የሙዑሚን ጀማኣ channel


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


"እውቀትን በስልጣን እና በመኩራራት ተምሮ የሚሳካለት አንድም ሰው የለም። ነገር ግን ራሱን መስዋእት አድርጎ፡ በችግር እና ምሁራንን እያገለገለ የተማረ ይሳካለታል።"
ኢማሙ ሻፊዒ (አላህ ይዘንላቸው)

እነዚህንና ሌሎችንም እናገኛለን።
🌙እንዲሁም🎬Habesha Islamic Tube ለመቀላቀል ይግቡ 👇👇👇 https://youtube.com/channel/UContiXSAssqaw74hPcXNKPg

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter




"🤍በዚች ምድር ላይ እንደ ረሱል ﷺ ያፈቀረ እንደሳቸውም የተፈቀረ የለም። ወደፊትም አይኖርም!
          ሰሉ አለ ነቢ አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ነቢይና ሙሀመድﷺ🌹

መልካም ጁምዓ




ከሰዎች ትችት የሚተርፍ ማንም የለም።

فما أحدٌ من ألسُن الناس سالــــــــــمًا

ከሰዎች ምላስ የሚተርፍ አንድም የለም።

ولو أنه ذاك النبيُّ المطهـــــــــــــــــرُ

ያ!! ንፁሁ ነቢይ እንኳን ቢሆን...

فإن كان سكِّيتًا يقولون: أبكـــــــــمٌ

ዝምተኛ ቢሆን ዱዳ ነዉ ይሉታል።

وإن كان مِنطيقًا يقولون: مهــــــذرُ

ተናጋሪ ቢሆን ቀባጣሪ ይሉታል።

وإن كان مقدامًا يقولون: أهــــــوجٌ

ከፊት ለፊት ቀዳሚ ቢሆን ክልፍልፍ ይሉታል።

وإن كان مفضالاً لقالوا: مبـــــــــذِّرُ

እጂግ ለጋሽ ቢሆን አባካኝ ይሉታል።

وإن كان صوّامًا وبالليل قائـــــمًا

ፆም የሚያበዛና ሌሊት የሚሰግድ ቢሆን.

يقولون: كذَّابٌ يرائي ويمكـــــرُ

ዉሸታም ለይዩልኝ እየሰራና እያሴረ ነዉ ይሉታል።

فلا تكترث بالناس في المدح والثنا

(ስለዚህ) በሰዎች ዉዳሴና ሙገሳ አትበገር።

ولا تخش غيرَ الله والله أكبـــــرُ

ምንም አይነት ነገር ከማንም መጠበቅ የለብንም ሁሌም መልካሙን እናርግ

https://t.me/momen_jemma_channel


🤍 ጨለማ ባይኖር ጨረቃን እንደማናያት ሁሉ፣
ችግሮቻችን ባይኖሩ የራህማኑን ኒዕማ ባልተረዳን ነበር!
አልሀምዱሊሏህ *......🤗.....*

@momen_jemma_channel


ንጉሱ ሶስት ባለስልጣናቱን ጠርቶ ለእያንዳንዳቸው ጆንያ በማስያዝ ወደ ማሳ ሂደው የተለያዩ ጣፋጭ ፍራፍሬዎችን እንዲለቅሙ እና ማንንም እገዛ እንዳይጠይቁ አዘዛቸው።

ባለ ስልጣናቱ የንጉሱ ትዕዛዝ ግራ ቢያጋባቸውም የታዘዙትን ለመፈፀም ጆንያዎቻቸውን ይዘው ወደ ማሳው አቀኑ።

አንደኛው ጆንያውን ይዞ ወደ ማሳ በመግባት ንጉሱን ለማስደስት ጣፋጭ እና ልዩ የሆኑ ፍራፍሬዎችን ለቅሞ በጆንያው ሞላ።

ሁለተኛውም  ንጉሱ ይህን ሁላ ፍራፍሬ ፈትሾ ያያል ብሎ ስላልገመተ ለምርጫ ብዙም ሳይጨናነቅ ያገኘውን ሁሉ ለቃቅሞ ጆንያውን ሞላ።

ሶስተኛው ደግሞ ጭራሹኑ ንጉሱ ጆንያውን ይፈትሻል ብሎ ስላልገመተ አሰስ ገሰሱን ሰብስቦ በጆንያው ሞላ።

በቀጣዩ ቀን ንጉሱ ባለ ስልጣናቱን ከነጆንያዎቻቸው እንዲቀርቡ አዘዘ። ከዝያም ወታደሮቹን ጠርቶ ሶስቱንም ባለ ስልጣናት ራቅ ወዳለ ቦታ ወስደው ለ 1 ወር እንዲያስሯቸውና ከጆንያዎቻቸው ውጭ ምንም አይነት ስንቅ እንዳይሰጧቸው ያዛል።

አንደኛው ባለስልጣን ቀድሞ የሰበሰበውን ጣፋጭ ፍራፍሬ እየበላ ለ1 ወር ያህል በድሎት ቆይቶ ተፈታ።

ሁለተኛውም ባለስልጣን  ለምርጫ ሳይጨነቅ የለቀማቸውን ፍራፍሬዎች ሳይጥመ እየበላ ብዙ ተጎድቶ ወሩን አጠናቀቀው።

ሶስተኛው ግን በረሀብ ሞተ።

ተፈፀመ!

አንተም አሁን በዱንያ ማሳዎች ያሻህን እንድትለቅም ሙሉ ፈቃድ ተሰጥቶሀል። ግና ነገ የንጉሶች ንጉስ በቀብርህ እንድትታሰር የሞት ወታደሮቹን ሲልክብህ የለቀምካቸውን መልካም ፍሬዎች ብቻ ነው ይዘህ ምትታሰረው።

💛መልካም ውሎ


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


👂👂👂👂👂


ከቱርክ የመሬት መንቀጥቀጥ ምን እንማራለን

1.ሳታስበው ወይም ሳታውቀው ሕይወትህ በሰከንድ ውስጥ ሊለወጥ ይችላል። ምንም ዓይነት ዋስትና የለህም

2. ያለ ምንም የገንዘብ ችግር ተረጋግተህ እየኖርክ  በድንገት የዘካ ገንዘብ ተቀባይ ልትሆን ትችላለህ።

3. ህይወት በጣም አጭር ናት እንዳለመታደል ሆኖ ያለንበትን  ህይወት ለሰከንድ አመስግነን አናቅም

4. ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ቂም ይዘን ሌሊት እንተኛለን ጠዋት ምን እንደሚፈጠር በማናቅበት ሁኔታ  ቱርክ ላይ ይህ ነው የተፈጠረው ወደ ንጋት ላይ ነበር የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው የደረሰው ነገ እነቃለሁ ብሎ በዚህ ሁኔታ የተኛ ስንቱ ይሆን

5. ብዙዎቹ ሟቾች የረመዳንን ወር አቅደው እና በጉጉት ሲጠባበቁ የነበሩ ይሆናሉ።  ረመዳን እንደማይደርሱ ግን አያውቁም ነበር😢

አንተስ ነገ ለመኖርህ ምን ዋስትና አለህ ???

★★ዛሬን ባለንበት ሁኔታ ለአኼራ የሚጠቅመንን እንሰንቅ ኸይር ስራዎች እናብዛ ተውበት እናድርግ

#አላህ_ሆይ! ረመዳን ከሚደርሱት አድርገን ። የሞቱትን አንተው ማራቸው የተጎዱትንም አንተው ጠግናቸው  🤲

اللهم ردنا إليك رداً جميلاً. اللهم ردنا إليك وأنت راضٍ عنا


#የተሰጠንን_ብናውቅ_የጎደለን_የለም!
                        
ሁለት የሚዋደዱ ጓደኛሞች ጉዞ ላይ ሳሉ አንደኛው ያማረ ቪላ ቤቶችን ያይና ለጓደኛው እንዲህ አለው።

«ፈጣሪ ይህን ሁሉ ሀብት ለእነዚህ ሰዎች ሲያድል እኛ የት ነበርን?»

ጓደኛውም አጠገቡ ነበረና ና ብሎ ወደ ሆስፒታል ይዞት ሔዶ እንዲህ አለው።

«ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሽታን ሲያድል እኛ የት ነበርን?»

"የተሰጠንን ብናውቅ የጎደለን የለም!!
ምንግዜም ባለን ነገር እናመስግን።


Share share share


💚 ከአላህ ጋር 5ት ጊዜ በሰላት
እየተገናኘነው ስለ ሀዘን ማውራት
አይገባንም ነበር…😊

💫አልሀምዱሊሏህ


T.me/momen_jemma_channel


ነገሮችን በቀና እይ!!!
ከምንም ነገር በላይ ሰው ላይ አትክፋ መልካም ሁን ሲያሸንፉ ስታይ አይንህ ደም አይልበስ ተደሰት ጠይቃቸው እንዴት አድርጋችሁ አሳካችውት በላቸው እንጂ ፈጣሪ ለእነርሱ አደላ አትበል ሌሎች ቀድመው ማሸነፍ ስለቻሉ አንተ ወድቀህ የቀረህ አይምሰልህ ከቀደሙህ ተምረህ የባሰ ከፍ እንድትል ነው ከእነርሱ ኋላ ያለኸው ስለዚህ ወዳጄ የሰዎችን ስኬት ከማኮሰስ እና በመቀደምህ ከማዘን እንኳን ተሳካላቸው እኔስ ከእነርሱ ምን ልማር በል!

Share 😎 share 😎 share

https://t.me/momen_jemma_channel


✅:ለሁሉም #ሰው መልካም ነገርን እንድመኝ ሕይወት አስተማረችኝ።

🪴:የነርሱ መደሰት ከኔ ደስታ አይቀንስም።
🪴:የነርሱ ማግኘት ከኔ ሲሳይ አያጎድልም።
🪴:የነርሱ ጤና መሆን የኔን ጤና አይረብሽም።
🪴:የነርሱ ሰላም መሆን የኔን ሰላም አያደፈርስም።


ሼር አድርጉት https://t.me/momen_jemma_channel




ኢና ሊላሒ ወዒና ዒለይሒ ራጂዑን

የክብርት ሙፈሪሃት ካሚል አባት ሀጅ ካሚል አህመድ ከዚህ ዐለም በሞት ተለዩ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል አባት የሆኑት ሀጅ ካሚል አህመድ በጅማ ሙኒር መስጂድ ለ 42 አመታት በሙዓዚንነት ሲያገለግሉ የቆዩ የመስጂድ እርግብ፣ ሰዉ አክባሪ፣ ትሁትና የመልካም ስነ ምግባር ባለቤት ነበሩ። በጅማ የተጣላን አስታራቂና ሸምጋይ እጅግ የተከበሩ ሰዉም ነበሩ።

ከወራቶች በፊት በሕመም ምክንያት ወደአዲስ አበባ በመምጣት በኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ህክምናቸዉን ሲከታተሉ ቆይተዉ በዛሬው እለት ማናችንም ወደማንቀርበት የአኼራ ጉዞ አድርገዋል።

በነገዉ እለት ከረፋዱ 4:00 ህዝብ ሙስሊሙ በሚታደምበት ሁኔታ በታላቁ አንዋር መስጂድ ከተሰገደባቸዉ ቡኃላ ወደጅማ አቅንተዉ የቀብር ስነ ስርዓቱ ይፈጸማል።

አላህ በጀነተል ፍርደውስ ይወፍቃቸዉ። ለቤተሰቦቻቸው፣ ለመላዉ ሙስሊም ማህበረሰብ እንዲሁም ለጅማ ሕዝብ ሰብርን ይስጥልን። አሚን🤲
▬▬▬▬▬▬▬▬▬


https://t.me/momen_jemma_channel


ከቀናት ሁሉ በላጩ ቀን #ጁምአ
#ℎ𝑎𝑝𝑝𝑦_𝑗𝑢𝑚𝑚𝑎 🥰
መልካም ቀን🤎
ደግ ደጉን ያሰማን 🤎
ሀገራችንን ሠላም አድርግልን🤎
አሚን🤲🏼




ማስታወቂያ

M.K Electronics 🛠

ፍሪጅ ልብስ ማጠቢያ ጥገና ግዥ እና ሽያጭ                

የቤት ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ዲሽ ጥገና ፣ ፍሪጅ ፣ ፍላት ቲቪ ፣ ልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ ስቶቭ፣ ኦቭን ጥገና ግዢ እንዲሁም ሽያጭ ስራዎችን እንሰራለን። አገልግሎታችን ሲያስፈልግዎ ቢደውሉልን በታማኘነት ልናገለግልዎ እና በስራችን ጥራት ልናስደስትዎ ዝግጁ ነን።
ያሉበት ቦታ ድርስ መጥተን አስተማማኝ ጥገና ከዋስትና ጋር እንሰጣለን።

 0940249715 ይደዉሉ


ሚንበር ቲቪ ድምፅ ብቻ ሆኖብዎታል?
ከሆነ እንደአዲስ ሰርች ያድርጉት። በአንዳንድ SD ሪሲቨሮች ሲጭኑት ካልመጣ የቀድሞውን አጥፍተው እንደ አዲስ ሰርች ለማድረግ ፍሪኩዌንሲውን በድጋሚ ይጫኑ።

የምስል ጥራት የማሻሻል ለውጥ በመደረጉ የተፈጠረ ሲሆን በነበረው ቁጥር ድጋሚ ሰርች ያድርጉት! አሁን ሚንበር ቲቪን በተሻለ የምስል ጥራት መከታተል ይችላሉ!



ኢትዮ ሳት
ፍሪኩዌንሲ:– 11545
ሲምቦልሬት:– 30000
ፖላራይዜሽን:–ሆሪዞንታል



20 last posts shown.

227

subscribers
Channel statistics