#አይሰለቸኝም_ከቶ
አይሰለቸኝም ከቶ ውዳሴ መዝሙር ቅኔ
ብዙ ነው ያረገልኝ እግዚአብሄር በዘመኔ2×
አዝ://
ቸርነትና ፍቅሩን ያላራቀ ከባሪያው
ከለመለመ ስፍራ ልጆቹን ሚያሠማራው
ታራቅ ነው የኛ ንጉስ ታላቅ ነው የኛ ጌታ
መፅሀፉን የዘረጋ ማህተሙን የፈታ
አዝ://
አንገቱን ፍፁም ደፍቶ ቀና አንድል አድርጎኛል
እየቃተተ ሞቶ በህይወት አቁሞኛል
አልችልም የሡን ፍቅር መዘርዘርና ማውራት
ዉለታውን ለመግለፅ የለኝም ብርቱ ቃላት
አዝ://
ያንተ ክንድ የማይንደው ተራራ ጋራ የለም
ወጥቻለው ከጥልቁ ታላቅ ነህ ዘለአለም
የተከፈተ ደጃፍ ሠተኸኛል ከፊቴ
ተመስገን ክበርልኝ ንገስልኝ አባቴ
አዝ://
ለይተህ የጠራኸኝ ያበዛህልኝ ፀጋ
ትዝታዬ ነህ ጌታ ሲመሽና ሲነጋ
ወዳጅ እና ዘመዴ ብዬ ስጠራህ ልኑር
እየሡስ የእግዚአብሄር ልጅ ለወጠኝ ያንተ ፍቅር
አዝ://
አንገቱን ፍፁም ደፍቶ ቀና እንድል አድርጎኛል
እየቃተተ ሞቶ በህይወት አቁሞኛል
አልችልም የሡን ፍቅር መዘርዘርና ማውራት
ዉለታውን ለመግለፅ የለኝም ብርቱ ቃላት
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇
@ney_ney_emye_maryam #ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊