መዝሙረ ዳዊት


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


🔔🔔🔔 መዝሙረ-ዳዊት 🔔🔔🔔

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረቦችን ትምህርቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉ
@mezmurochh
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@Estifo_17 ላይ ያገኙናል

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱


❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅

'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>📜 የሀገራችን የኢትዮጵያ ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት እንሰጣለን። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
📜


✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝️


እንኳን ለጾመ ነነዌ በቸር አደረሳችሁ

➣ ዘነነዌ ዘሰኑይ ➣


✝️ የቅዳሴ ምንባባት ✝️

ሮሜ ም ፪ ቁ ፩ - ፲፯
ያዕ ም ፭ ቁ ፩ - ፲
ግብ.ሐዋ ም ፪ ቁ ፴፯ - ፍ.ም



✝️ ምስባክ ✝️


ወኢትትሀጐሉ እምፍኖተ ጽድቅ
ሶበ ነደት ፍጡነ መዓቱ
ብፁዓን ኵሎሙ እለ ተወከሉ ቦቱ


    መዝ ፪ - ፲፪



✝️ ወንጌል ✝️


ማቴ ም ፲፪ ቁ ፴፰ - ፵፫



✝️ ቅዳሴ ✝️


ዘእግዚእነ


ፆሙን ለማበርከት ያብቃን ሰብአ ነነዌን የማሩ ዘላለም ሥላሴ ኹላችንም ይማሩን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           💚
@mezmurochh 💚   
           💛
@mezmurochh 💛   
           ❤
@mezmurochh ❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✝ ጾመ ሰብአ ነነዌ ✝            

✞ ጾመ ነነዌ ከአዋጅ አጽዋማት አንዱ ሲሆን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሙ የሚጀመርበት ቀን ደግሞ ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር 17 ቀን ድረስ ነው፡፡ ሲወጣ ወይም ወደፊት ሲገፉ ደግሞ እስከ የካቲት 21 ድረስ ነው፡፡ በእነዚህ 35 ቀናት/ዕለታት/ ስትመላለስ ትኖራለች፡፡ ከተጠቀሱት ዕለታት አይወርድም አይወጣም ማለት ነው፡፡

✞የሦስት ቀኑን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች ሲሆኑ ከተማዋ በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ መሥራቿም ናሞሩድ ነው፡፡ ዘፍ.10፥11-12 ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የሆነ ከተማ እጅግ ሰፊና ያማረ ፤ የከተማው ቅጥር ርዝመት አሥራ ሁለት ኪሎ ሜትር ነበር፡፡ ሰናክሬም ብዙ ሕንፃዎችንም ሠርቶበት ነበር፡፡ /ዮናስ. 4፥11/

✞የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ በኃጢአታቸው ምክንያት ሊጠፉ ሲሉ ቸርነትና ምህረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር ነቢዩ ዮናስ መክሮ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ወደ ነነዌ ሕዝብ ሂድ አለው፡፡ ሉቃ.11፥30 ዮናስ የስሙ ትርጉም “ርግብ” ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ትንቢትን ተናግሯል፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል ፡፡ 2ነገ14፥25፣ ት.ዮና1፥1

✞እግዚአብሔርም “ሄደህ በነነዌ ላይ ስበክ” ባለው ጊዜ “አልሄድም” አለ፡፡ “አንተ መሀሪ ነህ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ስትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ፡፡” ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔር ግን ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧበማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩት ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባህሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ “በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባህር ጣሉኝ” ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነሱም “የሰው ደም በእጃችን እንይሆንብን አይሆንም” አሉት፡፡ ዕጣም ቢጣጣሉ ዮናስ ላይ ወጣ፡፡ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያው የእግዚአብሔር የማዳን መልእክት ዮናስ እንዲያደርስ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ነነዌ አደረሰው፡፡ ዮናስም ከእግዚአብሔር መኮብለል አለመቻሉን ሲረዳና ነነዌ መሬት ላይ መድረሱ ሲነገረው ለነነዌ ሰዎች “ንስሐ ግቡ” ብሎ መስበክ ጀመረ ዮናስ 1እና2 ፡፡ የነነዌ ሰዎች ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ማራቸው /ዮና.3/

✞ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስህተት መሆኑን እግዚአብሔር ቅልን ምሳሌ በማድረግ አስረዳው፡፡ /ዮና.4/ ነቢየ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል፡፡ በስንክሳር ታኅሣሥ 5 እንደሚነግረን ፤ወበልዓ አሐደ ኀምለ ይላል ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር አጥፍቶአል፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የስራጵታ መበለት ሕፃን ዮናስ እንደሆነ /1ነገሥ.17፥19/ ሲያስረዳን ፤ክርስቶስ የዮናስን ከዓሣ ሆድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎታል፡፡ /ማቴ.12፥19-42/ ሉቃ.11፥30-32/፡፡

✞ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፡፡ ይሄውም አስቴር አስቀድማ ሦስት ቀን ጾማ ጸልያ በእሥራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች ኢሳ.4፥15-16፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ልጇ ሕፃኑ ኢየሱስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ እንዳገኘችው ሁሉ ሉቃ.2፥46 ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መሆኑን ገልጿል ሉቃ.13፥32፡፡

✞የነነዌ ሰዎች የተነሳህየን ምሳሌ ናቸው ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺህ በላይ ሕዝቦችና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለሆኑ ያሳዝኑኛል ያለው፡፡

✞ዛሬ ዓለማችን በኃጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለበት ወቅት እኛም ብንመለስ እና ንስሐ በንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለሆነ “ወደኔ ተመለሱ እኔም ይቅር እላችኋለሁ ”ብሎ አስተምሯል፡፡ ቀደምት አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ለምሳሌ ጾመ ነነዌ የሚከተሉትን ምሳለዎች እናገኝባታለን ታሪኩን በማስታወስ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሀሪነት የምናስታውስበት ነው፡፡ ይኸውም ፍጥረቶቹ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርጋል፡፡ ዮናስ ፈቃደኛ ባይሆን እንኳ በተለየ ጥበቡ እንዲሄድ አድርጎታል፡፡ ሌላ ነቢይ አጥቶም አይደለም እሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለፈለገ እንጂ፡፡

✞በዮናስ አማካይነት የተደረጉ ተአምራትን መገንዘብና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመሆኑን ተገንዝበን ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሃይማኖት አባቶች አና ለወላጆች መታዘዝን እንማርበታለን፡፡ እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን ጸልየን ከኃጢአታችን እንድንነፃ ነው፡፡ ብንጾም እራሳችን፣ ሃገራችንን፣ እጽዋቱንና እንስሳቱም ሳይቀር በኛ በደል ምክንያት በድርቅ በቸነፈር እንዳይጠፋ እግዚአብሔር ይቅር ስለሚል ነው፡፡

✞ እግዚአብሔር የበረከት፣ ሀጥያታችን የሚሰረይበት፣ ፀሎታችን ቅድመ እግዚአብሔር የሚደርስበት ጾም ያድርግልን። ለሁላችሁም እንኳን አደረሳችው።

❤️ስለ  ማይነገር ስጦታው   እግዚአብሔር ይመስገን ❤️

ለመቀላቀል   👇
      ┏━━° •❈• ° ━━┓
     💚@mezmurochh💚
     💛@mezmurochh💛
     ❤@mezmurochh
      ┗━━° •❈• ° ━━┛

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን


✞ ጥር ፳፰ ቀን እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የተአምራት በዓል መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረስን ✞

✣ ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ ✣

ወአዝነመ ሎሙ መና ይብልዑ
ወወሀቦሙ ኀብስት ሰማይ
ወኀብስት መላእክቲሁ በልዑ ዕጓለ እመሕያው

ይበሉም ዘንድ መናን አዝመናላቸው
የሰማይንም እንጀራ ሰጣቸው
የመላዕክትንም እንጀራ ሰው በላ

✤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ✤

ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ስም ለዘይጼውዖ ኢየሱስ ክርስቶስ ኀብስት ለዘይበልዖ ኢየሱስ ክርስቶስ ጽዋዓ መድኃኒት ለዘይጸምዖ

✟ የመልክዐ ኢየሱስ ደራሲም አባ ዓምደ ሐዋርያትም ✟

ሰላም ለሐቌከ እንዘቦ ልዕልና ከመ ገብረ ደኩም ዘቀነተ ሐብለ ትሕትና ኀብስት ሕይወቶሙ ክርስቶስ ለእለ ይነሥኡ ስመ ክርስትና አኮአ ኀብስት እስራኤል መና ዘዕሤተ ሞት ፈደየ በሲና

✝ ፫፻፲ወ፰ቱ ርቱዓነ ሃይማኖት በቅዳሴያቸው ✝

ገብረ ተአምራት እስከ ረስየ ማየ ወይነ እስከ አጽገበ አእላፈ ብዙኃ በገዳም

ውኃን ጠጅ እስከማድረግ ድረስ ተአምራትን አደረገ በምድረ በዳም ለብዙ ስዎች እስኪያጠግብ ድረስ

❖ ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያው በወንጌል ❖

ወነሥአ ሰብዑ ኀብስት ወዓሣኒ ወይእተ ጊዜ አአኵቶ ፈተተ ወወሀባ ለአርዳኢሁ ወአርዳኢሁ ለሕዝብ ወበልዑ ኵሎሙ ወጸግቡ

ሰባቱንም እንጀራ ዓሣውንም ይዞ አመስገነ ቈርሶም ለደቀመዛሙርቱ ሰጠ ደቀመዛሙርቱም ለህዝቡ ኹሉም በሉና ጠግቡ

ጥር ፳፰ በዓለ ቸሩ ቅዱስ አማኑኤል

✍️ ምኑን በኀበ ሰብእ ✍️ ፳፻፲፬ ዓ.ም




👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

     ✝️  ታላቅ የበረከት የንግስ ጉዞ ✝️

👉  👉የፊታችን  ጥር  29 /05/17👈👈

★ግመልን በመርፌ ቀዳዳ ያሾለኩ ድንቅ አባት
★በሰማዕትነት ዐርፈው ደማቸው ከፈሰሰበት ከገደሉ ስር በፈለቀው ጸበላቸው
‹‹ታዴዎስ ወማትያስ›› እያለ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያለ የተጠመቀ ሰው እንደ
40 ቀን ሕፃን እንደሚሆን ጌታችን ቃልኪዳን የገባላቸው
★ብዙ መንክራትን የፈፀሙ በብዙ የተረሱ
★ታላቅ ሲሆኑ እንደታናሽ የሚያገለግሉ የትህትና እውነተኛ ተምሳሌት
★ታላቅ ሰማእት ሊቀ ካህናት ገባሬ መንክር
      
    ★ አቡነ ታዴዎስ ዘፅላልሽ ★

ቤተ ክርስቲያኑም ከኢቲሣ በእግር የአንድ ሰዓት ተኩል ርቀት ላይ ይገኛል ነገር ግን በአሁኑ ሰአት መኪና መግባት ስለሚችል ገዳሙ ድረስ ይደርሳል እንደ እግዘብሔርን ፍቃድ በአቅራቢያው የሚገኙትን ገዳማትን  አደሬ ኪዳነ ምህረት ኢቲሳ ተክለሐይማኖት ዳግማዊ ቆሮንቶስ ዋሻ ቅዱስ ሚካኤል እና ማርያም ገዳምን እንሳለማለን ፡፡
    
   የጉዞ ዋጋ 550 መስተንግዶ ሳይጨምር

መነሻ ቀን➡️ ጥር 28 /05/2017 ዓ.ም
መመለሻ ቀን➡️ ጥር  29/05/ 2017 ዓ.ም
መነሻ ሰአት ➡️ ንጋት 3.00 ሰአት

👉ጉዞው ከወዲሁ ምዝገባ ስለተጀመረ  ቀድመው ይመዝገቡ።
ስልክ ቁጥር ፦ 09 01 24 31 49
                  ፦09  37 90 33 87
                  ፦ 09  26 77 06 37

            ✝️ ዋናው አላማ ✝️
👉በጉዞው የተሰበሰበውንም ሆነ የተገኘውን ገንዘብ ለቤተክርስትያኑ ሙሉ በሙሉ ገቢ እንደሚሆ ሊያውቁልን ይገባል !!!

በምክንያትም ሆነ በሌላ ነገር መምጣት ላልቻላችሁ በእግረ መንገዳችን ላይ እጣን ጧፍ ሻማ ለ ገዳሙ የሚያስፈልገውን ንዋያተ ቅዱሳትን ለበረከት መስጠት ማገዝ የምትፈልጉ እህት ወንድሞቻችን ☝️ ከላይ ባለው ስልክ ይደውሉልንዋናው አላማ እርሱ ስለሆነ። 
ሌላው ላልሰሙት እህት ወንድሞቻችንshare በማድረግ የበረከት ድርሻዎን እንዲወጡ ስንል እንጠይቃለን 🙏🙏🙏


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

✣ ልጅህ ስለሆንኩኝ ✣

✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
💚@mezmurochh💚
💛@mezmurochh💛
@mezmurochh
|❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ልጅ ስለሆንኩኝ

ልጅ ስለሆንኩኝ የሥላሴ ፍጥረት
ተክለ ሃይማኖት ስጠኝ የእጅህን በረከት
ጥቂት ይበቃኛል ባዶዬን ልሙላበት

ቤተ ሰልዮም ነች የሰም መጠርያ
ፈለቀ ትምርትህ ከወንጌል ገበያ
ምንጭ ሆኖ ፈሰሰ እኛም እረካን
የአምላክህን ዝና በገድልህ አየን

አዝ----------------

እልፈ አእላፍ ሆነው በዝተዉ ቢሰለፉ
የጥፍትን ጉድጓድ አጋንንት ቢያሰፉ
ቅዱስ መሰቀልህን ይዘ ትነሳለ
ለነብሴ ዋሰ ሆነ ትቆምላታለ

አዝ----------------

ተክለ ሃይማኖት እኔን በምልጃ አሰበኝ
ረዴት በረከት ከኔ እንዳይለኝ
ታሪኬን ቀይረ ጓዶሎዬን ሞልተ
መራራ ህይወቴን በወንጌል አጣፍጠ

አዝ----------------

ዛሬም ታምራት በዓለም ይሰማል
ቁስለኛው አካሌ በፀበል ድኖል
ፀበል ፈዉሰ ሆኖኝ ከሞት ተርፌሀለው
በኤድኩበት ሁሉ ተክልዬ እልአለው


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
✥ 💚 @mezmurochh 💚 ✥
✥ 💛 @mezmurochh 💛 ✥
✥ ❤ @mezmurochh ❤ ✥
╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


👉 ሰላም ለሰኮናከ ዘተሴሬ በደም አመ እግርከ ተሰብረ በብዙኃ ቀዊም ተክለሃይማኖት ኢዮብ ዘትዕግስትከ ኢዮብ ዘትዕግሥትከ ፍጹም ለደቂቅከ እለ ውስተ ኵሉ ዓለም ከመ ባረኮሙ ኖኀ ለያፌት ወሴም 👈

   መልክአ ተክለሃይማኖት

✝  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

🙏 እንኳን ለሐዲስ ሐዋርያ ለመምህረ ትሩፋት አባታችን ለአቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ በዓል  አደረሳችሁ አደረስን 🙏

👉 ጥር ፳፬(24) ወስብረተ እግሩ ለአቡነ ተክለሃይማኖት ማርያም እስክንድራዊት ወአባ አብሳዲ ወሲፉ ሰማዕት ወአባ መርሐ ክርስቶስ 👉

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

እስመ መምህር ህግ ይሁብ በረከተ
ወየሁውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያሰተርኢ አምላክ አማልክት በጽዮን

✤ ትርጉም ✤

የህግ መምህር በረከትን ይሰጣልና
ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ
የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል

              መዝ ፹፫-፮
                     83   6

✤ ወንጌል ✤

ማቴ ም ፭ ቁ ፩-፲፯
            5    1   17

✝ የቅዳሴ ምንባባት ✝

ቲቶ ም ፪ ቁ ፩-፱
፩ ጴጥ ም ፫ ቁ ፩-፭
ግብ.ሐዋ ም ፳ ቁ ፳፰-፴፩

❖ ምስባክ ❖

ካህናቲከ ይለበሱ ጽድቁ
ወጻድቃኒከ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑ
በእንተ ዳዊት ገብርከ

🙏 ትርጉም 🙏

ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ
ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው
ስለ ዳዊት ስለ ባርያህ

            መዝ ፻፴፩-፱
                   131   9

❖ ወንጌል ❖

ሉቃ ም ፲፰ ቁ ፩-፱
           18    1   9

❖ ቅዳሴ ❖

ዘባስልዮስ

" አቤቱ ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና ያልታሰበውን ቅዱስ ስምህን ለሚወዱ ያዘጋጀህ አምላክ ምን ትደንቅ "
            ቅዳሴ ባስልዮስ
               ም ፩ ቁ ፻፴፪
                    1     132


❖ ማሳሰቢያ የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ጥር ፳፬ ቀን የሚከበረው የአንድ እግራቸው አገዳ ከመቆም ብዛት የተሰበረበት ቀን አንድ እግራቸው አገዳ የተሰበረው ጥር ፬ ቀን ነው ግን አባቶች በሠሩት ሥርዓት በዓላቸው በሚከበሩበት ዕለት በ፳፬ እንዲሆን በማድረጋቸው ጥር ፳፬ ቀን ይከበራል
 
✝ በዓሉን በዓለ ምህረት በዓለ በረከት በዓለ ፀጋ ያድርግልን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ ይማረን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ አትለየን በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ይጠብቀን ቤተክርስቲያን በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክትን አያሳጣን የ አባታችን የ አቡነ ተክለሃይማኖት በረከታቸው ይደርብን በቅዱሳኑ ፀሎት ይማረን ዝማሬ ዳዊት ቅዳሴ መላዕክት ዕጣነ አሮን መልክአ ተክለሃይማኖት የተቀበለ የኛንም ፆም ፀሎት ምስጋና ምጽዋት በብሩህ ገጽ ይቀበልልን ለአበው ቅዱሳን ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ለአባ ሕርያቆስ ለቅዱስ ያሬድ ለአባ ጊዮርጊስ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት ለቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ ለቅዱስ ደቅስዮስ ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ለቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ለአባ ኪሮስ ለአቡነ አቢብ ለአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ለአባ ሳሙኤል ዘቀልሞን ለገብረክርቶስ መርዓዊ ለአቡነ ሃብተማርያም ለቅዱስ ላሊበላ ለአባ ጽጌድንግል ለአባ ገብረማርያም ዘደብረ ሐንታ ለአባ ገብረኢየሱስ ዘመጓዬና ለቅዱስ ቴዎድጦስ ዘእንቆራ ለአቡነ ተክለሃይማኖት ለአበው ቅዱሳን ሁሉ የተለመነች እመ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምህረት ትለመነን ለሃገራችን ስላም ለኛ ጤና ለህዝባችን አንድነት ይስጥልን ሁላችንም ለንስሐ ያብቃን ✝️

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           💚
@mezmurochh 💚   
           💛
@mezmurochh 💛   
           ❤
@mezmurochh ❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
@teksochina_meslochi
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

  ሙሀዘ-ስብሐት ልዑልሰገድ ጌታቸው

       ✧ ነፍሴ የወደደችውን ✧

  ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           💚 @mezmurochh 💚   
           💛 @mezmurochh 💛   
           ❤ @mezmurochh ❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ነፍሴ የወደደችውን አገኘች

ነፍሴ የወደደችውን አገኘች/2×/
እኔም ለዘላለም በእርሱ እረካለሁ/2×/

የጎደለኝ የለም በነፍስ በስጋዬ
ይሄ ነው አልልም ያልሰጠኝ ጌታዬ
ወደ ሰርጉ ጠራኝ ሁሉን አዘጋጅቶ
እውነተኛ መብልን እራሱን ሰውቶ
እውነተኛ መጠጥ እራሱን ሰውቶ

አዝ----------------

መልካሙ እረኛዬ ከቶስ ሳይተወኝ
በለመለመው መስክ አሰማራኝ
ከማይደርቀው ምንጩ ውሃን ጠጥቻለሁ
ከማር የጣፈጠ ቃሉን አግኝቻለሁ/2×/

አዝ----------------

ጌታ ሆይ በደጅህ መጣል ይሻለኛል
ከኃጥአን ድንኳን እጁጉን ይበልጣል
ምንም ሳልናወጽ በቤትህ እኖራለሁ
የነፍሴን ማረፊያ አንተን ስላገኘው/2×/

አዝ----------------

ማንን እንደምይዝ አሁን ተረድቼ
መጣሁ ወደ አምላኬ ዝናውን ሰምቼ
የምፈልገውን ለነፍሴ አገኘሁ
ከቤተመቅደሱ ጸሎት አኖራለሁ/2×/

                        ዘማሪ
    ️ ሙሀዘ-ስብሐት ልዑልሰገድ ጌታቸው

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

   ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥     💚 @mezmurochh 💚   ✥
   ✥     💛 @mezmurochh 💛   ✥
   ✥     ❤ @mezmurochh ❤   ✥
   ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ጥር ፳፩ ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ድንግል የዕረፍቷ መታሰቢያ በዓል ነው ✞

# ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙሩ #

በከመ ሰማዕነ ከማሁ ርኢነ
በሀገር እግዚአ በሀገረ አምላክነ
እግዚአብሔር ሣረራ ለዓለም

እንደ ሰማን እንዲሁ አየን
በሠራዊት ጌታ ሀገር በአምላካችን ከተማ
እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናታል

✣ ጠቢበ ጠቢባን መፍቀሬ ጥበብ አቡሃ ለእግዝእትነ ማርያም ወልደ ዳዊት ቅዱስ ሰሎሞን በመኃልይ ድርሰቱ ✣

ይእተ ጊዜ ረከብኩ ዘአፍቀረት ነፍስየ አኀዝክዎ ወኢየኀድጎ እስከ ሶበ  አባእክዎ ውስተ ቤተ እምየ

ነፍሴን የወደደችውን አገኘሁት
እቅፍ አድርጌም ያዝሁት
ወደእናቴም ወደ ወላጆቼም እልፍኝ

✥ ቅዱስ ያሬድም በድርሰቱ ✥

ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኵሉ

ሞት ለሚሞት ሰው የተገባ ነው የድንግል ማርያም ሞት ግን ከኹሉም እጅግ ይደንቃል

" ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና "  እንዳለ ደራሲ

✣ አባ ጊዮርጊስም በድርሰቱ ✣

ለጸአተ ነፍስኪ ዛቲ እምዓለም ሥጋ መዋቲ አንቲ ወለተ ለማቲ በስብሐት ዘትትአኰቲ በሰጊድ ስላም

❖ የመልክዐ ማርያም ደራሲ አፄ ናዖድም ❖

ሰላም ለግንዘተ ሥጋኪ በእደ ሐዋርያት አርጋብ በአፈወ ዕፍረት ቅድው ዘአሳብ ሤጡ ዕፁብ ማርያም ድንግል ወለተ ኀሩያን ሕዝብ ረሰይኩኪ እግዝእትየ ህየንተ እም ወአብ ይሕጽነኒ ከመ ጥብ ፍቅርኪ ሐሊብ

✟ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም ላይ ✟

ናጥሪ እነከ አርምሞ ወትዕግሥተ ከመ ማርያም እስመ ወደሳ እግዚእነ እንዘ ይብል ማርያምሰ ኀረየት መክፈልተ ሠናየ ዘኢየኀይድዋ

ጥር ፳፩ በዓለ ዕረፍታ ለእግዝእትነ ማርያም (አስተርእዮ ማርያም)

✍️ መነ ትብል ርእስከ ✍️ ፳፻፲፯ ዓ.ም


👉 ሰላም ለፀአተ ለነፍስኪ እንበለ ፃዕር ወፃማ ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ ማርያም ድንግል ክልልተ ሞገስ ወግርማ አጽንዒ በረድኤትኪ ለህይወትየ ድካማ እምሕይወት ኄራን አበው ኢታሕጽጺ ዐቅማ 👉
    
        መልክአ ማርያም

✝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝

🙏 እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ቅዱሳን እግዝእትነ ማርያም ድንግል በዓለ ዕረፍት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረስን 🙏

👉 ጥር ፳፩(21) በዓለ ዕረፍታ ለእግዝእትነ ወኢላርያ ቅድስት ወጎርጎርዮስ ወኤርምያስ ወጳውሎስ መኰንን ወሲላስ ካህን ወቀውስጦስ ወዮሐንስ ወአባ እስክንድርያ ወአስተርእዮተ እግዝእትነ ማኀው ምስለ ዮሐንስ 👉

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር
ወስብሐዮ ለአምላክኪ ጽዮን
እስመ አጽንዐ መናግሥተ ኆኃትኪ

✤ ትርጉም ✤

ኢየሩሳሌም ሆይ እግዚአብሔር አመስግኚ
ጽዮንንም ለአምላክሽ እልል በዪ
የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና

          መዝ ፻፵፮-፩
                 146   1

✤ ወንጌል ✤

ሉቃ ም ፩ ቁ ፷፯-ፍ.ም
           1    67   ፍፃሜው

✝ የቅዳሴ ምንባባት ✝

ገላትያ ም ፬ ቁ ፩-፲፪
፪ ዮሐ ም ፩ ቁ ፩-፯
ግብ.ሐዋ ም ፯ ቁ ፴-፴፭

❖ ምስባክ ❖

በከመ ሰማዕነ ከማሁ ርኢነ
በሀገረ እግዚአ ኃይላን በሀገር አምላክነ
እግዚአብሔር ሣረራ ለዓለም

🙏 ትርጉም 🙏

እንደ ስማን እንዲሁ አየን
በሠራዊት ጌታ አገር በአምላካችን ከተማ
እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናታል

            መዝ ፵፯-፰
                   47   8

❖ ወንጌል ❖

ሉቃ ም ፩ ቁ ፵፯-፶፯
           1     47  57

❖ ቅዳሴ ❖

ዘእግዝእትነ

" እናንተ የክርስቲያን ወገኖች ሆይ በዚህች ቀን እንደ ተሰብስባችሁ እንዲሁ ክብርት በምትሆን በደብረ ጽዮንና በሰማይ ባለች ነፃ በምታወጣ በኢየሩሳሌም ይሰብስባችሁ "
          ቅዳሴ ማርያም
            ም ፩ ቁ ፻፶፮
                1     156

✝ በዓሉን በዓለ ምህረት በዓለ በረከት ያድርግልን በብርሃነ ጥምቀቱ ለሁላችንም ይገለጽልን ቸሩ አምላካችን መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቸርነቱ ይማረን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ በምልጃዋ አትለየን ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን ታሳድርብን በዕፀ መስቀሉ ይባረከን ይጠብቀን ቤተክርስቲያን ቅድስትን በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን በቅዱሳን ፀሎት ይማረን የታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ በረከቱ ይደርብን በዓልን ተከትሎ ከሚመጣ መቅሠፍት አምላከ አቡነ ቀውስጦስ ይሰውረን ይጠብቀን ለሃገራችን ስላም ለህዝባችን አንድነት ይስጥልን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን አቤቱ ባሪያህ የሚሆነውን ሳዕለ ሥላሴን አስበው ድንግል ማርያም ስንል ፍቅሯን ታሳድርብን አቤቱ ለበላይሰብ የተለመነች ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ለቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ለአባ ጊዮርጊስ ለአባ ሕርያቆስ ለቅዱስ ያሬድ ለቅዱሳኑ ሁሉ የተለመነች ለኛም ትለመነን አመት ሰው ይበለን ✝

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           💚
@mezmurochh 💚   
           💛
@mezmurochh 💛   
           ❤
@mezmurochh ❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
@teksochina_meslochi
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔
         
      ገብርኤል ነው አምላክ የሾመው

  ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
            💚@mezmurochh💚   
            💛@mezmurochh💛   
            ❤@mezmurochh❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ገብርኤል ነው አምላክ የሾመው

ገብርኤል ነው አምላክ የሾመው(2)
አናንያን አዛሪያን ሚሳኤልን ከእሳት ያዳነው

ናቡከደነፆር አንተን በግልፅ አይቶ
ለእግዚአብሔር ሰገደ ያንን ምስል ትቶ
ሃሰት እንደሆን ይመስክሩ ሶስቱ
ከዚያች ከባቢሎን(2) የወጡ ከእሳቱ

አዝ----------------

ከአለም በላይ ከቅዱሱ ቦታ
የሰውን ልጅ መረጥክ ልትረዳ ጠዋት ማታ
አንጌቤናይቷ ቅድስትዬን ይዤ ልውጣ
ትመስክር ስላንተ (2) ከነልጇ ትምጣ

አዝ----------------

ልመስክር ስላንተ ነህና ህይወቴ
ገብርኤል (2) ሰመረ ስለቴ
ያአናብስትን አፍ የዘገሀው መላክት
ገብርኤል አንተ ነህ(2) በኛ ሁሉ የታመንክ

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥  💚 @mezmurochh 💚 ✥
   ✥  💛 @mezmurochh 💛 ✥
   ✥  ❤ @mezmurochh ❤ ✥
  ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
@teksochina_meslochi
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


✞ጥር 18 ” ዝርዎተ አጽሙ ” ቅዱስ ጊዮርጊስ

✞ዳግመኛም ያ ከሃዲ ንጉስ ዱድያኖስ ግንድ አምጥተው ቅዱስ ጊዮርጊስን በግንዱ ላይ እንዲቸነክሩት አዘዘ፤በላዩም ላይ ሰም አፍስሰው እሳት እንዲያነዱበት አደረገ ፤ ከዚህም በኃላ እንደመጭመቂያ ሆኖ ከተሰራ የስቃይ መሳሪያ ላይ አወጡት ሰውነቱን እንዲሰነጥቁት እንዲጨምቁት አዘዘ፤

✞አንጀቱ ሁሉ ወጥቶ ከምድር ላይ እስኪዘረገፍ ድረስ እንዲሁ አደረጉበት ነፍሱ ከስጋው ተለየች የሰማእቱን ሰጋ አቃጠሉት ፈጩት አመድም ሆነ በቀፎ አድርገው ይድራስ ወደሚባል ተራራ ላይ በነፋስ ዘሩት ደብረ ይድራስ ማለት ምድረ በዳ ነው ወታደሮቹ የታዘዙትን  ፈጽመው  ተመለሱ።

   ✞ያንጊዜም መብረቅ ነጎድጓድ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ ምድርም ከመሰረቷ እስክትናወጽ ድረስ ከሰማይ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ መላእክትን አስከትሎ በብሩ ደመና ወረደ በተራራውም ላይ ተቀመጠ አራቱን የምድር ነፋሳት የሰማእቱን ስጋ እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው ከሞትም አስነሳው ኃይሉን አሳደረበት ባርኮትም ወደ ሰማይ አረገ፤

  ✞ከዚህ በኃላ ቅዱስ ጊዮርጊስ እየሮጠ ወታደሮቹን ተከተላቸው ወንድሞቼ ቆዩኝ ከናንተ ጋር ልሂድ እያለ ተጣራ የነዚህ የወታደሮች ቁጥር አራት ነው ስማቸው ህልቶን፤አግሎሲስ፤ሶሪስና አስፎሪስ ነው፤

  ✞ይህንን ታላቅ ተአምራት አይተው አምነዋል፤ በኃላም በሰማእትነት ሞተዋል፤ ይህ የሆነው ጥር 18 በዛሬዋ ቀን ነው ይህንንም ቀን ” ዝርዎተ አጽሙ ” ስትል ቤተክርስቲያን ሰማእቱን አዘክራ ትውላለች፤

  ✞በስሙ በታነጹለት አብያተክርስቲያናት በሙሉ ታቦተ ህጉ ውጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል።

  ✞ አራዳ ጊዮርጊስን የተከሉት ደጉ ንጉስ እምዬ ምኒሊክ ናቸው ታዲያ የዚህን ታላቅ ደብር መሰረቱን ሲጥሉ የቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር ከሚገኝበት ቦታ አፈሩን በመርከብ አጓጉዘው በበቀሎ በፈረስ አስጭነው መሰረት አድርገውታል፤ይህንን ከአባቶቻችን የሰማነው ነው፤ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።

  ✞ ✞ ✞
ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ሰማዕት ፀሎት ይማረን በረከቱን ያሳድርብን አማላጅነቱ አይለየን ሰማዕት በረከት ያሳትፈን።

የተሣተውን ✍ ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት     
                         ✍     ✔
❤️ስለ  ማይነገር ስጦታው   እግዚአብሔር ይመስገን ❤️

ለመቀላቀል   👇
      ┏━━° •❈• ° ━━┓
     💚@mezmurochh💚
     💛@mezmurochh💛
     ❤@mezmurochh
      ┗━━° •❈• ° ━━┛

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን

20 last posts shown.