12ኛ ክፍልን ከልጃቸው ጋር ተፈትነው ዩኒቨርስቲ የገቡት አርሶ አደሯ የአራት ልጆች እናት
"የአስረኛ ክፍል ተማሪ ሳለሁ ቤተሰቦቼ ከምወደው ትምህርት አቋርጠውኝ ለማላውቀው ሰው አስገድደው ዳሩኝ፤ ቢሆንም ትምህርት በጣም ስለምወድ ልጆቼን ካስተማርኩ በኋላ ወደ ትምህርቴ ተመልሼ ዩኒቨርስቲ የመግባት እድል አግኝቻለሁ" ይላሉ የ47 ዓመቷ ወ/ሮ ይመኙሽ ምትኩ።
ወ/ሮ ይመኙሽ ምትኩ የአራት ልጆች እናት ሲሆኑ፣ በዚህ ዓመት የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ወለጋ ዩኒቨርስቲ ገብተዋል።
ከሦስተኛ ልጃቸው ጋር ከአስረኛ ክፍል ጀምሮ አንድ ክፍል የተማሩት ወ/ሮ ይመኙሽ፣ ወደ ቤት ሲመለሱም ሌሊት ከልጃቸው ጋር አብረው ቁጭ ብለው ያጠኑ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ወ/ሮ ይመኙሽ የአስረኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናን 3.7 ሲያመጡ፣ ልጃቸው ደቻሳ ደግሞ 3.9 በማምጣት ነበር ወደ መሰናዶ ትምህርት አብረው የገቡት።
ይህ የሆነው በ2011 ዓ.ም ሲሆን፣ የመሰናዶ ትምህርታቸውንም እናትና ልጅ በአንድ ክፍል ጎን ለጎን ተቀምጠው ነው የተከታተሉት።l
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT