⚪ ዕጣንና ጽንሃ ⚪
✞ ዕጣን/ጥና/ ✞
ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዕጣንን የተመላ ሰማያዊ ማዕጠንት በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እየሰገዱ ለአለም ድህነት የሚለምኑበት ነዉ፡፡ በቤተክርስቲያን ካህናት መንፈቀ ሌሊት፡ በነገህ ጊዜ በቅዳሴ ጊዜ በየማዕዘኑ ዕጣን ያጥናሉ ቅዳሴውን ጸሎቱንና ልመናዉን ወደ እግዚአብሔር ያሳርጉበታል ፡፡
ስለ እጣን የመፅሀፍ ቅዱስ ማስረጃ
ዘጸ 30፥1 የዕጣን መሰዊያዉን ስራ ከግራር እንጨት አድርገው።
ዘጸ 30፥35 በቀማሚ ብለሀት እንደተሰራ፥ በጨዉም የተቀመመ ንጹህና ቅዱስ እጣን አድርገው፡፡
ዘጸ 30፥34 እግዚአብሄርም ሙሴን አለዉ፦ ጣፋጭ ሽቱ ዉሰድ የሚንጠባጠብ ሙጫ በዛጎል ዉስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸትትም ሙጫ፥ ጥሩም ዕጣን ዉሰድ የሁሉም
መጠን ትክክል ይሁን፡፡
ዘፀ 40፥5 ለዕጣንም የሚሆነዉን የወርቅ መሠዊያ በምስክሩ ታቦት ታኖራለህ፥ በማደሪያዉም ደጃፍ ፊት መጋረጃዉን ትጋርዳለህ፡፡ ዘጸ 40፥27 የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን አጠነበት፡፡
ዘሌ 10፥1 የአሮንም ልጆች ናዳብና አብድዩድ በየራሳቸዉ ጥናዉን ወስደዉ እሳት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት በእግዚአብሔር ፊት እሱ ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ፡፡
ዘሌ 16፥12 በእግዚአብሔር ፊት ካለዉ መሠዊያ ላይ የእሳት ፍም አምጥቶ ጥናዉን ይሞላል፥ ከተወቀጠውም ከጣፋጭ እጣን እጁን ሙሉን ይወስዳል ወደ መጋረጃውም
ዉስጥ ያመጣዋል፡፡
ዘኁ 16፥7 ነገም በእግዚአብሔር ፊት እሳት አድርጉባቸው፥ ዕጣንም ጨምሩባቸው እንዲህም ይሆናል እግዚአብሔር የሚመርጠው እርሱ ቅዱስ ይሆናል እናንተ የሌዊ ልጆች
ሆይ እጅግ አብዝታችኀል ብሎ ተናገራቸው፡፡
ዘዳ 33፥10 ፍርድህን ለያዕቆብ፥ ህግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ ፤ በፊትህ ዕጣንን፥ በመሰዊያህም የሚቃጠል መስዕዋት ይሠዋሉ፡፡
መዝ 140፥2 ጸሎቴን በፊትህ እንደ እጣን ተቀበልልኝ ፥ እጅ መንሳቴም እንደሰርክ መስዕዋት ትሁን፡፡
ማቴ 2፥11 ወደ ቤትም ገብተው ህጻኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር እዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት ሣጥኖቻቸዉንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤን አቀረቡለት፡፡
ሉቃ 1፥10 በዕጣንም ጊዜ ህዝቡ ሁሉ በዉጭ ቆመውዉ ይጸልዩ ነበር፡፡
ራእ 5፥8 መጽሀፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንሰሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳዳቸም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ፡፡
ራእ 8፥3 ሌላም መለአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለዉ በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ እጣን ተሰጠዉ
✞ ጽንሃ ✞
ጽንሃ የእጣን ማሳረጊያ ወይም ማጠኛ ነው። ሦስት ሰንሰለቶች አሉት። ሰንሰለቶቹ ሶስት መሆናቸው የሚስጢረ ሥላሴ ምሳሌ ነው። በሰንሰለቶቹ ላይ ቢያንስ አስራ ሁለት (12) ቢበዛም ሃያ አራት (24) ሻኩራዎች ይኖሩታል።
‘’ሻኩራ’’ ማለት ሶስቱ ሰንሰለቶች ላይ ያሉት ክብ ነገሮች ናቸው። የሻኩራዎቹ ቁጥር አስራ ሁለት (12) መሆኑ የሐዋሪያት ምሳሌ ነው። ሃያ አራት (24) መሆኑ ደግሞ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ምሳሌዎች ናቸው ። ከስሩ እጣኑ የሚቀመጥበት ሙዳይ የመሰለ ክፍል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ሲሆን: መለኮት ከሥጋዋ ሥጋ ነፍሱዋ ነፍስ ነስቶ ሰው መሆኑን ያመለክታል። ፍሙ የጌታችን የመለኮትነቱ ምሳሌ ሲሆን እጣኑ እንደሚቃጠልና መዓዛው ሁሉን እንደሚያውድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ብዙዎች ኃጢያት ራሱን መስዋዕት በማድረግ አቅርቦ ዓለሙን ሁሉ ማዳኑን ያሳያል።
የተሣተውን ✍ ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት
✍ ✔
❤️ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን ❤️
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን
ለመቀላቀል 👇
┏━━° •❈• ° ━━┓
💚 @mezmurochh 💚
💛 @mezmurochh 💛
❤ @mezmurochh ♥
┗━━° •❈• ° ━━┛