ደጋዳሞት ብርጌድ እና መዝገቡ ዋለልኝ ብርጌድ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የአማራ ፋኖ በጎጃም 2ኛ ክ/ጦር ደጋዳሞት ብርጌድ በዛሬው ዕለት ማለትም የካቲት13/2017 ዓ.ም ሁለት ዋና ዋና መርሀ ግብሮችን አከናውኗል።
አንዱና ዋነኛው የደጋዳሞት ብርጌድ ሁለተኛ ሻለቃ በ2ኛ ክ/ጦር ስር ከሚገኘው ሌላኛው ብርጌድ ማለትም መዝገቡ ዋለልኝ ብርጌድ አራተኛ(ወይን ውሃ) ሻለቃ ጋር በጥምረት ለመስራት የሚያስችል ቀጠናዊ ትስስር ፈፅመዋል።
በዚህ መርሀ ግብር ላይ የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢ እና ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው በስፍራው ተገኝተው የትግላችንን እና የድርጅታችንን ወቅታዊ ቁመና እና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ንግግር አድርገዋል።
ሌላኛው በዕለቱ ከተከናወኑ አበይት ተግባራት መካከል ጀግናው እና አይበገሬው የደጋዳሞት አርሶ አደር ለትግሉ ያለውን ሁለተናዊ ድጋፍ ለመግለፅ በራሱ ተነሳሽነት የጦር መሳሪያ ባለቤት የሆኑ አርሶ አደሮች ሙሉ በሙሉ የተገኙበትን የተሃድሶ ፕሮግራም ያካሄደ ሲሆን በፕሮግራሙም ከዝቋላ ወገም እስከ አረፋ መድሃኒያለም ድረስ የሚገኙ የጦር መሳሪያ ባለቤቶች ተገኝተዋል።
ይህንን ፕሮግራምም እንደተለመደው የደጋዳሞት ብርጌድ አባ ሻውል ሃይሌ ሁለገብ የኪነት ቡድን አድምቀውት ውለዋል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!
የአማራ ፋኖ በጎጃም 2ኛ ክ/ጥር ደጋዳሞት ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል
https://youtube.com/@nibcnewsethiopia?si=_LD-OmtO1nJ0RVr2