የህይወት ቅኔ🥀


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Telegram


🙏WELCOME TO OUR CHANNEL 🙏
In our channel we provide
✍️1መልካምና አስተማሪ የሆኑ ሀሳቦችን ማጋራት
✍️2 አንድነትን ማጠንከር
ፍቅራችንን ያብዛው 🙏ሌሎችን ወደቻናሉ ውስጥ ማስገባት ቁም ነገር ያላቸውን ነገሮች ለሌሎች ሼር ማድረግ አንርሳ ያለንን እውቀት ማካፈል የሁል ግዜ ተግባራችን እናድርግ
📩For any comment, promotion
@Lil_ezrael

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Telegram
Statistics
Posts filter


Forward from: Best Folder
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ከ15 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

10+10×0+10=❓❓❓


Forward from: Both Folders
'https://t.me/addlist/6RlJJRbIF3Y4OTNk' rel='nofollow'>◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇


*    -    *    -     *     -     * *    -    *   

ስንቱን ቀን ሸኘሁት
ወይ አልሞት ወይ አልድን በህማም ሳቃስት
ችላ ያልኩት ጠጠር  ሆኖብኝ እንቅፋት

ስንቱን ቀን ሰደድኩት
ስንዴ አገኘው ብየ አንክርዳድ ስለቅም
ለካ....አንዳንድ ስህተት
ልክ ይመስላል እንጂ ልክ ሆኖ አያውቅም

ቶሎ አያስታውቅም
*    -    *    -     *     -     * *    -    *    -     *  
✍መኳንንት
❤️‍🩹


የሶስት ትውልድ ጀግኖች🫡


የሶስት ትውልድ ጀግኖች ፤


✨1, ፊታውራሪ ዳምጠው ከተማ (አባት)


በዳግማዊ አጤ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት ስመጥር መኮንን ነበሩ ከፍተኛ ዲፕሎማት በመሆን ለዓድዋ ጦርነት የሩሲያ መንግስትን የጦር መሳሪያ እና የህክምና እርዳታ እድናገኝ ያደረጉ ስኬታማ ሰው ናቸዉ። እኚህ ጀግና ሰው ታድያ ከሩሲያ በዲፕሎማሲያዊ ስኬት ተመልሰው እረፍት ሳያደረጉ ዓድዋ ድረስ ተጉዘው በ 1888 ዓ.ም የካቲት 23 ቀን ከወራሪው የጣሊያን ጦር ጋር ገጥመው የጀግንነት ጀብዱ ፈፅመው በዚያው ዕለት ህይወታቸው እዚያው ጦር ሜዳ ላይ አልፏል።
✨2, ራስ ደስታ ዳምጠው (ልጅ)
የእኚህ የጀግናው ልጅ የሆኑት ራስ ደስታ እንደ አባታቸው ሁሉ በርካታ መልካም ስራዎች ለሀገራቸው የሰሩ ናቸው። በ1928 ዓ.ም የጣሊያን ጦር ሀገራችንን ለ2ተኛ ጊዜ ሲወር በሱማሌ በኩል ይመጣ የነበረው ጦር በጀግንነት እና በወኔ ዶሎ ድረስ ወርደው በመግጠም የጀግንነት ስራ ቢሰሩም ጦሩ በደረሰበት ሽንፈት ሰራዊታቸው ተበተነ እሳቸው ግን በአርበኝነት ለአንድ ዓመት ያህል ሲፉለሙ ቆይተው በቡታጅራ አካባቢ በባንዶች ጥቆማ በጣሊያን እጅ ወደቁ። የካቲት 16 1929 ዓ.ም በጣሊያኖች በግፍ በጥይት ተደብድበው ተገደሉ።
✨3, ሪር አድሚራል እስክንድር ደስታ (የልጅ ልጅ)
እኚህ ወጣት ሰው ደግሞ እንደ አባታቸው እና አያታቸው ስኬታማ የአስተዳደር እና የዲፒሎማሲ ሰው ነበሩ። የኢትዮጵያ ባህል ሀይል ምክትል አዛዥ በመሆን ሲሰሩ የነበሩት ሪር አድሚራል እስክንድር
እናታቸው የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ልጅ የሆነችው የልዕልት ተናኘወርቅ ልጅ በመሆናቸው ብቻ ህዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም ከ60ዎቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በደርግ መንግስት በግፍ በጥይት ተደብድበው ተገደሉ።
እንግዲ እነዚህ የሶስት ትውልድ ቤተሰብ ለእናት ሀገራቸው በሙያቸው ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸዉ ፊታውራሪ ዳምጠው ከተማ እና ልጃቸው ራስ ደስታ ዳምጠው በጠላት እጅ ነው የተገደሉት የልጅ ልጃቸው እስክንድር ደስታ ያለምንም ጥፋታቸው የንጉሡ ቤተሰብ ናቸዉ ተብለው በሀገራቸው ሰዎች ነው የተገደሉት።

ክብር እና ዘላለማዊ እረፍት ለእነዚህ ጀግና ቤተሰብ


ፍቅር ካለ ስለ ዛሬ ማሰብ እንጀምራለን፤ ነገን እናልማለን፤ ተስፋችን ይፈካል ፤ የመኖር ጉጉታችን ይጨምራል። የልባችን ብርሀን የሚበራው በፍቅር ነውና ሁሌም ፍቅርን እናስቀድም💞


የዋሸህን ደግመህ አትመነው ብታምነውም እንኳን ሁሌም ውሸታም እንደ ሆነ አይዘነጋህም ይሄ እውነታ ነው!!


ከርሞም እንዲ ነበርኩ
አሁንም እንዲው ነኝ
የሄደን ማፈቅር....
ምሸሽ ከወደደኝ!!🥺


ደና እደሩልኝ ❤️‍🔥💋


በንግግር ወቅት የቃላትህን አቅም
እንጂ ድምፅህን አትጨምር አበቦችን የሚያለመልመው
ዝናቡ እንጂ ጉርምርምታው አይደለም።


"ህይወት ጨካኝ መምህር ነው!!! ምክንያቱም መምህር አስተምሮ ነው የሚፈትነው ህይወት ግን ፈትኖ ነው የሚያስተምረው።"


©ስብሃት ገ/እግዚአብሔር


እንዴት ዋላቹ🙂🤚


ሰው በሃዘን አይደምቅም
ለቅሶ ዳስን አያሞቅም
ሁሉም ቢገፋ ቢጥልሽ
መውደቅ መሞት እንዳይመስልሽ
ቁልቁል ዳገት ተራመጂ
ከእንባ ሳቅሽን ውደጂ
ከሞት ካፈር እስክትወድቂ
ሳቂ!!


እያሰብኩኝ ነበር

ቀለም ለመቀለም
ቆንጆ እንዲመስል፣😎
እያሰብኩኝ ነበር፣😇
የምኖር ሳሳስል፣😛
ጉንፋን አሰቃየኝ🥵
ሳል ሲበረታብኝ፣🥶
አምሮቴ ጨምሯል😛
ያቺ ስትቀርብኝ፣😋
የለመድኳት ነገር😋
የምትጣፍጠው
የምታንሸራሽር፣🥺
እያሰብኩኝ ነበር🤨
ለመጠጣት ቀሽር፣🤪
ግን ብር የለኝም ጋብዙኝ...🤣
@dagi1u


ባይስ said......🤌🏽😮‍💨


ወንዶች ሆይ የራስህ የዕድገት ማነቆ በመስታወት የምታየው ሰው ነው

አብዛኞቹ ወንዶች ችግራቸው ገንዘብ፣ ሴቶች ወይም የኢኮኖሚ ሁኔታ ይመስላቸዋል። እውነታው ግን፡ ትልቁ እንቅፋትህ በመስታወት ውስጥ የምታየው ሰው ነው።

ወደ ኋላ የሚጎትትህ ህይወት አይደለም።
ስርአት የሌላቸው ልማዶችህ፣ የስሜት ድክመትህ እና ለተለያዩ ትኩረት የሚሰርቁ ነገሮች ያለህ ሱሰኝነት ነው።

እውነታዎች የሚከተሉት ናቸው፡

1. ደካማ ሰው ለደስታ ባሪያ ነው።
ፈተናን መቋቋም አይችልም። የሴት ገላ ሲያይ ትኩረቱ ይበተናል። የወሲብ ፊልሞች፣ ጫት/ሀሺሽ፣ አልኮል እና ሌሎች ቀላል ፈንጠዝያዎች አእምሮውን ይቆጣጠሩታል።
ለደስታ ሱሰኛ አይደለም—ራስን መግዛትን ይጠላል። ለዚህም ነው ደጋግሞ የሚወድቀው።

2. ደካማ ሰው ከልክ በላይ ያወራል።
እያንዳንዱን እርምጃውን ይናገራል። ብልህ ለመምሰል ይፈልጋል፣ ስለዚህ ሚስጥሮችን ያባክናል። ያማርራል። ያሟል።
እውነተኛ ሃይል ራሱን አያሳይም። ጠንካራ ሰዎች አፋቸው ሳይሆን ውጤታቸው እንዲናገር ያደርጋሉ።

3. ደካማ ሰው ከዓላማው በላይ ሴቶችን ያስቀድማል።
ቀኑን ሙሉ ለሴቶች መልዕክት በመላክ፣ ስጦታ በመግዛት እና ትኩረት በመለመን ያሳልፋል።
ንጉሶች ግን ንግስቶችን አያሳድዱም—ግዛታቸውን ይገነባሉ። ዙፋኑ ሲጠነክር ትክክለኛዋ ንግስት ትመጣለች።

4. ደካማ ሰው ለ'ላይክ' እና ለጭብጨባ ይኖራል።
ሌሎችን ለማስደመም 'ፖስት' ያደርጋል። ሌሎችን ለማስደሰት ይተውነዋል። የህዝብ አስተያየት ባሪያ ነው።
እውነተኛ ወንዶች ግን እውቅና አያስፈልጋቸውም። ክፍል ውስጥ ሲገቡ ምንም ሳይናገሩ ድባቡን ይቀይራሉ።

5: ደካማ ሰው ህይወትን በቀላል መንገድ ይፈልጋል።
ጠንክሮ መስራትን ያስወግዳል። ስልት ሳይሆን አቋራጭ ይፈልጋል። ስርአትን ስለሚፈራ መካከለኛ ሆኖ ይቀራል።
ነገር ግን እድገት ያለ ህመም በጭራሽ አይመጣም። ጠንካራ ሰዎች ሂደቱን ያከብራሉ—ምንም እንኳን ሲኦል ቢመስልም።

6. ደካማ ሰው ወጥነት/ጽናት ይጎድለዋል።
100 ነገሮችን ይጀምርና አንዱንም አይጨርስም።
በአንድ ግብ፣ ልማድ ወይም እቅድ ላይ መጽናት አይችልም። ህይወቱ የስንፍና፣ የምክንያቶች እና የራስ-ርህራሄ የተሰበረ ዑደት ነው።
አለም የሚሸልመው ግራ የተጋቡትን ሳይሆን ጽኑዎችን ነው።

7 ደካማ ሰው ብቸኝነትን በጣም ይፈራል።
መርዛማ ከሆኑ ሴቶች ጋር ይጣበቃል። ስድብን ይታገሳል። ውድቅ መደረግን ይፈራል።
እውነተኛ ወንዶች ግን ያውቃሉ፡ ከሚያንቋሽሽህ ሰው ጋር ከመሆን ሰላም ይሻላል።

8 ደካማ ሰው ትኩረት በሚሰርቁ ነገሮች ውስጥ ይኖራል።
ያለማቋረጥ 'ስክሮል' ያደርጋል። ጨዋታዎች፣ ወሬዎች፣ ቀልዶች—ይዝናናል ግን እርካታ የለውም።
ከዚያም ለድህነቱ ስርዓቱን ይወቅሳል። እውነታው ግን ትኩረቱ ለስኬት የማይበቃ ደካማ ነው።

9. ደካማ ሰው በጫና ጊዜ ይንኮታኮታል።
ከባድ ጊዜ ሲመጣ ይሰበራል። በፍጥነት ተስፋ ይቆርጣል።
ህይወት ግን የጦር ሜዳ ናት። የሚዋጉ፣ የሚላመዱ እና የሚጸኑ ብቻ ከፍ ይላሉ።

10. ደካማ ሰው ከራስ ክብር ይልቅ ርህራሄን ይፈልጋል።
ሰዎች እንዲያዝኑለት ይፈልጋል።
አለም ግን እንባን አትሸልምም—ኃይልን፣ ጥንካሬንና ጽናትን ታከብራለች።
ተነስ፣ አስተሳሰብህን አስተካክል፣ ደረጃህን ከፍ አድርግ። ሊያድንህ የሚመጣ ማንም የለም።

የመጨረሻ ቃሌም

የወደፊት ህይወትህን የሚቀርጸው ልማዶችህ እንጂ ጥረትህ አይደለም።
ታሪክህን የሚወስነው ስርአትህ እንጂ ፍላጎቶችህ አይደሉም።
የራስህ ጠላት መሆንህን አቁም። ግንኙነት ለመገንባት ከመሞከርህ በፊት እራስህን ገንባ።

ስሜቶችህን ተቆጣጠር። አእምሮህን ግዛ። ጉልበትህን ጠብቅ።
የወደፊቱ የነሱ ነው - በዙሪያቸው ያለው ነገር ሁሉ ሊሰብራቸው ሲሞክር ለሚነሱ ወንዶች።

ወደ ታላቅነት ጉዞ እያደረጋችሁ ላላችሁ ወንዶች ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ።

እወዳችኋለሁ!

©️ተዋነይ - Tewanay


ሰወች ሰለማሉ ወይም ቃል ስለገቡልህ አትመናቸው ለቃል አትጓጓ የሰው ቃል እንዳተው የሰው ቃል ነው ይታጠፋል....
ሲታጠፍ ግን ያንተንም ልብ አብሮ ያጥፈዋል ወዳጄ...
እንዴት ማመን እንደምትችል ታቃለህ ?
እንግዲያውስ እውነቱን ልንገርህ

...
እኔም አላውቅም 😂
ግን ላለማመን ሞክር ዝርያ


ከ 119 ዓመት በፊት ልዑል ራስ መኮንን ወ/ሚካኤል አርፈው ቀብራቸው ሐረር በቅ/ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተከናወነበት ዕለት


ከ 119 ዓመት በፊት ልዑል ራስ መኮንን ወ/ሚካኤል አርፈው ቀብራቸው ሐረር ላይ እሳቸው በተከሉት በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተከናወነበት ዕለት ነበር።
በ 1894 ዓ.ም በመጀመሪያ ላይ በብርቱ ስለታመሙ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ጥር 4 ቀን ከከተማቸው ከሐረር ተነሱ። ጥር 9 ቀን ቡርቃ ወንዝ አድረው የጥምቀትን በዓል አክብረው ከዋሉ በኃላ ህመሙ ስለፀናባቸው ወደኀላ ተመልሰው ቁልቢ ገብተው በሐኪም ይታከሙ ጀመር።
እዚሁ ሲታከሙ ከቆዩ በኃላ መጋቢት 13 ቀን 1898 ዓ.ም ቁልቢ ላይ አርፈው ሐረር ላይ እሳቸው በተከሉት በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
አፄ ምኒልክ የአርባቸው ለቅሶ የሚለቀሰው አዲስ አበባ እንዲሆን ባዘዙት መሠረት ሰኞ ሚያዝያ 22 ቀን በአዲስ አበባ በዙሪያዋ ያሉት የየገዳማቱና የየአድባራቱ ካህናት የክርስቲያን የፍታት ጸሎት ተደርጎ በማግስቱም ማክሰኞ የጊዮርጊስ ዕለት ሚያዝያ 23 ቀን 1898 ዓ.ም በሰኢ ሜዳ ላይ ድንኳን ተተክሎ መኳንንቱና ሠራዊት ተሠብስቦ የራስ መኮንን የማዕረግ ልብሳቸውንና የራስ ወርቃቸውን ኒሻኖቻቸውና የጦር መሳሪያቸውን ተይዞ በፈረሰና በቅሏቸው በወርቅ እቃ ተጭነው በሠራዊት መካከል እየተመላለሱ ተላቅ ለቅሶ ተለቀሰላቸው:: ከአልቃሾቹም አንዱ ደግነታቸውን ለማስታወስ እንዲህ ብሎ አሟሸ


ስልከኛው ሲያረዳ ነገር ተሳሳተው
መኮንን አይደለም ድኃ ነው የሞተው


(ግንቦት 1 ቀን 1844 -- መጋቢት 13 ቀን 1898)


ዝም.........💔😔


አንብባችሁ like ማታረጉ ባላየ  የምታልፉት ነገር ደስ አይልም ከምር አድቡ 🙄😐😒😞


የሰው ልጅ ሲከማች እንደማንኛውም መንጋ ማመዛዘኑን ስሜት ይወርሰዋል። ዘዴውን ሀይል ይገስሰዋል። ሰው በተናጠል ሲቀርብ ነው ሰው የሚሆነው። በጅምላ ከተጠራ እንደማንኛውም እንስሳ መንጋ ነው። ስልጣኔው ቦታው ላይ አይገኝም። ዛሬም ቢሆን ኢየሱስ ብዙሃኑ ፊት ከቀረበ እጣ ፈንታው አትለወጥም። ይገረፋል፣ይወገራል፣ የእሾህ አክሊል ይደፋል፣ ይሰቀላል፣ በህዝቦች እጅ ውስጥ ጊዜ ስልጣን የለውም። ያኔ የሆነው ሳይዘንፍ ዛሬ ይደረጋል።


📓 ቅበላ
                        🪄አለማየሁ ገላጋይ


ሁድ ✨


ዳግም ትንሣኤ ይባላል፦በዚህ እለት ጌታችን መድሃታችን እየሱስ ክርስቶስ ለሶስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ስልጣን መስጠቱን ይሰበካል ❤️‍🔥


ዛሬ......🥹

ዳግም ትንሳዔ❤️‍🩹
እለተ ሰንበት❤️‍🩹
ቅዱስ ገብርኤል❤️‍🩹

ገብርኤል ገብርኤል ሲሉ ስሙ እንኳን ማማሩ
ከእሳት ያድናል በያዘው መስቀሉ 🥹❤️‍🩹


እንኳን አደረሳቹ❤️‍🔥

እንዴት አደራቹ ውዶች😌🙌🏽

20 last posts shown.