በመስቀል አደባባይ ለሚከናወነው የኢፍጣር ፕሮግራም የተወሰኑ መንገዶች እንደሚዘጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ!
***
ይኸውም ነገ መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 5:00 ሠዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የሚከናወነውን የኢፍጣር ፕሮግራም ምክንያት በማድረግ፦
👉 ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ )
👉 ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ሲሆን ከባድ ተሽከርካሪ አጎና ላይ )
👉 ከለገሃር መብራት ወደ መሰቀል አደባባይ (ለገሃር መብራት)
👉 ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድየም (ቴሌ ማቋረጫ ላይ)
👉 ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ሀራምቤ መብራት ላይ )
👉 ከብሔራዊ ቤተ መንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተመንግሥት ላይ )
👉 ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መታጠፊያ ድረስ የሚዘጋ መሆኑን በመገንዘብ አሽከርካሪዎች አማራጭ እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ያሳስባል።
Via
@mussesolomon