት አመሰገኑት
ዛሬ ሰማያዊው በበረት ተገለጸ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖
@mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ


ተወልደ_ኢየሱስ

ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም❨፪×❩
ዘይሁዳ በቤተልሔም
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ❨፪×❩
በቤተልሔም

#ትርጉም

የይሁዳ ቦታ በሆነችው በቤተልሔም
ኢየሱስ ተወለደ
ያን ጊዜም የጢሮስ ቆነጃጅቶ/ልጆች/ሰግደዋል

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖
@mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ


ተወለደ ሕጻን ሆነ

ተወለደ ሕጻን ሆነ በቤተልሔም ተመሰገነ
ቤዛ ኲሉ ዓለም ተወለደ ከማርያም

ሕጻናት እንሂድ❨፪×❩ ወደ በረቱ
ተኝቷልና በግርግም ታቅፎ በእናቱ
       /አዝ = = = = =
ሰማያዊ ነው❨፪×❩ ወላጅ አባቱ
የአዳም ልጅ ናት የዳዊት ልጅ ናት ድንግል እናቱ
       /አዝ = = = = =
ሰላም ሰፈነ❨፪×❩ በምድራችን
ተወልዷልና ሕጻን ኢየሱስ ለሁላችን

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖
@mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ


📌ክፍል አስራ አንድ የልደት መዝሙር


🎁 1000 ብር የሚያሸልመው ውድድር ሊጀመር ነው ፤ ዝግጁ ስትሆኑ ሊንኩን ይንኩት እና JOIN REQUEST የሚለውን ይጫኑት👇

          http://t.me/hrummebot/game?startapp=ref1088049228


'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>💁‍♂ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል።  ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
              'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'> ክፈት        ክፈት               
               ክፈት        ክፈት               
                                                   
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
                                                    
                                                   
                                                    
                                                    
                                                     
               ክፈት         ክፈት              
               ክፈት         ክፈት


Forward from: ወድሰኒ ​​
​​​​ታህሳስ 24

በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክልሃይማኖት የተወለዱበት ቀን ነው። የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ጽላልሽ አወራጃ ዞረሬ ነው፤ የአባታቸው ስም ጸጋ ዘአብ የእናታቸው ስም እግዚ ሐርያ ይባላል መካን ነበሩ ልጅ እንዲሰጣቸው ወደ እግዚያብሔር ዘወትር ይጸልዩ ነበር፤ መጋቢት 12 ቀን እንዲህ ሆነ።

ሞተሎሜ የተባለ ጣኦት አምላኪ ንጉስ አገራቸውን ወረረ መንደሩንም አጠፋ ጸጋ ዘአብ ወንዝ ውስጥ ገብቶ አመለጠ እግዚ ሐርያ ግን ተማርካ ሄደች፤ በጣም መልከ መልካም ስለነበረች ሞቶሎሜ ሊያገባት አሰበ ታላቅ ድግስም ደገሰ አገር ምድሩ ተሰብስቦ ሲዘፍን ሲጨፍር ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መብረቅ ነጎድጓድ አሰማ ብዙዎች ሞቱ እግዚሐርያን በክንፎ ተሸክሞ ዞረሬ ከቤተክርስቲያን ውስጥ አስቀመጣት ከባለቤቷ ጸጋ ዘአብ ጋር ተገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ፤ከሁለት ቀን በኃላ መጋቢት 24 ቀን ተክለሃይማኖት ተጸነሱ።

በዛሬዋ ቀን 1167 ዓ/ም ተወለዱ ቀኑ አርብ ነበር፤ በተወለዱ በ3ኛ ቀናቸው እሁድ በ 3 ሰዓት “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ብለው ሥላሴን አመሰገኑ፤ ሁለተኛ ተአምር ከዚህ በታች ያለው ስዕል ተክልዬ የአንድ ዓመት ከመንፈቅ ህጻን እያሉ ነው፤ በድፍን ሸዋ ርሃብ ተከስቶ ነበር በተለይም በዞረሬ እግዚሐርያ አዘነች አለቀሰች ምነው እርቧት ነው ጠምቷት ነው ቢሉ የለም እርቧትስ ጠምቷትስ አይደለም የቅዱስ ሚካኤል ዝክሩ ታጎለቢኝ ብላ እንጂ።

ህጻኑ ተክለሃይማኖት ከእናቱ ጭን ወርዶ እየዳኸ ወደ ጓዳ ሄደ አንስታ አቀፈችው እርሱ ግን አለቀሰ ዱቄት የተቀመጠበትን እንቅብ እንድትሰጠው በእጁ ጠቆማት ሊጫወትበት መስሏት ሰጠችው በትንንሽ እጆቹ እንቅቡ ላይ አማተበ ዱቄቱ ሞልቱ ፈሰሰ ዳግመኛ የቅቤ የዘይት ማስቀመጫ ማድጋዎች ላይ በተመሳሳይ አማተበ ሞልቶ ፈሰሰ ቤቱ በበረከት ተትረፈረፈ፤ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን አዘከረች አገሬውን ጠርታ መገበች፤ ለተቸገሩትም አብዝታ ሰጠች፤ ይህ በረከት ሁለቱም እስኪሞቱ ድረስ አላለቀም ይላል ገድላቸው።

ተክለ ሃይማኖት በ 99 ዓመት ከ8 ወር ከ5 ቀን በዚህ ምድር ኖረው ነሐሴ 24 ቀን አርፈዋል። በደብረሊባኖስ ገዳማቸው የንፍሮ ውኃ አይነስውር ያበራል ድውይ ይፈውሳል ገድላቸው ሊነበብ ሲወጣ አጋንንት ተቃጠልን ይላሉ ሲገርም ምን ያህል ባለጸጎች ነን። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።


💁‍♂እቤቶ ቁጭ ብለው ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?


📡 በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
       'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'> ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
               ይ🀄️ላ🀄️ሉ
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥

🔑 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዘማሪዎች ውስጥ የማንን 'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>ዝማሬ ማግኘት ይፈልጋሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
🔴የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
⚫️የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
ዝ?የቀዳሜጸጋ መዝሙር
⚫️የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
🔴የኪነጥበብ መዝሙር
⚫️የይልማ ኃይሉ መዝሙር
🔴የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
⚫️የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ እና      ወ.ዘ.ተ......
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
               ይ🀄️ላ🀄️ሉ
        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
🛑እነሆ አዲስ ቻናል ይዘንሎት መጣን🛑
በማርያም ይህን ቻናል ሳይቀላቀሉ እንዳያልፉ ይደሰቱበታል መርጠን ለናንተ አቀረብንሎ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

        ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥


         █   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲      █       

 
         ◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬


አንፈርዓጹ

አንፈርዓጹ ሰብአ ሰገል❨፪×❩
አምኃ ሆሙ ኧኸ አምጽኡ መድምመ❨፪×❩
      
ምድር አይታ ቸርነትህን
በበረት ውስጥ መጠቅለልህን
ትህትናህን እያደነቀች
በደስታ ለአንተ ዘለለች
     /አዝ = = = = =
ጥበቃ ላይ እያሉ ተግተው
ከመላእክት ዜማውን ሰምተው
እረኞችም እየተመሙ
ለምስጋና ተሽቀዳደሙ
     /አዝ = = = = =
ያለ ገደብ ስለወደደን
ስጋ ለብሶ የተዛመደን
መድኃኒት ነው ሃይሉ እወቁ
የተዋህዶ  ምስጥር አድንቁ
  /አዝ = = = = =
የተባለው ተስፋችን ደርሶ
የአብ ቃሉ ስጋዋን ለብሶ
ስላየነው በአይኖቻችን
እጥፍ ድርብ ሆኗል ደስታችን

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖
@mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ


በበረት ተመሰገነ

በበረት ተመሰገነ
በአርያም ክብሩ ገነነ
በሠማይ በምልዐት ያለ
በምድርም እኛን መሠለ

በኪሩቤል ጀርባ የሚቀመጥ ጌታ
ዘወትር የሚሠማ የመላዕክት ዕልልታ
እንግዳችን ሆኖ የመጣ ወደ እኛ
ነጻነት ሆነልን ለታሠርነው ለእኛ
       /አዝ = = = = =
ትንቢት ተፈጽሞ እውነት ተገለጠ
የእግዚአብሔር ልጅ ለእኛ ሊያድነን ተሠጠ
በጎል ቤተልሔም በበረት ተኝቶ
ሠላም ታወጀልን ልደቱ ተሠምቶ
       /አዝ = = = = =
ከአዳራሹ ወጣ ታላቁ ሙሽራ
ሰውን ወደ እውነት ወደ ጽድቅ ሊመራ
የእሴይ ቁጥቋጦ ወይን አፍርቶልናል
ይኸው ተወለደ በታላቅ ምሥጋና
       /አዝ = = = = =
ሠባት መጋረጃ ከፊቱ ሲኖር
እንደ ሕጻን ተወልዶ ታየ በክብር
ቤዛችን የሆነ የሕይወት ራስ
ከእናቱ ጋር ታየ ንጉሥ ክርስቶስ
     /አዝ = = = = =
በጎል ቤተልሔም በበረት ተኝቶ
ሠላም ታወጀልን ልደቱ ተሠምቶ
ትንቢት ተፈጽሞ እውነት ተገለጠ
የእግዚአብሔር ልጅ ለእኛ ሊያድነን ተሠጠ
               
ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖
@mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ


አማኑኤል ተወለደ

አማኑኤል ተወለደ❨፪×❩
ዓለም ነጻ ወጣ ጠላት ተዋረደ
ምድር ነፃ ወጣች ጠላት ተዋረደ

ከራድዮን ጌታ ስሙ ድንቅ መካር
በከብቶቹ ስፍራ ታይቶናል በፍቅር
ዓለምን ማረከ በበረት ተኝቶ
ድንገት በበብርሃን የሰውን ልጅ ሞልቶ
        /አዝ = = = = =
በጨርቅ ተጠቅልሎ እንስሳት ሲያሞቁት
ተገኝቷል ኢየሱስ በከብቶቹ በረት
እንደ ተርሴስ ንጉሥ ይዘናል አመሃ
ስላየን ተወልዶ የሕይወታችን ውሃ
        /አዝ = = = = =
ከዋክብትን የሚቆጥረው አማኑኤል ሊቆጠር
ወርዷል ቤተልሔም ከእናቱ ጋር ሊያድር
ያ ደገኛ ትንቢት ታይቶናል ማዳኑ
የመጎብኘት ዕለት መጥቶልናል ቀኑ
        /አዝ = = = = =
እስከ ቤተልሔም መርቶናል ኮከቡ
ዛሬም እንዲሰበክ የፈውስ ረሃቡ
ታዖስ ተገለፀ አዳኙ ማስያስ
በርስታቸን ቆመን ልንል ሥሉስ ቅዱስ
        /አዝ = = = = =
ማያት አፍላጋቱን በእፍኙ የሰፈረ
የሰው ሥጋ ለብሶ በማርያም አደረ
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ሆነ
ሰላምም ለሰው ልጅ በምድር ተወሰነ    
          
👉 ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
    
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

   ╔​✞═══●◉❖◉●═══✞╗
       ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
   ❖
@mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖
   ❖ @mezmuredawit  ❖  
      ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
  ╚✞═══●◉❖◉●═══​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

20 last posts shown.