ምርጥ ምሳሌያዊ ንግግሮች


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Linguistics


በቻናሉ አዝናኝ እና አስተማሪ ምሳሌያዊ ንግግሮች ከሁሉም የአለም ክፍል ተተርጉሞ ይቀርባል

ለማንኛውም አስተያየት ሆነ ጥያቄ @mirtababaloch1bot ላይ ያገኙናል

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Linguistics
Statistics
Posts filter


ጨለማ ውስጥ ብርሀን፤
ውጥንቅጥ ውስጥ ውበት፤
ሞት ውስጥ ህይወት አለ

#thefairytail @mirtababaloch


ህይወቴን ሙሉ ሁሌም ከለመድኩት ውጭ ተጨማሪ ነገር እንዳለ እገምት ነበር፤
ከዛ አንቺን አገኘሁ ያኔ ልክ እንደነበርኩ አረጋገጥኩ... ልክ ነበርኩ!!

#Free_Guy(movie) @mirtababaloch


ሰላም ከፈለክ
ለጦርነት ተዘጋጅ

#ጣልያን @mirtababaloch


ሲለምኗት እንቢ ብላ ሲጎትቷት

#ኢትዮጵያ @mirtababaloch


በቃልህ ልተኩስብኝ
በቅጥፈትህ ልትቆርጠኝ
በጥላቻህ ልትገለኝ....
ትችላለህ
.... ግን ልክ እነደ ህይወት
ዳግም እነሳለሁ

#ማያ_አንጅሎ @mirtababaloch


ፀልይ በደንብ ፀልይ ግን ምን ስጠኝ ብለህ እንደምፀልይ ተጠንቀቅ #ፈረንሳዮች @mirtababaloch


ከምታምነው በላይ ጀግና ከምትገምተው በላይ ጠንካራ ከምታስበው በላይ ብልህ ከምትመኘው እጥፍ ቆንጆ መሆንህን አትርሳ #ሩሚ @mirtababaloch


የሰውን ትክክለኛ ባህሪ ለማወቅ ከፈለክ ስልጣን ስጠው


#አብረሀም_ሊንከን @mirtababaloch


ሁሉንም ተመልከቺ
ዛዛታ እኮናቸው
ግን አንቺ...
ለመስማት ሚያሳሳ
ግጥም ነሽ

#ጆርጅ_ሄርማን @mirtababaloch


ፍቅር ብቻውን በቂ አይደለም፤ ሆኖም አያውቅም

#ያልታወቀ @mirtababaloch


ሰዎች በሁለት ይከፈላሉ: መንግስት ሰለነሱ ሚጨነቅ የሚመስላቸው እና አዕምሮ ያላቸው

#ናታን_ፍሬሰር @mirtababaloch


ለዝሆን እንቁራሪትን መግደል ጀግና አያስብለውም

#ታንዛኒያ @mirtababaloch


በእምነት ተራራም ይገፋል

#ቻይና @mirtababaloch


ጦርነትን የጃጁ ሽማግሌዎች አስጀምረውት፤
ገና ያልኖሩ ለጋ ወጣቶች ይሞቱበታል

#ሞዛምቢክ @mirtababaloch


እንኳን አደረሰን ፤ አደረሳችሁ!

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1442ኛው ዒድ አል አድሀ በዐል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን‼️

ዒድ ሙባረክ መልካም በዐል

🌙 •═•••🍃🌺🍃•••═• ​​🌙

@mirtababaloch


በሰላም ጊዜ ልጅ አባቱን ፤
በጦርነት አባት ልጁን ይቀብራል

#Vijaya @mirtababaloch


ወንዶች የራሳቸውን ነፃነት ከመጠቀም በላይ የሴትን ነፃነት መገደብ ያስደስታቸዋል

#Normal_People(movie) @mirtababaloch


ተአምር ፈልቋል በየመንገዱ

(በእውቀቱ ስዩም)

ዐይኔን ጨፍኜ -እስከምከፍተው
ስንቱ ታሪክ ነው- የተከሰተው
አፌ ላይ ሳይደርስ - ያፈስኩት ቆሎ
ስንቱ ተተክሏል- ስንቱ ተነቅሎ
በፊት በር ሲዘልቅ -ብስራት አብሳሪ
በጉዋሮ ገብቷል- መርዶ ነጋሪ ::

እባብ በረረ- ያለ ልማዱ
ርግብ መሬት ላይ -ሲሳብ በሆዱ
ተአምር ሞልቷል- በየ ሰከንዱ
ተአምር ፈልቋል- በየመንገዱ
አንዴ ከመላክ- አንዴ ከሰይጣን
ለመደነቂያ፥ ጊዜ ነው ያጣን፤


የረመዳን ወር በመጣ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የእሳት በሮች ይዘጋሉ፤ ሸይጣኖችም ይታሰራሉ።


#ነብዩ_መሀመድ(ሰዐወ) #mirtababaloch


ወቅታዊ ምርቃት... አሜን በል !
—----------------------------

ግንባርህን ከቄሮ ዱላ
የኪራይ ቤትህን ከደላላ
ጆሮህን ከመግለጫ
አውቶብስህን ካዲሳባ መውጫ
ያትርፍልህ !

አንገትህን ከገጀራ
አገርህን ከመከራ
ነፍስህን ከባለጊዜ
መንግስትህን ከድንዛዜ
ንብረትህን ከመንጋ አጥፊ
‹ኢሜልህን› ከጠላፊ
ያድንልህ!

እንደተኛህ ‹ሳትከበብ›
ቀን በቁምህ ‹ ሳትመረዝ›
እድሜህ ይርዘም እንዳባይ ወንዝ !
አገርህን ከግብፅ ዛቻ
ወጣትህን ከዘመቻ
ሰላምህን ከዓይን አውጣ
አዝመራህን ከአንበጣ
ያትርፍልህ!

ከመቅደስህ ቅዳሴ እንጅ
የዋይታ እንባ ከቶ አይፍሰስ
በሱብሂ አዛን እንጅ
ጧት ለመርዶ አትቀስቀስ

ዱኒያ ተትረፍርፎልህ
ርዚቅ ቤትህ ይከመር
በከሰረ የደም ምድር
አንደብር ሬሳ አትቁጠር
ከነጋልህ ቀንህ ይመር
ከመሸብህ ሰላም እደር !!


#አሌክስ_አብረሃም @mirtababaloch

20 last posts shown.

3 142

subscribers
Channel statistics