° የ Black Gangster ፊልሞች በአለም ላይ ተወዳጅነት ካተረፉ ፊልሞች ውስጥ ይመደባል። ተፅእኖ ከሚፈጥሩት ውስጥም ይመደባል። በዛው ልክም ደግሞ ለጥቁሮች የተሳሳተ አመለካከት እንዲኖረን ያደርጋል።በአብዛኛው ጥቁሮች አጫሽ እንዲሆኑ ፣ ለነገሮች መፍትሄ የሚሆነው መገዳደል ብቻ እንደሆነ ፣ ከማጨስ ውጪ ልላ ነገር የማያውቁ መሀይሞች አድርገው ነው የሚሰሩት ለዛም ነው በሁላችንም አይምሮ ውስጥ ይሄ አስተሳሰብ ያለው ገና ስማቸው ሲጠራ በአይምሯይን ብልጭ የሚልልን ይሄ ነው።ነገሩ ግን በተቃራኒ ነው Black Gangster ከሆኑት ውጪ ያሉት ከ85 % በላይ የሆኑ አስተዳደጋቸው እና የኑሮ ሁኔታቸው የሆነው... ሱሪ ዝቅ ማድረግ (እሱም የራሱ የሆነ ትርጉም አለው) ፣ ፍትህን ስለማያገኙ ለእውነት ቢኖሩም ውሸታሞች ስለበዙ ከነሱ ለመለየት ብለው በሚያደርጉት ተጋድሎ ያለ ስማቸው ስም በመስጠት ሁሉንም እንደ አንድ እንድናስባቸው አድርገውናል።
° ይህ እንዴት እንደሆነ ላሳያችሁ። የመጀመሪያው በቀጥተኛ መንገድ ሲሆን በፊልሞቹ ላይ በምናያቸው ምስሎች አማካኝነት ነው። የ Black Gangster ብቻ ቢሆን ጥሩ ነው ሆኖም ግን እንዳለ ጥቁሮችን እየወከሉ ነው የሚሰሩት (ሁሉም ግን አይደለም ከግማሽ በሊይ የሚሆኑት ግን እንደዛ ነው የሚሰሩት) የሚያሳዩት ምስሎች እንደ አደንዛዥ እፅ ያሉ ሲያጨሱ ወይም ደግሞ የተለያዩ ሽጉጦችን ሰርቀው ወይም ደግሞ ገዝተው ሲገዳደሉ አልያም ደግሞ ትምህርት ሲያቆሙ እና ወደ ሌላ ነገር ሲገቡ ከዛም ቆይቶ መሀይም እና ምንም እንደማይጠቅሙ ያሳያል። ይሆ በቀጥታው ስለሆነ ንቃተ ህሊናችን ልክ ናቸው ብሎ ይቀበላል። ምክንያቱም ይሄ የገር በሁሉም ፊልሞቻቸው ስለሚደጋገም ነው።ግን እውነታው የዚህ ተቃራኒ ነው።
° ሁለተኛው መንገድ ደግሞ ድብቁ (MESMERISM) የሚባለው ነው። ይሄን መንገድ ከድሮም ጀምሮ የሚጠቀሙበት እና ለብዙ ጥቁር ህዝብ ማለቅ እና ለዘረኝነት ጥቃ የዳረጋቸው ይሄ ነው። ይሄ MESMERISM የሚባለውን የአይምሮ ቁጥጥር ስልት እንዴት እንደሚከናወን ላሳያችሁ ለምሳል እናንተ የምትሰሙት ድምፅ "We should go to my place" /ወደ እኔ ቤት መሄድ እንችላለን/ የሚል ሊሆን ይችላል። ይሄን ድምፅ ግን አእምሮአችን ውስጥ የሚገባው "Kill all the Black's, They all are jealous of you, you must aware of them" /ጥቁሮችን ግደሉ ሁሉም ባንተ ይቀናሉ ከእነሱ መራቅ አለብህ/ የሚል ሊሆን ይችላል ይሄ እንዴት ሆነ ካላችሁ መጀመሪያ የሰማችሁትን ድፅ ወደ ፊት ስታፈጥኑት ከታች ያለውን ድምፅ ይሰጣል ንቃተ ህሊና ሳያስተውል ወደ ውስጠ ህሊና ሳናውቀው ይገባል የተለያዩ ድብቅ (Mesmerism) መልእክቶች ስለሚደጋገሙ ተፅዕኖ ያሳድራሉ።
° በዚህ MESMERISM መንገድ በርካታ ፊልሞች ተመልካቾችን በቀላሉ አእምሮአቸውን ይቆጣጠሩ ነበር በተለይ በቀኝ ግዛት አገዛዝ ጊዜ ካበቃ በኋላ በአሜሪካ ውስጥ በርካታ ጥቁር አሜሪካውያን ይጨቆኑ ነበር ከነጮች ጋር አብረው ምንም አያደርጉም ነበር። ጥቁሮች በሚያዩት ፊልሞች ውስጥ ግን ይሄን MESMERISM ይጠቀሙ ነበር። በዚም ምክንያት ጥቁሮች ቅናታም ፣ ሰው የማይወዱ ተደርገው መቆጠር ጀመሩ። ይሄም ሳይሆን በሁላችንም አይምሮ ውስጥ ስለ ጥቁሮች መሀይምነት ምንም ጥቅም እንደሌላቸው በአጠቃላይ ስሐ ጥቁሮች ትክክል ያልሆነ ነገር በመስበክ ስለ እነሱ ያለን አመለካከት እንዲለወጥ እድርገዋል።
° የሚገርመው ነገር ጎግል (Google) ላይ ስለ MESMERISM ብትፈልጉ ምንም ከዚህ ጋር የሚገናኝ ነገር አታገኙም አፈትልኮ እንደወጣ ከነሱ ቀን ሳይቆይ ነው ከሁሉም ነገሮች ያጠፉት ከዛ ግን 2019 ላይ በወጣው "Watchmen" ተከታታይ ፊልም ላይ በአንዱ ክፍል ላይ ለ 2 ደቂቃ ስለዚህ MESMERISM አሳይተው ነበር። ፊልሙ ላይ ብዙ ድብቅ እና ከፈጣሪ ጋር ተቃርኖ ያለው ስለሆነ በሌላ ጊዜ ሰፋ ባለ ትንተና እመለስበታለሁ።
° በአጠቃላይ የጥቁሮችን ስም የሚያበላሹት ከ 15% ያልበለጡ ሌላ አላማ ያላቸው ጥቁሮች ናቸው እንጂ የተቀሩት 85% የሚማሩ ለሰው በጎ የሚመኙ ግን በብዛት የአይምሮ አጠባ እና ቁጥጥር የተደረገባቸው ምስኪኖች ናቸው አኛንም ኢትዮጵያችንም ጨምሮ። ከሁሉም ደም እኛ ላይ በርትተውብናል ምክንያቱም ዋነኛ አላማቸው ስለሆንን። ከዛ በመቀጠል ነው አፍሪካ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት ለመቀራመት... ድሮ በቀኝ ገዥነት አሁንም ከቀኝ ገዥነት ባልተናነሰ አእምሮአችንን በመቆጣጠር ለእነሱ አላማ እያዘጋጁን ያሉት። ለመንቃት ስንሞክር በምናያቸው ፊልሞች ወይም ሙዚቃ መልሰው ያጠምዱናል። እነዚህን ፊልም እና ሙዚቃ በተቻለን መጠን እንቀንስ ከዛም እንተዋቸው ለጊዜያዊ መዝናኛ ብለን ወደ ፊታችንን አናበላሸው።
t.me/elohe19