STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


ያጋሩ፣ ያሸንፉ!

የመጋበዣ ማስፈንጠሪያዎ ይህ ነው:

https://t.me/Abay_Bank_Referral_Bot?start=mgpj0k1sqtj03b2

ለ50 እና ከዚያ በላይ ወዳጅ ዘመድዎ ሲያጋሩ ዓባይ ባንክ ለታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የመሮጫ ቲሸርቶችን ይሸልምዎታል፡፡

ሽልማቱ ኅዳር 6 ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ ለተሸላሚዎች ይደርሳል፡፡

ደንብና ግዴታዎች ተፈፃሚነት አላቸው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የጥሪ ማዕከል ቁጥራችን ☎️ 8834 ይደውሉ፡፡

መልካም ዕድል!
ዓባይ - የታላቅነት ምንጭ


የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦

በWebsite: https://placement.ethernet.edu.et 

በTelegram: https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

@NATIONALEXAMSRESULT


የቴሌግራም ድርጅት አዲሱ የመገበያያ መንገድ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው Major stars ከ6 ቀን በኋላ ይፋ የመሆን ጉዞውን እንደሚጀምር መግለጫ ተሰጥቷል።

ስንት ኮከቦችን አጠራቀማችሁ? ያልሰራችሁ ከጥቅምት 29 በፊት የቻላችሁትን ያህል star ሥሩ

እነሆ:- https://t.me/major/start?startapp=835671370


ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲን በእግር እስከ ራሱ ፈታ እያላችሁ ጎብኙት!

በዚህ አዲሱ የyoutube ገጽ በመጀመሪያው ፕሮግራም ያሬድ እና ናሆም ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲን እሳያቁ እና እያዝናኑ ያስጎበኙናል።

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሐሳብ አይግባችሁ  ልክ የመጀመሪያ ቀን ስትመጡ ያለአስጎብኚ ወደ ዶርም ቀጥታ መግባት ትችላላችሁ 🙈 የሴቶች ዶርምንም ይጨምራል ለሴቶች😁

በቀጣይ በሌሎች ቦታዎች ጭምር ከሌሎች ሳቢ ፕሮግፋጋች ጋር በበለጠ አቀራረብ ብቅ እንላለን... እስከዚያው

አዲሱን በነጻነት የተሰኘውን ቻናላችንን SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ሁኑን! ቪዲዮውንም like በማድረግ ለጊዜው ሐዋሳ ለተመደቡ ጓደኞቻችሁ SHARE በማድረግ አድርሷቸው። ወዳጅነት ለመች ነው ሄደው እንዳይጠፉ😁

እነሆ linkኡ
https://youtu.be/cs8b-FMFJoc?si=TOqxWRpGr2fMhW3G


ይህንን እድል ተጠቀሙበት!

X-Empire  ከቀናት በፊት ክፍያ መፈጸሙ ይታወሳል። በጉጉት እየተጠበቀ ከሚገኘው Major ቀጥሎ አሁን ደግሞ በዓለም ላይ ታዋዋቂ የሆነው እና ከ30 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚ ያለው bitget ዋሌት በቴሌግራም መተግበሪያ መጥቷል። ለመጀመያዎቹ 1M ከዓለም ዙሪያ በቴሌግራም ብቻ ለተመዘገቡ ተጠቃሚዎች በቴሌግራም ዋሌት በኩል ልዪ ሽልማት ማዘጋጀቱን ዛሬ አስታውቋል።

በቴሌግራም ብቻ በመመዝገብ ክፍያ ይቀበሉ

https://t.me/BitgetWallet_TGBot/BGW?startapp=sharetask-SPNQvVhQctQs5FM


Websiteኡ እየሠራ አይደለም
ከደቂቃዎች በኋላ ሞክሩ


#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@NATIONALEXAMSRESULT


#MoE

በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ተወስኗል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የወሰዱና እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ ተብሏል።

በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

@NATIONALEXAMSRESULT


#Attention🚨

በአዋሽ ፣ መተሀራ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

" በሬክተር ስኬል 4.9 ነው። 150 ኪሎሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የተፈፀመ ነው። ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል " ብሏል።

" በስምጥ ሸለቆች ውስጥ ንዝራቱ ከማሰማት  በሻገር የመሬት መንቀጥቀጥ ከፈንታሌ ተራሮች ውጭ የደረሰ ስለመኖሩ አልተረጋገጠም " ሲል አክሏል።

" በደሴ መስመር እስከ ኮምቦልቻ የተየውም ንዝራቱ ነው። ክስተቱ ከሰሞኑ ጀምሮ በፈንታሌ ተራራ እና አዋሽ አካባቢዎች የነበረ ስሜት ነው " ብሏል።

@NATIONALEXAMSRESULT


𝐁𝐚𝐠𝐚 𝐚𝐲𝐲𝐚𝐚𝐧𝐚 𝐈𝐫𝐫𝐞𝐜𝐡𝐚𝐚 𝐧𝐚𝐠𝐚𝐚𝐧 𝐠𝐞𝐞𝐬𝐬𝐚𝐧! 𝐈𝐫𝐫𝐞𝐞𝐜𝐡𝐢 𝐤𝐚𝐧 𝐣𝐚𝐚𝐥𝐚𝐥𝐚𝐚, 𝐧𝐚𝐠𝐚𝐚 𝐚𝐤𝐤𝐚𝐬𝐮𝐦𝐚𝐬 𝐤𝐚𝐧 𝐭𝐨𝐤𝐤𝐮𝐦𝐦𝐚𝐚 𝐧𝐮𝐮𝐟 𝐡𝐚𝐚 𝐭𝐚'𝐮.
𝐀𝐲𝐲𝐚𝐚𝐧𝐚 𝐠𝐚𝐚𝐫𝐢𝐢!⚫🔴⚪
እንኳን ለ እሬቻ በዓል በሰላም አደረሳቹህ! እሬቻ የ ሰላም የ ፍቅር የ መተሳሰብ እሴቶቻችን መገለጫ ነው!
መልካም በዓል!🖤❤️🤍🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Team :- @NATIONALEXAMSRESULT


ሰበር ዜና 🟥
ዓለም አቀፍ!

ከደቂቃዎች በፊት ኢራን ወደ እስራኤል ከ300 በላይ የሚሳኤል እና የሮኬት ጥቃት ለፍታለች። እስራኤል ከፍልስጤም፣ ሊባኖስ እና አሁን ደግሞ ከኢራን ጋር በሁሉም አቅጣጫ እጅግ ከባድ የሚባል ጦርነት ውስጥ ገብታለች።

የአሜሪካ ጦር እስራኤልን ለመደገብ ወደ ቀጠናው የባህር ኃይሉን እና ወታደሮችን ማስጠጋት ጀምሯል።

@NATIONALEXAMSRESULT


የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ውጤት ይፋ መሆኑ ይታወቃል።


በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰላ (70%) እና በተማሩበት ተቋም የሚሰላ (30%) በድምሩ 50% እና ከዚያ በላይ የማለፊያ ነጥብ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ተሰምቷል።

በተማሩበት ተቋም 30% ውጤት ያልተሞላላቸው ተማሪዎችን ውጤት በቅርቡ ተስተካክሎ ይሞላል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላቻንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT


#AASTU #ASTU

በ2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ ጥሪ ቀርቧል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና በቀጥታ (online) በመስጠት ነው የሚቀበሉት።

የትምህርት መስኮቹ ምን ምን ናቸው ?

/ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ /

#ኢንጂነሪንግ ፦ አርክቴክቸር፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ፣ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ፣ ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ፣ ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ ፣ ኤሌክትሮ መካኒካል ኢንጂነሪንግ ፣ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ፣ ማይኒንግ ኢንጂነሪንግ ፣ ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ

#አፕላይድሳይንስ ፦ ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ፣ ፉድ ሳይንስ፣ አፕላይድ ኒውትሪሽን ፣ ጂኦሎጂ፣ ባዮቴክኖሎጂ

/ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ /

#ኢንጂነሪንግ ፦ አርክቴክቸር፣ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ፣ ወተር ሪሶርስ ኢንጂነሪንግ ፣ ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ፣  ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ፣ ማቴሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪንግ ፣ ኤሌክትሪካል ፓወር እና ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪንግ፣ ኮምፒዩተር ሳይንስ ኢንጂነሪንግ፣ ሶፍት ዌር ኢንጂነሪንግ

#አፕላይድሳይንስ ፦ አፕላይድ ቦዮሎጂ፣ አፕላይድ ኬሚስትሪ፣ ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ፣ ፋርማሲ፣ አፕላይድ ፊዚክስ ፣ አፕላይስ ጂኦሎጂ፣ አፕላይድ ማቲማቲክስ

የምዝገባ ጊዜ፡- ከመስከረም 06 እስከ መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሆነ ተገልጿል።

ምዝገባው የሚጠናቀቀው መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ላይ ነው።

የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et / www.astu.edu.et ድረገጽን በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን በድህረ ገጽ የምዝገባው ቀን ካበቃ በኋላ ይደረጋል።

ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ ፤ በምዝገባ ወቅት በመረጡት ዩኒቨርሲቲ (የፈተና ጣቢያ) በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

NB. ለምዝገባና ለፈተና ምንም አይነት ክፍያ የማይጠየቅ ሲሆን የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ፍላጎቱ ያላቸው አመልካቾች ይህን አውቀው ቅድሚያ እንዲመዘገቡ ተብሏል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላቻንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT


ትምህርት ሰኞ ይጀመራል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለሁሉም ትምህርት ቤቶች በላከው መመሪያ የመውሊድ በአል ነገ ማለትም 5/01/17 ዓ.ም ስለሚከበር መደበኛ የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሰኞ ማለትም መስከረም 6/2017 ዓ.ም እንዲጀመር ትዕዛዝ አስተላልፏል።

እኛም በቻናላችን ስም መልካም የትምህርት ዘመንን እንመኛለን

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላቻንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT


🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌼

@NATIONALEXAMSRESULT


#ሬሚዲያል

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ተከትሎ ፈተና የሬሚዲያል መግቢያ ነጥብ ገና ያልተገለጸ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።

በዘንድሮ የምትምህርት ዘመን ግን ካለፉት ሁለት ዓመታት በቁጥር ያነሰ ተማሪ በሬሚዲያል ማካካሻ ትምህርት እንደሚካተት እና ቀስ በቀስም የሬሚዲያል የመቀበል አቅምን በማሳነስ ሙሉ ለሙሉ እንደሚቆም ትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በትናንትናው ዕለት መግለፃቸው ይታወሳል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላቻንን ይቀላቀሉ
@NATIONALEXAMSRESULT


የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 100 ፐርሰንት ተማሪዎችን ማሳለፍ ችሏል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT


#አኃዛዊ_መረጃ

674,823
በ2016 ዓ.ም ለ12ኛ ክፍል ፈተና የተቀመጡ

36,409 (5.4%)
ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች

1,363
አንድም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች

9%
ፈተናውን ከወሰዱ 321,536 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ውስጥ ማለፍ የቻሉት

2%
ፈተናውን ከወሰዱ 353,287 የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ውስጥ ማለፍ የቻሉት

26.6%
በኦንላይን ለፈተናው ከተቀመጡ ማለፍ የቻሉ

29.76%
ዘንድሮ የተመዘገበው አማካይ ውጤት (Mean)

575 (ከ600)
በተፈጥሮ ሳይንስ የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት (በአዲስ አበባ ካቴድራል ት/ቤት)

538 (ከ600)
በማኅበራዊ ሳይንስ የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት (በአዲስ አበባ ኢትዮ ፓረንትስ ት/ቤት)

675 (ከ700)
በትግራይ ክልል የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት
(ከቓላሚኖ ልዩ ትምህርት ቤት)

2 ትምህርት ቤቶች
ሙሉ በሙሉ ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ያሳለፉ
(እቴጌ መነን የሴት ተማሪዎች አዳሪ ት/ቤት እና ገላን የወንድ ተማሪዎች አዳሪ ት/ቤት)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

15k 0 53 68 66

#ውጤት የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መገለፁ ይታወቃል።

በሚከተሉት አማራጮች ውጤታችሁን ተመልከቱ፦

በፖርታል 👉 https://result.eaes.et

በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284

በቴሌግራም ቦት 👉 https://t.me/EAESbot

ከውጤት መግለጫ ፖርታል እና ቴሌግራም ቦት ላይ ጊዜያዊ ሰርቲፊኬት ማውረድና ማተም እንደምትችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ተፈታኞች በውጤት እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ቅሬታ ካላቸው ወደ አገልግሎቱ ቢሮ በአካል መሔድ ሳያስፈልጋችሁ ከSMS በስተቀር በውጤት መግለጫ አማራጮቹ ላይ Compliant የሚለውን በመጫን የቅሬታቸውን ዓይነት በተዘጋጀ የቅሬታ ፎርም ላይ በትክክል በመሙላት ማቅረብ ትችላላችሁ።

አገልግሎቱ በቅሬታችሁ ላይ ምላሽ ቅሬታቸውን ባቀረቡበት ተመሳሳይ አድራሻ የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጿል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT


#አማራ_ክልል

በ2016 ዓ.ም በፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መውሰድ ላልቻሉ ተማሪዎች በተለይ (በአማራ ክልል) 2ኛ ዙር ፈተና ከመስከረም 13-15/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

20 last posts shown.